#Ethiopia #France
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ለማድረግ አውሮፓ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ፈረንሳይ የገቡ ሲሆን ከፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው መወያየታቸው ተነግሯል።
ውይይታቸው የሁለቱን ሀገራት ግንኙነቶች እና ትብብሮች በሚያጠናክሩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እንደሆነና ፍሬያማ እንደነበር ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከውይይቱ በኃላ ገልጸዋል።
በፈረንሳይ ለተደረገላቸው አቀባበል እና በታኅሳስ ወር በአዲስ አበባ ከነበረው ውይይት ቀጥሎ ዛሬ ስለተካሄደው ውይይት አመስግነዋል።
" ትብብራችን በብዙ ጠቃሚ ዘርፎች የቀጠለ ሲሆን የንግድ ትስስሮቻችንን የበለጠ ማሳደግ ከቅድሚያ የትኩረት ማዕከሎቻችን አንዱ ነው " ሲሉም አክለዋል።
@tikvahethiopia