Postlar filtri


በቀይ አበቦች መስክ ላይ መመላለስ እንዴት መንፈስን ያድሳል? እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ልጆች የእናታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ጉልበት ስመው ሲሞሸሩ ማየት እንዴት ደስ ያሰኛል? ሰማንያ ስምንት ወጣቶች በሥጋ ወደሙ ከብረው በመላእክት ታጅበው በዝማሬ ባሕር ሲዋኙ ማየት እንደምን ያለ ደስታ ነው? ከእነዚህ አርባ አራት ሙሽሮች የሚወለደውን አዲስ ክርስቲያን ትውልድ ማየትስ እንዴት ያጓጓል? ልጆቻችን በእናንተ መታዘዝ ኮርተናል:: ሰይጣን የሚዋጋውን የቤተሰብ ቤተ መቅደስ ስትገነቡ የዓይን ምስክሮች ስለሆንን ደስ ይለናል:: እልፍ ሁኑ! እናንተን ለመዳር ወገባቸውን የታጠቁ እጅግ የሚወዷችሁ የቤተክርስቲያን ልጆች የኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ወጣቶች ሁሉ የእናንተን ደስታ አይተው ነፍስ አልቀረላቸውም! ትዳራችሁን እንደ ሰርጋችሁ ያማረ ያድርግልን!
#share
@diyakonhenokhaile


+ ሁለት ነበርን +

ገነት ውስጥ ሆነን ስናምፅ ባንተ ላይ
ያንተን መንግሥት ሽተን ዙፋንህን ስናይ
ዕፀ በለስ በልተን ካንተ ስንጣላ
ሁለት ነበርን እንጂ አልነበረም ሌላ

ሁለት የአፈር ሥራ ሁለት ወንጀለኛ
ዘር ልተካ ሳይል ሳይበዛ አመፀኛ
እዚያው ብትመልሰው ከመጣበት አፈር
ማን ይጠይቅሃል ከፍቅርህ በስተቀር?

ሁለት ጆንያ አፈር መልሰህ ከመሬት
ሌላ ሰው ብትሠራ ሌላ አዲስ ፍጥረት
የማያምፅ አዳም ታዛዥዋን ሔዋኒት
ደግመህ ብትፈጥር ላንተ ምን አለበት?

ሸክላህን አክብረህ ሲሰበር ያልጣልከው ሲያምጽብህ አይተህ በአየር ያልበተንከው
ከቶ ለምን ይሆን ዘሩን ያበዛኸው
እስኪገርፍህ ድረስ ጉልበት የሰጠኸው

ጠላትክን መግበህ እንዲህ የወዷድከው
ምድርን ሙላ ብለህ በሁሉ ያነገስከው
ምራቁን የተፋው በአንተ ላይ ጨክኖ
ማጥፋት ስትችል ነው ገና ሁለት ሆኖ

ማን ነበር ከልካይህ ፈጥረህ እንዳታጠፋ ምሕረትህ ነው እንጂ በዓለም የሰፋ
ቸርነትህ እንጂ ምድሪቱን የሞላ
አንተን የሚያስቆም ከቶ የለም ሌላ

“ሔት፡፡ ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና" ሰቆ ኤር. 3:22

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ግንቦት 23 2017 ዓ.ም.
#share
@diyakonhenokhaile




ግብፃውያን ጳጳሳት በኢትዮጵያ | Coptic Metropolitans in Ethiopia | Ethiopian Church History 2

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለ1600 ዓመታት በእስክንድርያ መንበር ጥላ ሥር ትተዳደር ነበር:: በእነዚያ ዓመታት የመጡት ግብፃውያን ጳጳሳት ቆይታ ምን ይመስል እንደነበር በዚህ ትምህርት በሰፊው ተዳስሶአል::

https://youtu.be/MZml82waOp4?si=vKkQZt006yBBqZcd

#share
@diyakonhenokhaile




"ሱሪዬን የበቃው ሰው ይለብሰዋል ብለህ አትጨነቅ" የሚል ብሂል አለ:: አንዳንዴ ከሁኔታዎች በላይ የእኛ ሕሊና የሚፈጥረው ምስል የከፋ ነው:: ከምጡ በላይ ምጡን እያሰብን የምናምጠው ምጥ ይበረታል:: የማታውን ጨለማ በመፍራት ብሩህ ቀናችንን እናጨልማለን::

"ጌታ ቅርብ ነው:: በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ" ፊልጵ. 4:6
Photography #mykeysjourney

#share
@diyakonhenokhaile

16k 0 103 562

ክርስትና እንዴት ወደ ኢትዮጵያ ገባ?

https://youtu.be/AFfsodZy4cQ?si=kmhlGkfFHNQj_OTP

#share
@diyakonhenokhaile


ይህንን ታሪክ የጻፍኩት 2012 ላይ ነበር:: ይህንን ታሪክ አንብበው በግንቦት ልደታ ዕለት ተስለው የወለዱ እናቶች በየዓመቱ ይጽፉልኛል:: አንዳንዶቹም ሳገኛቸው ይነግሩኛል:: ዓለምን በእጁ የያዘውን ጌታ በእቅፍዋ የያዘች እመብርሃን የወላጆችዋን የመካንነት ሕመም ለሚታመሙ ሁሉ በአማላጅነትዋ “ልጅ እኮ የላቸውም” ብላ ለምና ብዙ ውኃ ቤቶችን በልጅ ወይን ሞልታለች:: “ይሁንልኝ” ብላ አምላክን በእርስዋ እንዲያድርግ ነፃ ፈቃድዋን ለሰጠች ድንግል “ይሁንላቸው” ብላ በጸሎትዋ በመካኖች ማሕፀን ልጅ ማሳደር ከተሞላችው ጸጋ አንጻር ጥቂት ነገር ነው::

ይህንን የግንቦት ልደታ ተአምር በእኔ ብዕር ሲመሰከር ቆይቶ እንዳልነበር ጊዜው ደርሶ ባለ ታሪክዋ ነፃነት የእናቲቱን ምልጃ የልጅዋን ቸርነት በራስዋ አንደበት እንዲህ መስክራለች::

ፍቅርን እንደ ሸማ የለበሱት የቩርዝቡርግ ምእመናን አሁን የቅዱስ ማርቆስን ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ለመግዛት ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም እየታገሉ ነው:: መላው ዓለም ተረባርቦ ካገዛቸው በቅርቡ እውን ያደርጉታል:: በቩርዝቡርግ ግን ግንቦት ልደታ ከዝክር አልፎ ንግሥ እንደሚሆንና የልደታ ለማርያም ክብረ በዓል እንደሚከበርና መላው አውሮፓ ለግንቦት ልደታ ወደ ቩርዝቡርግ እንደሚጎርፍ ተስፋ አደርጋለሁ::

Meine lieben Brüder und Schwestern in Würzburg, ich wünsche Ihnen ein gesegnetes Fest der Geburt Mariens. Ich hoffe, Sie bald wiederzusehen. Möge Gott Ihnen helfen, das Kirchenbauprojekt abzuschließen.
https://youtu.be/HkXps7PbIKM?si=MS1y88vOuyNxhdlL
ሙሉ ቃለ መጠይቁን እንድትሰሙት እጋብዛለሁ::










Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
"ሬሳ የሌለው መቃብር"

አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና

#share
@diyakonhenokhaile


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
መጨረሻው መጀመሪያህ ነው

#share
@diyakonhenokhaile


ኢትዮጵያዊ ነገረ ሥዕል (Ethiopian Iconography) - Iconography part 2

https://youtu.be/6ldC6wMnr6c?si=2W5x48F7FxY6X4wc

#share
@diyakonhenokhaile


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የሦስት ዛፎች ወግ

#share
@diyakonhenokhaile




"ሰዎች ማን እንደሆኑ ሲያሳዩህ በመጀመሪያው ቀን እመናቸው" ትላለች ማያ አንጀሎ


ይህንን ጽሑፍ ከትናንት በስቲያ ጽፌው ስሜታዊ ሆኜ እንዳይሆን በሚል ትንሽ ቆይቼ ልመልከተው ብዬ አሳደርኩት:: በቆይታ ሃሳቤ ሊቀየር ስላልቻለ እንደወረደ ለጥፌዋለሁ:: የምናገረው ነገርም እሳቸው ስለ ድንግል ማርያም ከተናገሩት አይከፋም:: ነገረ ሃይማኖታዊ መልስ ከበቂ በአደባባይ ተሰጥቶበታል:: ጉዳዩ ላይ ግን የምለውን ልበል::
@diyakonhenokhaile
ፍኖተ ድድቅ የሚባል እባጭ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከወጣ ጀምሮ አንዴ ዘፈን በሚመስል መዝሙሩ ፣ አንዴ ምንፍቅናን በሚያገሣ ስብከቱ ምእመናንን ሲያወዛግብ ሰንበትበት ብሎ ነበር:: ጌታ በወንጌል "ኀበ ሀሎ ገደላ ህየ ይትጋብዑ አንሥርት" "በድን ባለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ" እንዳለው የፍኖተ ድድቅ ባለቤት ሙዳ ሥጋ ይጥላል ብለው ተስፋ ያደረጉ ሰዎች ዙሪያውን ስለከበቡት ላለፉት ጥቂት ዓመታት ቤተ ክርስቲያን ከነንፍጡ ካልወደደችው ብለው ሲሟገቱ ከርመዋል:: በመሠረቱ ሁኔታው ሰውዬው ደኃ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ተወግዞ ነበር እንድል ያደርገኛል:: ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ማኅበር ለማጥራት ጊዜው አሁን ነው::
"ከእኛ ወገን ነህ ወይንስ…?" የሚል ኢያሱያዊ ጥያቄ ለመጠየቅ ጊዜው አሁን ነው::

ሰሞኑን ደግሞ በፖለቲካ ቤዛነት የተሾሙ የሆኑ አንድ ጳጳስ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ብለው በፍኖተ ድድቅ አዳራሽ ሲያስጨበጭቡ ሰማን:: ከንዑሰ ክርስቲያን ያነሰ እውቀት ያላቸው እኚህ ጳጳስ ሽልማት እንደሚጠባበቅ አዝማሪ ሰውዬውን ያስደስታል ብለው ያሰቡትን ሁሉ ሲዘባርቁ ነበር::

ከቅርብ ዘመናት ወዲህ እንደ ፓስተር ለማውራት የሚጋጋጡ አባቶች ማየት ከጀመርን ሰነበትን:: አይናቸውን አስሬ የሚጨፍኑ ፣ በግድ እየጨመቁ ዕንባ ለማውጣት የሚታገሉ ፣ ከአሁን አሁን በልሳን ለፈለፉ ብለን በስጋት የምናያቸው ምሁር ለመባል የቤተ ክርስቲያንን ነባር እሴቶች የሚያጣጥሉ የቤተ ክርስቲያን ማድያቶች ብቅ ብቅ ካሉ ሰነበቱ::

ያሁኑ ጳጳስ ትንሽ የሚለዩት ምንም ፈሊጥ የሌለው ያልተለሳለሰ $@&@@  ስለሚናገሩ ብቻ ነው:: የሆነ ቪድዮ ላይ Faith Alone የሚለውን የሉተር ትምህርት የኦርቶዶክስ ቆብ ደፍተው ሲሰብኩ ትንሽ እንኩዋን አላፈሩም:: በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተሹመው ተሸልመው ክህደት እያስተማሩ መቀጠል እንደማይቻል ለማሳየትና አንዴ ከጰጰሱ ምንም አይኮንም ዓይነት አመለካከትን ለማረም ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዕድል ሊጠቀም ይገባዋል:: በ3ኛው ክፍለ ዘመን ጳውሎስ ሳምሰጢ (Paul of Samosata) በአንጾኪያ ሲኖዶስ የተወገዘው ፣ ንስጥሮስ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተወገዘው ጳጳስ ከሆኑ በኋላ ነው:: ቤተ ክርስቲያን መና () —ንን ለመለየት ጵጵስናቸውን ፈርታ አታውቅም::
@diyakonhenokhaile
በወላዲተ አምላክ የነገረ ድኅነት ሱታፌ ላይ በጳጳስ ደረጃ ሲቀለድ አይተን ዝም ልንል አንችልም:: ከቅዱስ ሲኖዶስ ጠንከር ያለ ውሳኔ እንጂ ማስተባበያ አንጠብቅም:: የተነቃነቀ ጥርስ ቀን ይጠብቃል እንጂ መውለቁ አይቀርም:: እንደ ተራ ስኅተት ይቅርታ እንዲጠይቁም አንጠብቅም:: ያስተማሩት የታሰበበት ክህደት ነውና የተብራራ መልስ ከቀኖና ጋር እንጠብቃለን:: "የበራላቸው" ለመባል የብርሃን እናትን ሊጋርዱ የሚጥሩ ሰዎች ማላገጫ ሆነንም አንቀርም::

ሙሴ ቤዛ በተባለበት መጽሐፍ ቅዱስ እያመኑ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ላሉት ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤዛ ሲሆናቸው ማየት አንፈልግም:: ጠንከር ያለ ቀኖናዊ እርምጃ እንጠብቃለን::

ርጉመ ይኩን ዘይረግመኪ
ወቡሩከ ይኩን ዘይባርከኪ
ነገራተ ክልዔ ኢይርሳዕ ልብኪ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ገሊላ ፳ኤል
ሚያዝያ 15 2017 ዓ.ም.

#share
@diyakonhenokhaile




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ከጌታ መቃብር በቀጥታ

#share
@diyakonhenokhaile

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »