🏢ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ትልቁን ሕንጻ ልትገነባ ነው
🏦62 ፎቅ ሲኖረው፣ 445 ሚ.ዶላር ይፈጃል ተብሏል
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያስገነባዋል የተባለው የዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻ ከሰሃራ በታች ትልቁ እንደሚሆን ተሰምቷል፡፡ ህንጻው 197 ሺህ 800 ካሬ ሜትር ስፋት፣ 327.5 ሜትር ርዝመትና 62 ፎቅ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
በዚህም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ትልቁን ሕንፃ - ንግድ ባንክን በ209.7 ሜትር እና በ53 ወለል ሕንጻ የሚበልጥ ይሆናል፡፡
ከሜክሲኮ አደባባይ አቅራቢያ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ሊገነባ የታቀደው ሕንጻ 445 ሚሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ የስፑትኒክ ዘገባ ያመለክታል፡፡
ፕሮጀክቱ በገንዘብና በሎጂስቲክስ ችግሮች ምክንያት ቆሞ የነበረ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሁን ለግንባታው ጨረታ እንዳወጣ ዘገባው ይጠቁማል፡፡
(አአ)