ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ዩናይትድ ኪንግደም ለጊዜው ከትራምፕ የ50 በመቶ የብረት ታሪፍ ተረፈች

ዩናይትድ ኪንግደም ከ 25 ወደ 50 በመቶ የብረታ ብረት እና የአልሙኒየም ታሪፍ በእጥፍ እንዲጨምር ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስፈፃሚ ትዕዛዝ ለጊዜው ተርፋለች። በትራምፕ የተፈረመው ትእዛዝ ከረቡዕ ጀምሮ ከሌሎች ሀገራት ለሚገዙ በአሜሪካ ላሉት ኩባንያዎች የማስመጣት ቀረጥ ይጨምራል። ነገር ግን ይህ ቀረጥ በእንግሊዝ 25 በመቶ ብቻ ሆኖ ይቀጥላል። ትዕዛዙ ባለፈው ወር በተፈረመው የዩናይትድ ኪንግደም እና የአሜሪካ ታሪፍ ስምምነት ላይ የሚመረኮዝ ሲሆን ይህም የብረት እና የአሉሚኒየም ቀረጥ የሚቀነሰው ቢሆንም ስምምነቱ ገና ተግባራዊ አልሆነም።

ይህም ማለት የዩናይትድ ኪንግደም ብረት ላኪዎች እስከዚያ ድረስ ባለው ታሪፍ ይስተናገዳሉ። ሆኖም ግን ስምምነቱ ከተደናቀፈ ከፍተኛውን የታሪፍ መጠን ሊጠብቃቸው ይችላል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት "የብሪታንያ ንግድ እና ስራዎችን ለመጠበቅ ቁርጠኛ ነኝ" ቢልም ወግ አጥባቂዎች ትዕዛዙን "ትኩስ የታሪፍ ውድቀት" ብለውታል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት ቃል አቀባይ አክለውም “ታሪፍ የሚወገድበትን ስምምነታችንን ተግባራዊ ለማድረግ ከአሜሪካ ጋር መስራታችንን እንቀጥላለን” በማለት ህጉ “በጊዜው” በፓርላማ የሚቀርበውን ስምምነቱን ተግባራዊ ያደርጋል ብለዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም ከሌሎች ሀገራት አንፃር ለጊዜው ከአሜሪካ ታሪፍ አንፃር በመጠኑ የተሻለ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ነገር ግን ከሚደርሰው ተፅእኖ ማምለጥ አትችልም። የኤኮኖሚ ትብብርና ልማት ድርጅት (OECD) የእንግሊዝ ኢኮኖሚ በ2024 ከነበረበት 3.3 በመቶ ዕድገት ወደ 2.9 በመቶ እንደሚቀንስና በቀጣይም በንግድ እንቅፋቶች ላይ ከፍተኛ ውድቀት ምክንያት እንደሚሆን ይተነብያል። ልክ ከሶስት ወራት በፊት የአለም አቀፍ ፖሊሲ ቡድኑ በአለም አቀፍ ደረጃ የ 3.1 በመቶ እድገትን ሲተነብይ ነበር። የኦኢሲዲ ዋና ኢኮኖሚስት አልቫሮ ፔሬራ እንደተናገሩት "በመሠረቱ ለሁሉም ሀገራር ማለት ይቻላል ቅናሽ እያደረግን ነው" ብለዋል። "ከዚህ ቀደም ከገመትነው በጣም ያነሰ ዕድገት እና የስራ እድል ይኖራል" ሲሉ የሚፈጠረውን የኢኮኖሚ ውድቀት ተንብየዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል




በደብረ ማርቆስ ከተማ ከ4ሺ በላይ ሰዎች በወባ በሸታ መያዛቸው ተነገረ

ባለፉት ወራት በጤና  ተቋማት እየተሰጡ ያሉትን  አገልግሎቶች ዝርዝር ተግባራትን በተመለከተ የደብረ  ማርቆስ  ከተማ  አስተዳደር ጤና መምሪያ ሃላፊ አቶ  ሃብታሙ ወርቁ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።የእናቶች  እና  ህፃናት የጤና  አገልግሎት  አሰጣጥ ባለፉት  ወራት በዕቅድ  ከተያዘው  የቅድመ ወሊድ 87 በመቶ  በላይ የሚሆኑ እናቶችን ክትትል መደረጉን እና በእርግዝና  ወቅት  የሚደረገው  ሁሉንም የላብራቶሪ  ምርመራዎችን በማድረግ የእናትና ልጅን ጤና መጠበቅ መቻሉን የመምሪያ  ሃላፊው ተናግረዋል።

አንድም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም በማለት የግንዛቤ ትምህርት በመስጠት ከ87.5 በመቶ በላይ የሚሆኑ እናቶች  በጤና ተቋማት ማዋለድ መቻሉን ገልፀዋል። የተወለዱ ህፃናትም ወቅቱን እየጠበቀ የወሳኝ ኩነት መዝገብ ለይ እንዲመዘገቡ  ተደርጓል ።ክትባት በተመለከተ ከ86 በመቶ በላይ ለሚሆኑ ህፃናት  ሁሉንም የክትባት ዓይነቶች ያጠናቀቁ ናቸዉ፡፡ ስር የሰደደ የስርአተ ምግብ ልየታም ችግር ያለባቸውን ህፃናትን በመለየት ክትትልና ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን  ተናግረዋል ።ተላላፊ  የሚባሉ  በሽታዎች ኤችይቪ፣ቲቪ፣ወባ እና  ሀተት  ከመቆጣጠር አኳያም ባለፉት ወራት ከ95 በመቶ በላይ መስራት መቻሉ ተገልጿል።ከ4ሺ በላይ ሰዎች በወባ በሸታ ተይዘው የተገኙ መሆኑን የመምሪያ ሃላፊዉ ገልፀው ስርጭቱ  ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል።

የጤና ተቋማት የመድሃኒት  አቅርቦትም  ከ93 በመቶ በላይ መሆኑን አና ምንም አይነት የመድሃኒት  ብክነትም እንዳይኖር ሁሉም ጤና ጣቢያዎች በቅንጅት እንደሚሰሩ  ተናግረዋል።ለጤና  ሙያተኞች  የአቅም ማጎልበቻ የተለያዩ ስልጠናዎች ከክልል  ቢሮው ጋር በመተባበር የተሰጠ ስለመሆኑንም ተናግረዋል ። ማህበረሰቡ  መጭው  ጊዜ  የክረምት  ወቅት  በመሆኑ የተለያዩ  ተላላፊ  በሽታዎች  እንዳይከሰቱ  የቅድመ መከላከል  ስራዎችን እንዲፈፅም ተጠቁሟል።

ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን በማፍሰስ  ሌሎችም ውሃ ወለድ በሽታዎች  እንዳይከሰቱ  የጤና  ስራ ለጤና ተቋማት ብቻ  የሚተው ስላልሆነ ሁሉም  ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ማህበረሰቡ ጤና   ለመጠበቅ  በጋራ  መስራት ይገባል ሲሉ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ  ሃላፊ አቶ ሃብታሙ ወርቁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል




ለጋዛ አሜሪካ እና እስራኤል የሚያቀርቡት ድጋፍ የማስመሰል ተግባር ነው ሲል ዩኒሴፍ ተቸ

በጋዛ የሚገኘው የዩኒሴፍ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት የጋዛ ሰብአዊ ፋውንዴሽን (GHF) ን በመተቸት የአሜሪካ እና የእስራኤል ድጋፍ  "የእርዳታ ማስመሰል" ነው ሲል አስታውቋል ። በትናንትናው እለት በጋዛ ያለውን ሁኔታ በተመለከተ የዩኒሴፍ ቃል አቀባይ ጄምስ ኤልደር ሲናገሩ እርዳታ ለማግኘት ከ15 እስከ 20 ኪ.ሜ. ተጉዘው የመጡ ወጣቶች በመኪና መስኮት ውስጥ የጎድን አጥንቶቻቸው የሚታይ እና በእንባ ውስጥ ያሉ ታዳጊዎች ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል።

አክለውም የታመኑ ድርጅቶች በአከባቢው እርዳታ እንዳያከፋፍሉ መታገዱ ቀጥሏል። "ይህ በእውነት የጎደለው ነገር ነው ትላልቅ ድርጅቶች በቀን ከ500 እስከ 600 የጭነት መኪናዎችን ማድረስ አለባቸው። ይልቁንም እኛ የምናወራው በቀን ከ500 እስከ 600 ሣጥኖች ወደ ግለሰቦች እንደሚሰጥ ነው ይህ ያሳዝናል" ሲሉ ተደምጠዋል።የእስራኤል ጦር ወደ ስፍራዎቹ የሚወስዱ መንገዶችን እንደ “የጦርነት ቀጠና” እንደሚቆጠሩ በመግለፅ በጋዛ የሚገኙ የእርዳታ ማከፋፈያዎች እሮብ እለት ተዘግተው ውለዋል።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ሚርጃና ስፖልጃሪች እንዳሉት ጋዛ ከሲኦል የከፋ ሆናለች ስትል ተደምጣለች። በጄኔቫ በሚገኘው የዓለም ቀይ መስቀል ዋና መሥሪያ ቤት በመሆን ስፖልጃሪች ባስተላለፈችው መልዕክት የሰው ልጅ እየተሳሳተ ነው። ጦርነቱን ለማስቆም ፣የፍልስጤማውያንን ስቃይ እንዲያበቃ እና የእስራኤል ታጋቾችን ለማስፈታት መንግስታት በቂ ስራ እየሰሩ አይደሉም ስትል ተናግራለች። ፍልስጤማውያን የሰው ክብር ተነፍገዋል። አለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ እየተበረበረ አይደለም ስትል አክላለች።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል


ድሬዳዋን በመጎብኘት የጅቡቲ ዜጎች ቀዳሚ ናቸዉ ተባለ

በድሬዳዋ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የውጭ ሀገር ቱሪስቶችን ቁጥር 20 ሺህ 250 ለማድረስ እና 170 ሚሊዮን ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 30ሺህ 210 የውጭ ሀገር ቱሪስቶች ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን ከዚህም ከ302 ሚሊዮን በላይ ቀጥተኛ ያልሆነ ገቢ ተገኝቷል፡፡ ከጎብኚዎቹ ውስጥ አብዛኛውን ቁጥር የሚይዙት ጂቡቲያዊያን መሆናቸዉ ተገልጿል ።

የሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ቁጥር እና ገቢ ከዕቅድ በላይ መሆኑን የገለፁት የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንደሰን አባይ ከሀገር ዉስጥ ጎብኚዎች ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ቀጥተኛ ያልሆነ ገቢ ማግኘት መቻሉን ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ቁጥር ከእቅድ በላይ የሆነበት ምክንያት በአስተዳደሩ ያለው አንፃራዊ ሰላም ፣ በርካታ ሀገር አቀፍ ስብሰባዎችና የእግር ኳስ ጨዋታዎች በከተማዉ መካሔዳቸው እንዲሁም የቁልቢ ገብርኤል ክብረ እንግዶች ከፍተኛ መሆናቸዉ ተጠቁሟል ። 14 የተለያዩ የማስተዋወቂያ ዘዴዎችን እና መድረኮችን በመጠቀም የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅ ተችሏል ።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ባዘጋጀው የኢጋድ ቱሪዝም ኤግዚቢሽን፣ በሀረሪ ክልል በተዘጋጀ ኤግዚቢሽን ላይ ገጽ ለገጽ የማስተዋወቅ ስራዎች እንዲሁም በተለያዩ ሚዲያዎች የማስተዋወቅ ስራዎች  መሠራታቸዉ ተገልጿል።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል


ሳውዲ አረቢያ ሀጃጆችን የሙቀት መጠን በሚጨምርበት ሰዓት በቤት ውስጥ እንዲሆኑ አሳሰበች

የሳዑዲ አረቢያ ባለስልጣናት ሐጅ የሚያደርጉ ተጓዦች ከፍተኛ የሙቀት መጠንን ምክንያት በማድረግ አብዛኛውን ጊዜያቸው በድንኳናቸው ውስጥ እንዲያሳልፉ ጠይቀዋል። የሳዑዲ አረቢያ የሃጅ እና ዑምራ ሚኒስትር ታውፊቅ አል ራቢያህ "በአራፋት ቀን ያለው ከፍተኛ ሙቀት ሀጃጆች ጤንነታቸውን ለመጠበቅ እና ማንኛውንም የሙቀት ጭንቀት ለመከላከል ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ቀን 10 ሰዓት ድረስ በካምፓቸው ውስጥ እንዲቆዩ እንደሚያስፈልግ አሳስባዋል።

የአረፋ ቀን በተለምዶ የሐጅ ጉዞ የሚደረግበት ሲሆን ይህም ተጓዦች ከመካ ወጣ ብሎ የሚገኘውን የአረፋትን ተራራ የሚወጡበት ኩነት ነው። እዚያም ለጃጆች የ70 ሜትር ከፍታ ባለው ኮረብታ ላይ እና በዙሪያው ባለው ሜዳ ላይ ለሰዓታት ፀሎት እና የቁርዓን ንባብ እያደረጉ እስከ ምሽት ድረስ ይቆያሉ። በአራፋት ተራራ ላይ ምንም አይነት ጥላ ስለሌለ ሀጃጆች በቀጥታ ለበረሃማ ፀሀይ ለሰአታት ይጋለጣሉ።

"በአራፋት ቀን ተራራ ወይም ከፍታ ቦታዎች ላይ መውጣት ከልክ ያለፈ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስለሚጠይቅ እና የሙቀት መጨናነቅን ስለሚጨምር ጥንቃቄ ማድረግ ይገባልም ብለዋል። የዚህ አመት የሙቀት መጠን ከ40 ዲግሪ ሴልሺየስ እንደሚበልጥ ተተንብያል።

በዚህ አመት ባለስልጣናት ከ40 በላይ የመንግስት ኤጀንሲዎችን እና 250ሺ ባለስልጣናትን በማሰባሰብ በ2024 ገዳይ የነበረውን ሙቀት ተከትሎ ከሙቀት ጋር በተያያዙ በሽታዎች ላይ የሚያደርጉትን የጥንቃቄ ጥረት በእጥፍ ማሳደግ ችለዋል። በቦታው በሺዎች የሚቆጠሩ የህክምና ባለሙያዎች በተጠባባቂነት እንደሚቀመጡና ከ400 በላይ የማቀዝቀዣ ክፍሎች እንደሚሰማሩ አል ራቢያህ ባለፈው ሳምንት ለኤኤፍፒ ተናግረዋል። እስከ እሁድ ድረስ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ ምዕመናን ለሀጃጅ ሳውዲ አረቢያ መግባታቸውን ባለስልጣናቱ አስታውቀዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል




የመቀሌ ቅርንጫፍ እምባ ጠባቂ ተቋም ከቀረቡለት 150 መዝገቦች ተቀባይነት ያገኙት 31ዱ ብቻ መሆናቸውን አስታወቀ

ባለፋት ዘጠኝ ወራት በአፈፃፀም ሂደት ላይ የነበሩ አምስት መዝገቦች ዉሳኔ ያገኙ መሆኑን የመቀሌ ቅርንጫፍ እምባ ጠባቂ ተቋም አስታውቋል ። ከእነዚህ አምስት መዝገቦች ዉስጥ የፖሊስ ጉዳይ አንዱ የነበረ ሲሆን ተቋሙ ወደ ስራ እንዲመለሱ በሰጠዉ ዉሳኔ መሠረት  3200 የሚሆኑት ወደ ስራ ይመለሳሉ ተብሎ ታስቦ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ወደ ስራ እንዲመለሱ ዉሳኔ አስተላልፎ መመሪያ በማዉጣት 1000 አከባቢ የሚሆኑት ወደ ስልጠና መግባታቸው ተገልጿል ።

ሌሎች አባላት ያልመጡበት ምክንያት አለመታወቁንና ቴሌቪዥንን ጨምሮ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ጥሪ መደረጉ ተገልፆ በስልጠና ላይ የሚገኙትም ወደ ስራ መመለሳቸዉ ተነግሯል:: ሌላም በአፈፃፀም ላይ የነበረ አንድ አይነስውር 250 ካሬ መሬት እንዲያገኝ ተደርጓል ።

እስከ ግንቦት 20 ድረስ ባሉት ቀናትም ከቀረቡ 150 መዝገቦች ዉስጥ ተቀባይነት ያገኙት 31ዱ ብቻ መሆናቸዉን ለብስራት ሬዲዮ የተናገሩት የተቋሙ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ፀሀዬ እምባዬ ናቸዉ ።  እነዚህም 31 መዝገቦች ወደ ምርመራ ተመርተዉ ዉሳኔ ያገኙ ሲሆን ሁለቱ ብቻ በሂደት ላይ እንደሚገኙ ሀላፊዉ ተናግረዋል ። ከ150 መዝገቦች ዉስጥ ተቋሙ የማየት ስልጣን የሌለዉ የወንጀል ፣የግል ፣የምክርቤት እና የፍርድቤት ጉዳዮች ይገኙበታል ። ከዚህም ባሻገርም ሁለት ተከታታይ እርከን ያላቸዉ ሀላፊዎች ወይንም አስፈፃሚ አካላት ምላሽ ባለመስጠታቸው ዉሳኔ ያላገኙ መዝገቦችም መኖራቸው ተገልጿል ።

በአስፈፃሚ አካል በኩል ያሉ ችግሮች አሁንም ድረስ አለመስተካከላቸዉን የተናገሩት ኃላፊዉ አስፈፃሚ አካላት ቅሬታ ለሚያቀርብ ማንኛውም ዜጋ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል ።ያጋጠመዉ የበጀት እጥረት እንዳለ ሆኖ የነዳጅ እጥረት ችግር ከበፊቱ በተወሰነ መልኩ ቢሻሻልም አስፈቅደን የሚመደብልን ለምንሄድባቸዉ ዘጠኝ ወረዳዎች እየበቃን አይደለም ብለዋል ። ህብረተሰቡም በታሪፍ ጉዳይ በጣም እየተቸገሩ መሆናቸውንና ለሽሬ በታሪፍ 550 የሚከፍሉትን 1200  እየከፈሉ መሆኑን አቶ ፀሀዬ ጨምረዉ ገልፀዋል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል




carra addaa warreen hordoftoota kuma shanifi (5000) isaa ol qabdaniif kan dhihaate.

Naannoo Oromiyaatti Afaan oromiiffanis ta’ee afaan amariffaan tiktookiidhan fi facebookiin dhiibbaa Uumuun hojjechaa kan Jirtan.

guyyoota lamaanf kan turu leenjii tola kan isinif qopheessine yoo ta’u Wal-dorgomiin adda addaa isinif qophaa’e Jira.
Hirmaatotaaf waraqaa ragaa, warreen dorgommicha mo’ataniifi immoo badhaasota adda addaa akka isinif qopheesinee Gammachuu guddaan isin beeksisuu barbaadna.
leenjicha fudhachuuf kan isin barbaachisuu.
Umuriin keessan 18-30 kan taatan.
murteessaa kan ta’e waa’ee digitaala hubannoo qabaachuu. Hordoftoota kuma shani hanga kuma Shantamaa (5000-50000) tiktookiidhan yookaan facebookiin qabaachuu.
Kanaan dura hojiiwwan hojjetan Afaan oromiiffaa fi amaariffaa kan ta’an.
Magaala finfinneetti argamtanii leenjicha fudhachu kan dandeessan.
Wantoota haaraa barachuuf qophaa’ o kan taatan.

Hirmaachuuf foormii Jala jiruun galma’aa.
https://forms.gle/H6XQAU65xJErtGrZ8
........................................
ልዩ እድል 5 ሺ እና ከዛ በላይ ተከታይ ላላቹ  የቀረበ ስልጠና
በኦሮምያ ክልል ዙሪያ በኦሮምኛ ቋንቋም ሆነ በአማርኛ በtiktok ወይም በfacebook እየሰራችሁ ያላችሁ ተፅኖ ፈጣሪዎች ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና በነፃ ያዘጋጀንላችሁ ሲሆን የተለያዩ አይነት ውድድሮችም  ተዘጋጅቶላችኋል፡፡ ለተሳታፊዎች ሰርተክፌት ለውድድሩ አሸናፊዎች ደግሞ በአይነቱ ለየት ያለ ሽልማት እንዳዘጋጀን ስናሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው፡፡
ስልጠናውን ለመውሰድ የሚያስፈልጋችሁ


•  እድሜያችሁ ከ18-30 የሆነ ፣መሰረታዊ የሆነ የዲጂታል ግንዛቤ ያላችሁ፣ከ5000-50000 ተከታይ በ tiktok ወይም  facebook  ያላችሁ፣ከዚህ ቀደም የሰራችዋቸው ስራዎች በኦሮምኛ ወይም በአማርኛ  የሆነ፣ አዲስ አበባ ተገኝተው  ስልጠናውን መውሰድ የምትችሉ፣አዳዲስ ነገር ለመማር ዝግጁ የሆናችሁ

ለመሳተፍ ከታች ባለው ፎርም ይመዝገቡ

https://forms.gle/HCTuCEM5ZbLr4aeY7




ድብርት እና ጭንቀት ካለበት የፍቅር አጋር ጋር መሳሳም እነዚሁኑ ስሜቶች እንደሚያስተላልፍ አንድ ጥናት አመላከተ

ድብርት እና ጭንቀት የጭንቀት ሆርሞን ኮርቲሶል እንዲለቀቅ ሊያደርግ ይችላል፣ይህም በአፍ ውስጥ ያለውን የባክቴሪያ ሚዛን ያበላሻል። ባለትዳሮች ይህንን ባክቴሪያ በሚሳሳሙበት ጊዜ ማስተላለፍ ይችላሉ ። በእርግጥ ቀደም ሲል በተደረገ ጥናት እስከ 80 ሚሊዮን የሚደርሱ ባክቴሪያዎች በ10 ሰከንድ መሳሳም ውስጥ ብቻ ይተላለፋሉ።

የአዲሱ ጥናት አዘጋጆች እንዳመላከቱት አንድ የትዳር አጋር የአእምሮ ጤና እና የእንቅልፍ ችግር ሲያጋጥመው ጤናማ የትዳር ጓደኛው ላይ ከስድስት ወራት በኋላ ተመሳሳይ ምልክቶች አጋጥሟቸዋል ይላል። በተለይ፣ አንድ የትዳር አጋር የመንፈስ ጭንቀት ባጋጠመው ወቅት ወደ ጤናማው የትዳር ጓደኛ በአፍ  ማይክሮባዮታ ይጎዳል ሲሉ ተመራማሪዎቹ በህክምና ጆርናል ኤክስፕሎራቶሪ ሪሰርች እና መላምት ላይ ጽፈዋል።
የጥናት ቡድኑ በ268 አዲስ የተጋቡ ኢራናውያን ጥንዶች ላይ ትኩረቱን አድርጓል። በጥናቱ መጀመሪያ ላይ አዳቸው የትዳር ጓደኛ ጤነኛ ሲሆኑ ሌላቸው ደግሞ በጫጉላ ወቅት ከድብርት፣ ከጭንቀት እና ከእንቅልፍ ችግር ጋር ሲታገሉ ነበር።

ተሳታፊዎች ስለ አእምሯዊ ጤንነታቸው የዳሰሳ ጥናቶች የተደረጉ ሲሆን ለዲኤንኤ ትንተና የኮርቲሶል መለኪያ እና ከአፍ የሚወሰድ ባክቴሪያ የምራቅ ናሙናዎችን ሰጥተዋል። ተመራማሪዎቹ ጤናማ ባለትዳሮች በተለይም ሴቶች ከስድስት ወራት በኋላ በድብርት ፣ በጭንቀት እና በእንቅልፍ ላይ ያሉ ችግሮች በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ተናግረዋል ። እነዚህ ምልክቶች እንደ አጋሮቻቸው ኃይለኛ አልነበሩም። በናሙናዎቹ ውስጥ አራት ዓይነት ባክቴሪያዎች ማለትም ክሎስትሪዲያ፣ ቬይሎኔላ፣ ባሲለስ እና ላችኖስፒራሴኤ በአንጻራዊነት በብዛት ተገኝተዋል። የእነዚህ ባክቴሪያዎች አንዳንድ ዝርያዎች ለጤና ጎጂ ናቸው።

ተመራማሪዎቹ በጥናቱ ላይ በርካታ ውስንነቶች እንዳሉ አምነዋል፣ ከእነዚህም መካከል መሰረታዊ የጤና ጉዳዮችን እና በአፍ ባክቴሪያ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ የአመጋገብ ሁኔታዎች ናቸው። ባክቴሪያ በሌሎች የአእምሮ እና ከአእምሮ ጋር በተያያዙ ሁኔታዎች ውስጥ ሚና ይጫወታሉ ወይ የሚለውን ማጣራት እንደሚያስፈልግ ይጠቁማሉ።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል




የደቡብ ኮሪያ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ሊ ጄ-ሚንግ የሀገሪቱ 14ኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ

የቀድሞ የደቡብ ኮርያ ፕሬዚደንት ዩን ሱክ ዮል የማርሻል ህግ ውድቅ ከተደረገ በኃላ በሀገሪቱ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ባለፎ ማክሰኞ ተደርጓል።የደቡብ ኮሪያ አዲስ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ሊ ጄ-ሚዩንግ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ድል በማግኘታቸው በርካታ የዓለም ሀገራት መሪዎች ረቡዕ እለት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። የደቡብ ኮሪያ ዋና ተቃዋሚ የዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪ ሊ ጄ-ሚንግ የሀገሪቱ 14ኛ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺገሩ ኢሺባ እና የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም የደቡብ ኮሪያን አዲስ የተመረጡ ፕሬዝዳንት ሊ ጄ-ሚንግን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሺባ በኤክስ ላይ አዲስ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው ከልብ የተሰማቸውን ደስታ ጽፈዋል።ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ አለም አቀፉን ማህበረሰብ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ለመፍታት አጋር ሆነው ሊተባበሩ የሚገባቸው ጠቃሚ ጎረቤት ሀገራት ናቸው ሲሉ ተደምጠዋል። የጃፓን-ደቡብ ኮሪያ ግንኙነት ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚቀጥል እና ሁለቱም መንግስታት በህዝቦቻቸው መካከል ለሚደረጉ ልውውጦች ቅድሚያ በመስጠት ግንኙነታቸውን እንደሚቀጥሉ ተስፋ አድርገዋል ብለዋል።

የማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከፕሬዝዳንት ሊ ጋር ለመስራት ዕድሉን በደስታ እንደሚቀበሉ ገልጸዋል። አንዋር በኤክስ ላይ “ለፕሬዚዳንት ሊ ጄ-ሚዩንግ የኮሪያ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው እንኳን ደስ ያሎት መልዕክት አስተላልፈዋል። የአውስትራሊያው ጠቅላይ ሚንስትር አንቶኒ አልባኔዝም ለሊ እንኳን ደስ አሎት በማለት አውስትራሊያ በሁለንተናዊ ስልታዊ አጋርነት በቅርበት ለመስራት በጉጉት ትጠብቃለች ብለዋል። የህንድ እና የኒውዝላንድ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ተመሳሳይ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል




በሻሸመኔ ከተማ በመድኃኒት መልክ የተቀነባበረ አደገኛ እፅ በቁጥጥር ስር ዋለ

በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር በመድኃኒት መልክ የተቀነባበረ አደገኛ እፅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ አስታዉቋል ።

የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል መከላከል ክፍል ሀላፊ እና የዋና መምሪያዉ ሀላፊ ተወካይ ኮማንደር ፈይሳ ቶላ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት በሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር ሀሩፋ ወረዳ መጂ ደማ ቀበሌ ዉስጥ ከ360 ኪሎግራም በላይ በመድሃኒት መልክ የተዘጋጀ ልቁጥ አደንዛዥ እፅ በቁጥጥር ስር ዉሏል ።

የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 138581 አ.አ የሆነ ዳማስ ተሽከርካሪ ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ልቁጥ አደንዛዥ እፆችን በፕላስቲክ አሽጎ በመድሀኒት መልክ አዘጋጅቶ ሲያጓጉዝ ከህብረተሰቡ በተገኘ ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊዉል ችሏል ።

እፁ በዚህ መልክ ተዘጋጅቶ ለህገወጥ ተግባር እንዲዉል ያዘጋጀው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዉሎ የምርመራ መዝገቡ ተጣርቶ በቅርብ ቀን ለአቃቤ ህግ እንደሚላክ ኮማንደር ፈይሳ ቶላ ገልጸዋል።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል


የሞባይል ስልክ ቀምቶ ለማለጥ የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ በእስራት ተቀጣ

ማሙሽ ጋጀቦ የተባለው ተከሳሽ ወንጀሉን የፈፀመው ሚያዚያ 18 ቀን 2017 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረደ 1 ልዩ ቦታው ቦሌ ቅዱስ ሚካኤል በተለምዶ ነዳጅ ማህበር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ወ/ሮ ራህማን አዋለ የተባለች የግል ተበዳይ በወቅቱ ከምሽቱ 3 ሠዓት ተኩል ገደማ በአካባቢው እየተጓዘች በነበረበት ወቅት ተከሳሹ ተከታትሎ በእጇ ይዛ የነበረውን እና ግምታዊ ዋጋው 20 ሺህ ብር የሆነን ሳምሰንግ ሞባይል ስልክ ቀምቶ ለመሰወር ሲሞክር በህብረተሰቡ ትብብር በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከሀርቡ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ።

በተከሳሽ ማሙሽ ጋጀቦ ላይ ምርመራ ተጣርቶ ዓቃቤ ህግ ክስ ከመሰረተበት በኋላ ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቦሌ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሹን ያርማል ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል በማለት በ2 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል።

ወንጀልን ለመከላከል እና ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ለማድረግ በሚከናወኑ ተግባራት ህብረተሰቡ እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ፤ ተመሳሳይ ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ በእንቅስቃሴ ወቅት በቂ ትኩረት መስጠትና ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግም መልዕክቱን አስተላልፏል።

#ዳጉ_ጆርናል


የፀጥታው ምክርቤት የጋዛን የተኩስ ማቆም እና የእርዳታ አቅርቦትን የሚጠይቅ ውሳኔ ላይ ድምጽ ሊሰጥ ነው

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በዛሬው እለት በጋዛ የተኩስ ማቆም እና ያልተገደበ የሰብአዊ አገልግሎት አቅርቦትን የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሏል። የእስራኤል ቁልፍ አጋር የሆነችው አሜሪካ ውጊያ እንዲያቆም የሚጠይቅ ጽሑፍ ከከለከለችበት ካለፈው ዓመት ህዳር በኃላ 15 አባላት ያሉት ጥምረት በጉዳዩ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ድምጽ ይሰጣሉ።

አዲሱ ውሳኔ "በሁሉም ወገኖች የተከበረ በጋዛ አፋጣኝና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ቋሚ የተኩስ አቁም ይጠይቃል" የተባለ ሲሆን በተጨማሪም "በሃማስ እና በሌሎች ቡድኖች የተያዙ ሁሉም ታጋቾች በአስቸኳይ፣ በክብር እና ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ" ይጠይቃል።

በፍልስጤም ግዛት ውስጥ ያለውን “አሰቃቂ የሰብአዊነት ሁኔታ” ላይ በማስመር፣ የውሳኔ ሃሳቡ የሰብአዊ እርዳታ ወደ ጋዛ መግባት ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ ይጠይቃል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል


በሸካ ዞን የገዛ ባለቤቱን ደብድቦ የገደለዉን ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በሸካ ዞን የኪ ወረዳ ፊዴ ቀበሌ ልዩ ስፍራዉ ጨቦ ተብሎ በሚጠራቅ አካባቢ ነው።

ተከሳሽ የሆነው ግለሰብ ተስፋዬ በቀለ የተባለ ሲሆን ከምሽቱ 2:30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በባል እና ሚስት መካከል በተፈጠረ ጊዜያዊ ፀብ ባል የገዛ ሚስቱን ላይ የግድያ ወንጀል መፈፀሙ ተገልጿል ።

ፖሊስ በምርመራዉ እንዳረጋገጠዉ በሁለቱ መካከል በዕለቱ በተፈጠረ አለመግባባት ባል የሚስቱን አንገቷን አንቆና ልቧ አከባቢ በቦክስ በበመምታት መሬት ላይ ይጥላታል።

በመቀጠልም በወደቀችበት እጇን ወደኋላ በኃይል ጠምዝዞ በመያዝ በእግሩ በእርግጫ በተደጋጋሚ በመደብደብ ህይወቷ  እንዲያልፍ ማድረጉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የሸካ ዞን ፍትህ መምሪያ የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ መነሻ በማድረግ ተከሳሽ ተስፋዬ በቀለ የኢፌድሪ ወንጀል ህግ አንቀፅ 539/1/ሀ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የግድያ ወንጀል በመፈፀሙ ዐቃቤ ህግ ግለሰቡን በከባድ የሰዉ መግደል ወንጀል ክስ መስርቶበት ፍርድ ቤት አቅርቦታል።

የክስ መዝገቡን ሲመለከት የቆየዉ የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችሎት  የሰዉ ምስክሮችን አድምጦ  ዐቃቤ ህግ ከሶ ያቀረበዉን ክስ ተከሳሽ የማስተባበል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛ ብሎታል።

በዚሁ መሠረት የሸካ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቴፒ ምድብ ችሎት ተከሳሽ ተስፋዬ በቀለን በ12 አመት እስራት እንዲቀጣ ዉሳኔ ማስተላለፉን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

Показано 20 последних публикаций.
OSZAR »