ታሪካችን ባያሌው የጦርነት ነው ፤ በጦርነት ያሸነፈው የተሸናፊውን ንብረት እና ሚስት ይማርካል፤ ዳግማይ ቴዎድሮስ በሀያልነታቸው አነጋግ ላይ የሸዋን ግዛት በጦር አስገበሩ፤ ያጤ ምኒክን አባት የሸዋው ንጉስ ሀይለመለኮት የድል አድራጊውን ፊት ከማየታቸው በፊት ታመው አረፉ: :
ቴዎድሮስ በተሸናፊው ቤት ሰተት ብለው ገቡ፤ ሀይለመለኮት ሁለት ሚስቶች ጥለው ሄደዋል ፤ የመጀመርያዋ የምኒልክ እናት ወይዘሮ እጅጋየሁ ሲሆኑ ሁለተኛይቱ ወይዘሮ ትደነቂያለሽ የተባሉት ወይዘሮ ናቸው ፤ ትደነቂያለሽ እጅግ ውብ ነበሩ ይባላል፤ ቴዎድሮስ ባልየውን ሊማርኩ መጥተው በሚስቲቱ ተማረኩ፤ ግን ፍቅር አለዝቧቸው፥ አሽከራቸውን “ ያዝና ጫናት “ ለማለት ሳይደፍሩ ቀሩ፤
“ እቴጌ! በጌምድር አብረን እንሂድ”
ብለው ጋበዟቸው፤
ሴት ያልፈለገችውን ሀይለኛ ወንድ የምታመልጥበት መሳርያ አላት፤ ያ መሳርያ መላ ወይም በሾፐንሀወር አገላለጽ “ ማታለል “ሊሆን ይችላል፤ ወይዘሮ ትደነቂያለሽ የአሸናፊውን ንጉስ ልብ በሚያቀልጥ ፈገግታ የታጀበ መልስ ሰጡ፤“ደስ ይለኛል ፤ ግን ከዛ በፊት ኢየሩሳሌምን ተሳልሜ ለመመለስ አስቢያለሁ፤ ይፍቀዱልኝ “
ንጉሱ ስንቅ ሰጥተው፥ አጃቢ ጨምረው ወደ እየሩሳሌም ሸኗቸው፤
ውቢተን ሸኝተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የሀይለመለኮት እናት ወይዘሮ በዛብሽ ፤ “ሸዋ እንዲገብር እርዳታ አድርጊያለሁና ሹመት ይስጡኝ “ ብለው ጠየቁ፤
በዚህ ጊዜ ነበር አሸናፊው ንጉስ ከወደ ኢየሩሳሌም መርዶ የሚያክል ዜና የመጣላቸው፤ "ወይዘሮ ትደነቂያለሽ “ከሀይለመለኮት ወድያ አለም አልሻም ብለው መንነዋል “
ይህንን ሲሰሙ ቴዎድሮስ ይቺን ግጥም ወደ ታሪክ ወረወሩ፤
“አወይ ጉድ
ሚስቱ መናኝ
እናቱ ሹመት ለማኝ “
ታሪክ መዝጋቢው ዘንግቶት ይሆናል እንጂ ግጥሙ “ እኔን ብሎ ሰው አማኝ “ ብሎ የሚደመደም ይመስለኛል።