የወተት ደህንነትን ለማረጋገጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዘ የተጀመረው የቁጥጥር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ
አዳማ፣ ግንቦት 19/2017 – የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የወተት ደህንነትን ለማረጋገጥ ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመጠቀም የቁጥጥር ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ። የባለሥልጣኑ የምግብ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ እንደገለጹት ባለስልጣኑ የወተት ምርቶች ለተጠቃሚው በጤናማ ሁኔታ እንዲደርሱ የቁጥጥር ስርዓቱን እያዘመነ ይገኛል።
በዚሁ መሠረት ባለሥልጣኑ ከፌዴራል እስከወረዳ ለሚገኙ ተቆጣጣሪዎች ላክቶስ ስካን የተባለውን ዘመናዊ መሣሪያ በአግባቡ መጠቀም በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ሥልጠና እየሰጠ ነው። ይህ ሥልጠና በወተት ደህንነት ቁጥጥር ዙሪያ የሚታየውን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
አቶ ነጋሽ ስሜ የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የወተት ደህንነትን ለማረጋገጥ ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከግብርና ባለሥልጣንና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። "ከእርሻ እስከ ጉርሻ ባለው የወተት ደህንነት ቁጥጥር ሂደት የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው" ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል። በተጨማሪም የወተት አምራቾች ጤናማ ምርት ተቀብለው ለሸማቹ ማቅረብ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎችና ሁሉም ባለድርሻ አካላት ህብረተሰቡ የሚጠቀመው የወተት ምርት ደህንነቱ የተረጋገጠ እንዲሆን የጀመሯቸውን የጋራ ሥራዎች አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።
ከSNV ኢትዮጵያ የመጡት አቶ መላኩ ደበላ በበኩላቸው ባለስልጣኑ የወተት ደህንነትን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል። SNV ኢትዮጵያም ከባለሥልጣኑ ጋር ያለውን የትብብር ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።