የጉምሩክ ኮሚሽን በአዲስ ዓለም ዐቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በተዘጋጀው የኢትዮጰያ ቴክ ኤክስፖ(ETEX 2025) ላይ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
*************
ግንቦት 9/2017 ዓ.ም (ጉምሩክ ኮሚሽን)
በትናንትናው እለት በተከፈተው ETEX 2025 የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ላይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እየተሳተፈ ይገኛል።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት ኤክስፖውን የጎበኙ ሲሆን የከፍተኛ አመራሮች የምክክር መድረክንም አስጀምረዋል፡፡
በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን ለማዘመን በርካታ ተግባራትን እያከናወነች እንደምትገኝ የገለጹ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አንዱ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ነው ብለዋል፡፡
ቴክኖሎጂ ዓለምን እየመራ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያም ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደሆነም አስታውቀዋል፡፡
ከዚህም በተጓዳኝ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ መሠረተ ልማት እና የክሕሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች በአርዓያነት ሊጠቀሱ የሚችሉ ተግባራትንም ማከናወኗንም ጠቅሰዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽንም በኤክስፖው ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ሲሆን በመድረኩ ከ7 በላይ የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን የሚያቀላጠፉ እና የህግ ማስከበርን የሚያጠናክሩ ቴክኖሎጂዎችን ይዞ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡
በኤክፖው የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሚጠቀምባቸው የኢትዮጵያ ከስተምስ ማኔጅመንት ሲስተም፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ አንድ መስኮት አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሮኒክ ካርጎ ትራኪንግ ሲስተም እና ሌሎች ቴክኖሎጂዎች እየቀረቡ ይገኛሉ።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ሴልማ ማሊካ፣ ከሌሎች ሀገራት የተውጣጡ የስራ ሃላፊዎች፣ ክቡራን ሚኒስትሮች እንዲሁም ሌሎች የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት ተቋሟት እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡
ለሶስት ቀናት የተዘጋጀው ይህ ኤክስፖ በነገው እለት የሚጠናቀቅ ይሆናል።
ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission