አንዳንዴ የምንኖርበት ምክንያቱ ሁሉ ይጠፋናል። ጨለማው ሲጫነን ፈተናው ሲበዛብን "ለምን ይሆን የምኖረው" እንላለን አደል ? አምላካችን ጋር እንጣላለን ። ለበጎ መሆኑን ፈፅሞ እንረሳዋለን።
ሳይደግስ አይጣላም ማለት ይሳነናል ። ማማረሩ መጮሁን ማልቀሡን እንመርጣለን ። ግን በእነዚህ ነገሮች ፈተና እና ችግርን ያለፈ ማንም የለም።ማንም‼
ዛሬ ያለነው በምክንያት ነው። በፈጣሪ ደግ ፈቃድ ፈተናው ችግሩም የመጣው ፈጣሪ ስለወደደ እና ደና ደረጃ የምንደርስበት ደረጃ ወይም መሠላል ስለሆነ እና ድጋሚ እንዳንወድቅ ነው እንጂ ፈተና እና ችግሩ የበዛው ። እሱ ልጆቹ ሲቸገሩ እና ሲፈተኑ ማየት አስደስቶት አደለም እንዲያውም ከእኛ በላይ እሡ ነው የሚያዝነው ።
ስለዚህ ማማረር መፍትሄ ሆኖ አያቅም ።
ለማማረር የሚከፈቱትን ልሳኖች ለምስጋና እንጠቀማቸው ። ስንነሳ ምስጋናን እንልመድ ። ከተኙበት ያልተነሡ ብዙ አሉ እና።
መልካም ቀን ተመኘሁ 🙏🏽🙏🏽