ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወርን በተመለከተ አስቸኳይ ማሳሰቢያ!~የተከበረው ኡስታዛችን ኢብኑ ሙነወር መታመማቸውን ስንሰማ ልባችን በእጅጉ ተሰብሯል። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ሙሉ አፊያውን በፍጥነት ይመልስላቸው!
በዚሁ አጋጣሚ አንድ ጠቃሚ ማሳሰቢያ ማስተላለፍ እወዳለሁ፦
አንዳንድ ጊዜ፣ የሱና ኡስታዞች በሽታም ሆነ ሌላ ችግር ሲያጋጥማቸው፣ ሳያውቁት ወይም ፈቃዳቸውን ሳይሰጡ፣ አንዳንድ እህቶችና ወንድሞች የገንዘብ ማሰባሰቢያ ወይም መዋጮ ሲያደርጉ ይስተዋላል። ይህ የሚደረገው የተለያዩ ግሩፖችን በመክፈት ሲሆን፣ ገንዘቡ የሚሰበሰበውም ማንነቱ በማይታወቅ አካል ወደተሰጠ አካውንት ነው።
ይህ ተግባር ሁለት ትላልቅ ችግሮች አሉት፦
1.
የኡስታዞቹን ፍቃድ አለማግኘት፦ኡስታዞቹ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ወይም ሳያውቁ ገንዘብ መሰብሰብ መልካም አይደለም። የክብርና የግለሰብ መብታቸውን መዳፈር ሊሆን ይችላል።
2.
ለመ'ጭበርበር መጋለጥ፦ ገንዘቡ የሚሰበሰብበት አካውንት ወይም ግለሰብ ማንነቱ ግልጽ ካልሆነ፣ የሰበሰበው ገንዘብ ለሌቦችና ለአጭበርባሪዎች የመጋለጥ ዕድሉ እጅግ ከፍተኛ ነው። በዚህም ምክንያት የሙስሊሞች ገንዘብ በአግባቡ ሳይውል ሊባክን ይችላል።(ከ አሁን በፊት መሰል ጥፋት ስላጋጠመን ነው።)
ስለሆነም፣ ከዚህ መሰል ተግባር እንድንጠነቀቅና፣ ለመርዳት ባሰብን ጊዜ ኡስታዞቹን በግል ወይም በሚታወቁ ወኪሎቻቸው በኩል ማረጋገጥ እንዳለብን እናሳስባለን።
አላህ ኡስታዛችንን ኢብኑ ሙነወርን ከህመማቸው ያሽርልን፤ ሙሉ ጤንነታቸውንና ጥንካሬያቸውን ይመልስላቸው። አሚን!
=
t.me/AbuSufiyan_Albenan