THIQAH


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ዩክሬን 40 የሩሲያ ጦር ጄቶችን መትታ ጣለች።

ዩክሬን ጥቃቱን በሩሲያ ግዛት ገብታ እንደፈፀመችው አንድ የሀገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ተናግረዋል።

ኪቭ ይህን እርምጃ ለመውሰድ 18 ወራት እንደፈጀባት አመራሩ አብራርተዋል።

ዩክሬን ጥቃቱን እንደፈፀመች ያረጋገጠው የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር፣ በኢርኩትስክ ክልል ዘልቃ መግባቷን አስታውቋል።

ሩሲያ እና ዩክሬን በነገው እለት በቱርክ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል። 
#thewashingtontimes   #dailyausaf

@ThiqahEth


በጃፓን በሬክተር ስኬል 6.1 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ።

አደጋው የተከሰተው በሰሜን ጃፓን ሆካይዶ ግዛት በምትገኘው ኩሺሮ ከተማ መሆኑን የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ (USGS) አስታውቋል።

እስካሁን በመሬት መንቀጥቀጥ አደጋው የተመዘገበ ጉዳት የለም ተብሏል።

የጃፓን ባለስልጣናት የመሬት መንቀጥቀጡን በተመለከተ የሰጡት ማብራሪያም ሆነ ማስጠንቀቂያ አልተሰጠም።
#yenisafaq

@ThiqahEth


#Update

የሟቾች ቁጥር 151 ደርሷል።

በናይጄሪያ የደረሰው የጎርፍ አደጋ አድማሱን እያሰፋ መምጣቱን የሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር (SEMA) አስታውቋል።

ጎርፉ 380 ኪሎሜትር መሸፋኑን የገለፀው አስተዳደሩ ሌሎች ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የማፈላለግ ስራው ቀጥሏል ብሏል።

በዚህ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ ከ3000 የሚበልጡ ዜጎች መፈናቀላቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይ መልኩ 500 የሚደርሱ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተወስደዋል ተብሏል።
#associatedpress #pbsnews #telegraphindia

@ThiqahEth


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
#ቪዲዮ፦ ግብፅ በበረዶ አዘል ከባድ ዝናብና ከባድ አውሎ ነፋስ ተመታች።

እስክንድርያ ከተማ በበረዶ ስትጥለቀለቅ፣ በአውሎ ነፋስ ስትታመስ ተስተውላለች።

@ThiqahEth


ዩክሬን በ11 የገጠር ቀበሌዎች የሚገኙ ዜጎቿን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች።

ዜጎቹ እንዲለቁ ማሳሰቢያ የተሰጠባቸው ሁሉም ቀበሌዎች ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ የሚገኙ ናቸው ተብሏል።

ውሳኔው ሩሲያ በነዋሪዎቹ ላይ የምታደርሰው የቦምብ ጥቃት ባለመቋረጡ የተላለፈ መሆኑ ተገልጿል።
#france24

@ThiqahEth


"አሁንም ከባድ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥርና የጉዳት መጠን መጨመሩ አይቀርም" - ናይጄሪያ

ናጀሪያ በጎርፍ አደጋ የሞቱ፣"እስካሁን 115 አስክሬኖች አንስተናል" አለች።

በናይጄሪያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ቢያንስ የ115 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።

በማክዋ ከተማ የጣለው ከባድ ዝናብ በሺዎች የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶችን አውድሟል።

የናይጄሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አደጋ አስተዳደር (SEMA) ቃል አቀባይ ኢብራሂም ሁሴን "አሁንም ከባድ ዝናብ እየጣለ በመሆኑ የሟቾች ቁጥርና የጉዳት መጠን መጨመሩ አይቀርም" ሲሉ ተናግረዋል።

በባለፈው አመት በተከሰተ ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋ ከ1200 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
#aljazeera

@ThiqahEth


#Ethiopia #Dirivers

"በ27 ቀናት 53 ሾፌር እና ረዳቶች ታግተዋል" - የሹፌሮች አንደበት

የሹፌሮች አንደበት፣ "ከ25/08/2017 እስከ 21/09/2017 ዓም 53 ሹፌር እና ረዳቶች በ 27 ቀን ውስጥ በዘራፊዎች ታፍነው ታግተው ተወስደው መከራ አይተው እንልፍ አጠው በሀሩር ቀልጠው ያጠራቀሙትን ጥሪት እየከፈሉ ተለቀዋል" ብሏል።

አክሎ፣ "እውነታው ይሄ ነው" ሲል አስታውቋል።

የኢትዮጵናያ ፌደራል ፓሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ሰሞኑን ለፋና፣ "ሰው ወደፈለገበት ቦታ መንቀሳቀስ የሚችልበት ሁኔታ ተፈጥሯል" ማለታቸውን የጠቀሰው የሺፌሮች አንደበት፣ ለዚህም አስተያየት ሰጥቷል።

"ተው እንጂ ችግራችንን ባትፈቱ፣ በደላችን ባትመለከቱ፣ መታገታችን ባይሰማችሁ መዘረፋችን ባይገዳችሁ፣ ሞታችን ምንም ባይመስላችሁ እንኳ መሬት ላይ ያለን ሀቅ ክዳችሁ 'እገታን አስቀረን' ማለታችሁ የሚያሳፍርም የሚያሸማቅቅም ነው" ብሏል።

"እንዴት በየመንገዱ እየደረሰብን ያለን በደል ዝርፊያ እገታ መገደል እንደ ቀረ አድርጋችሁ ትናገራላችሁ ? የትኛው ሹፌር ያገተ አጋች ነው የጠፋው ማን ጠይቆት ማን ተከታትሎ ይዞት ነው እገታውስ የሚቆም?" ሲልም ጠይቋል።
(ፌደራል ፓሊስ በዚህ ጉዳይ ማብራሪያ ከተሰጠን የምናቀርብ ይሆናል)

@ThiqahEth


ትራምፕ 500,000 ስደተኞችን እንዲያባርሩ ከፍተኛው ፍርድቤት ወሰነ።

የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድቤት የአራት ሀገራት ማለትም ኩባ፣ ሀይቲ፣ ኒካራጉዋና ቬንዙዌላ ስደተኞች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ መብትን አንስቷል።

ፍርድ ቤቱ በተጨማሪም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጊዚያዊ የመኖሪያ ፍቃድ የነበራቸው 350,000 የቬኔዙዌላ ስደተኞችን ከሀገር እንዲያስወጡ ፍቃዱን ሰጥቷል።

ይህን ተከትሎ የዶናልድ ትራምፕ መንግስት ከሀገር የሚያስወጣቸው ስደተኞች ብዛት አንድ ሚሊዮን ደርሷል ተብሏል።

የአሜሪካ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፕሬዚዳንቱን የስደተኞች በኃይል ማስወጣት እርምጃ የሰብዓዊ መብት አያያዝን ይጣረሳል በሚል ሲቃወም ቆይቷል።
#france24

@ThiqahEth


ተመድ 20% በጀቱን ሊቀንስ ነው ተባለ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከአሜሪካ የሚያገኘው ድጋፍ መቀነሱን ተከትሎ አንዳንድ እቅዶቹን ለመሰረዝ ተገዷል ተብሏል።

የ2025 በጀቱ 3.72 ቢሊዮን ዶላር የነበረው ተመድ በ2026 የዚህን በጀት 80% ብቻ እንደሚጠቀም ተገልጿል። 
#sputnikafrica

@ThiqahEth


የናይጄሪያ ጦር 60 አሸባሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ጦሩ ታጣቂዎቹ በቅርቡ፣ በሰሜን ናይጄሪያ በምትገኘው የሀዲን ካይ ከተማ በንጹሐን ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ብሏል።

ከሳምንት በፊት በቦኮሐራም ታጣቂዎች ላይ ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱንም ገልጿል።

በዚህ ዘመቻ ሁለት የሀገሪቱ ወታደሮች ህይወት ማለፉን አስታውቋል።  
#naijanews

@ThiqahEth


"እቅዱ የቡድኑን ፍላጎት አላማከለም" - ሀማስ

ሀማስ አሜሪካ ያቀረበችውን የተኩስ አቁም እቅድ ውድቅ አድርጓል።

በዚህም፣ "እቅዱ የቡድኑን ፍላጎት አላማከለም" ብሏል።

እስራኤል በበኩሏ፣ የስምምነት እቅዱን ለመተግበር ፍቃደኛ መሆኗን ገልፃለች።
#theindependent

@ThiqahEth


የሞሪታኒያ የቀድሞ ገንዘብ ሚኒስትር የአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

ሲዲ ኡል ታህ ናይጄሪያዊውን አኪንውሚ አደሲናን በመተካት ነው የባንኩ ፕሬዝዳንት ሆነው የተመረጡት።

የ60 አመቱ ሞሪታኒያዊ የአረብ ባንክን ለአስር አመት መርተዋል።

ታህ 76.18% በማግኘት ማሸነፋቸውም ተገልጿል።

ዛምቢያዊው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ ሳሙኤል ሙንዘሌ ሁለተኛ፣ ሴኔጋላዊው አማዱ ሆት ሦስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል። #allafrica#kuwaittimes

@ThiqahEth


የፕሬዝዳንት ቲኒቡ መንግስት 10,000 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል መባሉን አስተባበለ።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል "ፕሬዝዳንት ቲኒቡ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ 10 ሺሕ 217 ናይጄሪያዊውያን ተገድለዋል" ሲል ከቀናት በፊት ባወጣው አመላክቷል።

ጥቃቱ የተፈጸመው በመንግሥት ኃይሎች እና በአማፂያን አማካኝነት እንደሆነ ሪፓርቱ ገልጿል።

ይሁን እንጂ የናይጄሪያ ብሄራዊ ፀረሽብር ማዕከል (NCTC) "በማስረጃ ያልተደገፈና ግልጽነት የጎደለው" ሲል ሪፖርቱን አጣጥሎታል።

16ኛው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ቦላ ቲኒቡ ከሁለት አመት በፊት በ2023 ነበር ምርጫ አሸንፈው በትረስልጣን የጨበጡት።
#legit

@ThiqahEth


"የስምምነት እቅዶችን ለይተናል" - ሰርጌ ላቭሮቭ

የሩሲያና የዩክሬን ልዑካን ሁለተኛውን ዙር ድርድር ሊያካሄዱ መሆኑ ተሰምቷል።

ሁለቱ ሀገራት ሁለተኛ ዙር ድርድራቸውን ለማድረግ መስማማታቸውን ተከትሎ በቀጣይ ሳምንት ሰኞ በቱርክ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፣ ከአሜሪካ አቻቸው ማርክ ሩቢዮ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸው፣ "የስምምነት እቅዶችን ለይተን አስቀምጠናል" ሲሉ ተናግረዋል።
#euronews

@ThiqahEth



15 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »