Zena Adis Ethiopia


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ይህ ዜና አዲስ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
👇#ጥቆማ ለመስጠት 📢ማስታወቂያ ለማሰራት @ZenaAdis_Ethiopiabot 👈
#Ethiopian_News
🇪🇹#ዜና_አዲስ_ኢትዮጵያ
🇪🇹#ወቅታዊ #መረጃዎች
🇪🇹#ልዩ_ልዩ #ዘገባዎች
🇪🇹#መዝናኛ #ዜናዎች_but
🇪🇹#ጠቃሚ #ጥቆማዎች_ይደርሶታል

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ግብር ይቀነስ ይሆን❓❓
ገንዘብ ሚኒስቴር በደመወዝ ላይ የሚጣለውን የግብር ምጣኔ ለማሻሻል በባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ ጀምሮ ጥናት መጀመሩን አዩዘሀበሻ መዘገቡ ይታወሳል‼️
አሁን ላይ ጥናቱ ተጠናቆ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያ ለማድረግ ገንዘብ ሚኒስቴር በደመወዝተኛው ሆነ በንግድ የገቢ ግብር ምጣኔ ላይ ማሻሻያዎችን የያዘ ረቂቅ አዋጅ አዘጋጅቷል።
በመጭው ሰኞም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከባለሙያዎች ጋር ለመመካከር ጥሪ ማድረጉ ተሰምቷል።
የኢትዮጵያ ሰራተኞች ኮንፌዴሬሽንና ሌሎችም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች በተለይ ቋሚ ደመወዝተኛው የኑሮ ጫናውን ለመቋቋም እንዲችል የሚቆረጥበት የገቢ ግብር ትርጉም ባለው መልኩ እንዲሻሻልለት ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

#Zena_Adis_Ethiopia

⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ


ኢንተርኔቱን ያጨናነቀው የትራምፕና የኤሎን መስክ ፀብ ።

በዚህ ሰአት አለም አቀፍ ሚዲያዎች ከዚህ ሌላ ምንም ወሬ የላቸውም ። ስለነሱ ከማውራታችን በፊት ግን.. ከዛሬው ፀብ ጋር ስለሚገናኝ አንድ ሰው እናንሳ ።
...

ይህ ሰው በወቅቱ ከግማሽ ቢሊየን ዶላር በላይ የነበረው ኢንቨስተር ነበር ። Jeffrey Epstein ይባላል ፡ እና በ 2019  የተለያዩ ሴቶችን በወሲብ ንግድ በማሰማራት ወንጀል ተከሰሰ ።
...
ይህ ሰው ሲከሰስ በአሜሪካን ምድር እጅግ የታወቁ ፖለቲከኞችና ታዋቂ ሰወች ስም ይፋ ባልሆነው የክስ መዝገብ ላይ ሰፍሮ ነበር ፡ ሆኖም  ይህ ክስ በሂደት ላይ እያለ ..  ጄፍሪ በታሰረበት እስር ቤት ውስጥ ራሱን አጠፋ ተባለ ።
.....
ሆኖም ብዙዎች ይህንን ነገር ይጠራጠራሉ ምክንያቱም በዛን እለት ምሽት እሱ በታሰረበት ክፍል አካባቢ ያሉ የእስር ቤቱ ካሜራዎች ተበላሽተው ነበር ተብሏል ።
ለምን ተበላሹ ? ማን አበላሻቸው ?
በየደቂቃው ይጎበኙት የነበሩት የወህኒ ቤቱ ጥበቃዎች የዛን እለት ምሽት እንዴት ችላ ሊሉት ቻሉ ?
በተጨማሪም በተደረገው ምርመራ አንገቱ አካባቢ የመሰበር ምልክት ተገኝቷል ፡ ይህ ደግሞ ራስን በማጥፋት ወቅት የሚከሰት ነገር አይደለም ።
.....
ስለዚህ Jeffrey Epstein ከወሲብ ቅሌት ጋር በተያያዘ ስማቸው እንዳይነሳ የፈለጉ ወይም ስጋት ያደረባቸው ታላላቅ ሰወች ( ባለስልጣናት ) ሚስጥር እንዳይወጣ ሲሉ ፡ አስገድለውት ይሆናል ተብሎ የሚገመት (  ኮንስፓይረሲ ) ነገር  አለ ።

ይህ በእንዲህ እያለ ታዲያ ፡ ከወራት በፊት ፡ ለአመታት ሳይገለፅ የቆየው የ Jeffrey Epstein ፋይል ሙሉ ለሙሉ ለህዝብ ይፋ ይሆናል የሚል ነገር ከአሜሪካ አቃቤ ህግ ተሰምቶ ነበር ። ( ይህችን ነገር ያዟትና .. ወደሰሞኑ ፀብ ስንሄድ )
.......
ሰሞኑን በዶናልድ ትራምፕና በኤሎን መስክ መሀከል  ያለው የቃላት ልውውጥ አድጎ ዛሬ ፡ አንዱ በሌላው ላይ ሚሳይል ሲተኩስ አምሽቷል ።
እና ዛሬም እንደሰሞኑ ፡ አንዱ አንድ ነገር ሲናገር ሌላው ሲመልስ ቆየና ፡ ከሰአታት በፊት ትራምፕ ፖሊሲያቸውን መተቸት የጀመረውን ኤሎን መስክ በሀይለኛ ቃላት ሸንቆጥ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከአንድ ሰአት በኋላ ፡ ትራምፕ ለሰነዘሩበት ትችት ኤለን መስክም አፀፋ ነው ያለውን የመልስ ምት በX አካውንቱ ጻፈ ።
...
ኤለን መስክ በዚህ የመልስ ምት ከላይ በመግቢያችን ላይ ያነሳነውን ሰው ጠቅሶ. ....
"  ይፋ ይደረጋል የተባለው የJeffrey Epstein ፋይል  ( የወሲብ ቅሌት ሊስት ) ተደፋፍኖ የቀረው የዶናልድ ትራምፕ ስም ስላለበት ነው "  የሚል አደገኛ ቦንብ በትራምፕ ላይ ጥሏል ።
....
የሁለቱን ግጭት ተከትሎም የቴስላ ሼር በ 15% ቀንሷል እና የሚገርመው ፡ ከወርና ሶስት ወር በፊት ሲሄዱም አንድ ላይ ሲበሉም አንድ ላይ የተባለላቸው ሁለት ሰወች እንዲህ መሆን መጀመራቸው ያስገርማል ።


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከኤርትራ ጋር “የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባንም” አሉ

በኤርትራ በኩል “ትንኮሳ” ቢኖርም፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከሀገሪቱ ጋር “የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባም” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ተናገሩ። ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ የሆኑ የሀገራዊ ጥቅም ጉዳዮች ስታነሳ “ትኩሳታቸው የሚጨምሩ ሀገራት አሉ” ያሉት ሚኒስትሩ፤ መንግስት በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ያለው አቋም “አይዛነፍም” ሲሉ ለፓርላማ አባላት ገልጸዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት፤ ከፓርላማ አባላት በቃል ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ዛሬ ሐሙስ ግንቦት 28፤ 2017 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ምላሽ በሰጡበት ወቅት ነው። ጥያቄ ካቀረቡት አንዱ የሆኑት የአብኑ የፓርላማ ተወካይ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ የኢትዮጵያ እና ኤርትራን ወቅታዊ ሁኔታ አንስተዋል።

ኤርትራ እና ኢትዮጵያን “ወደ ጦርነት ጅማሮ” እየወሰዳቸው ያለ “የቃል ጦርነቱ የተጀመረ ይመስለኛል” ያሉት የፓርላማ አባሉ፤ ሁለቱ ሀገራት በአሁኑ ወቅት ያላቸው “ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት” በምን መልኩ እንደሚገልጽ ጠይቀዋል። ዶ/ር ደሳለኝ ከኤርትራ ጋር “ወደ ጦርነት መግባት እድል አለ ወይ?” ሲሉም ተጨማሪ ጥያቄ አክለዋል።  

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለዚህ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፤ “ከኤርትራ መንግስት ጋር የኢትዮጵያ መንግስት የቃላት ጦርነት ውስጥ አልገባም” ሲሉ አስተባብለዋል። ጉዳዩ የሚያሳስባቸው፣ የሚመለከታቸው ዜጎች፣ የህዝብ ተወካዮች እና የቀድሞ የመንግስት ኃላፊዎች “የራሳቸውን ምልከታ” እንደሚያጋሩ ግን ሚኒስትሩ አልሸሸጉም። እነዚህ አካላት “ጆሮ ሊሰጣቸው ይገባል” ሲሉም አሳስበዋል።


አሜሪካ በፀጥታው ምክር ቤት የቀረበውን የጋዛ ተኩስ አቁም የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ አደረገች

ዩናይትድ ስቴትስ በጋዛ "ቅድመ ሁኔታ የሌለው እና ቋሚ" የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚጠይቀውን የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ረቂቅ ውሳኔ ሽራለች።

በተመድ የአሜሪካ አምባሳደር ውሳኔው የሰላም ስምምነት ለማምጣት የሚደረገውን "ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ያስተጓጉላል" ብለዋል።

ሰነዱ በሌሎች 14 አባላት ድጋፍ አግኝቷል።

#Zena_Adis_Ethiopia


ኤርትራን ጨምሮ የ12 ሀገራት ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ታገዱ
።።።።።።።።።።።።።።።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስራ ሁለት ሀገራት ላይ ሙሉ ለሙሉ የጉዞ እግድ መጣላቸው ተሰምቷል።

ለብሄራዊ ደህንነት ስጋት ናቸው ያሏቸው የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ላይ ነው ሙሉ ለሙሉ የጉዞ እግድና ሰባት ሀገራት ላይ እንዲሁ የጉዞ ገደብ የጣሉት፤

ሙሉ ለሙሉ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ የጉዞ እግድ ከተጣለባቸው 12 ሀገራት አፍጋኒስታን ፣ ቻድ፣ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ሀይቲ፣ ኢራን፣ ሊቢያ፣ ማይናማር፣ ሶማሊያ፣ የመንና ሱዳን ሀገራት ዜጎች ናቸው።

ሙሉ ለሙሉ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ከታገዱ ሀገራት ዜግች ባሻገር ቡሩንዲ ፣ ኩባ፣ ላኦስ ፣ ሴራሊዮን ፣ ቶጎ፣ ቱርኪሚስታንና ቬንዝዌላ የጉዞ ገደብ ከተጣለባቸው ሀገራት መካከል መሆናቸውን ነጩ ቤተመንግሥት አስታውቋል።

ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቱን የሚያግደውን ፊርማ ካሰፈሩ ኋላ " የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነትና የህዝባቸውን  ፍላጎት ለማሟላት ውሳኔ ማሳለፉቸው የግድ መሆኑን" አንስተዋል።

ትራምፕ አክለውም በህገወጥ መልኩ በአሜሪካ የተጠራቀሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞች አሉ ብለዋል።

ከሰሞኑ በአሜሪካ ኮሎራዶ ግዛት የተፈፀመው ጥቃት ሀገራችን ላይ የተቃጣው አደገኛ ስጋት ማሳያ ነው ብለዋል።

ከነጩ ቤተመንግስት በተላለፈው የቪዲዮ መልዕክት በአሜሪካ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚሹ ፤ ወደ ሀገራችን እንዲገቡ በጭራሽ አንፈቅድም ብለዋል።

ዶናልድ ትራምፕ በመጀመሪያው የስልጣን ዘመናቸው ማለትም በፈረንጆቹ 2017 ሰባት የኢስላም ሀገራት ላይ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ዕግድ መጣላቸው ይታወሳል።

ዘገባው የአልጀዚራ ነው።


የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ልዩ ቃለ ምልልስ!

ዛሬ ምሽት 2 ሰዓት ከ30፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተካሄደውን አዲስ ቃለ ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል

ይህ ቃለ ምልልስ የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታዎች፣ አዲስ አቅጣጫዎችን እና ወደፊት የታቀዱ ስራዎችን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰፊው የሚያብራሩበት ወሳኝ ክፍል ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ምን ሊያነሱ ይችላሉ?

-የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እና እድገቶች
-የሀገር ውስጥ የሰላም ጉዳዮች
-ከቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች
-እንዲሁም ለዜጎች አሳሳቢ የሆኑ የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሊሰጡ ይችላሉ።


አሜሪካ ትራኦሬን ይቅርታ ጠየቀች‼️
ከአሁን በፊት በአሜሪካ ሴኔት ቀርበዉ የቡርኪናፋሶውን መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ የከሰሱት የ AFRICOM አዛዥ ጄኔራል ማይክል ላንግሌይ ይቅርታ ጠየቁ።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፉት ግጭቶች ላይ ከማተኮር ይልቅ ከዋጋዱጉ ጋር ወደፊት ለመቀጠል ማተኮር እንደሚገባ መመርያ መስጠታቸው እየተበላሸ የመጣዉን የዩናይትድ ስቴትስና የአፍሪካ  ግንኙነት ለማርገብ እና አዳዲስ የውይይት መንገዶችን ለመፍጠር በዩናይትድ ስቴትስ የምዕራብ አፍሪካ ዋና ፀሐፊ ዊል ስቲቨንስ የሚመራ ልኡክ ቡድን ወደ ዋጋድጉ  መላኳን ተከትሎ ከአሁን በፊት ለተናገሩት ንግግር ይቅርታ መጠየቃቸው ነዉ የተገለጸው ።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትላንትናው እለት " በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ዳግም ማስጀመር" በሚል የልዑካን ቡድን ዋጋዱጉ የነበራቸው ቆይታ በተመለከተ ስቲቨንስ በሰጡት በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ "እኛ ማንንም ለማስተማር እዚህ አይደለንም። ግባችን ማዳመጥ እና በጋራ መከባበር እና ሉዓላዊነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነታችንን መገንባት ነው" ይህም የዋሽንግተን ዓይነተኛ አቋም ነዉ ።

ከውጭ ተጽእኖ ነፃነታቸውን በሚያረጋግጡ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች ላይ የሚታይ ጉልህ ለውጥ ያሳያል። "

አስፈላጊም ከሆነ ጄኔራል ማይክል ላንግሌይን የሰጡት ሀሳብ ሙያዊ ስነምግባር የጎደለው እና ያለመረጃ ያቀረቡት ክስ ይቅርታ ካልጠየቁ ከስልጣናቸው ይነሳሉ ማለታቸው ተከትሎ ምላሽ ሰጥተዋል ።

በምላሻቸውም ፦ ቀደም ብዬ የገለጽኩት የግል ምልከታዬ እንጂ የትራምፕ አስተዳደር አቋም አይደለም ያሉት ጀነራሉ " የሰጠሁት አስተያየት ትራኦሬ ወደስልጣን ከመምጣቱ በፊት የነበረዉን ወታደራዊ እይታ አንጻር ነው።  አዎ፣ በቡርኪናፋሶ ብዙ እየተከሰተ ነው። ሀገሪቱ በመሰረተ ልማት፣ በኢኮኖሚ እና በትምህርት ፈጣን እድገት እያስመዘገበች ነው። ለተፈጠረው አለመግባባት ይቅርታ እጠይቃለሁ " ሲሉ መናገራቸውን የዘገበው ኦል አፍሪካ ነዉ።


እስራኤል ደቡብ ሶርያን ደበደበች

የእስራኤል መከላከያ ኃይል በዳራ ጠቅላይ ግዛት የጦር መሳሪያ መምታቱን ገልጿል።

በማሕበራዊ ሚዲያ የተለቀቀው ምሥል በ175ኛ ክፍለ ጦር ቦታ ላይ የተካሄደውን የአየር ድብደባ የማያሳይ ነው ተብሏል።

የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአየር ድብደባውን ያወገዘ ሲሆን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥቃቱን እንዲያስቆም ጠይቋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል ።

💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9a


ኤርትራ ጦሯን ታስወጣ ተባለ‼️
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የኤርትራ ጦር በሃይል ወሮ ከያዘው የኢትዮጵያ  (ትግራይ) ግዛት በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ የአለማቀፍ ማህበረሰብ ጫና እንዲያደርግ አሳሰቡ‼
አምባሳደሩ ኢትዮጵያን በቃላት ብቻ ሳይሆን የታጠቁ ቡድኖችን በትጥቅ የመደገፍ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍላል ብለዋል።

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፕሬዜዳንት ኢሳያስ በ34ኛ የኤርትራ ነጻነት ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኤርትራዊያን ከነጻነት በኋላ ስላገኟቸው ለውጦች የመጥቀስ ፍላጎትና ሞራል እንዳልታየባቸው ገልፆል።
“ፕሬዜዳንት ኢሳያስ ኤርትራዊያን ከነጻነት በኋላ ስላገኟቸው ለውጦች የመጥቀስ ሞራል የላቸውም” ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ ዕለቱን በማይወክል እና በማይመለከት የጎረቤት ሃገራት ውስጣዊ ጉዳይ እንዲሁም ጂኦ ፖለቲክስ በንግግራቸው ሲፈተፍቱ እንደነበር እንዲሁም ንግግራቸው በበቂ ዕውቀት ላይ የተመሰረተ እንዳልነበር አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ትዘብታቸውን በፅሁፍ አስፍሯል።
ከ20 ደቂቃ በላይ በወሰደው ሙሉ ንግግራቸው  ስለ ሃገረ ኤርትራ አንድ አምስተኛ ያህል እንኳን ሳያካትቱ ጨርሰዋል ሲሉ የኢሳያስ አፈወርቂን ንግግር ተችተዋል።
ኤርትራ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ውስጥ የሰፈረውን ጦሯን እንድታስወጣ ጫና እንዲደረግ ጠይቀዋል።

💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ


የ 1 ብር ፌስታል 5000 ቅጣት‼️
ለእንጀራ፣ ለዳቦ እና ለተለያዩ የሸቀጥ እቃዎች መጠቅለያነት የሚውለውን የአንድ ብሩን ፕላስቲክ ይዞ መገኘት ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር የሚያስቀጣው አዋጅ ጸደቀ፡፡

ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኘ ከ2 እስከ 5 ሺህ ብር የሚያስቀጣው አዋጅ፤ ዜጎችን በማያውቁት ጉዳይ ለቅጣት የሚዳርግ ነው የሚል ትችት ከምክር ቤት አባላት ቀርቦበታል፡፡

የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ የጸደቀው #የደረቅ_ቆሻሻ_አያያዝ_እና_አወጋገድ_አዋጅ ፤ ማንኛውም ሰው አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል የፕላስቲክ ከረጢት ይዞ ከተገኝ ከ2 እስከ 5 ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፡፡

ያመረተ ወይም ወደ ሀገር ውስጥ ያስገባ፣ ለገበያ ያቀረበ ወይም የሸጠ፣ ለንግድ ዓላማ ያከማቸ ወይም ይዞ የተገኘ ከ50 ሺህ ብር በማያንስና ከ200 ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እና ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት  እንዲቀጣ አዋጁ ያዝዛል፡፡

የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ አካባቢና አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) የአዋጁን ይዘት በንባብ ባቀረቡበት ወቅት፤ የምክር ቤት አባሉ አለሙ ጎንፋ (ዶ/ር) ህዝባችን በፕላስቲክ እቃ ይዞ ወደ ቤቱ ከገባ ይጣለው? ወይስ መልሶ ለአካባቢ ጥበቃ ያስረክበው? የሚል ጥያቄ ከጠየቁ ብኋላ የምናመርተው የፕላስቲክ ውጤት ዳግም እንድንጠቀምበት የሚያደርግ ቢሆን አይሻልም ወይ? ምክንያቱም 10 ጊዜ የምጠቀምበትን ፕላስቲክ አንድ ጊዜ ብቻ ተጠቀም ማለት ተገቢ አይደለም፣ አዋጁ ፕላስቲኩን ከተጠቀምኩበት ወዲያ የት ማስቀመጥ እንዳለበት አላስቀመጠም ብለዋል፡፡

አዋጁ ይዞ የተገኝ እንዲቀጣ ይደነግጋል ህዝባችን የዚህ ግንዛቤ ይኖረዋል ወይ? የትኛው ፕላስቲክ እንደሆነ የመለየት ግንዛቤስ አለው ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ሌላ አንድ የምክር ቤት አባል በበኩላቸው ማንኛውም ሰው #ፕላስቲክ ይዞ ከተገኘ ከሁለት እስከ አምስት ሺህ ብር እንዲቀጣ ይደነግጋል፤ ይህ ከእኛ ነባራዊ ሁኔታ ጋር  እንዴት ታየ? በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሊጠቀመው ስለሚችል ጫና አይፈጥርም ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ለጥያቄዎቹ ምላሽ የሰጡት የውሃ፣ መስኖ፣ ቆላማ  አካባቢ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ አወቀ አምዛዬ(ዶ/ር) ለአንድ ጊዜ ብቻ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ፌስታሎችን ዝቅተኛው የማህበረሰብ ክፍልም ስለሚጠቀማቸው ቅጣቱ ያን ግንዛቤ ውስጥ ያስገባ ነው ብለዋል፡፡

ለምሳሌ «አንዲት አሮጊት ወይም ሽማግሌ የሁለት ብር ዳቦ ወይም የአስር ብር ስኳር ገዝተው ሲሄዱ 5 ሺህ ብር ክፍሉ ቢባሉ ላይኖራቸው ስለሚችል ቅጣቱ ከ5 ሺህ ወደ 2 ሺህ ዝቅ እንዲል ተደርጓል ይህም የህብረተሰቡን የመክፈልም አቅም ከግንዛቤ ያስገባ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የፕላስቲክ ከረጢቶች ከቅጣቱ በላይ ሀገርን የሚጎዱ ናቸው እስከ መቶ ዓመት ድረስም አይበሰብሱም ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህ አንጻር ቅጣቱ ሃያም ሰላሰም ሺህ ቢሆን ሀገርን ለማትረፍ ነው ብለዋል፡፡
ሸገር ኤፍኤም

💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ


ሳልሳይ ወያነ ፓርቲ ለጦርነት የሚንቀሳቀሱ አካላትን አሳሰበ

ሳልሳይ ወያነ ባወጣው አዲስ መግለጫ የኢትዮጵያና ኤርትራ መንግስታት እያደረጉት ካለው የሚዲያ ቃላት ምልልስና ከሁለቱ መንግስታት ባህርይ አኳያ የጦርነት ጫፍ ላይ መድረሳቸውን እንደሚገምት ገልፆ ጦርነቱ ከተጀመረ የትግራይ ህዝብ እንደሚጎዳ አሳስቧል፡፡

ስለሆነም ይህንን ድርጊት እንደሚያወግዝ የገለፀው ፓርቲው ሁለቱም አገራት ልዩነታቸውን በውይይትና በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱት ጥሪውን አቅርቧል፡፡

#Zena_Adis_Ethiopia

ቻናላችንን ቢያንስ ለ10 ሰው ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ!
               👇👇👇
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ


የአማራ ክልል ትምህርት ዘርፍ በግጭት ሳቢያ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ገብቷል፡ ትምህርት ቤቶችን ነጻ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

በአማራ ክልል ቀጥሎ ባለው ግጭት ምክንያት የትምህርት ዘርፉ ከፍተኛ ቀውስ ውስጥ መግባቱን የአማራ ክልል የትምህርት ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው ሁሉም ተፋላሚ አካላት የያዟቸውን ትምህርት ቤቶች በአስቸኳይ ነጻ እንዲያደርጉ ጠንካራ ጥሪ አቅርቧል።

በግጭቱ ምክንያት 4.1 ሚሊዮን ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሲሆኑ፣ ከ6,154 በላይ ትምህርት ቤቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ወይም ወድመዋል። በተጨማሪም ከ160 ሺህ በላይ መምህራን የስነ-ልቦና ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

የአማራ ክልል የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉነሽ ደሴ፣ ትምህርት ቤቶችን ለጦርነት ዓላማ መጠቀም የጦር ወንጀል እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት መሆኑን አስምረውበታል። "ግጭቱ የልጆችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሊጎዳ አይገባም" በማለት፣ የፖለቲካ ልዩነት የሚፈታበት ሜዳ ከትምህርት ቤት ውጪ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሕፃናት ፈንድ (UNICEF) የትምህርት ቀውስ በአገሪቱ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ እንደሚፈጥር አስጠንቅቋል። ለትምህርት ዘርፉ አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግ፣ በተለይም የተበላሹ ትምህርት ቤቶች ጥገናና መልሶ ግንባታ፣ ለተማሪዎች ምግብና የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ፣ እንዲሁም ለተፈናቀሉ ተማሪዎች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል። የአማራ ክልል የትምህርት ቢሮ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ አጋር አካላት በጋራ እንዲሰሩ አሳስቧል።


#Zena_Adis_Ethiopia

ቻናላችንን ቢያንስ ለ10 ሰው ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ!
               👇👇👇
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ


አቶ ታዬ ደንደአ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው መወሰዳቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ‼️

የቀድሞው የፌደራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ በዛሬው ዕለት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ባለቤታቸው ተናገሩ።ከሥልጣናቸው ተነስተው ለረጅም ጊዜ በእስር ላይ ከቆዩ በኋላ በዋስትና ተለቀው ጉዳያቸውን ከውጪ ሲከታተሉ የነበሩት አቶ ታዬ ዛሬ በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት በቀጠሯቸው መሠረት ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

በዛሬው ጠዋቱ የፍርድ ቤት ውሎ ነጻ ተብለው በነበሩባቸው ሁለት ክሶች በድጋሚ እንዲታዩ የተወሰነ ሲሆን ከችሎት መልስ ከሰዓት በኋላ እንደታሰሩና የት እንዳሉ እስካሁን እንደማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ ገልጸዋል።ባለቤታቸው ወ/ሮ ስንታየሁ አለማየሁ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 25/2017 ዓ.ም. ከሰዓት 10 ሰዓት በኋላ በፖሊሶች ለጥያቄ እንደሚፈለጉ በመግለጽ ከመኖሪያ ቤታቸው ተይዘው መወሰዳቸውን አረጋግጠዋል።

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ፣ የገዢው ብልጽግና ፓርቲ እንዲሁም የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ታዬ ደንደአ ባለፈው ኅዳር ከእስር ከተለቀቁ በኋላ ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት ሲከታተሉ ቆይተዋል።ባለቤታቸው ለቢቢሲ እንደተናገሩት ወደ መኖሪያ ቤታቸው የመጡት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በር አንኳኩተው ለጥያቄ በፌደራል ፖሊስ እንደሚፈልጉ በመግለጽ ወስደዋቸዋል።

ከፀጥታ ኃይሎቹ ውስጥ የታጠቁ እንደነበሩ የጠቀሱት ባለቤታቸው ወደ ቤት በመግባት አቶ ታዬን ይዘው እንደወጡ እና በዚህ ጊዜም የጨፌ (የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት) አባል መሆናቸውን እና የሕዝብ ተወካይ መሆናቸውን በተደጋጋሚ ሲናገሩ ነበር ብለዋል።ከአስር በላይ የሚሆኑ የፖሊስ አባላት አቶ ታዬን ለመያዝ ታዘው መምጣታቸውን እንደተናገሩ እና ተወሰዱ ወደተባለበት መሃል አዲስ አበባ ወደ ሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ጽሕፈት ቤት እንደሚሄዱ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።

ነገር ግን የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ እና የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት አባል አቶ ታዬ ደንደአ በፀጥታ ኃይሎች ከቤታቸው ተይዘው ከተወሰዱ በኋላ እስከ ሰኞ ምሽት ድረስ የታሰሩበትን ማወቅ እንዳልቻሉ ባለቤታቸው ወ/ር ስንታየሁ ዓለማየሁ ለቢቢሲ ገልጸዋል።

#Zena_Adis_Ethiopia

ቻናላችንን ቢያንስ ለ10 ሰው ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ!
               👇👇👇
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ


የሃድያ ዞን ነዋሪዎች ለመልካም አስተዳደር እጦት ለፌዴራል መንግሥት አመለከቱ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሃድያ ዞን ነዋሪዎች፣ በክልሉ መንግሥት የከፋ የመልካም አስተዳደር በደል እየደረሰባቸው መሆኑን በመግለጽ ለፌዴራል መንግሥት አቤቱታ አቀረቡ። የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምም በቀረበው ቅሬታ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።

ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ከሃድያ ዞን የተውጣጡ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትና ለተለያዩ የፌዴራል ተቋማት በአካል አቅርበዋል። ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ነዋሪዎች ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለጹት፣ የዞኑና የክልሉ አስተዳደር አካላት የጥቅም ሰንሰለት በመፍጠር የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ሰዎች በጅምላ እያሠሩ ነው።

ነዋሪዎቹ ከሚያቀርቧቸው ዋና ዋና ቅሬታዎች መካከል፦ የክልሉ የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጪ እስር መፈጸማቸው፣ በፍርድ ቤት ነፃ የተባሉ ሰዎች ከእስር አለመለቀቃቸው፣ የታሰሩ ሰዎችን ወደ ፍርድ ቤት አለማቅረባቸው፣ የፍርድ ቤት ውሳኔዎችን አለመፈጸማቸው፣ ለመንግሥት ቅሬታ ሲያቀርቡ ‹‹ፀረ ሰላም ናችሁ›› የሚል ስያሜ መሰጠቱ እና የመሬት ወረራ ይገኙበታል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ እንደሻው ጣሰው የነዋሪዎቹን ቅሬታ በተመለከተ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፤ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ግን ቅሬታውን አረጋግጦ ባለሙያዎችን ወደ ስፍራው መላኩንና በቅርቡ ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጿል።

#Zena_Adis_Ethiopia

ቻናላችንን ቢያንስ ለ10 ሰው ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ!
               👇👇👇
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ


ከእሁድ እስከ እሁድ ፈጣን የመረጃ ምንጭ! 🌍

#ዜና_አዲስ_ኢትዮጵያ || መረጃ ህይወት ነውና ለሁሉም ይድረስ!

የሃገር ቤት ትኩስ ትኩስ መረጃዎች፣ የአፍሪካ አዳዲስ ዜናዎች፣ እና ከዓለም ዙሪያ የሚመጡ አበይት ክንውኖች በሙሉ፣ በየቀኑ በፍጥነትና በትክክለኛ ማስረጃዎች ተደግፈው ይቀርባሉ!

ቻናላችንን ቢያንስ ለ10 ሰው ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋ!
               👇👇👇
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ
https://t.me/+T4nCtrKz_-DWg9aJ


የ 2017 ዓ.ም የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የማጠቃለያ ፈተና መሰጠት በዛሬው ዕለት ተጀምሯል !

ፈተናውም ዛሬ አንስቶ እሰከ ቅዳሜ ድረስ የሚያቆይ ይሆናል።

ለተፈታኖች መልካም ዕድል 🙌

@ZenaAdis_Ethiopia
@ZenaAdis_Ethiopia


በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክትን ለሱዳኑ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሀን አቀረቡ

በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መልዕክትን ለሱዳኑ ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሀን አቅርበዋል።

መልዕክቱን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ በፖርት ሱዳን አቅርበዋል። 

በፖርት ሱዳን ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው የገለፁት የልዑኩ መሪ “ሱዳን ሰላም እና መረጋጋቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ጥረት ኢትዮጵያ የማይናወጥ ድጋፏን እንደምትቀጥል” በአፅንኦት መግለጻቸውን ተናግረዋል።

ዘገባው የኢዜአ ነው።

@ZenaAdis_Ethiopia
@ZenaAdis_Ethiopia


የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖች በራሺያ ላይ በፈፀሙት ከባድ ጥቃት 40 የጦር አውሮፕላን ወደሙ

ዩክሬን በ40 የሩሲያ የጦር አውሮፕላኖች ላይ በአራት ወታደራዊ ካምፖች ላይ ተከታታይ ከባድ ጥቃቶችን ከፈጸመች በኋላ ከሩሲያ ጋር በሚደረገው ጦርነት ትልቁን የረዥም ርቀት ጥቃት እሁድ እለት ማጠናቀቋን ገልጻለች። ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንዳሉት 117 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በኤስቢዩ የደህንነት አገልግሎት “የሸረሪት ድር” እየተባለ በሚጠራው ተግባር ላይ “34 በመቶ የሩሲያ ስትራቴጂካዊ የክሩዝ ሚሳይል ተሸካሚዎችን” መቷል ብለዋል። የዩክሬኑ ደህንነት ኤስቢዩ ምንጮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት የጥቃቱን ሂደት ለማደራጀት አንድ ዓመት ተኩል ፈጅቷል ሲሉ ተደምጠዋል። ሩሲያ በአምስት ክልሎች የተፈፀመባትን የዩክሬን ጥቃቶችን "የሽብርተኝነት ድርጊት" በማለት ጠርታለች።

ጥቃቱ የደረሰው የሩሲያ እና የዩክሬን ተደራዳሪዎች ዛሬ ሰኞ ለሁለተኛ ዙር የሰላም ድርድር ወደ ኢስታንቡል ቱርክ በሚያቀኑበት ወቅት ነው።ውይይቱ በሲራጋን ቤተ መንግስት እንደሚጀመር ይጠበቃል። ጦርነቱን እንዴት ማቆም እንደሚቻል ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች በጣም የተራራቁ በመሆናቸው የሚጠበቀውም ውጤት ዝቅተኛ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩክሬን ባለስልጣናት በሳምንቱ መጨረሻ በግዛታቸው ላይ ግዙፍ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙን አስታውቀዋል። በካርኪፍ የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የሰባት አመት ህፃንን ጨምሮ ቢያንስ 6 ሰዎች ቆስለዋል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተናግረዋል። በሌላ ቦታ የሩስያ መንግስት የዜና ወኪል ሪያ የሀገሪቱ የጸጥታ አገልግሎት በምስራቅ ሩሲያ የተፈፀመውን የጥቃት ሙከራ ማክሸፉን ገልጿል።

በፕሪሞርዬ ክልል ሁለት ነዋሪዎች በዩክሬን ትእዛዝ የባቡር ሀዲዱን ለማበላሸት እየሞከሩ ነበር ብሏል። የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በየካቲት 2022 በዩክሬን ላይ ሙሉ በሙሉ ወረራ ጀምረዋል። ሞስኮ በአሁኑ ጊዜ በ 2014 የጠቀለለቻትን ደቡባዊ ክራይሚያ ልሳነ ምድርን ጨምሮ 20 በመቶ የሚሆነውን የዩክሬን ግዛት በእጇ ይገኛል።የኤስቢዩ ምንጮች እንደተናገሩት ከተመቱት የሩሲያ አውሮፕላኖች መካከል ቱ-95 እና ቱ-22ኤም 3 የሚባሉ ስልታዊ የኒውክሌር አቅም ያላቸው ቦምቦች እንዲሁም ኤ-50 የቅድመ ማስጠንቀቂያ የጦር አውሮፕላኖች ይገኙበታል። አጠቃላይ ስራውን “እጅግ የተወሳሰበ ነበረ” ሲሉ ገልጸውታል።

@ZenaAdus_Ethiopia
@ZenaAdus_Ethiopia


ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ አሸማጋይ ድርጅት መሥራች አባል ሆነች‼️

በቻይና የሆንግ ኮንግ ልዩ አስተዳዳር በትናንትናው ዕለት በተካሄደ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት የዓለም አቀፍ አሸማጋይ ድርጅት በይነ መንግሥታዊ ተቋም መመሥረቱ ይፋ ሆኗል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ በቪዲዮ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ መሥራች አባል ሆና መፈረሟ በመንግሥታት መካከል የሚፈጠሩ ግጭቶችና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በሽምግልና ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም፤ ተቋሙ በመንግሥታት፣ በመንግሥታትና በግሉ ዘርፍ መካከል የሚፈጠሩ ከኢንቨስትመንት ጋር የተያያዙ አለመግባባቶችን በሠላማዊ መንገድ በሽምግልና ለመፍታት ያቀደ መሆኑን መጠቆማቸውን  የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል

@ZenaAdis_Ethiopia
@ZenaAdis_Ethiopia


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ድብድብ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ፖሊስ እና አሽከርካሪ ሲደባደቡ ተመልክተናል።
ይህ ክስተት የተከሰተው ሳሊተ ምህረት አካባቢ ነው ብለውናል።

@ZenaAdis_Ethiopia
@ZenaAdis_Ethiopia

Показано 20 последних публикаций.
OSZAR »