#ExitExam
የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከነገ ሰኔ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።
ከ190 ሺህ በላይ ተፈታኞች የመውጫ ፈተናውን በ51 ዩኒቨርሲቲዎች በተዘጋጁ 87 የፈተና ማዕከላት ይወስዳሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 88 ሺህ የሚሆኑት ዳግም የመውጫ ፈተናውን የሚወስዱ ናቸው።
የመውጫ ፈተናው በ238 የትምህርት መርሐግብሮች በበይነ መረብ ነው የሚሰጠው።
የተከለከሉ ነገሮች ምንድናቸው ?➡️ የማይፈቀዱ የሂሳብ ማሽኖች (በአንዳንድ ፕሮግራሞች #ካልኩሌተር ማምጣት ይፈቀዳል፡፡ ሆኖም ግን ስልክ፣ ስማርት ዋች፤ ታብሌትና ተመሳሳይ ቁሶችን እንደ ካልኩሌተር መጠቀም ፈፅሞ አይፈቀደም። ሥራ ላይ የሚውሉ ካልኩሌተሮች የተራቀቁ እንዲሁም ፕሮግራመብል እንዳይሆኑ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል)፣
➡️ ተንቀሳቃሽ ስልክ፣
➡️ ሜሞሪ ያለው የእጅ ሰዓት፣
➡️ የተጭበረበሩ ሰነዶች፣
➡️ የራስ ያልሆነ መታወቂያ፣
➡️ አጫጭር ማስታወሻዎች፣
➡️ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት ክልክል ነው።
በተጨማሪም ፦
⚠️ አደንዛዥ ዕጽ ተጠቅሞ መምጣት፣
⚠️ ከፈተና አስፈጻሚዎች ጋር አሉታዊ ተጽእኖ ያላቸው ውዝግቦችን መፍጠር፣
⚠️ያለመታወቂያ ካርድ ወደ ፈተና ማእከል መሄድ፣
⚠️ ያለፈቃድ ፈተና ማዕከል መገኘት፣
⚠️ ለሌላ ሰው መፈተን ፍጹም የተከለከሉ የዲሲፒሊን ጥሰቶች ናቸው።
ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ ቀድመው በተመደቡበት የፈተና ክፍል መገኘት የሚኖርባቸው ሲሆን ፤ ከተመደቡበት ክፍል ውጪ መፈተን ውጤት ያሰርዛል።
✅ ተፈታኞች የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ይኖርባቸዋል።
መያዝ የሚፈቀደው የፋይዳ መታወቂያ ፦
- በኢትዮ ቴሌኮም ወይም የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት አማካኝነት የታተመ የፋይዳ መታወቂያ፣
- ከ "Fayda ID" ሞባይል መተግበሪያ ፣ ከቴሌብር ሱፐር አፕ፣ እንዲሁም ሲቢኢ ብር ሞባይል መተግበሪያ ላይ #QR_ኮድ በማውረድ እና በወረቀት በማሳተም መያዝ ይቻላል።
📵 ዲጂታል የፋይዳ መታወቂያ ኮፒ በስልክ ይዞ መገኘት አይቻልም።
✅ በሌላ ሰው ስም፣ User Name እና Pasword መፈተን አይቻልም፡፡
ከላይ የተዘረዘሩ የፈተና ስርአቶችን የጣሰ ተፈታኝ ውጤቱ ተሰርዞ በዲሲፒሊን ጥሰት የሚጠየቅ መሆኑ ተገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመላው ተፈታኞች መልካም እና በውጤቱም የምትደሰቱበት የልፋታችሁን ፍሬ የምታዩበት የተሳካ ፈተና እንዲሆን ይመኛል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ትምህርት ሚኒስቴርተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ ‼️
https://t.me/Tmhrt_Ministerhttps://t.me/Tmhrt_Minister