የዓለማችን 7 ሀብታም ደራሲዎች 1️⃣
J.K. Rowling (ጄ.ኬ. ሮውሊንግ): የ"ሃሪ ፖተር" (Harry Potter) መጽሐፍ ተከታታይ ደራሲ ስትሆን 1 ቢሊዮን ዶላር የተጣራ ሀብት ያላት የመጀመሪያዋ ቢሊየነር ደራሲ እንደሆነች ይታመናል።
2️⃣
James Patterson (ጀምስ ፓተርሰን): እጅግ በጣም ዝነኛ ከሆኑ ደራሲዎች አንዱ ሲሆን በአሌክስ ክሮስ (Alex Cross) ተከታታይ ልብ ወለዶቹ ይታወቃል። የተጣራ ሀብቱ ወደ 800 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል።
3️⃣
Danielle Steel (ዳንኤል ስቲል): በሮማንቲክ ልብወለዶቿ የምትታወቅ ሲሆን ከ170 በላይ መጽሐፎችን አሳትማለች። ሀብቷ ከ600 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ይገመታል።
4️⃣
Stephen King (ስቲፈን ኪንግ): "የሆረር ንጉስ" በመባል የሚታወቀው ስቲፈን ኪንግ እንደ "The Shining" እና "It" ባሉ ስራዎቹ ዝነኛ ናቸው።ሀብቱ ወደ 500 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ይገመታል።
5️⃣
Paulo Coelho (ፓውሎ ኮኤልሆ): የብራዚላዊው ደራሲ "The Alchemist" በተሰኘው ታዋቂ መጽሐፉ የሚታወቅ ሲሆን ከ500 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሀብት እንዳለው ይገመታል።
6️⃣
John Grisham (ጆን ግሪሻም): በህግ ነክ ልብ ወለዶቹ ("The Firm," "The Pelican Brief") ዝነኛ ሲሆን ከ400 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሀብት አለው።
7️⃣
Nora Roberts (ኖራ ሮበርትስ): ሌላዋ ታዋቂ የሮማንስ ደራሲ ስትሆን፣ በርካታ ስራዎቿ የኒው ዮርክ ታይምስ የሽያጭ ዝርዝር ውስጥ መግባት ችለዋል። ሀብቷ ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል።
📚
@Bemnet_Library