📙 ይድረስ ለውዷ ፊያሜታ ጊላይ... እንደምን አለሽልኝ..? እኔ በልጅነቴ ፍቅር እስከ መቃብር ነው ሲሉ ሰምቼ ዙቤይዳን እስከማገኝ ድረስ ኦሮማይን የሙጥኝ ብየ ነበር የቆየሁት። ሳድግ የፍርድ ቀን ዘመቻ ላይ ሆኜ በትኩሳት እየተንቀጠቀጥኩኝ... መልህቅ እንደሌለው መርከብ እየተናወጥኩኝ... ሌቱም አይነጋልኝ ስል ተገኘሁ። ሌላ ጊዜ ደግሞ ከአመጓ እስከ ዝጎራ እያካለልኩ መርበብትና ሰበዝን ይዤ በጠበኛ እውነቶች ስም አንፈርስም አንታደስም የሚል መፈክር ማሰማት ጀመርኩኝ። አይይይ... ይሄ ነገሬ እንኳን ለኔም አልገባኝም... ብቻ ሌላ ሰው ላይ ስፎክር እንደ ኢያሪኮ ግንብ በቅፅበት ለመፍረስ እንዳይሆንብኝ ሁሉቱ ጊዮርጊሶች ይጠብቁኝ።
📙 ይገርምሻል አንዳንድ ቀንና ህይወት ርዕስ የለውም ይባላል። ብዙ ሰው የሚስማማበት ሃሳብ ግን ያፍቃሪ ሰው ትንፋሽ ልክ እንደ መንደሪን ጣፋጭ መድሃኒት መሆኑን ነው። ከዕለታት ግማሽ ቀን ቤተልሄምን ተይው ፖለቲካን ዝም ብለሽ ሳሚኝ እያልኳት ሀገር ያጣ ሞት ድንገት በጠቢባን መንገድ በኩል ሲመጣብኝ ምንሽሮን ዋስ ጠርቼ አመለጥኩት። በሰሞነ ህማማት ደግሞ ገላና ገላዬ ሲታመሙብኝ ትዝታሽን ለኔ ትዝታየን ለአንቺ እያሰብኩኝ አሳለፍኩ።
📙 አንቺዬ ደግሞ ያልተነገረ ተረክና ያልተፃፈ ኑረት ታሪክ አይሆንምና አንድ ቀን ሜሎሪናን ህልምሽን አጫውችኝ ብያት ስታወጋኝ የአማኑኤል ሆስፒታል ታሪኮችን አስታወሰችኝ። እግረ መንገድ ይሁን እንጅ ዶክተር አሸብር የታካሚውንና የልብ ጠጋኙን ማስታወሻ እያገላበጠ ፊት ለፊቱ አሳንቲ የሰማይ ላይ ስዕል መስላ እንደተሰየመች በምናቤ ውል አለችብኝ። በመጨረሻም ከዚህ በላይ የነገርኩሽን ታሪክ ጨምሮ የአና ማስታወሻ፣ ዮቶርና ፖፒዮ የተሰኙትን ዜማዎች ከወንድም ሐሽማል ጋር ጋብዠሻለሁ።
.
.
ያንቺው ጠኃ ባላደራ ...!
የመፅሃፍት ስምና ገፀባህርያትን በመጠቀም የተፃፈ ታሪካዊ ደብዳቤ::
✍️ መሳይ አርቀው
ፊያሜታ ተናፍቀሻል🥰
ስንቶችን አንብበዋል?😊