🎤✨ድምፀ ተዋሕዶ✨🎤


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


#News_Tewahdo
#ዜና_ተዋሕዶ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ወቅታዊ ዜናዎች እና ትምህርቶችን ለሕዝብ ክርስቲያ የሚስተላለፍ ቻናል ነው።
አሁን ባለንበት በዚህ ጊዜ ማስታወቂያ ለማስነገር ትክክለኛ ቦታ ማህበራዊ ሚዲያ ነው ።
📊ዉጤታማ የሆነ የማስታወቂያ አገልግሎትን ከእኛ ዘንድ ያገኛሉ
📢ለማስታወቂያ ሥራ👉 @mane_tekel21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


◇አክሽን ◇የጦርነት ◇የጫካ ◇የወንጀል  እንዲሁም የፍቅር ፊልም ሚመችክ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በለው  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ  ፊልሞችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇






ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መንፈሳዊነትና ፖለቲካን ለይተን መጎዝ ይኖርብናል ሲሉ ጥሪ አቀረቡ !

ግንቦት 25 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሀይማኖት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተመረጡት ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የአቀባበል መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት አባታዊ መልዕክት የእግዚአብሔር ቤት በእግዚአብሔር መንገድ ብቻ መመራት ይኖርበታል ብለዋል።

የእግዚአብሔር ቤት በአምልኮተ እግዚአብሔርና በጸሎት ከመራነው ሁሉም ነገር ቀና ይሆናል ዓለማዊ መንገድ ከተደባለቀበት ግን አደገኛ ነው "ጋሻና ቅል ለየቅሉ ይሰለል።" እንደሚባለው መንፈሳዊነትና ፖለቲካን ለይተን መጎዝ ይኖርብናል ብለዋል።

አያይዘውም ለአዲሶቹ አመራሮች የሁላችንም ድጋፍና ጸሎት ያስፈልጋቸዋል፤ ስለሆነም ሁላችንም እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ልብ መካሪ በመሆን በሀቅና በቅንነት ልናግዛቸው ይገባል ብለዋል።

ይህችን ታላቅ ቤተክርስቲያን በእግዚአብሔራዊ መንገድ ሰርተን ካልጠበቅናት አደጋው የከፋ ይሆናል። ያሉት ቅዱስነታቸው ይህን በመገንዘብም ቤተክርስቲያናችንን በቀና መንገድና በመንፈሳዊነት መምራት ይኖርብናል ብለዋል።

ሰላም የሚገኘው ከሰላማዊቷ ቤተክርስቲያን ነው ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አበነ ማትያስ ከቤተክርስቲያን ያልተገኘ ሰላም ከየት ሊገኝ ይችላል? የተሰጠን ኃላፊነት መንፈሳዊ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባትም ለሀገራችን ሰላም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት በትጋት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

ጥላቻ፣ዘረኝነት፣ጎጠኝነት አይጠቅምም እኛ መንፈሳዊያን ነን እግዚአብሔር ሲፈጥረን ንፁሃን አድርጎ ነው የፈጠረን እኛ በራሳችን መንገድ በመጓችን ነው ወርደን ተጠባቂዎች የሆነው፤
ያሉት ቅዱስነታቸው እኛ ጠባቂዎች መሆናችንን አውቀን የጠባቂነት ሚናችንን ከጥላቻና ከዘረኝነት በራቀ መንገድ በመፈጸም ለሰይጣን ሳይሆን ለእግዚአብሔር ተመችተን መገኘት አለብን ነው ያሉት።

በመጨረሻም አሁን ለተመረጡት አባቶች እግዚአብሔር አምላክ ጽናትንና ብርታትን ይስጥልን፤ የአገልግሎት ጊዜአቸውን ጨርሰው የተሰናበቱትን አባቶችም እግዚአብሔር አምላክ በቸርነቱ ይጠብቅልን ሥራዎቻቸውን ሁሉ ይባርክ በማለት መርሐ ግብሩን በጸሎት አጠናቀዋል።

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══


ብፁዕ አቡነ አብርሃም የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት
ሊቀ ጳጳስ የሦስት ዓመታት የጠቅላይ ሥራ አስኪያጅነት የሥራ ጊዜያቸውን አጠናቀው ወደ ሀገረ ስብከታቸው መመለሳቸውን ምክንያት በማድረግ በባህርዳር ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
#የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ_ሕዝብ_ግንኙነት_መምሪያ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯


ገብታችሁ እዩልኝ🙏🙏🙏🙏🙏




"እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕርገት በዓል አደረሳችሁ!"

በዚችም ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ በነሣው ሥጋ ከአባቱና ክመንፈስ ቅዱስ ጋራ ወደአለው የአንድነት አኗኗሩ ከሰማያት በላይ ያረገበት ሆነ።

እርሱም በረቀቀ ጥበቡ በመከራው በሞቱና በመነሣቱ ሥራውን ከፈጸመ በኋላ አርባው ቀን ሲፈጸም በነፋሳት ክንፍ ላይ ሁኖ ዐረገ። ያን ጊዜ በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ ወጣ በነፋሳትም ክንፎች ላይ ሁኖ ወጣ ያለው የዳዊት ትንቢት ተፈጸመ።

በዚህም ዕርገቱ ለሚያምኑበት በልዕልና ወደሚኖሩበት የሚዐርጉ መሆናቸው ተረዳ ተረጋገጠ ራስ በአለበት ሕዋሳት ሊኖሩ ይገባልና።

አዳም አስቀድሞ በምድራዊ ርስቶች በሲኦልም እንደኖረ መኖርንም እንደ ቀደመ እንዲሁ ዳግማዊ አዳም ጌታ በመንግሥተ ሰማያት ርስት መኖርን ቀደመ።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዕርገቱን ከትንሣኤው አከታትሎ ወዲያውኑ አላደረገም መናፍቃን ዕርገቱ ምትሐት ናት ብለው እንዳያስቡ።

ጌታችንም በረቀቀ ጥበቡ የደቀ መዛሙርቱን ተሸብሮ የነበረ ልቡናቸውን እያጽናና መነሣቱንም እያስረዳቸው ከትንሣኤው በኋላ አርባ ቀን ኖረ።

በጌታችንም ዕርገት የዳንኤል ትንቢት ተፈጸመ እንዲህ የሚል ሌሊት በራእይ አየሁ እነሆ ታላቅ እንደ ሰው ልጅ የሆነ መጣ ዘመናትን ወደ ሚያስረጃቸው ደረሰ ከፊቱም አቀረቡት።

የዘላለም አገዛዝ ጌትነት መንግሥት የዘላለም ሥልጣን ተሰጠው ሕዝቡና አሕዛቡ ሁሉ መንደር መንድረው የሚኖሩትና ነገዱም ነገሥታቱም ሁሉ ይገዙለታል አገዛዙም የዘላለም አገዛዝ ነው መንግሥቱም የማያልፍ የማይጠፋ ነዋሪ ነው።

ለእርሱም ምስጋና ይሁን ከቸር አባቱ ሕይወት ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ለዘላለሙ አሜን።

ምንጭ፡- መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯




ዲ/ን ዶር ቴዎድሮስ በለጠ ከአንድ ዓመት የጽሙና ጊዜ በኋላ ቀሪ ጊዜያቸውን በምንኩስና ሕይወት ለመኖር ጉዞውን ጀምረዋል። አባ ክፍለ ሥላሴም እንደ ተባሉ ምንጮች ገልጠዋል። የአበውን ጸጋ ሰጥቶ ያጽናልን
“ያላገባው ጌታን እንዴት ደስ እንዲያሰኘው የጌታን ነገር ያስባል፤” 1ኛ ቆሮ 7፥32

        ምንጭ፦ማ/ሚድያ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯


ተጋበዙልን እየገባችሁ አዳምጡ ሰብስክራይብም በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🙏🙏🙏




ሰበር ዜና
--
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ባደረገው ስብሰባ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላልፏል፦

1. ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆርስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
2. ብፁዕ አቡነ  ሳዊሮስን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ 
3. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን የሐዲያ ሀ/ስብከትን እንደያዙ የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
4. ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘኮሎራዶን የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤
5. ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ሚኒሶታን እንደያዙ የኮሎራዶ ሀ/ስብከትን እንዲመሩ፤
6. ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የደቡብ አፍሪካ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳ ጳስ፤
7. ብፁዕ አቡነ ዕንባቆምን የገዳማት መምሪያ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ፤
8. ብፁዕ አቡነ ሙሴ አውስትራልያን እንደያዙ የግቢ ቅዱስ ገብርኤልና የበዐታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲመሩ ወስኗል።

ምንጭ፦ የኢ/ኦ/ቤ/ክ ሕዝብ ግንኙነት


ስለ 3 ዓመት ታማኝ ኖላዊነትዎ እናመሰግናለን
***

በዘር፣በሱሁት አስተምሕሮ እና በፓለቲካ ለምድ የተሸፈኑ ጠላቶቻችን ዝናራቸው አራግፈው ቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ የወረወሩትን ቀስት ለመመከት ከሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነጳጳሳት ጋር ላደረጉት ተጋድሎ እናመሰግናለን።

ወጀብ በጸናብን ሰዓት እረኝነትዎ ባለመጣል ስላልታሙ እናመሰግናለን። በፈርዖን እና ቄሳር ፊት ግልገሎችን የመጠበቅ አደራዎትን ስላልጣለ እናመሰግናለን።

ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ክብር ሲሉ ብቻ ከዘርዎ እስከ ማንነትዎ ተብጠልጥለው በመከራ ስለማጽናት አማናዊ መምህር ስለሆኑ እናመሰግናለን።

ይህን እውነት እና ታሪክ አካል ሆነን ተመልከትናል እና ሃቅን እንመሰክራለን

በረክትዎ ይደርብን !!!

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
       @News_Tewahdo
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯


እየገባችሁ አዳምጡ




                        †                        

🕊 💖  ክብራችን : ሞገሳችን  💖  🕊

🕊

እንኳን የዜማው ሊቅ ለሆነው ለቅዱስ ያሬድ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሰን።

ግንቦት ፲፩ [ 11 ] በዚህች ቀን የዜማው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ወደ ብሔረ ሕያዋን የተሰወረበት ቀን ነው።

🕊

† ቅዱስ ያሬድ :- ከእግዚአብሔር ያገኘነው አባታችን : ክብራችን : ሞገሳችን ነውና በምን እንመስለዋለን ?

- አንደበቱ ጣፋጭ [ ጥዑም ] ::
- ልቡናው የቅድስና ማሕደር::
- ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ ነው::
- እስከ አርያም ተነጥቆ የማይፈጸም ምሥጢርን የተመገበ ማን እንደርሱ !

ሊቀ ሊቃውንት እዝራ ሐዲስ እንደሚሉት :- "ቅዱስ ያሬድ ለኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ : ሙሉ አካሏ ነው::"

🕊  💖                             💖  🕊

† " እንዲህ ያለው ሰው ከአሥራ አራት ዓመት በፊት እስከ ሦስተኛው ሰማይ ድረስ ተነጠቀ:: እንዲህ ያለውንም ሰው አውቃለሁ:: በሥጋ እንደ ሆነ ወይም ያለ ሥጋ እንደሆነ አላውቅም:: እግዚአብሔር ያውቃል:: ወደ ገነት ተነጠቀ:: ሰውም ሊናገር የማይገባውን: የማይነገረውን ቃል ሰማ:: " † [፪ቆሮ.፲፪፥፪-፭]


[ የመንፈስ ቅዱስን ምግብን የጠገበ ፤ ከመጻሕፍት ሁሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማኅሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለሆነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል። ]

[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ]


እኒህ ሦስቱ:-

፩. የተሸከሙት ሸክም ያላጎበጣቸው

፪. የመከራ ቀን ጥብዐታቸው

፫. መከራውን ያለፉበት ጥበባቸው

፬. ለሲኖዶሳዊ ልዕልና ተጋድሏቸው

እናት ቤተ ክርስቲያንን በጃት!

"በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።”
 
#ሐዋርያት ፳፥፳፰

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!


መልካም ቀን ይሁንላችሁ (ሰብስክራይብ ማድረግ እንዳይረሳ🙏🙏🙏🙏



Показано 20 последних публикаций.
OSZAR »