በመንታ ጡቶቿ መሃል ተጋድሜ በጥርሷ ዘበኛ በከንፈር ታድሜ ስነቃ ባዶ ቤት ናፍቆት ተሸልሜ ላላገኛት ነው ወይ ላይፈታ ህልሜ ላላገኛት ነው ወይ ይሄ ሁሉ ህልሜ በጥርሷ ዘበኛ በከንፈር ታድሜ በጡቶቿ መሃል ሳድር ተጋድሜ ስነቃ ባዶ ቤት ናፍቆት ተሸልሜ ላላገኛት ነው ወይ ላይፈታ ህልሜ ላላገኛት ነው ወይ ይሄ ሁሉ ህልሜ እንዴት ያስደስታል ፍቅር በህልም አፍ ገጥሞ ጨዋታ ሲያስለመልም ጽድቅ ነበር በዝያ ጭንቅም የለም ሚኞት ባጥቢያ ዳኛ ላይታገድ በህልም አለም ጉዞ በሃሳብ መንገድ ሌት መባከን ይሻል ከኡጉል መውደድ ሃገሯ ወዲያ ማዶ ናፍቆቷ መጣ ማልዶ ስጋጃ እንጥፌ ግምጃ ብጋርድ እንኳን ሊሞቀኝ አለኝ ብርድ ብርድ ጤዛ ወሮታል የኛውን ሰፈር ብቻ መኝታ እንደምን ልድፈር ሌት ሌት ለመንገስ ቀን ከመሰወር ምነው እንደ አጥብያ ብትወረወር
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏
👇👇👇
@old_musica
ሼር🙏