አሰልጣኝ ፔፕ ሌንደርስ ሲቲን ሊቀላቀሉ ነው !
የቀድሞ የሊቨርፑል ምክትል አሰልጣኝ የነበሩት አሰልጣኝ ፔፕ ሌንደርስ ማንችስተር ሲቲን ለመቀላቀል መስማማታቸው ተገልጿል።
የ 42ዓመቱ አሰልጣኝ ፔፕ ሌንደርስ ከሊቨርፑል ጋር ከተለያዩ በኋላ ሬድቡል ሳልዝበርግን ተረክበው ከሰባት ወራት በኋላ መሰናበታቸው ይታወቃል።
አሰልጣኝ ፔፕ ሌንደርስ አሁን ላይ የአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላን አሰልጣኝ ቡድን ለመቀላቀል መስማማታቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
አሰልጣኝ ፔፕ ሌንደርስ በሊቨርፑል ቤት በሁለት ዙሮች አጠቃላይ ዘጠኝ እና ግማሽ አመት ማሳለፍ ችለዋል።
አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚፈትናቸው ሀሳብ ያለው እና ፈጠራዎቻቸውን ለማስቀጠል የሚረዳቸው አዲስ ምክትል አሰልጣኝ ሲያፈላልጉ እንደነበር ተገልጿል።
አሰልጣኙ ከአለም ክለቦች ዋንጫ ውድድር በፊት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላን በመቀላቀል ስራቸውን ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
@Tikvahethsport @kidusyoftahe