#ጥቆማ
#CyberTalentChallengeSummerCampProgram2025
" የ11 አመት እድሜ ካላቸው ጀምሮ ወደዚህ ስልጠና መግባት የሚችሉ ወጣቶችን እንመለምላለን "- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) ላለፉት ሶስት አመታት ያከናወነው የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ሰመር ፕሮግራም ስልጠና መርሃግብር የ2017 ዓ/ም ምዝገባ መጀመሩን ይፋ አድርጓል።
ለአራተኛ ጊዜ የሚከናወነው የባለ ልዩ ተሰጥኦ ታዳጊ እና ወጣቶች የሳይበር ሥልጠና የክረምት መርሃ ግብር ሥልጠና ምዝገባ እስከ ግንቦት 24/2017 ዓ/ም ድረስ ይቆያል ተብሏል።
ከአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሚሰጠው ይህ ስልጠና ፦
- በሳይበር ደህንነት፤
- በሳይበር ዴቨሎፕመንት፤
- በኢምቤድድ ሲስተም
- በኤሮስፔስ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ልዩ ችሎታ እና ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች ቢመዘገቡ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተቋሙ አሳውቋል።
በዘንድሮው ስልጠና ለመሳተፍ የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠናን ቀደም ብለው የወሰዱ ተመዝጋቢዎች የተሻለ እድል እንደሚኖራቸው ተገልጿል።
ተያያዥ የሆነ ሰርተፍኬት ያላቸው ተመዝጋቢዎችም በምዝገባው ወቅት በማስገባት ስልጠናውን ለመሳተፍ የተሻለ እድል ይኖራቸዋል።
የተቋሙ የሳይበር ልህቀት ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ቢሻው በየነ " ሰልጣኞች ከስልጠና በኋላ በቀጥታ ወደ ኢንሳ ፣ሌሎች የግል ተቋማት ወይም የመንግስት ቁልፍ መሰረተ ልማት የሚያስተዳድሩ ቦታዎች ላይ ሊሰሩ ይችላሉ " ብለዋል።
ዳይሬክተሩ " ከ11 አመት ጀምሮ ወደዚህ ስልጠና መግባት የሚችሉ ወጣቶችን እንመለምላለን " ያሉ ሲሆን " ምዝገባው እንዳበቃ ለቦታው ፍላጎት ያላቸው እና በቂ የሚባል ግንዛቤ ያላቸው መሆኑን የማረጋገጥ ስራ ይሰራል " ነው ያሉት።
ዘንድሮ ለአራተኛ ጊዜ በሚከናወነውን ሥልጠና ተካፋይ ለመሆን ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች በ
https://talent.insa.gov.et ላይ በመግባት እስከ ግንቦት 24/2017 ዓም ድረስ መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia