ጥገኝነት የመጠየቅ መብት ስንል ምን ማለታችን ነው?
✅ ጥገኝነት የመጠየቅ መብት ማለት ከግጭት ወይም አደጋ የሚያመልጡ ሰዎች በሌላ ሀገር ከለላ የሚያገኙበት ሥነ ሥርዓት ነው። ሰዎች ለጥገኝነት ሲያመለክቱ በዘራቸው፣ በሃይማኖታቸው፣ በብሔራቸው፣ በፖለቲካ አስተሳሰባቸው ወይም በአንድ የተወሰነ ማኅበራዊ ቡድን ውስጥ አባል በመሆናቸው ምክንያት የሚፈጸም ጥቃት ስለሚያስፈራቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው ነው። ከለላ ለማግኘትም ወደ ሀገራቸው ቢመለሱ በእርግጥ ወይም በተጨባጭ ሊደርስባቸው የሚችል ማሳደድ፣ ማሠቃየት፣ መንገላታት ስለመኖሩ ማሳየት አለባቸው።
ጥገኝነት የመጠየቅ መብት የሕግ መሠረቶች ምንድን ናቸው?
✅ ዓለም አቀፍ እና ብሔራዊ የሕግ ማዕቀፎች ተጨባጭ ከሆነ ጥቃት/ጭቆና ጥበቃ ለማግኘት ጥገኝነት የመጠየቅ መብትን እና ሂደቶችን ይደነግጋሉ። ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ (Universal Declaration of Human Rights) አንቀጽ 14 ከጥቃት/ጭቆና ሸሽቶ በሌሎች ሀገሮች ጥገኝነት የመጠየቅ መብትን እውቅና ሰጥቷል። ማን እንደ ስደተኛ እንደሚቆጠር እና ሀገራት ለጥገኝነት ጠያቂዎች ከለላ ለመስጠት ያለባቸውን ግዴታዎች ከመዘርዘር አኳያ እ.ኤ.አ. በ1951 የወጣው የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ስምምነት እና እ.ኤ.አ. በ1967 የስደተኞች ሁኔታን ለመደንገግ የወጣው ፕሮቶኮል ጥገኝነትን ለተመለከቱ ሕጎች መሠረት በመሆን ያገለግላሉ።
#Ethiopia🇪🇹 #HumanRightsForAll
በነጻ የስልክ መስመራቸው 7307 ላይ በመደወል የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አቤቱታ ማቅረብ ወይም ጥቆማ መስጠት ይችላሉ።
✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅
@LawStudentsUnion @LawStudentsUnion