አዳማጭ ሁኑ!
፨፨፨/////፨፨፨
ለአፍታ ዝም ብላችሁ አካባቢያችሁን ቃኙ፣ አስተውሉ፣ ዞር ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፣ መስማት የምትችሉትን ነገር ከልብ አዳምጡት። በየቦታው ጩሀት አለ፣ የህመም፣ የሲቃ ድምፅ አለ፣ ትርጉም አልባ ግርግር አለ፣ ብዙ የተጨነቁ ነፍሳት አሉ፣ ብዙ ውስጣቸው የቆሰለ፣ ስቃይ ያደከማቸው፣ ተስፋ የራቃቸው መጮህም ማውራትም ያልቻሉ ምስኪን ነፍሳት አሉ። ዝም ብላችሁ አዳምጡ። ንግግሩን ብቻ ሳይሆን መንፈስንም ማዳመጥ ሞክሩ፣ ገፅታን፣ ስሜትን፣ ተግባር ከልባችሁ ማስተዋል ጀምሩ። ዓለም ያለማቋረጥ የሚጮህ እንጂ አዳማጭ የላትም፣ የሰው ልጅ የሚፈልገው ወረኛን ሳይሆን የሚያዳምጠውን ነው። ጫጫታ በዝቷል፣ እዚም እዛም አለመግባባት ተስፋፍቷል፣ ሁሉም ተናጋሪ ሆኗል፣ ሁሉም በየፊናው ወከባ ይፈጥራል፣ አቋሙን በግድ ለማራመድ ይጥራል። በሁካታ ብዛት የሚጨነቁ ነፍሳትን የሚያስብ የለም፣ በትርምሱ መሃል ልባቸው ስለሚያነባ ነፍሳት የሚያስታውስ የለም። አብዛኛው ችግር ፈጣሪ ለሌላው ያዘነ፣ አብዛኛው የግርግሩ ባለቤት ለህዝብ የሚያስብ፣ የሰው ችግር የሚያስጨንቀው ይመስላል። ነገር ግን የወገኑን ጩሀት እንደተረዳ ከማስመሰሉ በፊት ውስጡን እንኳን በቅጡ አያውቀውም።
አዎ! አዳማጭ ሁኑ! በቅድሚያ ወደራሳችሁ ተመለሱ፣ ለራሳችሁ ጉዳይ ቅድሚያ ስጡ፣ ውስጣችሁን አዳምጡት፣ ሁኔታችሁን መርምሩ፣ ፍላጎታቸውን አጥኑ። ከልብ የማዳመጥን ልማድ ስትገነቡ ማስተዋል ትጀምራላችሁ፣ ከሸንጎ ፍርድ ትቆጠባላችሁ፣ ከእያንዳንዱ እርምጃችሁ በፊት ደጋግማችሁ ታስባላችሁ፣ ችግር በበዛበት ዓለም የመፍትሔ ሰው ሆናችሁ ብቅ ትላላችሁ። የምታዳምጡት የምትናገሩት አጥታችሁ፣ እውቀት አንሷችሁ ወይም ፈርታችሁ አይደለም። ይልቅ ከመናገራችሁ በላይ ትርፋማ የሚያደርጋችሁ፣ ይበልጥ ጥበብን የሚያድላችሁ፣ ተጨማሪ ግበዓትን የሚያጎናፅፋችሁ ማዳመጣችሁ እንደሆነ ስለገባችሁ ነው። ሰዎች ስላሉበት ሁኔታ ሊያወሯችሁ ቢፈልጉ ከልብ ጆሮ ስጧቸው፣ በሙሉ ሰውነታችሁ አዳምጧቸው፣ ትኩረታችሁን እነርሱ ላይ አድርጉ። ማዳመጥ በእራሱ እራሱን የቻለ የስነስልቦና የህክምና ዘርፍ (therapy) እንደሆነ እወቁ።
አዎ! ጀግናዬ..! አትዋከብ፣ እዚም እዛም አትበል፣ ነፍስህን አታስጨንቃት፣ የጫጫታው አድማቂ፣ የትርምሱ መሪ አትሁን። ሰከን በል፣ ተረጋጋ፣ ወደራስህ ተመለስ። አንተ እራስህን ካላዳመጥክ ማን እንዲያዳምጥህ ትፈልጋለህ? አንተ እራስህን ካልተመለከትክ ማን ይመለከትሃል? እራስህን አስታውስ። የዓለም ግርግር አያታልህ፣ የምታየው ጌጥና ጫወታ ከፈጣሪህ ጋር ያለህን ግንኙነት አያበላሽ ። ከእግዚአብሔር በቀር ምንም ነገር እንደነበረ አይቀጥልም ፣ ምንም ነገር ቋሚ አይደለም ። ዛሬ የምትጓጓለት የተመቻቸ ህይወትም ቢሆን በእጅህ ሲገባ የሆነ ጊዜ ምንም እንደሆነ ይገባሃል ። ከየአቅጣጫው ጩሀትና ዋይታ ሲበረታ አዳማጭ የመፍትሔ ሰው ያስፈልጋልና እራስህን ለእርሱ አዘጋጅ ። ማንንም ከመከተልህ በፊት ከስሜት በላይ ሆነህ ፣ ከጥላቻና ከፍርጃ ርቀህ ልብ ገዝተህ አዳምጥ ። አንተም ተምታተህ ሰዉን አታምታታ ። አዳምጥ ፣ እወቅ ፣ መርምር ፣ ችግር ፈጣሪ ሳይሆን ችግር ፈቺ ፣ የሁካታ መሪ ሳይሆን የመፍትሔ ሰው ሆነህ ተገኝ ።