🚨 ዌስትሃም የቼልሲን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል !
ቶክ ስፖርት ማለዳውን ይዞት በወጣው መረጃ መሰረት ቼልሲ ለመሃመድ ኩዱስ ያቀረበው የዝውውር ጥያቄ በዌስትሃም ውድቅ መደረጉን ገልፆል።
ዌስትሃም መሀመድ ኩዱስን ለማስፈረም ከቼልሲ የቀረበለት የተጫዋች እና የጥሬ ገንዘብ ውል የነበረ ቢሆንም ክለቡ ውድቅ አድርጎታል።
ቼልሲዎች ግብ ጠባቂያቸውን ሮበርት ሳንቼዝ እና አማካዩን ኪየርን ዴውስበሪ-ሃልን እንዲሁም ተጨማሪ ገንዘብ አክለውበት ለመስጠት ፍቃደኞች ነበሩ፤ ነገር ግን ዌስትሃም ፍቃደኛ አልነበረም።
መሀመድ ኩዱስ በፕሪምየር ሊጉ መቆየት ስለሚፈልግ ከሳዑዲ አረቢያ የመጡ የዝውውር ጥያቄዎችን ውድቅ አድርጓል።
አጥቂው መዶሻዎቹን በ2023 ከአያክስ በ38 ሚሊየን ፓውንድ የተቀላቀለ ሲሆን በዚህ የውድድር ዘመንም 35 ጨዋታዎችን አድርጎ 5 ጎል ሲያስቆጥር 4 ግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
በአጠቃላይ ተጫዋቹ ለለንደኑ ክለብ ዌስትሃም ዩናይትድ 80 ጨዋታዎችን አድርጎ 19 ጎሎችን ሲያስቆጥር እና 10 አሲስቶች አድርጓል።
SHARE"
@EthioZena_Chelsea@EthioZena_Chelsea