👩‍🎓Hi-Tech Academy(Harar)👨‍🎓


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


From our progressive family-friendly school.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


በክልል ደረጃ  ሰኔ 4 ለሚደረገው የፈጠራ ስራ ውድድር አሻሽላችሁ ለመስራት ስራችሁን የወሰዳችሁ ልጆች ያሻሻላችሁት ስራ ማክሰኞ እንድታቀርቡ ይሁን።


📝 ፈተና ላይ 📝



📚 ስለ ፈተና አሰራር የምናወራው  አንድ ተማሪ ለፈተናው በሚገባ ዝግጅት አድርጓል የሚለውን ግምት ውስጥ በማስገባት ይሆናል። ፈተና በምንሰራበት ጊዜ የሚከተሉተን ነገሮች መከተል አለብን ፦


✅ 1ኛ፦ ፈተናውን አሰራዋለሁ የሚል ወኔ (Courage) ሊኖረን ይገበል። ምክንያቱም ምንም ያክል ብናነብ ፈተና ገብተን የምንፈራ ከሆነ አደለም የማናቀውን የምናቀውን ጥያቄ ሁሉ ሊጠፋብን ይችላል ስለዚህ በራስ መተማመን  ሊኖረን ይገባል ማለቴ  ምችለውን ያክል አንብቢያለሁ ስለዚህ ፈጣሪ ይረዳኛል አሰራዋለሁ የሚል ወኔ💪 ያስፈልጋል።


     ❇️2ተኛ ፈተናውን ስንሰራ ማስተዋል አለብን። ይህ ምን ማለት ነው ለምሳሌ አንዳንድ ጥያቄዎች ቀላል ሲመስሉን አራቱንም አማራጮች ሳናይ  Choice A ወይንም B ን ብቻ አይተን ልንሸወድ እንችላለን ምክንያቱም ሌላ የተሻለ መልስ ሊኖር ይችላል ስለዚህ እንደ Citizenship, Social, GS, ነክ ጥያቄዎችን ስንሰራ ሁሉንም አማራጮች ትክክል ያልሆኑትን እና የሆኑትን የ✖️አና ✔️ምልክት እያደረግን ብንሰራ ጥሩ ነው እኔ በዚ ብዙ ጊዜ ተሸውጄ ስለማቅ ነው።

     ✳️ 3ተኛ ሰዓታችንን ባግባቡ መጠቀም  በፈተና ጊዜ ከ ጥያቄው በተጨማሪ ሌላኛው ፈተና ሰዓት  ነው so ሰዓታችንን ባግባቡ መጠቀም አለብን ማለት ነው  ከቻላቹ በሆነ ጋፕ ፈታኙን ሰዓት በመጠየቅ ስንት ሰዓት እንደቀረን ማወቅ እንችላለን።ፈተናችንን on time  ለመጨረስ የሚያስፈልጉ የተውሰኑትን ነጥቦች ልጥቀስ፦


⭕️ ፈጠን ብለን ፈተናችንን ለመስራት አንሞክር ፤ በተቃራኑው ደግሞ አንድ ጥያቄ ላይ አረጋግጣለሁ በማለት አለመተኛት ፤ የስር ነውን በፍጥነት እያጠቆርን ስንሄድ እንዳንሳሳት ጥንቃቄ ማድረግ(በየገፁ የሰራናቸውን መልስ መስጫ ላይ እያጠቆርን መሄድ) ።

✏️  እንግሊዝኛ አይነት ፈተናውችን ስንሰራ reading comprehension ማለትም passage አንብበን የምንሰራቸው ጥያቄዎች ሰዓት ስለሚያስፈልጋቸው በመጨረሻ ብንሰራቸው ሰዓት የመቆጠብ እድላችን ሰፊ ነው ፦

🟥 የ calculation ጥያቄዎችን እንደ Maths  ስንሰራ ደግሞ እስክርቢቶ ወይንም እርሳስ ከወረቀታችን ጋር ከማገናኘታችን በፊት ጥያቄውን መረዳታችንን ማረጋገጥ አለብን because ከንቱ ላንሰራው ሁላ ጊዚያችንን ልንወስድ እንችላለን።

1⃣ መሰረታዊ መርሆችን (Fundamental Rules) መረዳት።

    2⃣ ቁልፍ መረጃን(key information ) መለየት::

3⃣ ችግሩን (problem) በጥንቃቄ መገንዘብ እና አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች እና የሚጠየቁትን ያደምቁ (ምልክት) ወይም ያስተውሉ

    4⃣ ንድፎችን መተጠቀም (diagram) ፡- • ለፊዚክስ ነክ ጥያቄዎች አስፈላጊ ሲሆን ዲያግራም መሳል ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለማየት እና አቅጣጫዎችን ወዘተ ለመለየት ይረዳል

አዚ ጋ መጨመር ምፈልገው ደግሞ የከበደንን ጥያቄ ሲገዛገዙ መዋል ሳይሆን አንዱን ሞልተን ሰዓት ካለን ተመልሰን ማየቱ የተሻለ ነው።

     ❇️ 4ተኛ፦ሌላኛው ወሳኝ ነጥብ መፈተኛ ቦታ ቢቻል ቀደም ብለን ብንገኝ ጥሩ ነው ካልሆነ በትክክለኛው ሰዓት መገኘት አለብን ምክያቱም ካረፈድን ጭንቀት ውስጥ ልንገባ እንችላለን::


ምክር ለተፈታኞች

ተፈታኝ ተማሪዎች እንኳን በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረው ፈተና  በሰላም አደረሳችሁ። ይህ ለእናንተ ወሳኝ ጊዜ ነው። እስካሁን ትምህርታችሁን እያጠናችሁ ቆይታችኋል። መልካም ነው። ነገር ግን በፈተና ወቅት የምታከናውኗቸው ተግባራትም የጥናታችሁን ያህል ውጤታችሁ ላይ ተጽዕኖ አላቸው። ስለዚህ በዚህ ወቅት ምን ማድረግ እንዳለባችሁና ምን ማድረግ እንደሌለባችሁ ጠንቅቃችሁ ማወቅ ይጠበቅባችኋል። ለዚህም ይረዳችሁ ዘንድ የሚከተሉትን ምክሮችን ከወዲሁ ተረድታችሁ ለመተግበር ዝግጁ ሁኑ!

⓵ በዋዜማው ከሚረብሹ ነገሮች ራስን ማራቅ ያስፈልጋል። ሀሳባችሁን ሊሰርቁ ከሚችሉ ማህበራዊ ሚዲያዎች መራቅ ይገባችኋል። በዚህ ወቅት ትኩረታችሁን ፈተናችሁ ላይ ብቻ አድርጉ፤

⓶ በቂ እንቅልፍ ተኙ። በፈተና ዋዜማ ለማንበብ ብላችሁ በፍጹም አታምሹ። ባጭሩ በዚህ ቀን ተጨማሪ ሰዓት ከማንበብ ይልቅ ተጨማሪ ሰዓት መተኛት የተሻለ ዉጤት አለው። በቂ እንቅልፍ አለመተኛት በፈተና ወቅት ለድብርትና ለራስ ምታት ሊዳርግና ሥራችሁን ሊያበላሽ ይችላል። ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ከባድ ምግቦችን አለመመገብ፤ ብዙ ቡና አለመጠጣት፤ እና ሌሎች አነቃቂ ነገሮችን አለመውሰድ ይመከራል፤

⓷ ጠዋት ማልዶ መነሳት: በጊዜ ተነስቶ መዘጋጀት ከመቻኮል ጋር ተያይዞ ከሚመጣ መታወክ ያድናል። በተጨማርም ወደፈተናው አዳራሽ በጊዜ ለመድረስ ያስችላል፤

⓸ ቁርስ በአግባቡ መብላት: በፈተና ወቅት ቁርስ አለመብላት አእምሮአችን የሚፈልገውን ያህል ኃይል እንዳያገኝ ስለሚያደርግ ለማሰብ አቅም እንዲያንስ ያደርጋል። ስለዚህ ቀለል ያሉ ምግቦችን ተመግባችሁ መሄድ ይኖርባችኋል። ከባድ ምግቦችን መመገብ ደግሞ አእምሮአችን ምግብ የመፍጨት ሥራ ላይ ብቻ እንዲወጠር ስለሚያደርግ ድካምና እንቅልፍ ያመጣል፤

⓹ ወደ መፈተኛ ቦታው ፈተናው ከሚጀምርበት ሰዓት በፊት ቀድሞ መድረስ ያስፈልጋል። ይህም ለመረጋጋት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው፤

⓺ ከቤት ስትወጡ የፅህፈት መሳሪያዎቻችሁንና የመታወቅያ ካርዳችሁን መያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ይህም ከመንገድ ከመመለስና ከማርፈድ ያድናችኋል። ትርፍ እርሳሶችን እና የእርሳስ መቅረጫዎች መያዝ በጣም አስፈላጊ ነው፤

⓻ ወደ ፈተና አዳራሽ ከመግባት በፊት ወደ መፀዳጃ ቤት መሄድ መልካም ነው። ምናልባት በፈተናው ሰዓት ሽንት ቢይዛችሁ መጨናነቅን ያመጣል።

⓼ የመልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ስማችሁን እና የመፈተኛ ቁጥርን እንዲሁም ሌሎች ሊሞሉ የሚገባቸውን መረጃዎች በአግባቡ መጻፋችሁን እርግጠኛ ሁኑ። አንድ ፊደል እንኳን ብትሳሳቱ ኋላ የት/ት ማስረጃችሁ ላይ ስለሚቀመጥ ለማስቀየር ዋጋ ያስከፍላል፤

⓽ መመሪያዎችን (instructions) በአግባቡ ማንበብና መተግበር ያስፈልጋል። በእያንዳዱ ፈተና ወረቀት ላይ ወይም የፈተናው ክፍሎች ላይ የሚሰጡትን መመሪያዎች በአግባቡ ማንበብና መተግበር ይኖርባችኋል፤

⓾ አትደንግጡ! በደንብ ተንፍሱ! ብዙ ኦክስጂን ወደ ውስጣችን ማስገባት ብዙ ምግብ እንዲቀጣጠልና ኃይል እንዲመረት ስለሚያደርግ ጉልበትና ድፍረት ይጨምርላችኋል፤

⓫ መልስ መመለስ ከመጀመራችሁ በፊት እያንዳንዱ የፈተና ክፍል ስለያዛቸው የጥያቄ አይነቶች ገረፍ ገረፍ እያደረጋችሁ ብታዩ መልካም ነው። ይህም የተሰጣችሁን ሰዓት በጥያቄው ክብደት ልክ ከፋፍላችሁ ለመጠቀም ያግዛችኋል፤

⓬  አንዱ ጥያቄ ከከበዳችሁ ዝለሉት፤ አንድ ጥያቄ ላይ ተጠምዳችሁ ብዙ ጊዜ የምታጠፉ ከሆነ ቀጥለው ለሚጠብቋችሁ ጥያቄዎች ጊዜ ሊያጥራችሁ ይችላል። ስትዘሉት ግን የጥያቄ ወረቀቱ ላይ ምልክት ማድረጋችሁን እንዲሁም መልስ መስጫ ወረቀቱ ላይ ከተሰጡት አማራጮች አንዱን መልስ በግምት ማጥቆራችሁን አትርሱ። አጥቁሮ ማለፍ ምናልባት በኋላ የተሰጠው ጊዜ ቢያልቅና ወደ ጥያቄው መመለስ ቢያቅታችሁ መልስ መስጫ ቦታው ባዶ ሆኖ እንዳይቀር ያደርጋል፤

⓭ ቶሎ ለመውጣት አትቸኩሉ፤ ምንም አይጠቅማችሁም፤ ሰዓታችሁን አሟጥጣችሁ መጠቀማችሁን፤ ሁሉንም ጥያቄዎች በአግባቡ መመለሳችሁንና ማጥቆራችሁን አረጋግጡ። ጊዜ ቢተርፋችሁ ጥያቄዎቹን ለመከለስ ተጠቀሙበት፤

⓮ ያልገባችሁ ማንኛውንም ነገር ሲኖር ፈታኞችን ለመጠየቅ አትፍሩ፤

⓯ ልክ የፈተና ወረቀቱን ከመለሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የዚያ ትምህርት (subject) ነገር ማክተሙን በመገንዘብ ለቀጣዩ ፈተና እራስን ማዘጋጀት ይገባል። እንጂ፤ ስላለፈው ፈተና እያሰላልሰሉ መጨነቅ ለቀጣዩ ፈተና በምታደርጉት ዝግጅት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።




IT note G -10










#አስደሳች_ዜና!
ለዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና (ማትሪክ) ተፈታኝ ተማሪዎች
በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚያረጋችሁ የኦንላይን መተግበሪያ ይዘንላቹ መጥተናል።

#ESSLCE_With_Model_Exams: የማትሪክ ዝግጅት ፓኬጅ - ከ2012 እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ የተፈተኑትን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ጥያቄዎች ከነመልሶቻቸውና ሙሉ ማብራርያ  ጋር የቀረበ።

#Concise_Summary_With_Model_Exams(Grade 9-12): ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ያሉትን ትምህርቶች  በሙሉ በማጠቃልያ መልክ  የያዘ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መዘጋጀት በዋናነት የሚጠቅም።

#Ethiopian_New_Curriculum_All_Subjects: ሙሉ ኮርስ– ለእያንዳንዱ ትምህርት በከፍተኛ ጥራት የተቀረጹ  ቪዲዮዎች፣ Virtual Labs  ፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ(AI) የታገዙ ትምህርቶች፣ እና እየተዝናኑ የሚማሩበትን ጌሞችን ያካተተ።

#Short_Notes: አጫጭር ኖቶች– የየአመቱ  ትምህርቶችን ቀለል ባል መልኩ ፣ በእያንዳንዱ ትምህርት  ዋና ነጥቦችን አጠቃሎ የያዘ

ይፍጠኑ ይህ እድል እንዳያልጥዎ
www.selectacademy.edu.et በመመዝገብ ዝግጅቶን አሁኑኑ ይጀምሩ።
መልካም እድል ለመላው ተፈታኞች

ለበለጠ መረጃ
+251 926 913 404 | 9521

————————————————




The postponed exam will be given starting from May 25




Grade 9 Chemistry,
Sorry for being late!


Grade 12 4th Online Mock Examination Schedule

Wednesday Genbot 13 Afternoon: English
Thursday Genbot 14 Morning: Mathematics
Thursday Genbot 14 Afternoon:
SAT
Friday Genbot 15 Morning: Physics
Friday Genbot 15 Afternoon: Chemistry
Saturday Genbot 16 Morning: Biology




G-8 Harari Language Worksheets


Grade 7, 9, 10 and 11 Test

Thursday - Tuesday




Репост из: Grade 8 Info & Materials
Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
Grade 8: Social Studies

Unit 7: Unit 7: Contemporary Global Issues

Part 3: The development of climate action

══════════════

ይ🀄ላ🀄ሉን👇👇👇 share👇

Join our channel

t.me/Grade1_4Info

t.me/Grade5and6Info

t.me/Grade7Info

t.me/Grade8Info

t.me/Grade9Info

t.me/BasicComputer_Skills

Показано 20 последних публикаций.
OSZAR »