በ2017 ዓ.ም የሚሰጠውን ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚፈተኑ ተማሪዎች የኦንላይን መለማመጃ ፈተና መስጠት ተጀምሯል፡፡
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጅ ስራ አስፈጻሚ በተሰራው ሶፍትዌር አማካኝነት ከእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና በኦንላይን ለሚፈተኑ ተማሪዎች የመለማመጃ ፈተና በመሰጠት ላይ ነው።
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኢንፎርሜሽን ኮምኒኬሽን ቴክኖሎጅ ስራ አስፈፃሚ አዱኛው አለበል እንደገለጹት የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ኢንተርኔት ባለባቸው አካባቢዎች የሚማሩ ተማሪዎች በበይነ መረብ እንደሚሰጥ ከትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ለሚገኙ ሶስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1,670 ለሚሆኑ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የአይሲቲ ባለሙያዎች በተሰራው ሶፍትዌር የበየነ መረብ የመለመጃ ፈተና ከትናንት ጀምሮ እየተሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ስራ አስፈጻሚው አያይዘውም የመለማጃ ፈተናው አስፋላጊነት ተፈታኝ ተማሪዎች ቴክኖሎጅው ጋር አንዲግባቡና ለቀጣይ ለዋናው ፈተና ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የመለማመጃ ፈተናው ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 07/2017ዓ.ም እንደሚሰጥ ጠቅሰው በቀጣይ የአዊ ብሄረሰብ ትምህርት መምሪያ በሚያወጣው መርሀ ግብር መሰረት የበየነ መረብ (ኦንላይን) ሞዴል ፈተና እንደሚፈትኑም ገልፀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር
ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️
https://t.me/Tmhrt_Minister