እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ እስካሁን የታገስኩት ይበቃኛል‼️
🗣 አቶ ጌታቸው ረዳ
በትግራይ ያለው ህገወጥ የወርቅ ንግድ ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኃላ የጀመረ ሳይሆን በጦርነቱ ጊዜም ሳይቀር ሲሰራ የነበረ እንደሆነ የቀድሞው የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የአሁኑ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አደረጉ።
አቶ ጌታቸው፤ "ብዙ ሰው የወርቅ ንግድ የፕሪቶሪያ ስምምነት ከተፈራረምን በኃላ የጀመር ይመስለዋል" ያሉ ሲሆን ግን ጦርነቱም እየተካሄደ ንግዱ ነበር ብለዋል።
"እኔ የማምንበትን ትግል ነው ያካሄድኩት ብዬ አምናለሁ በዛ በማምንበት ትግል ውስጥ የትግራይን ህዝብ አጀንዳ ይዘው የታገሉ ብዙ የጦር መኮንኖች አሉ ለሰሩት ስራ ያለኝ ክብር በፍጹም አይቀንስም ግን ደግሞ ገና ገና ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን ይበላ በነበረበት ወቅት ሳይቀር ምሽግ ለመቆፈር ብለን የወሰድነው ኤክስካቫተር ወርቅ ለመልቀም ይጠቀሙበት የነበሩ አዛዦችም ነበሩ" ሲሉ አጋልጠዋል።
"ሲዋሹ በጣም ነው የሚገርመኝ" ያሉት አቶ ጌታቸው "እኔ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል እስካሁን የታገስኩትም ይበቃኛል" ብለዋል።
አቶ ጌታቸው "የኤርትራን ሰራዊት እናፍርሰው" በሚል አላማ ዘመቻ የጀመረና ዘመቻውን የሚመራው አመራር ሰዎችን እያፈነ ገንዘብ ሲበስብ እንደነበር ተናግረዋል።
"ሰው ሲሸጡ የሚኖሩ ሰዎች አሉ፤ ኤርትራዊ መሸጥ ' ንብረት ' ነው የሚባለው ወርዷል ወይ ? ይባላል፤ ታፍንና ይዘህ 27 ወጣት አንድ ቤት ትዘጋና ቤተሰቦች አላቸው ውጭ ሀገር የሚባሉት ሰዎች አካውንት እየተጠየቀ እያንዳንዱ ሰው በትንሹ 4000 ዶላር እንዲያስገባ ተደርጎ (20 ሰው ካፈንክ 80 ሺህ ዶላር ታስገባለህ) በዚህ የውጭ አካውንት ከፍተው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እየሸጡ፣ እያገቱ ገንዘብ እንዲሰበሰብ የሚያደርጉ አመራር የሚሰጡ ከፍተኛ አመራሮች አሉ" ብለዋል።
ይህ ተግባር መጀመሪያ በኤርትራውያን መጀመሩን ከዛም ወደ ትግራይ ተወላጆች መዞሩን ተናግረዋል።
እዚህ ጉዳይ ላይ ጥናት ተደርጎ አመራሮቹ ለህግ እንዲቀርቡ ሙከራ ቢደረግም ማቅረብ እንዳልተቻለና 2 ዓመት እንደሆነው ጠቁመዋል።
አቶ ጌታቸው "ይሄን የሚመራ የመረጃ መምሪያ ኃላፊ እርምጃ እንዲወሰድበት ወይ ከስራ እንዲነሳ ብለን ወስነን ስናበቃ ለማስፈጸም ኃላፊነት የሚሰጣቸው የፀጥታ አመራሮች አላስፈጸሙም" ሲሉ ተናግረዋል።
የፀጥታ አመራሮች በባህሪያቸው ጥፋት ያጠፋውም ያላጠፋውም የመተጋገዝ ባህሪ አላቸው ሲሉ ተደምጠዋል።
ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በወርቅ ንግድ ውስጥ ስላሉ አመራሮች ተናግረዋል።
"ወርቅ ንግድ ውስጥ የገባ ' ለትግራይ ነጻነት እስከመጨረሻው እሰዋለው ' እያለ የሚፎክር ጀነራል አለ አሁንም፤ እንዲህ አይነቱን የወርቅ ንግድ ውስጥ ነው ያለኸው ሊባል ይገባል" ብለዋል።
አቶ ጌታቸው እነ ጀነራል ምግበ በወርቅ ንግድ ውስጥ ተሰማርተው እንደሚገኙ በስም ጠቅሰው ይፋ አድርገዋል።
"እነ ምግበ የሰሩት ጀግንነት የወጣት መስዕዋት መሰረት ተደርጎ የመጣ ጀግንነት ነው" ያሉት አቶ ጌታቸው "እነዛን ወጣቶች ለስደት በሚዳርግ ደረጃ ወደ ተራ የወርቅ ንግድ ገብተው ሲያበቁ የስርቆት ተግባራቸውን የትግራይ ግዛት አንድነት የማረጋገጥ አርገው እየገለጹ እንደገና ይሄን ወጣት ለሌላ መስዕዋትነት ሊዳርጉ እየተንቀሳቀሱ ነው" ብለዋል።
"እነ ኃይለስላሰም አሁን በትግራይ ህዝብ አንድነት ስም የትግራይን ወጣት ከኤርትራም ጋር ቢሆን አብሬ ለማገዶነት እንዳርገዋለው በሚል በጀግንነት ስም እየፎከረ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
እነ ምግበ ፣ እነ ኃይለስለሰን "በወንጀል የተነከሩ ሰዎች ናቸው" ብለዋቸዋል።
ድንገት ሰላም ቢፈጠር "ተጠያቂ እሆናለሁ፤ አደጋ ውስጥ እገባለሁ" ብለው ስለሚያስቡም ግርግር እንዲያልቅ አይፈልጉም ሲሉ ገልጸዋቸዋል።
የትግራይን ህዝብ ለሌላ ጦርነት ለማስገባት እያሰቡ እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ጌታቸው " የፌዴራል መንግሥት ድንገት ውጊያ ይገጥመናል " በሚል ስጋት ውጊያው ትግራይ ውስጥ እንዲካሄድ የሚያስችል ስትራቴጂ ተቀይሶ እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል።
" ሰላም መፈጠር አለበት፤ በኢትዮጵያም በኤርትራም መካከል ጦርነት መፈጠር የለበትም፣ የኤርትራ ህዝብ ለአደጋ መዳረግ የለበትም እምነቴ ነው። ግን መምረጥ ካለብኝ የትግራይ ህዝብ ድጋሚ የጦር አውድማ የሚሆንበት ሁኔታ እስከመጨረሻው ድረስ እንዳይሆን እታገላለሁ " ብለዋል።
በዚህ ትግል እንቅፋት የሆኑት የወርቅ ንግድ ላይ የተሰማሩት ዘራፊዎች ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።
" ' ግንባር አዛዥ ነኝ ' ይላል ወርቅ ሲዘርፍ ነው የሚውለው " ብለዋል።
"በ2014 ወጣቶች በየግንባሩ ሲተናነቁ በርቀት ዳባት፣ደባርቅ ፣ሊማሊሞ ሆኖ ውጊያ ይመራ የነበረ ሰው በተመሳሳይ ሰዓት በኤክስካቫተር ወርቅ እየቆፈረ ይሸጥ ነበር" ሲሉ ተደምጠዋል።
በዚህ የዝርፊያ ኔትዎርክ ፖለቲከኛውም እንዳለ ገልጸዋል።
ከዚህ ባለፈ አቶ ጌታቸው በመቶ ሚሊዮን ዘርፏል ስላሉት ኃለስላሰም ተናግረዋል።
" ኮምቦልቻ issue account ነበር፤ በዛ ሰዓት ጦርነት ላይ ገንዘብ ስለሚያስፈልገን ትክክለኛ ውሳኔ ነው የወሰነው የግል ባንኮች ሳንነካ የመንግሥት እንውሰድ ብለን ፓለቲካሊ ወሰንን እኔ እንደማውቀው 4 ቢሊዮን ብር ነበረው issue account ላይ ይሄን ከብሔራዊ ባንክ ማረጋገጥ ይቻላል ጊዜያዊ አስተዳደር ከሆንኩም በኃላ ወረቀት መጥቶልኛል ምን እንደተፈጠረ ባንኮች ውስጥ ግለጹልን የሚል እና issue account ውስጥ ያለውን ገንዘብ እንዲሰበስቡ ከተመደቡት ሰዎች መሃል አንዱ የግምባር አዛዥ የሚባለው ኃይለስላሰ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ነው የወሰደው ወደ አንድ ቢሊዮን አካባቢ ገንዘብ ነው የወሰደው እሱ ስር ተፍ ተፍ የሚሉ የሱ አገልጋዮች የተወሰነ ድርሻቸው የወሰዱ አሉ " ብለዋል።
አብዛኛው ሰው ትግሉን ለትግራይ ህዝብ ካለው የህልውና ጥቅም አንጻር እንጂ "ገንዘብ አገኝበታለሁ" ብሎ አይደለም የተሳተፈው ሲሉ ተናግረዋል።
"እኔ በማውቀው ባረጋገጥኩት በሰነድ ጭምር እነ ኃይለ የወርቅ ማሽኖችን ሲያስገቡ ነው የሚውሉት" ብለዋል።
የፖለቲካ አመራሩም አብሮ የወርቅ ንግድ ውስጥ መሰማራቱን ጠቁመዋል።
ሰዎቹ ማሽን ሲያዝባቸው የፌዴራል ሰዎች ጋር እየተደዋወሉ "እናተን የመሰለ ሰው የለም" እያሉ እየተለማመጡ ማሽን ለማስለቀቅ እንደሚሞክሩ ገልጸዋል።
በጥናት " እገለ እግሌ 300 ሚሊዮን ወስዷል በቁጥጥር ስር ይዋል፣ እገሌ ይሄን ያህል ማሽነሪ ወስዷል በቁጥጥር ስር ይዋል እርምጃ ይወሰድ " ከተባለ 2 ዓመት እንደሆነው አመልክተዋል።
የቀረበውን የጥናት ዶክመት እነ ደብረጽዮን (ዶ/ር) እንደሚያውቁት ጠቁመዋል።
ትግሉ ውስጥ ትልልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው ሰዎች ስም ሌሎችን ይዞ እንዳይጠፋና የውሸት አንድነት ለማስቀጠል ሲባል እምርጃ መውሰድ አልተቻለም ብለዋል።
"የመረረኝ ሰዓት እርምጃ እንዲወሰድ ዶክመንት አቅርቤም ተግባራዊ አልተደረግም" ብለዋል።
እነ ምግበን፣ እነ ኃይለስላሰን በስም ጠቅሰን መጠየቅ ስላልቻልን "ሁሉም የሰራዊት አመራሮች ዘርፈዋል" የሚል የጅምላ መልዕክት እያስተላለፍን ነው የመጣነው ይህ ውሸት ነው ብለዋል።
ተጠያቂነት እንዳይሰፍን የፖለቲካ መሪዎቹ እንቅፋት እንደሆኑ ይህን የሚያደርጉትም እነሱም ተጠያቂ ስለሆኑ እንደሆነ አቶ ጌታቸው ረዳ ይፋ አድርገዋል።
አብዛኛው የሰራዊት አመራር ግን ሰላም ፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል።
@Esat_tv1