Postlar filtri


አማዞን በአውስትራሊያ በ13 ቢሊዮን ዶላር የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዳታ ሴንተር ሊገነባ ነው፡፡
የአማዞን የክላውድ ኮምፒዩቲንግ እና የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፍላጎቱ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ በአውስትራሊያ የዳታ ሴንተር ለመገንባት እስከ 2029 ባሉት ዓመታት እስከ 13 ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
አማዞን እንዳስታወቀው ዳታ ሴንተሩ ሲገነባ ምርታማነትን በማሳደግ የአውስትራሊያን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ያዘምናል፡፡
እንደ ብሉምበርግ ዘገባ የአውስትራሊያ ኢንዱስትሪ፣ ሳይንስ እና ሪሶርስ ዲፓርትመንት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና በአውቶሜሽን ዘርፍ በ2030 ለሀገሪቱ አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት እስከ 600 ቢሊዮን ዶላር አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


የካንሰር ምርመራ ሂደትን የሚያቀላጥፍ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌር ተዋወቀ፡፡

የእንግሊዝ ተመራማሪዎች የሳንባ ካንሰር እና ኢንፌክሽንን በፍጥነት ለመመርመር የሚያስችል የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሶፍትዌር አስተዋውቀዋል፡፡

በሙከራ ሂደቱ እንደተረጋገጠው ሶፍትዌሩ በደቂቃዎች ውስጥ እስከ 85 የሚደርሱ ከበሽታ ጋር ተያያዥ ሁኔታዎችን ይለያል፡፡ ከበሽታ ልየታ በተጨማሪም የደረት ራጅን በማንበብ ታካሚዎች በፍጥነት እና ደህንነቱ የተጠበቀ ህክምና እንዲያገኙ ያስችላቸዋል፡፡

ቢ.ቢ.ሲ በዘገባዉ እንዳመለከተዉ ሶፍትዌሩ በርካታ በሽተኞችን በፍጥነት ሕክምና እንዲያገኙ በማድረግ ታካሚዎችን ከመጥቀሙም በሻገር ዶክተሮችን በማገዝ ስራን እንደሚያቀላጥፍ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡


የጀነሬቲቭ ኤ.አይ ዉጤቶችን ለይቶ ማወቂያ ሥርዓት ሊተገበር ነው።

እጅግ በተራቀቀ ዘዴ የሚሰሩት የጀነሬቲቭ ኤ.አይ ዉጤቶችን በቀላሉ መለየት አዳጋች ሆኗል።በመሆኑም በርካቶች የማጭበርበር ሰለባ ሲሆኑ ይስተዋላል። ሲንት አይ.ዲ ዲቴክተር የመፍትሔው አካል ለመሆን መጥቷል።

ሥርዓቱ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆኑ ምስሎችንም ሆነ ጽሁፎች ለይቶ ማወቅ ያስችላል። በጀነሬቲቭ ኤ.አይ ቴክኖሎጂ የሚፈጠሩት ይዘቶች በሚሰሩበት ወቅት በግልጽ የማይታዩ መለያ ምልክቶች (watermark) ይካተቱባቸዋል። ሥርዓቱ እነዚህን ምልክቶች ከይዘቶቹ ላይ ፈልጎ በማግኘት ያሳዉቃል።

የጉግል ኩባንያ ዉጤት የሆነዉ ሥርዓቱ ከኤንቪዲያ እና መሰል የቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በመተባበር በስፋት አገልግሎት መስጠት ያስችላል ተብሏል።

ሥርዓቱ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ በስፋት ጥቅም ላይ በሚውልበት በዚህ ዘመን ግልጽ፣ ተዓማኒ እና አካታች የሆነ የቴክኖሎጂዉን ትግበራ ዕዉን ለማድረግ ያግዛል።


የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የቻት ጂፒ.ቲ ፕላስ አገልግሎቶችን ለዜጎቿ በነፃ አቀረበች፡፡

በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የሚኖሩ ሰዎች የቻት ጂፒ.ቲ ፕላስ አገልግሎቶችን በነጻ መጠቀም እንዲችሉ የሀገሪቱ መንግስት ከኦፕን ኤ.አይ ኩባንያ ጋር ስምምነት አድርጓል፡፡ ስምምነቱ በክፍያ ይቀርቡ የነበሩ የቻት ጂፒ.ቲ ፕላስ አገልግሎቶችን ለመላው ሕዝቧ በነፃ ያቀረበች የመጀመሪያዋ ሀገር ያደርጋታል።

እቅዱ በኦፕንኤ.አይ እና በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ መንግስት መካከል የተደረገ የቀጣይ አጋርነት አንድ አካል ነው። ስምምነቱ በአቡዳቢ ውስጥ ስታርጌት ኤምሬትስ የተባለ ግዙፍ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መረጃ ማዕከል መገንባትንም ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ለሁለቱም ወገኖች ትልቅ እርምጃ ሲሆን ኦፕንኤ.አይ እና አጋሮቹ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና ማሽን ለርኒንግ አገልግሎት የሚውሉ ባለከፍተኛ አቅም የኮምፒዩተር መሠረተ ልማቶችን በመገንባት ላይ ናቸው ሲል ኢንዲያንቱዴይ በድረገፁ አስነብቧል፡፡

አጋርነቱ ዓለማቀፍ ተነሳሽነት ከመፍጠር ባለፈ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የኦፕንኤ.አይ ምርት እና አገልግሎቶችን በመጠቀም በኃይል፣ በጤና አጠባበቅ፣ በትምህርት እና ትራንስፖርት ዘርፍ ፈጠራን እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማፋጠን እንደሚረዳ ኦፕንኤ.አይ በድረ-ገጹ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።


ኢትዮጵያ ዓለማቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ልታዘጋጅ ነው::

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በጋራ በመሆን Ethiopian Tech Expo (ETEX 2025) የተባለ ዓለማቀፍ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ሊያዘጋጁ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በሁሉም ዘርፎች ሰፊ ተግባራት ያሉት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ኤክስፖ ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ በተለያዩ የቴክኖሎጂ መስኮች ያስመዘገበችውን ስኬት ለማሳየት የሚያስችል መድረክ ነው ብለዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ የሁነቱን ዓላማ አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት በኢትዮጵያ የሚገኙ ስታርታፖች በዚህ ዓለማቀፍ መድረክ ላይ ስራዎቻቸውን እንዲያስተዋውቁ እድል ይሰጣቸዋል፡፡
በኤክስፖዉ ላይ ከ10ሺህ በላይ ታዳሚዎች የሚሳተፉ ሲሆን ጥናታዊ ጽሑፎች፣ የፖናል ውይይቶች እና የቴክኖሎጂ ውድድሮች ይኖራሉ።

በሳይበር ደህንነት፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ የፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ ስማርት ከተማ፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ትምህርት ላይ ትኩረቱን የሚያደርገው ኤክስፖው ከግንቦት 8 እስከ 10 ፣ 2017 ዓ.ም በአዲስ ዓለማቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ይካሄዳል፡፡
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


የኤአይ ክፍሎች (categories of AI)
===========@=============
1. Machine Learning (ML)
   - Supervised Learning
   - Unsupervised Learning
   - Reinforcement Learning
2. Natural Language Processing (NLP)
   - Text Analysis
   - Sentiment Analysis
   - Language Translation
3. Computer Vision
   - Image Recognition
   - Object Detection
   - Image Generation
4. Robotics
   - Autonomous Systems
   - Human-Robot Interaction
   - Robotic Process Automation (RPA)
5. Expert Systems
   - Decision Support Systems
   - Knowledge-Based Systems
6. Speech Recognition
   - Voice Assistants
   - Speech-to-Text
7. Generative Models
   - Generative Adversarial Networks (GANs)
   - Variational Autoencoders (VAEs)
8. Recommender Systems
   - Collaborative Filtering
   - Content-Based Filtering
9. Ethics and Fairness in AI
   - Bias Detection
   - Accountability in AI Systems
10. AI in Healthcare
    - Diagnostic Systems
    - Predictive Analytics


ሰው ሠራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) ምንድነው
ሰው ሠራሽ የማሰብ ችሎታ (AI) ከሰዎች ወይም ከእንስሳት ዕውቀት በተቃራኒ የማሽኖች ወይም የሶፍትዌሮች የማሰብ ችሎታ ነው። የማሰብ ችሎታ ያላቸውን ማሽኖች የሚያዳብርና የሚያጠና የኮምፒውተር ሳይንስ የጥናት መስክ ነው። እንደነዚህ ያሉት ማሽኖች ኤአይስ ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ።
ኤ አይ ቴክኖሎጂ በመላው ኢንዱስትሪ፣ መንግሥትና ሳይንስ በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል። አንዳንድ ከፍተኛ ግምት ያላቸው መተግበሪያዎች- የተራቀቁ የድረ-ገጽ ፍለጋ ሞተሮች (ለምሳሌ, Google Search), የድጋፍ ስርዓቶች (በ YouTube, Amazon, እና Netflix ጥቅም ላይ የዋሉ), የሰው ንግግር መረዳት (እንደ Google Assistant, Siri, እና Alexa), ራስን የሚያሽከረክሩ መኪኖች (ለምሳሌ, ዌይሞ), generative እና የፈጠራ መሳሪያዎች (ቻትጂፒቲ እና AI ጥበብ), እንዲሁም superhuman ጨዋታ እና ትንታኔ በ ስትራቴጂ ጨዋታዎች (እንደ ቼዝ እና ጎ) ናቸው. የተለያዩ ጥናቶች በሰው ሠራሽ የማሰብ ችሎታ ረገድ ከፍተኛ እድገት እንዲኖር ምክንያት ሆኗል።
የተለያዩ የ AI ምርምር ንዑስ መስኮች በተወሰኑ ግቦች እና በተወሰኑ መሳሪያዎች አጠቃቀም ላይ ያተኮሩ ናቸው።
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ቻይና ብላክ ፓንተር 2.0 የተባለ አዲስ ፈጣን ሯጭ ሮቦት ሰራች፡፡

በቻይና ዢጂያንግ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝ የጥናት ቡድን በሴኮንድ 10 ሜትር መሮጥ የሚችል ሮቦት መስራቱን ገልጿል። ይህም የዓለማችን ፈጣን ባለ አራት እግር ሮቦት ያደርገዋል። ሮቦቱ ብላክ ፓንተር 2.0 የሚል መጠሪያ ተሰጥቶታል፡፡

ብላክ ፓንተር 2.0 38 ኪሎግራም የሚመዝን ሲሆን 0.63 ሴንቲ ሜትር ቁመት አለው። በ2018 (እ.ኤ.አ) የተጀመረው ሮቦቱን የማበልፀግ ስራ ፍጥነቱን በሰከንድ ከ6 ሜትር እንዲበልጥ ለማድረግ የተለያዩ ማሻሻያዎች ሲደረግ ቆይቷል።

በውሻ አምሳያ የተሰራዉ ሮቦቱ ለወታደራዊ ተልዕኮዎች፣ ለነፍስ አድን ስራ እና ለአሰሳ እንደሚያገለግል ተጠቁሟል፡፡

በ100 ሜትር ሩጫ ላይ የሚሳተፉ አትሌቶች ዉድድሩን ለማጠናቀቅ በሰኮንድ 10 ሜትር ይሮጣሉ፡፡ ተመራማሪዎቹ በቀጣይ የሮቦቱን ፍጥነት በሴኮንድ 15 ለማድረስ እየሰሩ መሆኑንን ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል፡፡

════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን : Gettechinfofb
የቴሌግራም አድራሻችንን: https://t.me/Gettechinfonow


ለ1 ሳምንት ወደ ጠፈር የተላኩት ተመራማሪዎች፣ 9 ወር ቆይተው ተመለሱ
**

የናሳ የጠፈር ተመራማሪ የሆኑት ቡች ዊልሞር እና ሱኒ ዊሊያምስ ከ286 ቀናት የጠፈር ላይ ቆይታ በኋላ ወደ ምድር መመለሳቸው ተገልጿል።

ሁለቱ ተመራማሪዎች እ.ኤ.አ ሰኔ 2024 ወደ ጠፈር ማቅናታቸው የሚታወስ ነው።

ታሪካዊ የጠፈር ጉዞ በማለት የተሰየመው ተልዕኳቸው መቋጫውን በሜክሲኮ ባሕረ ሰላጤ ላይ አድርጓል።

ተመራማሪዎቹ የቦይንግ ስታር ላይነር የጠፈር መንኮራኩር ጥቅም ላይ ከመዋሉ በፊት ለሚደረግ ሙከራ ለአንድ ሳምንት ወደ ጠፈር ማቅናታቸው የሚታወስ ነው።

ሆኖም ግን በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ከታቀደው ቀን በላይ ሊቆዩ ችለዋል።

በዚህም ምድርን ከ4 ሺህ 500 ጊዜ በላይ የዞሩ ሲሆን፤ ይህ በድምሩ 195 ሚሊዮን ኪሎ ሜትር ይደርሳል።

ሱኒ ዊሊያምስ 62 ሰዓታትን ከጠፈር መንኮራኩር ውጪ በሚከወን ተልዕኮ ላይ ያሳለፈች ሴት በመሆን ክብረወሰን አስመዝግባለች።

ተመራማሪዎቹ ከአስፈላጊ የጤና ምርመራ እና የእረፍት ጊዜ በኋላ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ስኬት ያገኟቸውን ጠቃሚ ልምዶች እና የገጠሟቸውን እክሎች እንደሚያጋሩ ይጠበቃል።


የሮቦቶች ማራቶን ውድድር ሊዘጋጅ ነው
+++++++++++++++++++++++++
ቻይና የመጀመሪያውን አለም አቀፍ የሮቦቶች ማራቶን ውድድር አዘጋጀች፡፡ ይህ ውድድር የፊታችን ኤፕሪል 13 በቤጂንግ የሚከናወን ሲሆን በውድድሩ ላይ በሰው ቅርፅ የተሰሩ ሮቦቶች እንደሚወዳደሩ ተገልጿል፡፡
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ኢትዮ-ቴሌኮም ለፋይናንስ ተቋማት አዲስ በክላውድ ላይ የተመሰረተ ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን ይፋ አደረገ!

ኩባንያው የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን እና የቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራትን በዘመናዊ የዲጂታል ፋይናንሺያል መሳሪያዎች ለማስታጠቅ የሚያስችል የኮር ባንኪንግ ሶሉሽን ተግባራዊ አድርጓል፡፡

ሶሉሽኑ የፋይናንስ ተቋማት አሰራራቸውን በማቀላጠፍ፣ የደንበኛ ተሞክሮን በማሻሻል እና አገልግሎታቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ ክላውድ አማካኝነት ለብዙኃን ተደራሽ በማድረግ፣ የመሠረተ ልማት ወጪዎችን እንዲቀንሱ ያስችላቸዋል።

ኩባንያው አስተማማኝ የኮር ባንኪንግ ሶሉሽን በማቅረብ የፋይናንስ ተቋማት ደንበኞቻቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲያገለግሉ እና በሀገራችን የፋይናንስ አካታችነት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል ።
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ቲክቶክ ወደ ቁም ነገር እየተቀየረ ነው
ቲክቶክ (Tiktok) በአዲሱ  (updated) በሆነው አፕልኬሽኑ (Application)  ላይ አዲስ ፊውቸር (future) ጨምሮአል።
ይህም STEM የሚባል ሲሆን ፖለቲካ ኢንተርቴይመንት እና መሰል ጉዳዮችን የሚያስቀር እና ሳይንስን እና ቴክኖሌጂ እንዲሁም ትምህርታዊ ጉዳዮችን ብቻ የሚያስመለክትነው። በተለይ በነዚህ ዘርፍ መረጃ ለሚፈልጉ ምቹ አማራጭ ነው። ቲክቶካችሁን update  በማድረግ ይጠቀሙት።
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ከ50 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍነው የባሕር ውስጥ ኬብል ዝርጋታ በሜታ ኩባንያ ሊከናወን ነው

በሜታ “ፕሮጀክት ዋተርዎርዝ” የሚል ስያሜ የሰጠውን በዓለም ረጅሙ የባህር ውስጥ ኬብል ዝርጋታ ለማከናወን ማቀዱን አስታውቋል።

የኬብል ዝርጋታው 24 ፋይበር-ጥንድ ሲስተም የሚጠቀም ሲሆን÷ ይህም ከፍተኛ አቅም እንደሚሰጠው ተገልጿል።

ይህም አገራትን ከማገናኘት በተጨማሪ ከፍተኛ አቅም ያለው ቴክኖሎጂ በመጠቀም በዓለም ላይ ረጅሙ የባህር ውስጥ የኬብል ፕሮጀክት ያደርገዋልም ነው የተባለው።

ፕሮጀክቱ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሌሎች ሀገራትን ከማገናኘቱ በተጨማሪ በመካከላቸው ጥሩ ግንኙነት እንዲኖር በማድረግ የበለጠ ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማጠናከር ይረዳል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ተፈታኞች ውጤታችሁን ለማየት
https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።


የፋይዳ መተግበሪያ ይፋ ሆነ

ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የፋይዳ አገልግሎቶችን አጠቃሎ የያዘ የፋይዳ መተግበሪያ ዛሬ ይፋ አድርጓል።

መተግበሪያው በተቋሙ ባለሙያዎች እንዲለማ መደረጉ የተገለጸ ሲሆን÷ በአንድሮይድ እና በኣይ ኦ ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች በዛሬው እለት ለዜጎች ይፋ ተደርጓል።

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የስትራቴጂክ ኮሙኒኬሽን አማካሪ አቤኔዘር ፈለቀ በዚህ ወቅት፥ ይፋ የተደረገው መተግበሪያ የተለያዩ ሙከራዎች እና የደህንነት ማረጋገጫ የተደረገበት መሆኑን ተናግረዋል።

የሞባይል መተግበሪያው ህብረተሰቡ የሚያገኛቸውን የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በተደገፈና ቀልጣፋ በሆነ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችል ነው ብለዋል።

መተግበሪያው ዜጎች የጠፋባቸውን ወይም ያልደረሳቸውን የፋይዳ ቁጥር ዳግም ለማግኘት፣የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን በካርድ መልክ አሳትሞ ለመያዝና የካርድ ህትመት ለመጠየቅ የሚያስችል ነው መባሉን የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

በተጨማሪም የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን ለማግኘት በሚመለከተው አካል ሲመዘገቡ የተሳሳተባቸው መረጃ ካለ በስልካቸው ላይ መረጃውን ማስተካከል የሚችሉበትን ሁኔታ የሚፈጥር መሆኑም ተጠቁሟል።

ምንጭ
ኤፍ ኤም ሲ


የመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያው ሰው አልባ አውሮፕላኖች አቅርቦት ስርዓት ተጀመር (Drone Delivery System)
------------------------------------------------------------------------
ታህሳስ 10፣ 2017፣ ዱባይ የመካከለኛው ምስራቅ የመጀመሪያውን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን የቤት ለቤት አገልግሎት ስርዓት በይፋ ጀምሯል፣ ይህም በሀገሪቱ የቴክኖሎጂ እድገቶች ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። ይህ ተነሳሽነት በዱባይ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን (DCAA) የሚመራ ሲሆን የመጀመሪያውን የስራ ፍቃድ ለቻይና የቴክኖሎጂ ግዙፉ Meituan ቅርንጫፍ የሆነው ኬታ ድሮን ሰጠ። የስርአቱ የሙከራ ምዕራፍ በዱባይ ሲሊኮን ኦሳይስ (ዲኤስኦ) የጀመረው ስድስት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም አራት የመላኪያ መንገዶችን ለመፍጠር ነበር። የሚቀርቡት ቁልፍ ቦታዎች የሮቸስተር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (RIT-Dubai) እና ዱባይ ዲጂታል ፓርክን ያካትታሉ፣ ምግብ፣ መድሃኒት እና አስፈላጊ ነገሮች በፍጥነት ማድረስ ላይ ያተኮሩ።
የዱባይ አልጋ ወራሽ ሼክ ሃምዳን ቢን መሐመድ ቢን ራሺድ አል ማክቱም የመክፈቻ ሥርዓቱን የመንግስት የቴክኖሎጂ እድገትን ለመምራት ያለውን ቁርጠኝነት በማሳየት የዚህ ጅምር አስፈላጊነት ጎልቶ ታይቷል። ይህ ተነሳሽነት ምሳሌን ብቻ ሳይሆን ከተማዋን ከሦስቱ ዋና ዋና የከተማ ኢኮኖሚዎች ተርታ ለማሰለፍ ካለው ከዱባይ የኢኮኖሚ አጀንዳ ጋር ይጣጣማል ብለዋል። ════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow


ለገና በቴሌ ብር እስከ 15 ሚሊዮን ያሸንፉ
ቴሌ ለገና እስከ 15 ሚሊዮን ብር የሚያሸንፉበትን ጨዋታ አዘጋጅቷል።ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም አፑን አውርደው ይጫወቱ
I am inviting you to download telebirr SuperApp, register and make a transaction to get reward. https://superapp.ethiomobilemoney.et:38443/customer/mgm/index1230.html#/?notoolbar=true&CampaignId=MGM1722184804351104&inviterId=980093187200004&language=en&campaignType=christmas&time=Jan-01-2025-Jan-07-2025




ኢትዮ ቴሌኮም የ4ጂ ሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎትን በ67 ከተሞች አስጀመረ
**

ኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ፍጥነት እና አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት ማቅረብ የሚያስችለውን ዘመናዊ የ4ጂ LTE የሞባይል አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 67 ከተሞች አስጀምሯል፡፡

የ4ጂ LTE ኔትዎርክ ማስፋፊያው በከተሞቹ በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ ላይ የሚገኘውን የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተቋሙ በቀጣይም የቴሌኮም ኔትዎርክ እና የዲጂታል መሰረተ ልማቶችን የማስፋፋት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከኢትዮ ቴሌኮም የማኀበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡


#NGAT
ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) አመልካቾች ምዝገባ ከታህሳስ 21 እስከ 25/2017 ዓ.ም ይከናወናል፡፡
ለመመዝገብ 👇
HTTPS://NGAT.ETHERNET.EDU.ET
ከምዝገባ ጋር ለተያያዘ ማንኛውም ጥያቄ በሥራ ሰዓት በኢሜል አድራሻ [email protected] ወይም በስልክ ቁጥር 0920157474 (Enatnesh Gebeyehu) እና 0911335683 (Fasil Tsegaye) ማብራሪያ መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን ተገልጿል።
የመፈተኛ USER NAME እና PASSWORD በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ሲሆን፤ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 750 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈጸም ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡

ፈተናው የሚሰጥበትን ጊዜ በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
════❁✿❁ ═══════
ለበለጠ መረጃ
ከዚህ ታች ባለው አድራሻ በፌስቡክና በቴሌግራም ይከተሉን
ፌስቡክ አድራሻችንን
Gettechinfofb (
https://www.facebook.com/profile.php?id=100022088745521)
የቴሌግራም አድራሻችንን
https://t.me/Gettechinfonow

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »