Postlar filtri


Online ስራ መስራት እምትፈልጉ በአጠቃላይ
እናም በአጭር ጊዜ መለወጥ እምትፈልጉ
ምንም አይነት ኢንቨስት ሳታደርጉ በቀን እስከ 30$ መስራት እምትችሉበት እድል

መስራት እምትፈልጉ ብቻ እፈልጋለሁ እያላችሁ በዚህ ሊንክ አሳውቁኝ

https://t.me/Online123u


" ታጣቂዎቹ በየመኪናው የነበሩ ሹፌሮችንና ተሳፋሪዎችን ሳይቀር ነው እየዞሩ የገደሉት " - የአይን እማኝ

ከጎንደር ወደ መተማ በእጀባ ሲሄዱ በነበሩ አሽከርካሪዎች ላይ ከጫካ የወጡ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከ20 በላይ አሽከርካሪዎች እና ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።

ከትላንትና በስቲያ ሰኞ ሰኔ 16/2017ዓ.ም ከጎንደር ተነስቶ በእጀባ ወደ መተማ ሲጏዙ በነበሩ ብዛት ባላቸው መኪኖች ላይ " መቃ" ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ከጫካ የወጡ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት ከ20 በላይ አሽከርካሪዎችና ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገራቸ የአይን እማኞች ገልፀዋል።

ስሙ እንዳይጠቀስ የጠየቀን በቦታው የነበረ አንድ በተለምዶ " አባዱላ " ተብሎ የሚጠራው መኪና አሽከርካሪ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፦

" ከጎንደር ወደ መተማ ለመሄድ አጃቢ ስጠብቅ ቆየሁ ከ9:00 በኃላ አንድ አራት ከሚሆኑ ሹፌር ጏደኞቼ ጋር ተነጋግረን እንሄድ በቃ ቀረጥ ከፍለን ብናልፍ ይሻላል ተባብለን ጉዞ ጀመርን።

ከዛ ' መቃ ' የሚባለው ቦታ ላይ ቆመን ለታጣቂዎቹ ቀረጥ ለመክፈል ተራ እየጠበቅን እያለ ከኃላ ሌሎች መኪኖችን ያጀበ አንድ ፓትሮል ሙሉ አድማ ብተና ፖሊስ መጣ ከዛም ታጣቂዎቹ ' መኪኖቹን አስቁሟቸው ቀረጥ ከፍለው ነው የሚያልፉ ' ሲሉ ነገሯቸው ፖሊሶቹም ወርደው ወደ ታጣቂዎቹ ' የታጀበ ተሽከርካሪማ አይከፍልም ' በማለት መልስ ሰጡ። ታጣቂዎቹ መልሰው ' እና ጫካ ያለው ታጣቂ ምን ሊበላልህ ነው ? ' ብለው መለሱ። በዚህ ጭቅጭቅ ተነሳ። በጭቅጭቁ መሀል አንድ ታጣቂ ይመታል ወዲያውኑ ሁኔታው ተቀያየረ።

ከጫቃ በርካታ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች እየተኮሱ ወጡ ፖሊሶችና ታጣቂዎች ሲጨቃጨቁ ከመኪናቸው ወርደው ጭቅጭቁን ከበው ሲሰሙ የነበሩ አሽከርካሪዎች በሙሉ ተገድለዋል።

በኃላም ታጣቂዎቹ በየመኪናው የነበሩ ሹፌሮችንና ተሳፋሪዎችን ሳይቀር ነው እየዞሩ የገደሉት በአጠቃላይ ከ20 በላይ ሹፌሮችና ንፁሃን ተገድለዋል።

አስከሬናቸውም ትላንት ነው የተነሳው የጎንደር መተማ መንገድ ከትላንት በስቲያ ጀምሮ ተዘግቷል እኔም ትላንት በአብድራፊ ዞሬ ነው ወደ ጎንደር የገባሁት " ብሏል

ጭኑ ላይ በሁለት ጥይት ተመትቶ በመተማ ሆስፒታል እየታከመ ያለ አንድ የአይሱዚ ረዳት መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የተናገረው የአይን እማኝ ደግሞ፦

" ወደ መተማ በእጀባ እየተጏዝን እያለን ነበር ተኩሱ የተጀመረው።

እኔና ሹፌሩ መኪና ውስጥ ተቀምጠን እያለ አንድ ታጣቂ መጥቶ ሹፌሩን ገደለና እኔን ሁለት ግዜ ጭኔ ላይ ተኩሶ አቆሰለኝ።

ይህ የሆነው ከ10:30 እስከ 11:00 ሰዓት ነው ታጣቂዎቹ የሚፈልጉትን ከገደሉ በኃላ ሄዱ ብዙ ቆይቶ መከላከያ መጣ የመጣውም ከምሽቱ 2:30 አካባቢ ነበር እኔንም አንስተው ወደ ሆስፒታል የላኩኝ በዚህ ሰዓት ነው።

ከ10:30 እስከ ምሽቱ 2:30 ድረስ ከጏደኛየ አስከሬን ጋር መኪና ውስጥ ነበር የነበርኩት።

ትላንት 18 አስከሬን ተነስቶ ወደ መተማ መጥቷል ከእነዚህ ውስጥ አብዛኛዎቹ የማውቃቸው ሹፌሮች ናቸው " ብሏል።

ሌላው በአንድ ሚኒ ባስ ውስጥ ተሳፍሮ ሲጏዝ የነበረ እና አሁን ቆስሎ መተማ ሆስፒታል የሚገኝ ተሳፋሪ ደግሞ ፦

" ተኩሱ ሲበዛ ወርደን በአንድ የጭነት መኪና ጉማው ስር ተኛን እንደገና ተነስተን እየሮጥን እያለን እግሬ ላይ በጥይት ተመትቼ ወደኩ " ብሏል።

በመተማ ሆስፒታል የሚሰራ አንድ ስሙን መግለፅ ያልፈለገ የህክምና ባለሙያ ትላንት የ3 ሹፌር አስከሬን በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ መመልከቱንና ቆስለው የመጡ ሰዎች በሆስፒታሉ ማከሙን ነግሮናል።

ይህው የህክምና ባለሙያ ቆስለው የገቡ ሰዎች ነግረውኛል ያለውን መረጃ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲገልፅ " እርስ በራሳቸው ሲለሚተዋውቁ ሲነጋገሩና ሲደዋወሉ ነበር ከዚህ ተነስተው 21 ሹፌሮች ብቻ ሙተዋል ብለው ነግረውኛል " ብሏል።

የአብዛኛዎቹ ሟቶች አስከሬን ወደ ሆስፒታል አልመጣም ሲልም አክሏል።

ሌላው ተኩስ ከመጀመሩ በፊት በ3 ኬላዎች ላይ 6 ሺ ብር ቀረጥ ከፍሎ ያለፈው ሌላው አሽከርካሪ ሲናገር ምንም እንኳን መንገዱ አለም አቀፍ ቢሆንም ትኩረት ያልተሰጠው ሽፍታ እንደልቡ የሚፈነጭበት መንገድ ነው ይላል።

" በዚህ መስመር በሆና ፣ ግንትና መቃ በሚባሉ ቦታዎች ላይ 3 ኬላዎች አሉ እንደ ህጋዊ ተቆጥረው ነው ገንዘብ የሚሰበስቡት ሁለት አመትም እየተጠጋቸው ነው " ብሏል።

" ' መቃ ' ላይ ታጣቂዎች ምንም ነገር የሚፈሩ አይደሉም እንዴት የመንግሥት ፀጥታ ኃይል አጅቦ የሚያልፍን ተሽከርካሪ ቀረጥ ክፈል ይላሉ ከዛም አልፈው ይከራከራሉ ፤ ፀጥታ ኃይል ላይም ይተኩሳሉ ? ሽፍታ ይሄን ያህል ድፍረት ከየት አመጣ ከጀርባቸውስ እነማን ቢኖሩ ነው ? " ሲል ጠይቋል።

በጥቃቱ ዙሪያ እስካሁን ከመንግስትም ሆነ ከሌላ ሶስተኛ ወገን የተባለ ነገር የለም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ባህር ዳር
#TikvahEthiopiaFamilyBD

@tikvahethiopia


በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የሚፈጠሩ የእርቃን ምስሎች ስጋትነታቸው ጨምሯል !

➡️ " አንዳንዶች እነዚህን ምስሎች የቀድሞ የፍቅር አጋራቸውን ለመበቀል ይፈጥራሉ " - ተመራማሪዎች


ዓለማችን በተለያየ ጊዜ በርከት ያሉ የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን እያስተናገደች ነው የመጣችው። ከቴክኖሎጂዎቹ ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩ ስጋቶችንም በዛው ልክ አስተናግዳለች።

አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የወቅቱ አነጋጋሪው ቴክኖሎጂ ሲሆን ጥቅሙም ስጋቱም በዛው ልክ እየጨመረ መጥቷል።

በዓለም ላይ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በመታገዝ የሚፈጠሩ የእርቃን ምስሎች ስጋትነታቸው ከቴክኖሎጂው መዘመን ጋር እየጨመረ መጥቷል።

የአሜሪካ 38 ግዛቶች በዲፕፌክ የሚሰሩ የህፃናት የእርቃን ምስሎች ላይ እገዳ ቢጥሉም የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዌብሳይቶች የእርቃን ምስሎችን ለመስራት በመቅለላቸው ስጋታቸው አይሏል።

በእነዚህ ዌብሳይቶች ሰዎች የሚያውቋቸውን ሰዎች ምስል በማስገባት ወደ እርቃን ምስልነት እንደሚቀይሩ ተገልጿል። ምስሎቹ ለእውነትነት የቀረቡ በመሆናቸው ሰዎች ለመለየት እንደሚቸገሩ ባለሙያዎች አስረድተዌ።

የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያው ማይክል ዚመር ፤ ምስሎቹ ፍፁም እውነተኛ እንደሚመስሉና በርከት ያሉ የመተግበሪያ ድርጅቶች እንደዚህ አይነት ምስል የሚሰሩ መተግበሪያዎችን ማስወገዳቸውን ገልጿል።

ይህንን የሚሰሩ ድህረገጾች ግን አሁንም መኖራቸውን ባለሙያው ተናግሯል።

ዚመር " የፎቶ ኤዲቲንግ ቴክኖሎጂው በጣም ዘምኗል " ያለ ሲሆን " አሁን ላይ እነዚህን የእርቃን ምስሎች ለመፍጠር አንድ ክሊክ ብቻ በቂ ነው " ሲል አብራርቷል።

ኤሊስተን ቤሪ የተባለች የ14 አመት ልጅ በእንደዚህ አይነት መንገድ የእርቃን ምስል እንደተሰራባት ትናገራለች።

ይህንን ምስሏንም ከ2400 የሚበልጡ የትምህርት ቤቷ ተማሪዎች እንደተመለከቱት ገልጻለች።

' ቶርን ' የተሰኘ ድርጅት ዕድሜያቸው ከ13-20 በሚሆኑ 1200 ልጆች ላይ ጥናት ማድረጉን ገልፆ በጥናቱ ከስምንቱ ልጆች አንዱ በዲፕፌክ በተሰራ የእርቃን ምስል የተጠቃ ሰው እንደሚያውቅ እንደዚሁም ደግሞ ከ17 ሰዎች አንዱ እራሱ የዚህ ድርጊት ሰለባ አንደሆነ መታወቁን ይፋ አድርጓል።

ተመራማሪዎች አንዳንድ ህፃናት እነዚህን ምስሎች ማወቅ ስለሚፈልጉ ብቻ ይፈጥራሉ ያሉ ሲሆን አንዳንዶች የቀድሞ የፍቅር አጋራቸውን ለመበቀል ይፈጥራሉ ብለዋል።

በአሜሪካ በርካታ ግዛቶች ያለ ግለሰቡ ፈቃድ የእርቃን ምስል መፍጠርና ማጋራት ወንጀል ቢሆንም አሁንም ጉዳዩ አስጊነቱ በመጨመሩ ጥንቃቄ ያሻል ተብሏል።

በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በመታገዝ የሚፈጠሩ ምስሎች እና ቪዲዮዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ውስብስብ እየሆኑ የመጡ ሲሆን እውነተኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ስለሚከብድ ነገሩን በጥንቃቄ ማየት ይገባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከፎክስ 6 ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia




" በተወሰኑ ቦታዎች ኃይል እየተመለሰ ነው " - የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ በከፊል የተቋረጠው ኃይል በተወሰኑ አካባቢዎች መመለስ እንደጀመረ የኢትዮጵያ ኤሌትክሪክ ኃይል አሳውቋል።

" በተቀሩት አካባቢዎችም በየደረጃው መልሶ ኃይል የማገናኘት ስራ እየተሰራ ነው " ብሏል።

የዩቱብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
አዳዲስ መረጃዎችን ያግኙ

👇👇👇
https://www.youtube.com/@TIKVAHNEWS12


" ኃይል ተቋርጧል ! "

አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል።

በዋናው የኤሌክትሪክ መስመር /ግሪድ/ ባጋጠመ ቴክኒካል ብልሽት ምክንያት አዲስ አበባን ጨምሮ በሃገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።

የተቋረጠውን የኃይል አቅርቦት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በበኩሉ በተወሰኑ አካባቢዎች በሲስተም ላይ በተፈጠረ ችግር ከፊል የኃይል መቋረጥ ማጋጠሙን ገልጿል።

" አዲስ አበባን ጨምሮ በአንዳንድ የሀገሪቱ ከተሞች ያጋጠመውን የኃይል መቋረጥ ለመመለስ የብሔራዊ የኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል፣ የኃይል ማመንጫዎች እና የማከፋፈያ ጣቢያዎች የኦፕሬሽን ሰራተኞች ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛሉ " ነው ያለው።

ኃይል በተቋረጠባቸው አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች የተቋረጠው ኃይል እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንዲጠብቁም ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia


#UndercoverInvestigation

" ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን አዋጁ አይፈቅድም " - የፍትሕ ሚኒስቴር

የፍትሕ ሚኒስቴር ፤ በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን እንደማይፈቅድ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ሰሞኑን በፓላማው የፀደቀውን የተሻሻለ አዋጅ በተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

በዚህም " አዋጁን አንዳንዶች የተረዱበት መንገድ ልክ አይደለም " ብሏል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር ምን አለ ?

" አዲሱ አዋጅ ከመደበኛ የወንጀል መርመራ ሂደት የወጣ መንገድን የሚከተል እንደሆነ ሰው ሊረዳው ይገባል።

አዲሱ አዋጅ ልክ በመደበኛው የምርመራ ሂደት እንደሚደረገው ተጠርጣሪዎችን በፍርድ ቤት መያዣ መያዝ ፣ ሰነዶችን ማሰባሰብ፣ ምስከሮችን መስማት እና መሰል ሂደቶችን አይከተልም።

አዋጁ ወስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን ከመሰረቱ ለመለየት የሚስችል የምርመራ ሂደትን የሚከተል ነው።

ለምሳሌም፦ መርማሪው አካል ወንጀለኞችን መስሎ ተቀላቅሎ ወይንም አብሮ በመስራት፣ ተባባሪ መስሎ አብሮ ውሎ በማደር፣ ሲሸጡ ገዢ መስሎ ፣ ሲገዙ ሻጭ መስሎ ሊሆን ይችላል።

ምርመራውን የሚየካሂደው አካል ምረመራ ማድረግ የሚችለው የፍርድ ቤት ተዕዛዝ ካገኘ ብቻ ነው።

ፍርድ ቤት በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራ ተግባራዊ እንዲደረግ በአሳማኝ ምክንያት ሲፈቅድ ምርመራው የሚፈጸምበትን ዘዴ ፣ የአተገባበር ሁኔታ ፣ የሚከናወንበትን ጊዜ በትዕዛዙ ላይ በግልጽ ማስቀመጥ እንዳለበት አዋጁ ደንግጓል።

እንደሚባለው አዋጁ ተጠርጣሪን አስሮ እያሰቃዩ አይመረምርም ይህም  ፍጹም ስህተት ነው። በማስገደድ ማስረጃ የሚሰበሰብበትም አይደለም።

መርማሪው ፍርድ ቤት አሳማኝ ምክንያት ሲፈቅድለት በሽፋን ስር የሚደረግ ልዩ የምርመራ ዘዴን ይተገብራል ሲባል በተጠርጣሪዎች ወይም በሌላ ሦስተኛ ወገኖች ላይ ወንጀል ሊፈጽምባቸው ይችላል፤ ወንጀሉን ከፈጸመባቸው በኋላ በወንጀል አይጠየቅም የሚል አይደለም።

ከተጠርጣሪዎች ጋር የወንጀል ተካፋይ ወይም ግብረ-አበር በመሆን በራሱ ፈቃድ አስቦና ፈቅዶ ሳይሆን ፦
- ያለፈቃዱ፣
- ተገዶ፣
- በተጽእኖ፣
- በተጠርጣሪዎች ሕገ ወጥ ትዕዛዝ ወይም ከአቅሙ በላይ በሆነ ማንኛውንም ምክንያት ሌላ ከባድ ጉዳትን ለማስቀረት ወይም የተሰጠውን ሕጋዊ ተልእኮ ለማሳካት ሲል ወንጀል የሚፈጽምበት ሁኔታ ሲኖር ከወንጀል ክስ #ነጻ የሚደረግበትን ሁኔታ ለማመላከት የተደነገገ ድንጋጌ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። " ብሏል።

በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ከሰሞኑ መፅደቁ ይታወሳል፡፡

ይህም መርማሪዎችን ወንጀል እንዲፈፅሙ በር ይከፍታል በሚል ከምክር ቤት ትችት ሲቀርብበት ነበር።

#MinistryofJustice #FinancialIntelligenceService #ShegerFM

@tikvahethiopia


#Repost  #ExitExam

👉የመውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎች መረጃ አሰጣጥ


፨ለሁሉም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት

ጉዳዩ- የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ያላለፉ ተማሪዎችን መረጃ አሰጣጥን ይመለከታል!


የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሀገራዊ የቅድመ-ምረቃ መውጫ ፈተና ከሰኔ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ተወስኖ የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 919/2014 ወጥቶ ተግባር ላይ ውሏል፡፡ በዚህ መመሪያ አንቀጽ 12 (12.3) ላይ የመውጫ ፈተና ውጤት በተማሪዎች ሰርተፍኬት (Temporary Degree) ወይም ትራንስክሪፕት ላይ አልፏል (PASS) ወይም ወድቋል (FAIL) በሚል እንዲቀመጥ እና ከዚህ ደብዳቤ ጋር አባሪ በተደረገው ሰርተፍኬት ፎርማት መሠረት እንዲፈጸም እናሳውቃለን፡፡ (ትምህርት ሚኒስቴር)


የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በነፃ ተሰናበቱ።

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬን የሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነፃ አሰናበታቸው።

13 ዓመት ተፈርዶባቸዉ በማረሚያ ቤት የነበሩት የቀድሞው ከንቲባ በዛሬዉ ዕለት በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነበራቸው ችሎት የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከወሰነባቸው የፍርድ ዉሳኔ በነፃ መሰናበታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተነግረዋል።

የቀድሞው ከንቲባ በአጠቃላይ ከቀረበባቸዉ 7 የክስ መዝገቦች በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው 2 ክሶች  በነፃ ተሰናብተው የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ3 ክሶች ነፃ በ2 ክሶች ደግሞ 13 ዓመት እስራት ፈርዶባቸው እንደነበር ይታወሳል።

ከፍርዱ በኃላ ባለቤታቸው ወ/ሮ ዜናዬ ተሰማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ " ፀጋዬ ቱኬ የፖለቲካ እስረኛ እንጂ ጥፋተኛ እንዳልሆነ፣ ለሁለት ዓመት የሚጠጋ ጊዜ ያለ አግባብ በእስር ቤት እንደተንገላታ ፣ጉዳዩን የያዙ ዳኞች በባለስልጣን ጫና ሲቀያየሩ እንደነበር፣ በአጠቃላይ የፍርድ ዉሳኔዉ ጣልቃገብነት የታየበት እንደነበርና ይግባኝ እንደጀመሩ " ተናግረው ነበር።

የቀድሞው ከንቲባ በዛሬው ዕለት በሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በነጻ ተሰናብተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የችሎት ሂደቱን ቦታዉ ላይ በመገኘት የተከታተለ ሲሆን የዉሳኔዉን አፈፃፀም የክልሉ ማረሚያ ተቋም የወሰደ ሲሆን ከምሳ ሰዓት በኋላ ከእስር እንደሚለቀቁ ከስፍራዉ ማረጋገጥ ተችሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia


“ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል ” - ጤና ሳይንስ ኮሌጁ

ከተላላፊዎቹ ይልቅ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ህዝቡን ለሞት እያጋለጡት መሆኑን እና በህፃናት የሚስተዋለው የስኳር በሽታ አሳሳቢ ስለመሆኑ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የኮሌጁ ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ተባባሪ ፕሮፌሰር አለሙ ጫሚሶ በገለጹት መሠረት፣ “ድሮ ተላላፊ በሽታዎች ነበሩ፤ አሁን ግን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ናቸው ህዝቡን ለሞትና ለጤና ችግር እያጋለጡት ያሉት”።

ክትባትን ጨምሮ የተለያየ ሥራዎች በመሰራቸው በተላላፊ በሽታዎች የሚያጋጥሙ ሞቶች መቀነስ ትችሎ እንደነበር አስታውሰው፣ “በብዙ ምክንያቶች ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምረዋል” ብለዋል።

በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ተጓዳኝ በሽታ በማምጣት፣ በጤናና በፋይናንስ ጉዳይ በህዝቡ ላይ ጫና መፍጠሩን ገልጸው፣ “ድሮ ታይፎድ፣ ታይፈስ ነበር፤ አሁን ግን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ነው የምናክመው” ነው ያሉት።

“ህፃናት ላይ ስኳርና ካንሰር በጣም በዝቷል። እዛ አካባቢ ያለው ህክምናም ወጪው በጣም ከባድ ነው” ሲሉ ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

መንስኤው ምንድን ነው?

ዩኒቨርሲቲው ጥናት አጥንቶ እንደነበር የገለጹት ተባባሪ ፕሮፌሰሩ፣ “በእኛ የተለዩ ነገሮች አሉ፤ የበሽታው ስርጭት ሲዳማ በስድስት ወረዳዎች የግፊትና ስኳር በሽታ ከሌሎቹ ይሰፋል። ለምን? የሚለውን ስናጠና አፈር፣ ውሃ ላይ በተለየ ሁኔታ መጥናት ያለባቸው ነገሮች እንዳሉ” መረዳታቸውን ገልጸዋል።

ከግኝቱ በመነሳት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው በጥናቱ መሰረት “32% ደርሷል፤ የግፊት ፕሬቫለንሲ፤ የስኳር ደግሞ 12% ደርሷል። አንዱ በሽታ አንዱን ያመጣል። ግፊትና ስኳር እየበዛ በሄደ ቁጥር የኩላሊት በሽታም እየበዛ ነው” ብለዋል።

ብዙዎች ሳያውቁት ተጠቅተው እየተገኙ በመሆኑ በተለይ የስኳር በሽታን በተመለከተ በየወቅቱ የጤና ምርመራ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia


🆕

እስራኤል የፈጸመችውን ጥቃት ተከትሎ ኢራን አጸፋዊ ሚሳኤሎችን ያስወነጨፈችበት የሁለቱ አገራት ፍጥጫ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።

- እስራኤል በድጋሚ አርብ ምሽት በፈጸመችው ጥቃት በርካታ ኢላማዎች መምታቷን አስታውቃለች። በቴህራን የመኖሪያ ህንጻ ላይ በተፈጸመ ጥቃት 20 ህጻናትን ጨምሮ 60 ሰዎች መሞታቸውን የኢራን መንግሥታዊ ሚዲያ ዘግቧል።

- በኢራን አጸፋዊ የሚሳኤል ጥቃቶች ሶስት ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል።

- አሜሪካ ወደ ግጭቱ እንድትገባ ከተደረገች ሁኔታዎች በበለጠ ሊያገረሹ ይችላሉ ተብሏል።

- ኢራን ሚሳኤሎችን የምታስወነጭፍ ከሆነ መዲናዋ " ቴህራን ትቃጠላለች " ሲሉ የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ አስጠንቅዋል።

- የእስራኤል መከላከያ ኃይል ዘጠኝ የኢራን የኒውክሌር ሳይንቲስቶችን እና ባለሙያዎችን ገድያለሁ ብሏል። ጦሩ ሐሙስ ለአርብ አጥቢያ በፈጸመው ተከታታይ ጥቃት የገደላቸው የኒውክሌር ሳይንቲስቶች ስድስት ናቸው ብሎ ነበር።

- ኢራን በእስራኤል ላይ እየወሰደች ያለችውን አጸፋዊ እርምጃ ለማስቆም አሜሪካ፣ ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደም እስራኤልን የሚያግዙ ከሆነ በቀጣናው የሚገኙ የጦር ሰፈሮቻቸውን ኢላማ እንደምታደርግ ማስጠንቀቋን የኢራን መንግሥታዊ ሚዲያ ዘግቧል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የቢቢሲ ሲሆን ቪድዮው ከተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች የተወሰደ ነው።

የዩቱብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
አዳዲስ መረጃዎችን ያግኙ

👇👇👇
https://www.youtube.com/@TIKVAHNEWS12


የወረቀት ዘንቢል በዚህ ግዜ አዋጭ የቢዝነስ ስራ ሲሆን
በ10 ሺህ ብር መጀመር ይቻላል
ሙሉ አሰራሩን ተመልከቱ በአጭር ጊዜ ይለወጡ

https://youtu.be/TivhJ9hhsMI?si=i7IWYVkDZDNqemuV


እስኪ አዲስ አበባ ላይ ፔስታል መጠቀም እንደሚያስቀጣ ምታውቁ 👍👍 ምልክት አሳዩን




#Update

" ከ564 በላይ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ከእስር ተፈተዋል " - የወላይታ ዞን ፖሊስ

➡️ " የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ በወቅቱ የወሰዱት እርምጃ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ አድርጓል ! "

በአዲስ አበባ ፖሊስ በእስር ላይ የነበሩ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች መለቀቃቸውን የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ አሳውቋል።
 
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰኔ 01/2017 ዓ/ም የድቻ ደጋፊዎች በከተማ ውስጥ ተዘዋዉረዉ በፈጠሩት አለመግባባት ምክንያት የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፌዴራል ፖሊስና ሌሎች የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው የድቻ ደጋፊዎች መካከል፦
- በቂርቆስ ክፍሌ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፑፑላሬ ፖሊስ ጣቢያ 245 ፣
- ቦሌ ቡልቡላ 68 ፣
- በየካ ክፍለ ከተማ 50፣
- ልደታ ክፍለ ከተማ 201 የተጠረጠሩ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና ከአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ጋር በመነጋገር ከእስር እንዲፈቱ መደረጋቸው ተገልጿል።

አጠቃላይ በተለያየ ክፍለ ከተማ የታሰሩ  ከ564 በላይ የወላይታ ድቻ ደጋፊዎች ናቸው ከእስር የተፈቱት።

የዞኑ ፖሊስ " የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስና የአዲስ አበባ ፖሊስ የድቻ ደጋፊዎች በከተማዉ ውስጥ በተለያየ ቦታ ተንቀሳቅሰዉ የፈጠሩትን ያለመግባባት ለመፍታት በወቅቱ የወሰዱት እርምጃ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ ያስቀረ በመሆኑ ያስመሰግናል " ብሏል።

አሁን ላይ ሌሎች የተወሰኑ በወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው ጉዳዮች በፍርድ ሂደት የሚገኙ መኖራቸው ተጠቁሟል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
የዩቱብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
አዳዲስ መረጃዎችን ያግኙ

👇👇👇
https://www.youtube.com/@TIKVAHNEWS12


“ አልተያዘም፤ በፓሊስ ቁጥጥር ሥር አይደለም ” - የአዲስ አበባ ፓሊስ  ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

አትሌት ገለቴ ቡርቃ 10 ቤቶች እና 4 ተሽከርካሪዎች በቀድሞ ባለቤቷ እንደተሸጡ በመግለጽ ሰሞኑን ፍትህ ስትጠይቅ ተስተውላለች።

አትሌቷ በገጠማት ጉዳይ ፍትህ እንዲሰጣት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንም ትላንት መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል።

የአትሌቷ ጉዳይም ብዙዎችን በማስቆጣት “ፍትህ ለገለቴ” የሚል አስተያየትን በማስተጋባት በማኀበራዊ ሚዲያው በሰፊው እየተሰራጨ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እያለ ከትላንት ምሽት ጀምሮ ደግሞ “ የአትሌት ገለቴ ቡርቃ ባለቤት አቶ ታደለ ገብረመድህን በአዲስ አበባ ፓሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ ” የሚሉ መረጃዎች በማኀበራዊ ሚዲያው በሰፊው ተሰራጭተዋል።

የአትሌት ገለቴ ቡርቃ ባለቤት በፓሊስ ተይዟል?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ፤ የአትሌት ገለቴ ቡርቃ ባለቤት በፓሊስ ቁጥጥር ሥር ውሏል መባሉ እውነት ነው ? ሲል የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽንን ጠይቋል።

የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፣ “ ብዙ ሰው ያወራል። የለምኮ ፤ ፓሊስ ጋ የለም። እኛ ጋ የለም ” የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

ግለሰቡ እንዳልተያዘና “ የሀሰት መረጃ ” እንደሆነ የገለጹት ኮማንደር ማርቆስ፣ “ አልተያዘም። በፓሊስ ቁጥጥር ሥር አይደለም ” ሲሉም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

የዩቱብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
አዳዲስ መረጃዎችን ያግኙ

👇👇👇
https://www.youtube.com/@TIKVAHNEWS12


የዩቱብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ
አዳዲስ መረጃዎችን ያግኙ

👇👇👇
https://www.youtube.com/@TIKVAHNEWS12


" የኢትዮጵያን ሰላም የሚያናጋው 60% የኢትዮጵያ ሃብታም ነው " - ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)

➡️ " እየቀለባችሁ ፤ ፋይናንስ እያደረጋችሁ እኔን መልሳችሁ ' ሰላም ' ብትሉኝ አይሆንም። ሰላም ከፈለጋችሁ ፋይናንስ አታድርጉ ! "

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ከመላው ሀገሪቱ ከተውጣጡ የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት ባለሃብቶች የሰላም ችግር በስራቸው ላይ እንቅፋት መሆኑን አንስተዋል፡፡

ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ስለ ሰላም በሰጡት ማብራሪያ ባለሃብቶች ጫካ ያሉትን ታጠቂዎች በገንዘብ መደገፍ ወይም ማበረታታት እንዲያቆሙ አሳስበዋል።

ባለሃብቶች እውነተኛ ሰላም ፈላጊ ከሆኑ በጫካ ያሉ ኃይሎችን መደገፍ ፣ መቀለብ አቁመው ወደ ሰላም እንዲመጡ መምከር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

" ሰላም የሚፈልግ ካለ በእኛ በኩል ምንም ችግር የለውም እንቀበላለን እናተ ጫካ ብር አትላኩ " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ " መንግስት በሰላም የሚመጡ አካላትን ተቀብሎ ለማወያየት ዝግጁ ነው " ሲሉ ተናግረዋል፡፡

" ህግ ማስከበር ስራችን ስለሆነም የሚቀጣ ካለ እንቀጣለን " ሲሉ አክለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ሃብታሞች የሀገሪቱን ሰላም በማደፍርስ ላይ 60 በመቶ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ሲሉ ገልጸዋል።

" እየቀለባችሁ ፤ ፋይናንስ እያደረጋችሁ እኔን መልሳችሁ ' ሰላም ' ብትሉኝ አይሆንም። ሰላም ከፈለጋችሁ ፋይናንስ አታድርጉ " ሲሉ አሳስበዋል።

" የሰላም ችግር ትልቅ ኪሳራ ነው " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " ተቃዋሚዎችም ሆኑ ባለሃብቶች ሰላምን የማረጋገጥ ግዴታ የመንግስት ብቻ አድርገው በመውሰድ ከሃላፊነት መሸሽ ተገቢ አይደለም " ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል መንግስት ኮንትሮባንድን እና ህገወጥ የመሳሪያ ዝውውርን ለመቆጣጠር ባዘጋጃቸው የፍተሻ ኬላዎች የኮቴ እያሉ ገንዘብ የሚጠይቁ አካላት እንዳሉ በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ምላሽ፥ እነዚህ የፍተሻ ኬላዎች የማይኖሩ ከሆነ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎች እየገባ የሰዎችን ህይወት እንደሚቀጥፍ ተናግረዋል፡፡

ነገር ግን ገንዘብ ሳይጠየቅ ፍተሻ የሚደረግበትን መንገድ ለማመቻቸት መንግስት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል፡፡

#PMOffice #Ethiopia

@tikvahethiopia

18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »