"የእሳት እራት" የኢትዮጵያ የአበባ ኤክስፖርት ላይ እክል ፈጠረች
📌 ምርቱ ወደ አውሮፓ ገበያ እንዳይገባ ሊታገድ ይችላል ተብሏል
ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ሀገራት የሚላክ የአበባ ምርት ውስጥ በተለምዶ "የእሳት እራት" ተብሎ በሚጠራው የቢራቢሮ ዝርያ መገኘት ምክንያት፤ ምርቱ የጥራት ጉድለት እንዳለበት ተደርጎ መቆጠሩን "ትሬድ ማርክ አፍሪካ" አስታውቋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የአውሮፓ ሕብረት በራሪው ነፍሳት ከአበባ ምርቶች ጋር ተቀላቅሎ እንዳይገባ ክልከላ ማድረጉ ተገልጿል።
የትሬድ ማርክ አፍሪካ ዳይሬክተር አቶ እውነቱ ታየ፣ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ከምታገኝባቸው ምርቶች መካከል አበባ አንዱ መሆኑን አስታውሰው፤ አበባ አምራቾች አበባው ላይ የሚታዩ ነፍሳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ስርዓት በፍጥነት ካልዘረጉ፣ የአበባ ምርት ወደ አውሮፓ ገበያ እንዳይገባ ሊታገድ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ተናግረዋል።
[ @MadoNews ]