Postlar filtri


ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር መሆኗን አንድ ሪፖርት ጠቆመ

የዓለማችን የኑሮ ውድነት ትልቅ የመረጃ ቋት፤ ኢትዮጵያ በኑሮ ውድነት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ ሀገር መሆኗን ገልጿል።

ቪርጂን አይላንድስ፣ ስዊዘርላንድ፣ አይስላንድ፣ ባሀማስ፣ ሲንጋፖር፣ ሆንግ ኮንግ፣ ባርባዶስ፣ ኖርዌይ፣ ፓፓዋ ኒው ጊኒ እና ዴንማርክ በኑሮ ውድነት ከአንድ እስከ አስር ያለውን ቦታ ይዘዋል።


እስራኤል የመጨረሻ ግቤ የኢራኑን መንፈሳዊ መሪ ማጥፋት ነው አለች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ  የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ኻሜኔይን “ሕልውና መቋጨት” በቴህራን ላይ የሚካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ አንዱ ዓላማ እንደሆነ ተናግረዋል።




አሜሪካ ጦር ጀቶቿን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ማንቀሳቀሷ ተሰማ

አሜሪካ ከእስራኤል ጋር ተሰልፋ ኢራንን ልታጠቃ ትችላለች የሚሉ መላምቶች በተበራከቱበት በአሁኑ ወቅት አሜሪካ በተለያዩ የጦር ሰፈሮች የሚገኙ የጦር ጄቶችን ጨምሮ የጦር መሳሪያዎች ወደ መካከለኛው ምስራቅ እያንቀሳቀሰች መሆኑ ተገልጿል።

አሜሪካ ኤፍ- 16፣ ኤፍ- 22 እንዲሁም ኤፍ-35 የተሰኙ ተዋጊ ጄቶችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ የጦር ሰፈሮች ማዛወሯን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።


የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ታገደ

የሲቪል ማኅበራት ባለሥልጣን፣ የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማኅበርን ከማናቸውም እንቅስቃሴ ማገዱን ዋዜማ ዘግቧል።

ባለሥልጣኑ ማኅበሩን ያገደው፣ "ሐሰተኛ ማኅተም" በመጠቀም እና ጠቅላላ ጉባኤ በወቅቱ ባለመጥራቱ እንደኾነ ገልጧል ተብሏል።

የጤና ባለሙያዎችን የሥራ ማቆም አድማ ሲያስተባብር የቆየው ንቅናቄ በበኩሉ፣ ማኅበሩ የታገደው የጤና ባለሙያዎች ለሥራ ማቆም አድማ ሲያደርጉት የነበረውን ንቅናቄ በመደገፉ ነው ብሏል።


ናይሮቢ ውስጥ የጦማሪው አልበርት ኦጅዋንግን ሞት ተከትሎ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

የ31 ዓመቱ መምህርና ጦማሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለ መሞቱን ተከትሎ በዛሬው ዕለት በናይሮቢ ማዕከላዊ የንግድ አካባቢዎች ተቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል።

ተቃዋሚዎች የፖሊስ ምክትል ኢንስፔክተር ጄኔራል ኤሊዩድ ላጋት ለኦጅዋንግ ሞት ምክንያት ናቸው በማለት እንዲታሰሩና ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡


ኢራን የአሜሪካን ጦር ሠፈሮች ለመምታት ተዘጋጅታለች ሲል ኒው ዮርክ ታይምስ ዘገበ

የኢራን ሚሳኤሎች ዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤልን ጦርነት ከተቀላቀለች በአካባቢው የሚገኙትን የአሜሪካ ጦር ሠፈሮች ለመምታት መዘጋጀታቸውን ኒውዮርክ ታይምስ የአሜሪካ የስለላ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።




''ኤርትራውያን የመብቶች ጥሰት ይፈጸምባቸዋል'' ተመድ

ኤርትራዉያን ስልታዊ የመብት ጥሰት እየደረሰባቸዉ መሆኑን የመንግሥታቱ ድርጅት ይፋ ባደረገዉ ዘገባ ገልጿል።

በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሦስት አስር ዓመታት የስልጣን ዘመን ኤርትራዊያን ከፍተኛ የመብት ጥሰር እየደረሰባቸዉ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት የኤርትራ የሰብአዊ መብት ልዩ ዘገባ አመልክቷል።

በአፍሪቃ ቀንድ ወደ 3.5 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ያላት ትንሿ አገር ኤርትራ አንዳንድ ጊዜ “የአፍሪቃ ሰሜን ኮርያ” በሚል ቅጽል ስም እንደምትታወቅም ዘገባዉ አስታዉሷል።


ትራምፕ ኢራን ያለ ቅድመ ሁኔታ እጅ እንድትሰጥ ጠየቁ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላ አሊ ኻሜኔይ የት እንደሚገኙ በትክክል እንደሚያውቁም ገልጸዋል። ይሁን እንጂ ዩናይትድ ስቴትስ እርሳቸውን ለጊዜውም ቢሆን ለማጥፋት ፍላጎት እንደሌላት ተናግረዋል።

ትራምፕ የኢራን አየር ክልል ሙሉ በሙሉ በአሜሪካ ቁጥጥር ስር መዋሉንም አስታውቀዋል። በሌላ በኩል የኢራን መሪ የት እንዳሉ ብናውቅም አሁን ላይ እንዲገደሉ አንፈልግም ሲሉ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ተናግረዋል።


ሶስት አሽከርካሪዎች 300ሺ ብር ተቀጡ!

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወሎ ሰፈር አካባቢ በእግረኛ መንገድ ላይ መኪና ሲነዱ የተገኙ ሦስት አሽከርካሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል በገንዘብ እንደቀጣቸው አስታውቋል፡፡


እነዚህ ደንብ ጥሰዋል የተባሉ 3 አሽከርካሪዎች በእያንዳንዳቸው 100,000 ብር መቀጣታቸውን ባለሥልጣኑ ጠቁሟል።


ምክር ቤቱ ዛሬ በሁለት ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ


የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በወንጀል የተገኘን ንብረት ሕጋዊ ማስመሰልና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበውን የማሻሻያ አዋጅ አፅድቋል፡፡


የማሻሻያ አዋጁ በሦስት ተቃውሞና በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል፡፡ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው 37ኛ መደበኛ ስብሰባ የተወያየበት ሌላኛው ጉዳይ የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅ ሲሆ፤ ረቂቅ አዋጁን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል፡፡




አዲስ የተሾሙት የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ በእስራኤል ተገደለ

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የኢራን የጦርነት ጊዜ ዋና አዛዥ እና ከአገዛዙ ከፍተኛ የጦር አዛዦች አንዱ የሆኑትን አሊ ሻድማኒ መገደሉን አስታውቋል።

ዋና አዛዡ የተገደሉት በማዕከላዊ ቴህራን በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ላይ በተደረገ የአየር ድብደባ መሆኑም ተዘግቧል።

አሊ ሻድማኒ በዚህ ወር መጀመሪያ እስራኤል የጥቃት ኦፕሬሽን ውስጥ የተገደሉትን የቀድሞ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አላም አሊ ራሺድን ተክተው ሚናውን መረከባቸው ይታወሳል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።


ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለዶናልድ ትራምፕ ያስተላለፈው የሰላም መልዕክት!

የዓለማችን ታላቁ የእግር ኳስ ኮከብ፣ የ5 ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለዓለም ሰላም ጥሪ አስተላልፏል።

እየተባባሰ ለመጣው የእስራኤል እና የኢራን ውጥረት መፍትሄ እንዲገኝ በመመኘት፣ ለአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክት አስተላልፏል።

ሮናልዶ በሀገራቱ መካከል ያለው ውጥረት እንዲረግብ እና ሰላም እንዲሰፍን ያለውን ጥልቅ ምኞት ገልጿል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕም "ጨዋታ ለሰላም" የሚል ያልተጠበቀ ስጦታ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ እንደተላከላቸው ይፋ አድርገዋል።

ይህ ስጦታ፣ ሮናልዶ የፈረመበትን የፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ማልያ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ኮስታ እጅ ተቀብለውታል።


ኢራን ለእስራኤል የሞሳድ የስለላ ድርጅት ሲሰራ ነበር ያለችውን ዜጋዋን በሞት ቀጣች

ኢራን በ2023 በቁጥጥር ሥር የዋለውንና ለእስራኤል የሞሳድ የስለላ ድርጅት ሲሰራ ነበር ተብሎ የተፈረደበትን ዜጋዋን በስቅላት ቀጥታለች፡፡

የኢራን የፍትህ አካላት እስማኢል ፈክሪ የተባለው ኢራናዊ የሞሳድ ወኪል፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ጦርነት እንዲቀሰቀስ ሲሰራ እንደነበር በዛሬው ዕለት ባወጡት መረጃ አስታውቋል።

ግለሰቡ ከሁለት የሞሳድ መኮንኖች ጋር ግንኙነት እንደነበረው እና በጣም ሚስጥራዊነት ያላቸውን የብሄራዊ ደህንነት መረጃዎች ማለትም፤ ስትራቴጂካዊ ቦታዎች ያሉበት ቦታ፣ የተወሰኑ ግለሰቦች ዝርዝር እና የውስጥ ድርጅታዊ ተልእኮዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ የመገናኛ መስመሮች በኩል ለማስተላለፍ መሞከሩ የዳኝነት መዝገቡ እንደሚያሳይ ቴህራን ታይምስ ዘግቧል፡፡


እስራኤል “የቴህራንን የአየር ክልል በሙሉ” መቆጣጠሯን ገለፀች

የእስራኤል እና የኢራን ጥቃት በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት እስራኤል የቴህራንን የአየር ክልል መቆጣጠሯን አስታወቀች።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ እስራኤል “ የቴህራንን አየር ክልል ሙሉ በሙሉ መቆጣጣር ችላለች” ሲሉ ተናግረዋል።

ብርጋዴር ጄኔራል ኤፊ ዴፍሪን ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ላይ “የኢራን አንድ ሦስተኛ የምድር ለምድር የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን አውድመናል” ሲሉ ተናግረዋል። የእስራኤል ጦር ከ120 በላይ የሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን ማውደሙን ገልጿል።




አስከሬን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ መኪና ተገልብጦ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰቆጣ ወረዳ 07 ቀበሌ ዳብል ማሪያም ዲብር ሳይል አፈራ ጎጥ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገልጿል።

የሰሌዳ ቁጥር አማ 30336 ኮድ 3 የሆነ ሚኒባስ ከደሴ ወደ ሰቆጣ አስከሬን ጭኖ በመጓዝ ላይ ሳለ ተገልብጦ በደረሰ ድንገተኛ የትራፊክ አደጋ 3 ወንድ 2 ሴት በድምሩ የ5 ሰዎች ሕይወት ማለፉን አሐዱ ከወረዳው ያገኘው መረጃ ያመላክቷል።

በተከሰተው የትራፊክ አደጋ 7 ወንድ 4 ሴት ቀላልና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑን፤ በሰቆጣ ፖሊስ ጽ/ቤት የመንገድ ደህንነት ትራፊክ ክፍል ኃላፊ ኢንስፔክተር ሲሳይ አበራው ገልጸዋል።


ትራምፕ ኢትዮጵያ ላይ የጉዞ እገዳ ሊጥሉ መሆኑ ተሰማ

የትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያን ጨምሮ የ36 አገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ለማገድ ሃሳብ እንዳለው ሮይተርስ እና ዋሽንግተን ፖስት የተመለከቱት የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ውስጣዊ ሰነድ አመለከተ። በዚህ የሁለት ወራት የጊዜ ገደብ በተቀመጠለት የዕገዳ ውሳኔ ውስጥ አብዛኞቹ አገራት ከአፍሪካ ሲሆኑ ኢትዮጵያ፣ጂቡቲ፣ደቡብ ሱዳን እና ግብፅ ይገኙበታል።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »