Commercial Bank of Ethiopia - Official


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Economics


Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1,940 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Economics
Statistics
Posts filter


እየቆጠቡ ንያዎትን ያሳኩ!
======

ሐጅ / ኡምራ የማድረግ ንያዎትን በለበይክ የቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት
በመቆጠብ እውን ያድርጉ!

እንደምርጫዎ በለበይክ ወዲዓህ የቁጠባ ሂሳብ፣ ወይም
ከትርፍ ላይ 70 በመቶ በሚያጋራው ሙዷራባህ ለበይክ
የቁጠባ ሂሳብ መጠቀም ይችላሉ፡፡
*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#CBE #cbenoor #interestfree #saving #mudarabah #wadiah #lebbeyk


ራስዎን ከአጭበርባሪዎች ለመከላከል፡
******

• ከባንክ ነው በሚል የሚደርስዎትን የስልክ ጥሪ ትክክለኛነት ወደ ባንካችን ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 951 በመደወል ሳያረጋግጡ ምንም ዓይነት እርምጃ አይውሰዱ፣
• የባንክ መረጃዎን በስልክ ለማንም አይስጡ፣
• የባንኩን መተግበሪያዎች (Apps) ከ Play Store እና App Store ብቻ አውርደው ይጠቀሙ፣
• የዲጂታል የባንክ አገልግሎት የሚስጥር ቁጥርዎን ለማንም አያሳውቁ፤ ሞባይል ስልክዎ ላይ ወይም ማንኛውም
ነገር ላይ አይፃፉ፣ ጠንካራ የሚስጥር ቁጥር ይጠቀሙ፣
• ከማይታወቁ ምንጮች የሚያገኟቸውን ማስፈንጠሪያዎች (Links) አይክፈቱ፣
• መረጃ ለማግኘት የባንካችንን ቅርንጫፎች፣ ወደ 951 በመደወል እና ትክክለኛ የባንካችንን የማህበራዊ ትስስር ገፆች ይጠቀሙ፡፡

*******
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!


7 ብር ጭማሪ ያግኙ!
*******

ከባንካችን ጋር በሚሠሩ የሐዋላ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ሲላክልዎ፣
ከእለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን በተጨማሪ በተላከልዎት እያንዳንዱ ዶላር
7 ብር ተጨማሪ ጉርሻ ያገኛሉ!
**************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #gift #moneytransfer #banking #ethiopia #forex #mto


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Friday, May 30, 2025.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia


ውድ ደንበኞቻችን፡
******

ባንካችን በቅርንጫፎች እና በዲጂታል የክፍያ አማራጮች በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ላይ እናንተ ክቡራን ደንበኞቻችን በምትሰጡን አስተያየት መነሻነት ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎችን በመተግበር ላይ እንገኛለን፡፡

አሁንም ለቀጣይ መሻሻል ይረዳን ዘንድ በቅርንጫፎች አገልግሎት ሲያገኙ እንዲሁም የኤቲኤም (ATM)፣ የፖስ (POS) እና የሲቢኢ ብር (CBE Birr) አገልግሎቶችን ከተጠቀሙ በኋላ ከፅሁፍ ማረጋገጫ መልእክት (SMS) ጋር የሚደርስዎትን ማስፈንጠሪያ (link) በመጠቀም አስተያየት እንድትሰጡን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በስልክ በሚላክ መጠይቅ ምንም አይነት የባንክ መረጃዎንና የሚስጢር ቁጥርዎን አይጠይቅም፡፡

***********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

13k 0 0 27 73

ነዳጅዎን በሲቢኢ ብር ፕላስ ከባንክ ሂሳብዎ!
****

የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ተጠቅመው
ከሲቢኢ ብር ሂሳብዎ ወይም ከባንክ ሂሳብዎ ጋር በማገናኘት በቀላሉ የነዳጅ ክፍያዎን መፈፀም ይችላሉ፡፡

በሚቀርብዎ ቅርንጫፍ በመገኘት የሲቢኢ ብር ሂሳብዎን ከባንክ ሂሳብዎ ያስተሳስሩ!
****
አሁኑኑ ወደ Google Play ወይም App Store በመግባት የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ይጫኑ/ያዘምኑ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች : https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች : https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787

#cbe #cbebirr #ethiopia #digitalbanking #banking #business #fuel #payment


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Thursday, May 29, 2025.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia


ክቡራን ደንበኞቻችን እና ባለድርሻ አካላት በሙሉ፡-
ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሚዲያ አገልግሎት በተሰኘ የዜና ማሰራጫ እንደ ሰበር ዜና የተላለፈ መልእክት “በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ መዘረፉ ተገለፀ” በማለት ባንካችን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተዘረፈ፣ ዘራፊዎቹ እንዳልተያዙ እና ባንካችንም ጉዳዩን አድበስብሶ እንዳለፈው የሚገልጽ የሐሰት ዜና ስለተዘገበ በጉዳዩ ላይ አጭር መግለጫ ለመስጠት ተገድደናል።
ከላይ የተጠቀሰው ሚዲያ እና ሌሎችም ይህንኑ ሚዲያ ያጣቀሱ ሚዲያዎች ከባንካችን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተዘረፈ የሚገልጽ ዜና ቢዘግቡም፣ እውነታው ግን፡-
➢ በሚዲያዎቹ ከተዘገበው በተቃራኒ ከባንካችን ምንም የተዘረፈ ገንዘብ አለመኖሩን፣ ይልቁንም ከፍተኛ ገንዘብ ለመዝረፍ የተደረገ ሙከራ መሆኑን፣
➢ ባንካችን ሙከራው በተደረገ በጥቂት ደቂቃዎች ዉስጥ በጠንካራው የውስጥ ቁጥጥር ስርአታችን አጠራጣሪ ግብይት መፈፀሙን ስለደረሰበት ምንም ዓይነት ገንዘብ ወጪ ሳይደረግ ሙከራው ወዲያውኑ እንዲከሽፍ መደረጉን፣
➢ ሙከራው በጥቂት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ባሰቡ ተጠርጣሪዎች የተፈፀመ እንጂ የባንካችንን ሲስተም ተላልፎ የተፈፀመ ጥቃት አለመሆኑን፣
➢ ባንካችን ሙከራ የተደረገበትን ገንዘብ ባለው ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት አማካኝነት ከጥቃት ከተከላከለ በኋላ ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማሳወቅ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉና የምርመራ ስራውም ተጠናክሮ እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑን፣
➢ በማጠቃለያም ባንካችን እንደማንኛውም የፋይናንስ ተቋም በተለይም እንደ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋምነቱ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት አስበው ለሚንቀሳቀሱ አካላት ኢላማ መሆኑ እሙን ቢሆንም እንዲህ አይነቱን ሕገ ወጥ ተግባር ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓትና የዘመነ ሲስተም ያለው ለመሆኑ ይህ የሙከራ ድርጊት መክሸፉ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅትም ጉዳዩ በሕግ አካላት ተይዞ ጥብቅ ክትትል እየተደረገበት የሚገኝ እና የምርመራ ሂደቱም ያልተጠናቀቀ መሆኑን እያሳወቅን በቀጣይ የሕግ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ዝርዝር መረጃውን የምናሳውቅ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

14.3k 0 68 33 203

ደንበኞች ምን ይጠይቃሉ?


በመረጡት ይላኩ፤ የበለጠ ያግኙ!
********************

ከባንካችን ጋር በሚሠሩ የሐዋላ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል ገንዘብ ሲላክልዎ፣
ከእለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን በተጨማሪ በተላከልዎት እያንዳንዱ ዶላር
10 ብር ተጨማሪ ጉርሻ ያገኛሉ!
**************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #gift #moneytransfer #banking #ethiopia #forex #mto


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Wednesday, May 28, 2025.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላ ዲስትሪክት በሲቢኢ በጄ (CBEBeje) የአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ አገልግሎት ላይ የግንዛቤ መስጫ መድረክ አካሄደ፡፡
****
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሰላ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ስንሻው ንጉሴ በአሰላ ከተማ በተካሄው  መድረክ ላ
ይ  እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነት እና አካታችነትን ለማስፋት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባንኩ የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማስፋት በሚያደርገው ጥረት ሲቢኢ በጄ የተሰኘ በዲጂታል አማራጭ ለደንበኞች ብድር ለማቅረብ የሚያስችል  አገልግሎት ይዞ መምጣቱን አቶ ስንሻው ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት ከተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሰራተኞች የአካታችነት ጥያቄዎች ሲነሱ መቆየታቸውን ያስታወሱት አቶ ስንሻው ሲቢኢ በጄ ሰራተኞች ለተለያዩ የግል ጉዳዮች መፈፀሚያ የሚውል እና ያለምንም ማስያዣ  የአነስተኛ ብድር አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ በማሰብ የተዘጋጀና ሲነሱ የነበሩትን ጥያቄዎች የሚመልስ አሰራር እንደሆነም አመላክተዋል፡፡

ተቋማት ሰራተኞቻቸውን የሲቢኢ በጄ  የብድር አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ደመወዝ በሲቢኢ ብር አገልግሎት መክፈል እንደሚጠበቅባቸውም አቶ ስንሻው አስረድተዋል፡፡

የተለያዩ ተቋማትን በመወከል የመጡት  የመድረኩ ተሳታፊዎች ላነሷቸው ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን፣  ተሳታፊዎቹ ባንኩ  የአግልግሎቱን ተደራሽነት እና የብድር አቅርቦት አካታችነትን እውን ለማድረግ የጀመራቸው አዳዲስ አሰራሮች አበረታች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ህልምዎን ወደመዳረሻዎ ይቀይሩ!
ሲቢኢ ጉዞ የቁጠባ ሂሳብ

*********
ሲቢኢ ጉዞ የቁጠባ ሂሳብን ከብር 1,000 ጀምሮ በመክፈት
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገራት ለሚያደርጉት ጉዞ ወጪ መሸፈኛ ገንዘብ አስቀድመው ይቆጥቡ!
ተጨማሪ ጥቅሞችን የሚያስገኘውን ጉዞ የቁጠባ ሂሳብ በአቅራቢያዎ በሚገኝ ቅርንጫፍ ይክፈቱ!
*********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #savings #ethiopia #banking


ወርሀዊ የውሀ ፍጆታ ክፍያዎን
በሲቢኢ ብር ይክፈሉ!
**
የአዲስ አበባ ውሀና ፍሳሽ ወርሃዊ  የአገልግሎት ክፍያዎን 
በሲቢኢ ብር ፕላስ  መተግበሪያ ለመክፈል የሚከተለውን መመሪያ ይከተሉ፡፡

  1.  ‎ ወደ ሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ይግቡ፤
  2.  'ክፈል’  / Pay/ ወደሚለው አማራጭ ይግቡ፤
  3.  የውሀ አቅርቦት /Water Supply / የሚለውን ይጫኑ፤
  4.  ‘Addis Ababa Water’  የሚለውን ይምረጡ፤
  5.  የቢል ማጣቀሻ  ቁጥር  /Bill Reference No/ ያስገቡ፤
  6.  የክፍያ መጠኑን በማረጋገጥ ክፍያዎን ይፈፅሙ፡፡

ወይም ወደ *847# በመደወል በሚከተለው መንገድ ክፍያዎን መፈፀም ይችላሉ፡፡

1. ወደ *847# ይደውሉ
2.  5 ቁጥርን ‘የአገልግሎት ክፍያ’ (Pay Bill) የሚለውን  ይምረጡ
3.  2 ቁጥርን የክፍያ አጭር ቁጥር (Input Short code) መርጠው 878787 ያስገቡ
4. የቢል ማጣቀሻ  ቁጥር  /Bill Reference Number/ ያስገቡ
5.  የክፍያ መጠኑን ለማረጋገጥ 1 ቁጥርን (አዎ) የሚለውን ይምረጡ
6 የሚስጥር ቁጥርዎን በማስገባት ክፍያዎን ሲያጠንቅቁ የክፍያ ማረጋገጫ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ይደርስዎታል።
***
የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያን ለማግኘት፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
*****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Tuesday, May 27, 2025.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia


ከየትኛውም ዓለም ሂሳብ ይክፈቱ!
*********

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ተግባራዊ ያደረገውን Unite.et መተግበሪያ በመጠቀም
ከየትኛውም የዓለም ክፍል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ መክፈት ይችላሉ፡፡

• መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶር ወይም አፕ ስቶር አውርደው፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በመምረጥ አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት ተመዝግበው የሚፈለጉትን የሂሳብ ዓይነት መክፈት ይችላሉ፡፡
**********
Unite.et መተግበሪያን ለማግኘት፡
• Android: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.viditure.uniteet&hl=en&pli=1
• IOS: https://apps.apple.com/us/app/unite-et/id6670190778

#cbe #nbe #banksinethiopia #digital #savings #ethiopia


የኤቲኤም ካርድዎን ረስተው ቢወጡና ገንዘብ ለአስቸኳይ ጉዳይ ቢያስፈልግዎ ምን ያደርጋሉ?
***************
መፍትሄ አለው!
የሲቢኢ ብር አገልግሎትን በመጠቀም
ያለካርድ ከኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ!
=======
የሲቢኢ ብር ፕላስ መተግበሪያ ለመጫን/ለማዘመን  የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ፡
ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
ለአይፎን ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787


Commercial Bank of Ethiopia
Exchange Rate Applicable for Monday, May 26, 2025.
For more information:
https://combanketh.et/en/exchange-rate
#exchangerate #CBE #commercialbankofethiopia #Birr #rate #currency #Ethiopia


መልካም የሥራ ሳምንት!
*****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#cbe #Ethiopia #banking #monday #bestwishes



20 last posts shown.
OSZAR »