👳🏽ባለዕዳው


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


ሁሉም ስለእኛ ነው ።
የምከትበው እይታዬን ብቻ ነው ! ወይ ልክ ነው ወይ አይደለም ፤ ልክ ካልመሰላቹ እየፈተፈትን እንወያይበታለን ወቢላሂተውፊቅ🙌
Buy ads: https://telega.io/c/baledaw

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


"ሺዓዋ እና የሙስሊሞች ጠላቷ ኢራን በከሀዲያን እየተጠፈጠፈች ነው" ። እናም ከፊሉ የሙስሊም አለም በደስታ ላይ ነው ....ተሳክቶላቸው ኢራንን ካጠፉ በኋላ ተራው የማን ይሆን ? የኳታር ? ወይስ የሳዑዲ ? ወይስ የሌላ ሙስሊም ሀገር ? ይህ ኡማ እያጨበጨበ የሚያስጠፋው የሙስሊም ሀገር ስንት ይሆን ?

እንዴት አቃጣይ እና ብሽቅ ኡማዎች ነን ግን ? አህ💔

231 0 2 10 19

ከ አንደኛው የአለም ጦርነት በፊት..... ማለትም በጣት ከሚቆጠሩት ጥቂት አመታቶች በፊት ስለነበረው አየርና የአለምን ሁኔታ አስተውላቹ ከነበር... ስታነቡ ከናንተው ጊዜ ጋር ስታነፃፅሩ ከነበር መደንገጣቹ አይቀርም ። አሁን አለም ያለችበት ሁነት የመጀመርያው የአለም ጦርነት ከመከሰቱ ጥቂት አመታት በፊት የነበረችውን ራሷን ነው ! ያን ሰቀቀን ከመቀበሏ በፊት ያሳለፈችውን አመታት አሁንም እየደገመችው ነው ።

ቀርበናል መሠለኝ ....ነገርዬው ሳይደረስ አልቀረም !


እኔ ምለው ቻናሉ ፍልስፍና የሚመስሉ ሀሳቦች ቢነሱበት ቅር አይላችሁማ ? ማለት የፈላስፎችን ንግግር መለጣጠፍ ምናምን ሳይሆን የዱንያን ልባስ ገልጠን ለመመልከት መሞከር...አይ ይሄ እንዲህ ነው ብሎ ማህበረሰቡ የወሰናቸውን ነገሮች እየተቃረኑ በሌላ አንግል ለማየት መሞከር በቃ የህይወትን ክፍለአካሎች የምንለካበት አይነት ቻናል ቢሆን ወይ እንዲህ አይነት ሀሳቦች ቢቀላቁ ይደብራል ? የግል እይታ በገፍ ቢለቀቅ ይደብራል ?


ባይዜ....ደስታ ይገባቹኋል

አትዘኑ❤️


ሲመስለኝ ደስተኛ የመሆኛው ሰበብ አሁንን መቀበል ነው ። አሁን ያለንበትን ተቀብለን ቦታችን የሚጠይቀንን ነገር በሟሟላት እና በሆንነው ነገር ላይ ስክነት እና ፍላጎት በመጨመር ደስታ የሚሉትን ነገር መሳብ ሳንችል አንቀርም ።
ማለትም ተማሪው በተማሪ ማንነት መኖር ...ተማሪነት በሚጠይቀው ነገር ውስጥ መዝናናት ...ተማሪነትን ተቀብሎ ትኩረትን መሰብሰብ ፤ ሰራተኛው ስራውን ተቀብሎ እንደሰራተኛ መኖር...በስራው ውስጥ ማማረርንና መሰላቸትን ትቶ የስራውን ሂደት ቀላል እና አዝናኝ ማድረግ ።
እናትነት
አባትነትን
ባልነትን
ሚስትነትን
በቃ ሁሉንም ነገር ተቀብሎ አዝናኝ በሆነ መንገድ መስራት ....ለዚች ዓመት የምን መሳቀቅ? ለዚች ዱንያ የምን መሰባበር?


ነገራቶች ግራ የሚያጋቡበት አጋጣሚ ብዙ ነው ። ሁሉም ነገር ይሄድበት ከነበረው መንገድ ያፈነግጣል ። በህይወታችን ላይ ማዕበል ይነሳል ልባችን በድርቅ ይመታል አለመኖርን አጥብቀን የምንፈልግበት ከበድ ያለ ድክመት ይጫጫነናል መሰላቸት ይጠናወተናል ...
ከዛ አንዳንዴ መፍትሄው ዝም ብሎ መመልከት ይሆናል ....
ማዕበሉ እስኪረጋጋ መመልከት
ድርቁን የሚያርሰው ዳመና እስኪያዘንብ መጠበቅ በቃ መጠበቅ ! የምጠብቁት አይቀርም ❤️

(ባለዕዳው)

505 0 10 2 18

እእ....ተኙ በቃ😶


ኡፋ ትንፍስ😮‍💨


እምነቱን እንጂ አማኙን ተከታይ አንሁን ።

ብዙ ጊዜ እንደዚ አይነት ሀሳቦች አይነሱም ከተነሱም አብዛኛው ሰው በተቃራኒው ሀሳብ ላይ ስለሚሆን ፍራቻ ይኖራል ወይ ሀሳቡ ይዳፈናል ።

አሁን ላይ በኡስታዞች (በሰባኪዎች) ስሜት ኢስላምን መዝኖ እና ልኬት ሰጥቶ መገፋፋት ውስጥ ነን ...የሰውን ልጅ እጅግ ስሜታዊ ከሚያረጉት ነገሮች ውስጥ ዋነኛው ሀይማኖት ነው ይህ ስሜት በግለሰብ ደረጃ ሲሆን የተለመደ ሊሆንና ተንፀባርቆ ላይወጣ ስለሚችል ጉዳቱ እስከዚም ነው ግን ደግሞ በሰባኪዎች ዘንድ ስሜት ሲነግስ ወይ ደግሞ የስሜት ብልህነት የምንለው ነገር ሲጎድል ጉዳቱ ከራስ አልፎ ዲኑ ላይ ይታያል ። ነብያቶች የስሜት ብልህነት ላይ ጥግ የደረሱ እንዲሁም በመለኮት የሚታገዙ እንደመሆናቸው እጅግ አድል እና ትክክለኛ ናቸው ...እነሱን እግር በእግር በመከተል ላይ መዳረሻዎ ለምለም እንጂ ሌላ አይደለም! ግና እንደኛው አይነት ግለሰብ በሆነ እና እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ስሜት በሚፈተን ሰው ስር እምነትን ጠቅልሎ " በሄድክበት ውሰደኝ" አይነት መሰጠት ልክ ነው ብዬ አላስብም ። ሰባኪው የጠላውን መጥላት...የወደደውን መውደድ...የሰደበውን ማዋረድ...ያከበረውን መሰቃቀል አይነት አዕምሮን የማስረከብ አካሄድ እጅግ ቀፋፊ ነው ወላህ ።
ኢስላም የመጣው አቂል ለሆኑት...ማስተንተን ለሚችሉት ነው ..አቅል የሌላቸውማ ሁጃም የለባቸው ። አላህስ በቁርዓኑ ደጋግሞ "አታስተነትኑምን " ሲል ለምን ጠየቀን ?

በእምነት ሰበብ አለማሰብ...በእምነት ሰበብ ዝቅ ያለ ማህበረሰብ እንደመሆን የሚያናድድ ነገር የለም ! ኢስላም እኮ እጅግ ኋላ ቀር የነበሩን ማህበረሰቦች ...እጅግ ማሰብ ተስኗቸው በማሰብና ባለማሰብ መሀል ሲዋልሉ የነበሩ ማህበረሰቦችን በጥቂት አመታት ውስጥ ሀያል ያደረገ ትልቅ ሀይማኖት ነው ! አለምን ወደሚያንቀጠቅጡ ..አለምን ቅርፅ ወደሚያስይዙ ማህበረሰቦች የቀየረ ጥልቅ እምነት ነው ። ተውዋ በኢስላም ስም ጭፍን አትሁኑ...ተውዋ በኢስላም ስም አዕምሯችንን ከጥቅም ውጪ አናርግ።


ኢስላምን በሰባኪ ማንነት ልክ አሰፍተን አንልበስ...ዲኑን በጥቂቶች እሳቤ ጠቅልለን አንጉረስ ...ተው ግን 🙂


ውደዱ...አፍቅሩ ደስተኛም ሁኑ ።
የዚችን አለም ድክመት ማየት ከጀመራቹ...የህይወትን ዝቅታ ብዛት መቁጠር ከጀመራቹ ...የህመማቹን ክብደት መመዘን ከጀመራቹ ደስታችሁን እያጣችሁ ትሄዳላችሁ። የእይታችሁ ማረፍያ ዱንያ ስትሆን ውስጧ ባሉት ወንበዴዎች ሰበብ ሁሉ ነገር ያስጠላችኋል..እይታቹ በሰዎች አይን ሲሆን ደግሞ ህይወትን የመኖር እድል ታጣላቹ....በቃ የእይታቹ ማረፍያ የምትወዷቸው ሰዎች ይሁኑ ! የህይወትን ትርጉም በዛው በውዴታቹ ክብ ውስጥ አስገቡና ለምትወዱት በምትወዱት መንገድ ኑሩ...የዚች አለም ክርፋቷ የሚወገደው በፍቅር ሽታ ነው ።

በቃ ተፋቀሩ🙂

598 0 11 6 27

ነገሮች የሚስተካከሉት ምናልባት ጀነት ውስጥ ይሆናል ...አሁን ባላችሁበት ሁኔታ ውስጥ የተሻለ እስኪመጣ በሚል በማማረር አታሳልፉት ...አለ ኣ በጥንጡ ተቀብሎ አሁንን ማሳመር ነገር🙂


የሰው ልጅ ብዙ ነገር ይለያዩታል ከነዛም ውስጥ አንዱ ጥቅም ነው ።

የአረፋ ስጋ በዚህ ልክ ለያየን ማለት ነው☹️ ሶስት ቀን ሆነና🚶


እህ አህባብ አልጘፈላችሁማ .....ከዝሁር በኋላ ለመተኛት ያሰባቹ ወጣቶች አደብ ግዙ👐


መልካም ኢድ🫶


እና ኢድ ሙባረክ🫶


ጌታችን ሆይ በልቅናህ ይሁንብህ ካለንበት እታች ከፍ አርገን...በጥበብህ ወዳንተው አስጠጋን...በእዝነትህ ኋላችንን ሁሉ ምረህ ፊታችንን አስውብልን...በአዳኝነትህ ውጫዊውንም ውስጣዊውን ህመማችንን አሽርልን...በለጋስነትህ ውቧን ጀነት ለግሰን...በሀያልነትህ ጭቁኖቹን ከጭቆና አላቅልን ጋዛንና የሙስሊሙን አለም ሁሉ ካለበት ጭንቅ ፈርጀህ ድልን አምጣልን ።

ጌትዬ ላባችን ሁሉ ለውዴታህ ይሁን....ሀያታችን ሁሉ ለፍቅርህ ይሁን ...ውደደን🤍

አሚን!


ዱዓ እያረጋቹ ነው ?

ትርፍ ቦታ ካላቹ አንዲት ፍሬ ዱዓ ጨምሩልኝ🙂


ነገ የመጨረሻውም...ኸሚስም ነው ። የነገው ፆም እንደግል ሀላችን ፈርድ ነውና እንዳናሳልፈው ።


ዱዓም አደራ🙌


ፀዴ ኢፍጣር❤️


እየኖርን አይደለም !

የብስ ላይ የሚኖር አካል ውሀ ውስጥ ገብቶ ቢያልፍ ዋኘ እንጂ ሮጠ አይባልም ...ከውሀ አካል ወጥቶ አየር ላይ ቢቀዝፍ በረረ እንጂ ዋኘ አይባልም........አይደል ?
እንዲሁ ህይወትን ሳያውቅ በየሆኑ አካሎች የተቀመረ ጊዜ ያሳለፈ አካል ኖረ ሳይሆን ተወነ ነው መባል ያለበት ።
ከምዕተ አመታት በፊት የነበረው የህይወት ትርጓሜ እና አሁን ያለው የህይወት ትርጓሜ...ከምዕተ አመታት በፊት የነበረው አማኝነት እና አሁን ያለው አማኝነት ፍፁም የተለያዩ ሆነዋል ...ከመሆን ወጥተው ወደማስመሰል ወይ ደግሞ ወደመምሰል ተቀይረዋል ።
በርግጥ ሙሉ በሙሉ የሚፈረድብን አይደለንም ምክንያቱም የህይወት ጣዕም ተበርዞ...የመኖር ትርጉም ተሰርዞ የመጣን ትውልዶች ነን ! ለመወለድ ከመታሰባችን በፊት በተዘረጋ ወጥመድ ላይ የወደቅን ነን ። የኛ ትልቁ ችግር ይህን ወጥመድ ህይወት ብለን መቀበላችን ብቻ ነው ! ጥቂትም ከዚ ወጥመድ ለመላቀቅ አለመሞከራችን ነው ። ምናልባት አባቶቻችን ይህን ወጥመድ ተረድተው ቢሆን....እኛን ደግሞ ከመሰረቱ አሳውቀውን ለመላቀቅ እንሞክር ነበር...ከኛ የሚመጡት ደግሞ ይህን ወጥመድ በጥሰው ማለፍ ይችሉ ነበር ።
ስለዚህ ቢያንስ አባቶቻችን ያላስተዋሉትን የእድሜልክ ወጥመዳችንን እንመልከተው ...የታሰርንበትን ገመድ እንወቀው ...የተደበቀብንን ህይወት እንረዳው ከዚያ ኋላ ምናልባት የልጅ ልጆቻችን ከዚህ ወጥመድ አልፈው አለምን ውብ እና ኢስላምን የበላይ ያረጋሉ ።


እኛ ካልነቃን አንድ ትውልድ ነው የሚባክነው !


መልካም ኢፍጣር🙄

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »