የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደረጉበእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ ነገ ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረው 1 ሺሕ 446ኛው የኢድ አል አድሀ (አረፋ) በዓል ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሚከናወነው የኢድ ሶላት ስነ ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በመሆኑም የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከዚህ በታች የተገለፁት መንገዶች ዝግ መሆናቸውን ተገንዝበው ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ አሳስቧል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
• ከመገናኛ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ
• ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ
• ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ደንበል የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
• ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ
• ከጎፋ በአዲሱ መንገድ ወደ ለገሃር መብራት የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛ ላይ
• ከቡልጋሪያ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ላንድ ማርክ ሆስፒታል አካባቢ
• ከሳር ቤት ወደ ሜክሲኮ አደባባይ የሚወስደው መንገድ አፍሪካ ህብረት ትራክ መብራቱ መስቀለኛ ላይ
• ከጦር ኃይሎች በልደታ ከፍተኛ ፍ/ቤት ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ከፍተኛ ፍ/ቤትአደባባይ አካባቢ
• ከኑር ህንፃ ወደ ባልቻ ሆስፒታል የሚወስደው መንገድ ኑር ህንፃ መስቀለኛ ላይ
• ከፈረሰኛ መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ የሚወስደው መንገድ ጨፌ ሜዳ ትራፊክ መብራት አጠገብ
• ከበርበሬ በረንዳ ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚወስደው መንገድ በርበሬ በረንዳ አካባቢ
• ከተ/ሃይማኖት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ጎማ ቁጠባ ተ/ሃይማኖት አደባባይ
• ከሰንጋ ተራ 40/60 ኮንደሚኒየም ወደ ሠንጋ ተራ መብራት ሰንጋ ተራ 40/60 መስቀለኛ አካባቢ
• ከጌጃ ሰፈር በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የሚሄዱ አሽከርካሪዎች ጎማ ቁጠባ አካባቢ
• ከተ/ሃይማኖት አደባባይ ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ተ/ሃይማኖት አደባባይ አካባቢ
• ከሜትሮሎጂ መታጠፊያ ወደ ድሮ EBC የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መታጠፊያ
• ከጎላ ቅዱስ ሚካኤል መስቀለኛ ወደ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ኢምግሬሽን መስቀለኛ አካባቢ
• ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ
• ከ ንግድ ማተሚያ ቤት ወደ ፍልውሃ ንግድ ማተሚያ መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ
• ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ ፓርላማ መብራት ላይ
• ከኮንሰን መታጠፊያ ወደ ውጭ ጉዳይ የሚወስደው መንገድ ኮንሰን መታጠፊያ አካባቢ
• ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ የሚወስደው መንገድ ሴቶች አደባባይ ላይ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዓለም ባንክ መስቀለኛ አካባቢ ከሚከበረው በዓል ጋር ተያይዞ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ ተገልጿል፡፡
በዚህም መሠረት፡-
• ከዩኒሳ አደባባይ ወደ በላይ አብ መኪና መገጣጠሚያ የሚወስደው መንገድ
• ከቱሉዲምቱ - ወደ ጨፌ ይርጋ አደባባይ እስከ ዓለም ባንክ መስቀለኛ የሚወስደው መንገድ
እንዲሁም ከፌሮ ድልድይ እስከ ዩኒሳ አደባባይ የሚወስደው መንገድ ከሌሊቱ 10፡00 ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ በበዓሉ ዋዜማ ከምሽት 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረጅም ሠዓት ማቆም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ህብረተሰቡም ከፖሊስ የሚሰጠውን መረጃ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶች እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን አስተላልፏል።
[
@MadoNews ]