🎯 Date Rape Drugs" ስለሚባሉ ለወሲብ ጥቃት ስለሚውሉ መድኃኒቶች ታውቃላቹ? በብዛት GHB እና Rohypnol ናቸው የሚታወቁት ወይም ጥቅም ላይ እየዋሉት ያሉት፤ ሆኖም ብዙ መድኃኒቶች አሉ።
💊 "እነዚህ መድኃኒቶች ለሕክምና ነው የሚውሉት፤ ሆኖም በብላክ ማርኬት እየተሸጡ ለሌሎች አገልግሎቶች ለወንጀል ይውላሉ። አንዱና ትልቁ በጣም አሳሳቢና አስጊ የሆነው ለወሲብ ጥቃት መዋላቸው ነው።
🦠 እንደመድኃኒቱ አይነት የሚወስደው ሰው ላይም የሚያደርሰው ጉዳት ይለያያል። አንዳንዱ zombie ያደርጋል - እራሳችሁን አትስቱም አቅላችሁን እንጂ፤ ትንቀሳቀሳላችሁ እንደማንኛውም ጤነኛ ሰው ግን ምን እያደረጋችሁ እንደሆነ አታውቁም መድኃኒቱ ከሰውነታችሁ እስኪወጣ።
💉 ሌላው በተመሳሳይ መንገድ አቅላችሁን ያስታል - ከፍተኛ ጤናማ ያልሆነ የወሲብ ፍላጎት ያሳድርባችኋል፤ ብቻ በየትኛውም መድኃኒት ለወሲብ ጥቃት ትጋለጡበታላቹ።
"እራሳችሁን የምታውቁት መድኃኒቱ ከሰውነታችሁ ሲወጣ ነው፤ ችግሩ ምንም አታስታውሱም መድኃኒቱን ከወሰዳችሁበት ሰዓት ጀምሮ የተፈጠረውን።
መድኃኒቱ ታብሌት ፈሳሽም ሊሆን ይችላል፤ በምትበሉት በምትጠጡት ነገሮች ውስጥ ሊሰጣችሁ ይችላል።
🧬 ለህዝቦቻቸው የሚጨነቁ ሀገራት የጤና ባለሙያዎችና ፖሊስ ዲፓርትመንቶች ህዝቦቻቸው በተለይ ወጣቶች በሚዝናኑበት ወቅት የሚጠቀሟቸው ነገሮች ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እየመከሩ ነው፤ ምክንያቱም በከፍተኛ ደረጃ በዚህ መንገድ ጥቃት የሚፈፀምባቸው የተለያየ ወንጀሎች በመበራከታቸው ነው። የወሲብ ጥቃት ብቻ ሳይሆን ዝርፍያ የመግደልም ወንጀል ይሆናል።
🩸 አንዳንድ መድኃኒቶች በምርመራም መወሰዳቸው ላይታወቅ በደም ላይገኙ ይችላሉ ከረጅም ሰዓታት በኋላ። እድሜ ለቴክኖሎጂ በዚህ መንገድ የወሲብ ጥቃት የተፈፀመባቸው ሰዎች መድኃኒቱ በደማቸው ባይገኝም ማስታወስ ባይችሉም እንኳን በሕክምና አንዲት ሴት ፈልጋ ነው ሳትፈልግ ወሲብ የተፈፀመው የሚለውን ማረጋገጥ ይችላል።
⚰ በጣም አስፈሪው ደግሞ አንድ ይህን መድኃኒት የተሰጠው ሰው እንደጤነኛ ሰው ስለሚንቀሳቀስ የታዘዘውን ስለሚያደርግ ይህን የተመለከተ ሌላ ሰው መድኃኒቱን መውሰዳቸውን ስለማያስተውል ፈልገው ጥቃት ከፈፀመባቸው ሰው ጋር ቤርጎ ሲይዙ እቤቱ መኪናው ላይ ሲገቡ የተለያየ ነገር በፍቃደኝነት ሲያደርጉ ስለሚታዩ ሰዎች ላያምኗቸው ይችላሉ "ተገደን ነው" ሲሉ መድኃኒቱ ከደማቸው ከወጣ ከነቁ በኋላ ፈልገው ያደረጉትን ለተለያየ ጥቅም እየዋሹ ሊመስል ይችላል።
እንዳልኳችሁ ለወሲብ ጥቃት በብዛት ቢውል እንጂ ለተለያየ ወንጀል ይውላል፤ በዚህ ወንጀል ሴቶች ብቻ ሳይሆን ወንዶችም ተጠቂ ናቸው። ብዙ በዚህ መንገድ የተገደሉ የተዘረፉ የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸው ወንዶች አሉ፤ ስለወሲብ ጥቃት ትንኮሳ ሲወራ የዚህ ሰለባዎች አብዛኛውን ብልጫ ሴቶች ቢይዙ እንጂ ወንዶችም ሰለባ ናቸው።
በየመዝናኛ ቦታው ስትዝናኑ ፍለፊታችሁ ያልተከፈተ ነገር አትጠጡ፤ የተቀዳላችሁን መጠጥ ሳትጨርሱ አስቀምጣችሁ ሽንት ቤት የመሳሰሉት ቦታ ሄዳችሁ መጥታችሁ አትጠጡ፤ ባጠቃላይ ዞር አትበሉ ከብርጭቆአችሁ። ከማታውቁት ሰው የምግብ የመጠጥ ግብዣ ስትቀበሉ ጥንቃቄ አድርጉ፤ መዝናኛ ቦታዎች ብቻ ሳይሆን በየቤቱ በተለያየ ቦታ በሚደረግላችሁ ግብዣ ላይም ጥንቃቄ ያስፈልጋል።
በቅርብ ኢራቅ ውስጥ አንድ ዶክመንተሪ ላይ አንድ ኡዝታዝ ቁርዓን የሚያስቀራ በአካባቢው ታዋቂ የሚከበር ሰው ቁርዓን እንዲቀራላቸው ቤቱ ይሄዱ የነበሩ ሴቶች እያደነዘዘ ደፍሮ በመጨረሻ አንዷ ተበቅላው ገላው ዶክመንተሪ ተሰርቶ አይቻለሁ።
🏺ምን ልላችሁ ነው ፍፁም ከማትጠረጥሯቸውም ሰዎች የኔ በምትሏቸውም ሰዎች የትም ማንም ብትሆኑ ጥቃት ይፈፀምባችኋል።
በዚህ ዙርያ የተሰሩ ዶክመንተሪዎችን ሳይ በጣም ያስገረመኝ በዚህ መድኃኒት ንግድ ውስጥ በብዛት ሴቶች ናቸው የተሰማሩት፤ በብዛት ታዋቂ ሴቶች አርቲስት ፖለቲከኞች የመሳሰሉት።
🩺 ለምሳሌ አርቲስቶች "instagram blogger YouTuber TikToker" የመሳሰሉት "money laundry" ጨምሮ ለአደገኛ ዕፅ ዝውውር ለመሳሰሉት ወንጀል ላይ ይሳተፋሉ፤ ለዚህ ለተለያየ ወንጀል የሚመለምሏቸው አሉ በብር እያታለሉ እና ባንዴ ከበርቴ ሲሆኑ በየሀገሩ ሲዞሩ መጠርጠር አይከፋም "ብሩ ከየት መጣ?" ብሎ። ይህ ብቻ ሳይሆን እራሳቸውም ለተለያየ ወንጀል ጥቃት ሰለባ ይሆናሉ፤ ሊያጠቃቸው ለሚፈልግ እነሱን ለማግኘት ከባድ አይሆንበትም።
ስለዚህም ለማውራት ፈልጌ አልነበረም፤ እራሳችሁን ጠብቁ።
Nani Adonai እንደፃፈችው (FB ገጿ የተወሰደ) ✍
📚📚📚
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us
@noahbookdelivery