EBS TV NEWS


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


Get the latest headlines and breaking news in politics, business, technology, sports, entertainment, and cryptocurrency. Join our channel for real-time updates and concise, reliable news delivered straight to your device!

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ-ዝግጅትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።


የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለግንቦት 20
የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላለፉ


የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በአነጋጋሪ ሁኔታ ለኢትዮጵያውን "የ34ኛ ዓመት የነጻነት በዓል" የመልካም ምኞት መልዕክት ማስተላለፋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ ድረ ገጽ ላይ የወጣው የማርኮ ሩቢዮ መግለጫ የተላለፈው ትናንት ማክሰኞ በግንቦት 20 ዋዜማ ነው።

በጉዳዩ ላይ በአዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ማብራሪያ ለማግኘት የተደረገው ጥረት ምላሽ ባያገኝም፤ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በይፋዊ ገጹ ላይ የወጣው መልዕክት መነሳቱን ዘገባው ጠቁሟል፡፡


ኢትዮጵያ በአህያ ብዛት የአለምን አንድ አምስተኛ መያዟ ተሰማ

ኢትዮጵያ አህዮችን ለኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በዋናነትም በመጓጓዣነት እና ለንግድ እንቅስቃሴ በመጠቀም በቀን ከ 200-400 ብር ገቢ እንደሚያገበት የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ፕሮግራም መረጃ ያመላክታል።

በዓለም ላይ ከ51.7 ሚሊዮን በላይ አህዮች እንደሚኖሩ የሚገመት ሲሆን ኢትዮጵያ ከ10 ሚሊዮን በላይ አህዮች እንዳሏት ይገመታል::


የትራምፕ አስተዳደር ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲን ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን እንዳይቀበል አገደ


የትራምፕ አስተዳደር ሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን እንዳይቀበል ያገደ ሲሆን ይህም ከአሜሪካ አንጋፋው ዩኒቨርስቲ ጋር ያለውን አለመግባባት አባብሶታል።

የአገር ውስጥ ደህንነት መስርያ ቤት ኃላፊ ክሪስቲ ኖኤም በኤክስ ገጻቸው ላይ እንደጻፉት አስተዳደሩ ሀርቫርድ “ተማሪዎች እና ስደተኛ ያልሆኑ ተማሪዎችን መቀበል የሚያስችለውን ዕድል ሕግን ማክበር ባለመቻሉ ምክንያት ተሰርዟል” ብለዋል።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


ከ 15 አመት በፊት ዛሬ Laszlo hanyechz የተባለ ግለሰብ 2 PIZZA በ 10,000 Bitcoin ገዝቶ ነበር

ያ BITCOIN አሁን ላይ 1.2 BILLION DOLLAR ዋጋ አለዉ


የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአስር ዓመት ከባድ የግድጅ ጉልበት ሥራ ተፈረደባቸው

245 ሚሊዮን ዶላር የመዘበሩት የቀድሞው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር በሙስና ወንጀል 10 ዓመት ከባድ የግዳጅ የጉልበት ሥራ እንደተፈረደባቸው ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ሆሴ ማሲንጋ ትግራይ ክልል መግባታቸው ተሰማ

አምባሳደሩ በጉብኝታቸው የአሜሪካ መንግስት ለተፈናቃዮች የሚያደርገው የሰብዓዊ ድጋፍ ያለበትን ሁኔታ ለመገምገም እና የፕሪቶሪያውን የተኩስ አቁም ሥምምነት የህወሓት ጄኔራሎች በትክክል በሚተገብሩበት ሁኔታ ላይ ለመምከር እና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ እንደሆነ አሳውቀዋል።




''ጦርነትና ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች አድራሻቸው የሚጠፉ ሰዎች እየጨመሩ ነው'' ተመድ

የመንግስታቱ ድርጅት እንዳለው ጦርነቶችና ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎች የሚጠፉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ነዉ፡፡

ዓለምዓቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ እንዳስታወቀው በ 2024 ብቻ 56 ሺ ሰዎች ስለመጥፋታቸው ሪፖርት ደርሶታል፡፡

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመካከለኛው ምስራቅ ረዳት ሴክሬታሪ ጄነራል ካሊድ ኪያሪ፤ይሄንን ችግር ለመፍታት የዓለምዓቀፍ ድጋፍና የዓለምዓቀፍ ህግ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡


''በጋዛ ባለው ሁኔታ ተረብሸናል'' አሜሪካ

የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በጋዛ ባለው የሰብዓዊ ሁኔታ ዩናይትድ ስቴትስ "መረበሿን" ገለፁ።

ሩቢዮ ይህንን ያሉት ሐሙስ ዕለት እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 114 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጤና ባለስልጣናት ከተናገሩ ወዲህ ነው።


ጣናነሽ-2 የሰው ማጓጓዣ እና የመዝናኛ ጀልባ ኢትዮጵያ ገባች

በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ለኢትዮ ፌሪስ ጣና የሀገር ውስጥ የውሃ ትራንስፖርት እንዲያገለግሉ ከተገዙት ሁለት ዘመናዊ ጀልባዎች መካከል ሁለተኛዋ ጣናነሽ-2 ጀልባ በዛሬው ዕለት ኢትዮጵያ ገብታለች፡፡

ከዚህ ቀደም ከጂቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ ጉዞ የጀመረችው የጣናነሽ-2 ጀልባ ለአንድ ወር ተኩል ያህል ተጉዛ በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያን ድንበር ማቋረጧ ነው የተነገረው።

በጉዞ ወቅት ያጋጠመውን አስቸጋሪ የመንገድ ሁኔታ ለመፍታት የተለያዩ የኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመንግሥት አካላት ከፍተኛ ርብርብ ማግረጋቸው ተገልጿል፡፡


"የፍቺ ቁጥርን ለመቀነስ የቅድመ ጋብቻ ሥልጠና እየሰጠሁ ነው" ማኅበሩ

የፍቺ ቁጥርን ለመቀነስ ያለመ የቅድመ ጋብቻ ሥልጠና እየሰጠ መሆኑን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ ሚኒስቴሩ ይህን ያስታወቀው በዛሬው ዕለት የሚከበረውን ዓለማቀፍ የቤተሰብ ቀን አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ ነው፡፡

ሰዎች ለፍቺ ከመዳረጋቸው አስቀድሞ፣ ወደ ትዳርም ከመግባታቸው በፊት የተለያዩ ሥልጠናዎችን እንደሚወስዱና የምክር አገልግሎት እንደሚሰጣቸው የገለጹት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሁርያ አሊ፤ ይህም ወደ ትዳር ከገቡ በኋላ የሚገጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ያግዛቸዋል ብለዋል፡፡

ሥልጠናው ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት፣ ወደ ትዳር ከገቡ በኋላና በትዳር ላይ ሳሉ የሚሰጣቸው መሆኑ ተጠቁሟል፡፡




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


ለትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች አዲስ ቀለም እና ኮድ ለሹፌሮቹም ዩኒፎርም ሊዘጋጅ መሆኑ ተሰማ


መንግሥት፣ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እንደየአገልግሎታቸው ዓይነት “ወጥ ቀለም” እና መለያ ኮድ እንዲኖራቸው እቅድ መያዙን ዋዜማ ዘግቧል። የተሽከርካሪዎች ቀለምና መለያ ኮድ ከከተማ ከተማ የተለያየ ይሆናል ተብሏል።

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ተሽከርካሪዎች ሹፌሮችም፣ ወጥ የደንብ ልብስ እንዲለብሱ ለማድረግ እቅድ እንደተያዘ ዋዜማ ተረድታለች። የትራንስፖርት ሚንስትር ዓለሙ ስሜ፣ ያረጁ ተሽከርካሪዎችን ከሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ውጭ ለማድረግ እንደተወሰነ ሰሞኑን ባንድ ስብሰባ ላይ መናገራቸውም ተመልክቷል።


ቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ደስታ ከረሜላ እንደገና መመረት መጀመሩን ገለጹ

ለ14 ዓመታት ከሥራ ውጭ የነበረው ደስታ ከረሜላ እንደገና መመረት ጀምሯል።

ወንጂ ስኳር ፋብሪካ በሠራው ሪፎርም የሥኳር ምርቱን ማሳደግ የቻለ መሆኑን በመግለጽ፤ ለ14 ዓመታት ከሥራ ውጭ የነበረው የብዙዎች ትዝታ፣ ደስታ ከረሜላ እንደገና ማምረት ጀምሯል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አሳውቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወንጂ ስኳር ፋብሪካ የዛሬ ሦስት ዓመት ለሠራተኞቹ ደሞዝ መክፈል ተስኖት እንደነበር አንስተው፤ በተሠራው የሪፎርም ሥራ፣ ዛሬ ከአንድ ሺህ 500 ኩንታል የቀን ምርት ወደ ሰባት ሺህ ኩንታል በቀን ለማደግ መቻሉን አብራርተዋል።

ፋብሪካው በዘጠኝ ወራት ውስጥ 8 ነጥብ 7 ቢልየን ብር ገቢ ማስገባቱንም አክለው ገልጸዋል።


''መብራት ያላበራ እቀጣለሁ” የአዲስ አበባ አስተዳደር


በአዲስ አበባ ከተማ በመንገድ ዳር የሚገኙ የንግድ ወይም አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከምሽት 12 እስከ ንጋት 12 ድረስ “የውጭ” እና “የውስጥ መብራት” ካላበሩ እንዲሁም በምሽት ለአገልግሎት ክፍት መሆናቸውን የሚያሳይ በመብራት የሚሰራ ምልክት ካላስቀመጡ እስከ 10 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት ሊያስቀጣቸው የሚችል ደንብ የከተማዋ አስተዳደር ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።

ደንቡ፣ በመንገድ ዳር የሚገኙ ማናቸውም የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የንግድ መደብሮች እንዲሁም መኖሪያ ቤቶች በሕንጻቸው የፊተኛው ገጽ መብራት ወይም የፋሳድ ላይት መብራት የማስገባት ግዴታ ጥሎባቸዋል።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »