EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Медицина


ETHIOPIAN FOOD AND DRUG AUTHORITY /EFDA/
This is EFDA'S official Telegram Channel
For more updates please visit
Free call 8482
join the Channel
t.me/ethiopianfoodanddrugauthority

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Медицина
Статистика
Фильтр публикаций


የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ከብሔራዊ የትምባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ተቋማት ጋር የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡

ሰኔ17/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን እና ብሔራዊ የትምባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ተቋማት መካከል የትምባሆ ቁጥጥር ህጎችን ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስፈጸም የሚያስችል የጋራ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
የፊርማ ስነ-ሥርዓቱን በንግግር ሲከፍቱ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ብሔራዊ የትምባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት የሆኑት መንግስታዊና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ትምባሆ በሰው ልጆች ሁለንተናዊ ሕይወት ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት በመገንዘብ አገሪቱ በአለም አቀፍ ደረጃ የተቀበለቻቸውንም ሆነ በራሷ ያወጣቻቸውን የትምባሆ ቁጥጥር ሕጎች ተፈፃሚነት በትኩረት እንዲሰሩ ጠይቀዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የሚያስተባብረው ብሄራዊ የትምባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ የትንባሆ የቁጥጥር ስራዎች ከሆኑት ውስጥ አንዱ የሆነውን የትምባሆ ኢንዱስትሪ ጣልቃ ገብነትን መከላከል ጋር በተያያዘ የኮሚቴ አባል ተቋማት ከትምባሆ ኢንዱስትሪ ጋር በተገናኘ ከመደበኛ ስራቸው ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት ሆነ ትምባሆን በጋራ ለመቆጣጠር ወይም የህብረተሰብ ጤና ለመጠበቅ በሚኖራቸው ግንኙነቶች ላይ ሊኖር የሚገባ ግንኙነት በተመለከተ የስነ-ስርዓት ደንብ መዘጋጀቱንም አብራርተዋል፡፡
በአዲስ መልክ የተዋቀረው ብሔራዊ የትምባሆ መከላከል ኮሜቲ ቀደም ሲል የታዩ የቅንጅት ክፍተቶችን ለማሻሻልና የትምባሆ ቁጥጥር ድንጋጌዎችን ይበልጥ በጋራ ኃላፊነት እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚያስችል ዋና ዳይሬክተሯ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡


የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የመድኃኒት ደህንነት ክትትል ማዕከል ከፈተ

አርባ ምንጭ፣ ሰኔ 17/2017 - የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ሆስፒታል የመድኃኒት ደህንነት ክትትልና ማስተባበሪያ ማዕከል ከፈተ። የማዕከሉ መከፈት በሀገሪቱ የመድኃኒት ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ያጠናክራል።

የባለስልጣኑ የመድኃኒት አምራቾች ኢንስፔክሽንና ህግ ማስፈፀም መሪ ስራ አሰፈፃሚ አቶ ጌታቸው ገነቴ ገነቴ በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት መድኃኒቶች ጎጂ የጎንዮሽ ጉዳት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ የጤና ባለሙያዎችና ማህበረሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ብለዋል። ባለስልጣኑ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት፣ የመድኃኒቶችን ደህንነት ስራዎች ለማስተባበርና ለመከታተል የተለያዩ ስልቶችን እንደሚከተል ገልፀዋል። በተለይም አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ሲባል፣ ባለስልጣኑ ቁልፍ የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ እና ዩኒቨርሲቲ ተቋማትን በመምረጥ የመድኃኒት ደህንነት ክትትልና ማስተባበሪያ ማዕከላትን እያቋቋመ እንደሚገኝ አስረድተዋል። የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ማዕከል ስምንተኛው መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሬንሲቭና ቲቺንግ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ደስታ ጋልቻ፣ ሆስፒታላቸው በማዕከሉ መመረጡ ትልቅ ክብር እንደተሰማቸው ገልፀው ለክልሉ ህብረተሰብ ጤና ትልቅ እድል እንደሚፈጥር አስረድተዋል።

በምረቃው ላይ የተገኙት የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ክቡር አቶ መኮንን ቶንቻ ባለስልጣኑ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በምርቃት ስነስርዓቱ ከባለስልጣኑ፣ ከአርባ ምንጭ ሆስፒታልና ከዞኑ የተለያዩ ቢሮዎች የተውጣጡ ኃላፊዎችና የመድኃኒት ደህንነት ላይ የሚሰሩ ባለመሙያዎች ተገኝተዋል።


በ2017 በጀት ዓመት ከባለድርሻ አካላት ጋር የተሰሩ ቅንጅታዊ የምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ስራዎች  ውጤታማ እንደነበር ተገለፀ፡፡

ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የምግብና ጤና ግብዓት ቁጥጥር ዘርፍ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ ሲካሄድ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እንደተናገሩት በ2017 በጀት ዓመት ከሁሉም ክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በተሰሩ ቅንጅታዊ የቁጥጥር ስራዎች ውጤታማና ለውጥ ያመጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡

https://www.facebook.com/100064606425124/posts/pfbid0SZg3xTbYmVX2uUygxrDo6V4phDUtFw2Z4kqrX7w2TGZtSKQZCMqsALYXQoGpnapWl/




አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ.ም. - የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በምግብ ዘርፍ የላቀ የቁጥጥር ሥርዓት ለመፍጠር የሚያስችል ወሳኝ አውደጥናት አካሂዷል። አውደጥናቱ የምግብ ማምረቻ ተቋማት የቅድመ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር እንዲሁም የአነስተኛ ወተት ተዋጽኦ አምራቾችን በሚመለከቱ መመሪያዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ ከክልል ተቆጣጣሪ አካላትና ከሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የምግብ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ነጋሽ ስሜ እንደገለጹት፣ በፌዴራልና በክልሎች መካከል ያለው የቁጥጥርና የመመሪያዎች ልዩነት ለምግብ ደህንነት ቁጥጥሩ ችግር እየፈጠረ ነው። ይህንን ችግር ለመፍታት ወጥ የሆነ መመሪያ በጋራ ማዘጋጀት ወሳኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል። ባለሥልጣኑ ያዘጋጃቸውን መመሪያዎች በመላው ሀገሪቱ በተቀላጠፈ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ይህ መድረክ ትልቅ ሚና እንዳለውም ጠቁመዋል። ከክልሎችና ከፌዴራል ተቋማት የተገኙ ተሳታፊዎች በመመሪያው ላይ ጥልቅ ግምገማ እንዲያደርጉና ለሚፈለገው ወጥ የቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የአደራ መልእክት አስተላልፈዋል።

በባለሥልጣኑ የምግብ አምራቾች ኢንስፔክሽንና ሕግ ማስፈፀም መሪ ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ሙላቱ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥ የሆነ የምግብ ተቋማት የፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋት በትኩረት እየሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በሁለት ቀናት ቆይታው፣ ተሳታፊዎች በምግብ ማምረቻ ተቋማት የቅድመ ፈቃድና ቁጥጥር መመሪያ እንዲሁም በአነስተኛ ወተት ተዋጽኦ አምራቾች መመሪያ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ያደርጋሉ። ይህም ለተሻለ አተገባበር የሚያስችሉ ግብአቶችን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።






Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


ሠኔ/07/2017 ሐዋሳ - የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ያዘጋጀው የምግብና ጤና ግብዓቶች ባለድርሻ አካላትን ያሰባሰበ የምክክር መድረክ በሐዋሳ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገረባ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት የህገወጥ ንግድና ዝውውር በዜጎች ጤናና ደህንነት ላይ ከሚፈጥረው አደጋ ባሻገር የሀገሪቱን ኢኮኖሚም በእጅጉ እንደሚጎዳ ገልጸዋል። አዋጅ ቁጥር 1112/2011 እነዚህን ምርቶች የመቆጣጠር ሃላፊነት ለባለስልጣኑ መስጠቱን በመግለጽ የሚታዩ ችግ ለመፍታት የተቀናጀ የባለድርሻ አካላት ትብብር ወሳኝ መሆኑን አሳስበዋል። መድረኩ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ተግዳሮቶችን ለመነጋገር የመፍትሄ መንገዶችን ለመፈለግና እና ቅንጅትና ትብብርን ለማጠናከር ያለመ እንደሆነም አብራርተዋል።

በስብሰባው ላይ ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሰላማዊት መንገሻ በበኩላቸው ክልሉ የህዝብ ጤናን ለመጠበቅ በትጋት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ይህንን ስብሰባ በማዘጋጀቱ ለባለስልጣኑ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ክልሉ በዚህ ረገድ እያከናወናቸው ያሉትን ስራዎች ዘርዝረዋል።

በባለስልጣኑ የሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች ግብዓት ቁጥጥር ባለስልጣን ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ተሳታፊዎቹ በሰፊው ተወያይተዋል። በውይይቱ ማጠቃለያም የህገወጥ ንግድና ዝውውርን ለመከላከል በጋራ ለመስራት እና ትብብራቸውን ለማጠናከር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በስብሰባው ላይ ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ፣ ከክልል ፕሬዝደንት ጽ/ቤት፣ ከክልሉ ምክርቤት ተወካዮች፣ በሀዋሳ ከሚገኙ የፌዴራል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ ከጉምሩክ ኮሚሽን፣ ከዞንና ወረዳ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም የሚዲያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።


ሠኔ/6/2017 - ሻሸመኔ – በኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አዘጋጅነት፣ በሻሸመኔ ከተማ የምግብ ዘይትና የስንዴ ዱቄት ማበልጸግ ደረጃዎች እና የምዝገባ መመሪያዎች ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለባለድርሻ አካላት ተሰጥቷል። በስልጠናው ከጉምሩክ፣ ከተስማሚነት ምዘና እና ከክልል ተቆጣጣሪ አካላት ኃላፊዎች ተገኝተዋል። ስልጠናው በሀገሪቱ የምግብ ደህንነትና የህብረተሰብ ጤና ማሻሻል ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የሀዋሳ ቅርንጫፍ የምግብ ቁጥጥር ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ብሩህ አለማየሁ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ፣ የምግብ ማበልጸግ ቀላል፣ በሳይንስ የተረጋገጠ እና ወጪ ቆጣቢ የመከላከል ስራ እንደሆነ አስረድተዋል። እንደ ምግብ ዘይትና ስንዴ ዱቄት ባሉ በስፋት በሚበሉ ምግቦች ላይ ወሳኝ ጥቃቅን ንጥረ ነገሮችን በመጨመር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን መድረስ እንደሚቻል ጠቁመዋል።
በመድረኩ "የተደበቀ ረሃብ" በመባል የሚታወቀው የንጥረ-ምግብ እጥረት፣ በተለይም የቫይታሚን ኤ፣ ቢ፣ ዲ፣ ፎሊክ አሲድ እና ዚንክ እጥረት በኢትዮጵያ ህዝብ ጤና ላይ እያደረሰ ያለውን ከፍተኛ ስጋት በስፋት አብራርቷል። ይህ እጥረት የህጻናትን ጤናማ እድገትና የአእምሮ ብስለት እንደሚያደናቅፍ፣ የማህበረሰብን በሽታ የመከላከል አቅም እንደሚያዳክም፣ ምርታማነትን እንደሚቀንስ እና የበሽታና ድህነት አዙሪትን እንደሚያባብስ ተብራርቷል።
በመጨረሻም የስልጠናው ተሳታፊዎች ለመመሪያው ተግባራዊነት በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።


አዲስ አበባ ሰኔ 6 / 2017 ዓ.ም የባለስልጣኑ የመድኃኒት ግምገማና ፈቃድ መሪ ስራ አስፈፃሚ ከብቃትና ሰው ኃይል ስራ አስፈፃሚ ጋር በመተባበር በአዘጋጁት የሠራተኛ መማማሪያ መድረክ ላይ ሠራተኛው ራሱንና ቤተሰቡን ከኤም ፖክስ በሽታ እንዲጠብቅ የሚያስችል ስለበሽታው መተላለፊያ መንገድ፣መከላከያውና አገራዊ ዝግጁነትን አስመልክቶ ሰፊ ገለፃ ተደርጓል፡፡
ገለፃውን ያደረጉት በባለስልጣኑ የመድኃኒት ግምገማና ፈቃድ መሪ ስራ አስፈፃሚ የባይሎጂካል ሕክምና ገምጋሚ ባለሙያ አቶ ቦዳና ባይሳ እንደተናገሩት በሠራተኛ መማማሪያ መድረኩ ላይ በኤም ፖክስ በሽታ ዙሪያ ገለፃ ማድረግ ያስፈለገበት አብይ ምክንያት በሽታው በአሁን ጊዜ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ሠራተኛው ከወዲሁ ግንዛቤ እንዲኖረው በማድረግ ራሱንና ቤተሰቡን ከኤም ፖክስ በሽታ እንዲጠበቅ ለማድረግ በመታሰቡ ነው፡፡
በመማማሪያ መድረኩ በቀረበው ገለፃ ዙሪያ ጥያቆዎችና አስተያየቶች ከሠራተኞች ቀርበው ከባለሙያው ሰፊ ማብራሪያ ቀርቧል፡፡






መግቢያና መውጫ ኬላዎች ላይ የሚሰሩ ተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ ፡ሰኔ/4/2017 -የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን የደቡብ ምሥራቅ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በአዳማና ቢሾፍቱ ከተሞች በቃሊቲ፣ ካርጎ፣ ተርሚናል፣ አዳማ እና ሞጆ ለሚገኙ የጉምሩክ፣ የአየር መንገድ፣ ፖሊስና ትራንዚት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከባለሥልጣኑ የአሠራር ሥርዓቶች ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቀቀ።
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንገለጹት "ወደ ሀገራችን የሚገቡ ምርቶችን ደህንነት፣ጥራት እና ውጤታማነት ማረጋገጥ የጋራ ኃላፊነት ነው" ብለዋል። "ይህ ስልጠና በሁሉም አካላት መካከል አንድ ወጥ የሆነ አሰራርን ለማጎልበት ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡ በመግቢያ እና መውጫ ኬላዎች ላይ ጠንካራ ቁጥጥር ማድረግ በህብረተሰብ ጤና ላይ ከፍተኛ አደጋ ከሚያስከትሉ ምርቶች ደረጃቸውን ያልጠበቁ እና ተመሳስለው የተሰሩ ምርቶችን ለመከላከል የመጀመሪያው መስመር መሆኑን እንገነዘባለን፡፡" ያሉ ሲሆን ስልጠናው ቅንጅታዊ አሰራርን ከማጠናከር አኳያ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ ስልጠናው በቢሾፍቱ ከተማ የተሰጠ ሲሆን በሁለቱም መድረክ በገቢና ወጪ ምርቶች ቁጥጥር ዘርፍ ከሚሰሩ ተቋማት ጋር መልካም ግንኙነት ቢኖርም፣ ለህብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማቅረብ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ሚና እጅግ ወሳኝ በመሆኑ፣ ባለሥልጣኑ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ግንዛቤ ለመፍጠርና የጋራ አሠራርን ለማጠናከር ይህ ስልጠና መዘጋጀቱን በመግለጽ በተጨማሪም ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የምግብ፣ የሕክምና መሣሪያዎችና የጤና ግብዓቶች ቁጥጥርን ለማሻሻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ወሳኝ ነው፡፡ስልጠናው የባለድርሻ አካላትን ቅንጅትና ትብብርን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግና የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የሚያግዝ መሆኑን አስታውቀዋል።

በሥልጠናው የተሳተፉት ከተለያዩ ተቋማት የተወከሉ ባለሙያዎች፣ የሥልጠናውን ጠቀሜታ በመግለፅ ይህ ዓይነቱ ሥልጠና ለሌሎች ባለሙያዎችም ተደራሽ እንዲሆን ሁኔታዎች እንዲመቻቹላቸው ጥያቄ አቅርበዋል።






Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram


የመድኃኒት አምራቾች ተግዳሮቶችን ለመፍታትና የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ለማሰደግ ሁለት ቁልፍ መመሪያዎችን በባለሥልጣኑ ፀድቀው ይፋ ሆኑ ።

1የመድኃኒት አዳኝ ንጥረ ነገር እና ግብዓቶች የማስመጣት ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 1062/2025

2.የመድኃኒት ማሸግ እና መለያ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 1091/2025

ፀድቀው ይፋ የሆኑት መመረያዎች የሀገር ውስጥ የመድኃኒት አቅርቦትን በከፍተኛ ሁኔታ ያሳድጋሉ ፣የሕዝብ ጤና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ያጠናክራሉ ፣የኢኮኖሚ እድገትን ያበረታታሉ እንዲሁም በጥራት ምርቶች እንደመሚረቱ ያረጋግጣሉ። በአገራዊ የማምረት አቅም ላይ በራስ መተማመንን ለማምጣት እና ከውጭ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥገኝነትን ለመቀነስ ቁልፍ ስትራቴጂ ናቸው። የሀገር ውስጥ ፋርማሲዩቲካል አምራቾች የሚያጋጥሟቸው ቁልፍ ተግዳሮቶች የፋርማሲዩቲካል አዳኝ ንጥረ ነገር እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች ተደራሽነት ውስንነት እንዲሁም የሙሉ አቅም የማምረቻ ሥራዎችን ለመመስረት የሚያስፈልገው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እና ጊዜን ያጠቃልላል።
እነዚህን ተግዳሮቶች ለመፍታትና የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ለመደገፍ ባለሥልጣኑ አሁን ፀድቀው በይፋ የተመዘገቡ ሁለት ቁልፍ መመሪያዎችን አዘጋጅቷል። የፋርማሲዩቲካል አዳኝ ንጥረ ነገር እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች የማስመጣት ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 1062/2025 ጥራት ያለው የፋርማሲዩቲካል አዳኝ ንጥረ ነገር እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች ለአገር ውስጥ አምራቾች ተደራሽ በማድረግ ዘላቂ ምርትን በማረጋገጥ የጤና ጥበቃ ስርዓትን በማሻሻል የሀገር ውስጥ የፋርማሲዩቲካል ኢንዱስትሪዎችን ተወዳዳሪነት ያሳድጋል።

የመድኃኒት ማሸግ እና መለያ አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 1091/2025 መድኃኒቶችን ለማሸግ እና ለመሰየም ስራዎች ለማከናወን አነስተኛ የቁጥጥር መስፈርቶችን ያስቀምጣል። ይህም ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል እንዲሁም የሀገር ውስጥ ምርትን እድገት ያሳድጋል። እነዚህ መመሪያዎች ሥራቸውን በመደገፍ፣ አዳኝ ንጥረ ነገር እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች አቅርቦትን በማሻሻል እና የሀገር ውስጥ የመድኃኒት ምርትን ለማሳደግ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ለነባርም ሆነ ለአዳዲስ የሀገር ውስጥ አምራቾች ጠቃሚ እድሎችን ይፈጥራሉ።





Показано 20 последних публикаций.
OSZAR »