👳🏽ባለዕዳው


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


ሁሉም ስለእኛ ነው ።
የምከትበው እይታዬን ብቻ ነው ! ወይ ልክ ነው ወይ አይደለም ፤ ልክ ካልመሰላቹ እየፈተፈትን እንወያይበታለን ወቢላሂተውፊቅ🙌

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


መልካም ኢፍጣር🙄


ብቻ መኖር ያለብን ህይወት አለ ....ያን ህይወት ፈልገን ማግኘት አለብን ።


ለመኖር ስል እየነካካው ያለኋቸው ርዕሶች ሁላ ከመኖር ሲያርቁኝ ነው የማስተውለው ። አማኝ ለመሆን ስጥር ከጌታዬ መራቅ ለምን ይሰማኛል ? ለማወቅ ስጥር የውሸት ትርክት የማጎር አይነት ስሜት....ለመጠንከር ስሞክር ድካም... ለምን ?
ጊዜያቶች ባለፉ ቁጥር እቺ አለም የውሸት ሹራብ እየደረበች ...የእውነትን ብርሀን እያደበዘዘች ...የመኖርን ጣዕም እያጎመዘዘች ነው ።
እቺ አለም እንደነበረችው አይደለችም...መሆን እንዳለባትም አይደለችም ። ከዘመናት በፊት የተቀየሰ አዲስ መንገድ ሳይኖር አይቀርም ። ይህ መንገድ ሁሉን ነገር አሳጥቶናል ...እምነታችንን ፣ ህይወታችንን ፣ እኛነታችንን ሁሉ ነጥቆናል ። አማኝነትን በራስ ወዳድነትና በተጨቃጫቂነት ለውጦብናል...ህይወታችንን ለሌሎች በማቀበል ስለሌሎች የሚገበር ተራ የጊዜያት ጥርቅም አድርጎብናል...እኛነታችንን ለማናውቀው እና ፍፁም ደስታችንን ለሚመጠው ሌላ ነገር አሳልፎ ሰጥቶብናል ።

ይህ ሌላ ነገር ግን ምንድነው ? እየኖርን ያለነው ምንድነው ? ምን እየተፈጠረ ነው ግን?


ሰው ግን "ሀራም ግኑኝነት...ስብራት" ወዘተ በሚባሉ ርዕሶች ተጠምዶ የሚገረፍ ትንሽ ነገር ነው እንዴ ? ከአኗሪ ጋር በሚደረግ ፍትጊያ ቀልጦ የሚቀር ትንሽ ነገር ነው እንዴ ? ልብ እኮ ከዱንያ ይበልጣል ...ልብ በዱንያ ምት ለመሰበር የሚበቃ ርክሰት የላትምኮ...ልብ በሰዎች ለመሰበር የሚገባት አይደለችምኮ ።

ተው ልባቹን አትልበሱት....ተው ልባቹን ሸፍኑት ።


መልካም ኢፍጣር አህባቦች ።

ምግብን የተዋችሁለት ጌታ ስህተቶቻችሁን ይተውላቹ ....የተጠማቹለት ጌታ በጀነቱ ውሀ ያርካቹ❤️


ሰው እስኪረዳ የሚደክም..እስኪያውቅ የሚከስል ...እስኪገነዘብ የማይኖር ፍጡር ነው ።
የሆነ ጊዜ ደርሶ እስኪነቃ ድረስ ሩሁን እያጠበበ ..በማያገባው ሩጫ እየደከመ ..በማይመለከተው ዝላይ እየተሰበረ ..እያለቀ የሚጠብቅ ሚስኪን ፍጡር ነው ። አይደለም ክፍያ ትኩረት ለማይገባቸው ነገሮች ሰላሙን...መረጋጋቱን...ደስታውን ሁሉ የሚገብር ነገርም ነው ።

አሁን ያላቹበት ቦታ መኖር አለባቹ? እየከፈላቹት ያለው ዋጋ የሚ'ገባው ነው ?


ዛሬም መልካም ኢፍጣር😁


መልካም ኢፍጣር የምወ*ቹ ❤️


"ይሄ ጨቅጫቃ ልጅ ያሰበውን አሳካለት" ብላቹ ከአፍጥር በፊት ዱዓ ብታደርጉልኝ እንደማይደብረኝ ታውቃላቹሀ? ለናንተም አርጉ❤️


ስለሴት ልጅ አይን እና ፀጉር መቶኛ ፅሁፍ እያነበብክና እየተመሠጥክ ሀቢቢን ﷺ የሚያሞግስ ፅሁፍ ስታነብ ከሸከከክ እና ከፍ ከፍ አታርጉኝ የሚል አባባል ትዝ ካለህ .....እንግዲ ምን እልሀለው☹️🚶

اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا محمد


ከዛ ለምን ይሄን ፅሁፍ ፅፌ እንደለቀኩ ማሰብ ጀመርኩ☹️


የሆነ ሰዓት ላይ በመጥላት ውስጥ አማኝ መሆን የተወሰነ  ልክነት ያለው ይመስለኝ ነበር ። ማህበራዊ ሚድያ ላይ "ለዲኔ"ብለው ሲጨቃጨቁ እና የምር በሆነ ጥላቻ ሲረጋገሙ ስመለከት " አይ ለዲን ነው እንጂኮ " ብዬ ኡዝር ለመስጠት እጋጋጥ ነበር ።

ከዛ ብዙ ብሽሽቅ ...ብዙ ስድድብ...ብዙ ርግግም...እና ሌላ ብዙ መጥፎ ነገሮችን አይቼ አይቼ እስከመጨረሻው ወጣልኝ🚶 ። ዲኔን በጥንጡ ስገልጠው...ኢስላምን እንደግለሰብ አይቼ ትንሽ ስረዳው ምናምን ሳልፈልግ መራቅ ጀመርኩ... ያኔ ኢስላም ማለት የአሊሞች...የዳዒዎች እና የሆኑ ስብስቦች ይመስለኝ ስለነበረ እጨነቅ እና እሰለች ነበር ።

አይቀርምና ትንሽ አደኩኝ😁 ያኔ ዲኑ የኔ ...ጀነቱ ለኔ...ጀሀነሙ በኔ እንደሆነ ገባኝ ...አላህ የኔ እኔም የኔ መሆኔን ተረዳው .....አለ ኣ እስልምና እንደሚተረከው ፤ የቃልአጋኖ መዓት የሞላው ፤ የራስ እምነት በሌሎች ስህተት የሚጠነክር ምናምን እንዳልሆነ ትንሽ አወኩ...ለካ ጉዳዩ ስለኔና ስለአላህ ብቻ ነው ....ለካ ስለውስጤ ብቻ ነው 🙂


መልካም ኢፍጣር አህባቦች🖤


ሸይጧን ሀያቱን በሙሉ የሰው ልጅን ሲያሳስት ..ለማጥመም ሲወጣ ሲወርድ ኖሮ መጨረሻ ላይ " እኔ ካንተ ንፁህ ነኝ እኔ የአለማቱን ጌታ እፈራለው " ይላል...ከዛም ብሶ " ጠራኋቹ እንጂ ስልጣን ኖሮኝ አላስገደድኳችሁም እኔን አትውቀሱ ራሳችሁን ውቀሱ " ጭራሽ አሳማሚ ቅጣት አለባችሁ ብሎም ይሳለቃል ☹️

እና እንግዲህ እሱ ለአላማው ሲል እስከቂያም ድረስ ይለፋልና እኛም እቺን 60 አመት ለአላማችን ..ለጀነታችን እንልፋ "ሸይጧን አሳስቶኝኮ ነው" የሚለው ቃል እንኳን አላህ ጋር ሸይጧን ጋርም ውድቅ ነውና እንንቃ ።

ነፍሳችሁን አደራ ...ጀነታችሁን አደራ


ደሞ ደሞ አትዘኑ እሺ☺️


ነገ ኸሚስ ነዋ ....ዙልሂጃም ነው😋

ፆሙም...ዚክሩም...ቁርዓኑም እንደተጠበቀ ነው👐


መልካም ኢፍጣር እንግዲህ🫶


ቀኑ እንዴት ነበር ? ቃል በተግባባነው መልኩ አለፈ ?


እና የረሳሁት.....ቁርዓን must ነው 🙌

የሩህ ሰላምም ይገባናልኮ❤️


ጨረቃ ያለፀሀይ የማይታይ ግዑዝ ድንጋይ ሆና ከኛ ትሰወር ነበር ግና በፀሀይ አማካኝነት ውብ ሆና የውበት መገለጫ ተደርጋ ተያዘች ። ጨረቃ ያለ ፀሀይ ግን ጨለማ ናት !

ህይወትም እንዲሁ ናት ! ህይወት ያለ ጌታዋ ጭልም ..ሽክር...ጉርብጥ ያለች ናት ። አላህን ጥለን የምናረገው እርምጃ እና ለመኖር የምናጣጥረው ህይወት ሁሉ ውስጥ አክሳሚና ደስታን ነጣቂ ነው ። ህይወት ያለ አላህ አሳማሚና ጨለማ ናት ።

ህይወት ከአላህ ጋር ግን ከጨረቃም በላይ ውብ ናት 🤍

ወላህ ስለናንተና ስለአላህ ብላቹ ከሆነ ምንም እጡ ...ስለናንተና ሌላ ብላቹ ግን አላህን አትጡ ! ያለ አላህ ሁሉ ነገር አድካሚ ነው...ሁሉ ነገር አሳማሚ ነው ።

እና ከአላህ ርቀን ሀያታችን ተዘበራርቋልና ልንቀርበው እና ደስታችንን ልናስመልስ ግድ ይለናል ! አልሃምዱሊላህ ከረመዷን በኋላ የዙልሂጃን ቀናት ለግሶናልና በደንብ ተጠቅመን ረሀ ነፍስ እንሰካካለን ።


so ነገ ፆም እንዳለ ሆኖ .....ተውባህ...ተስቢህ እና ተፈኩር ይኖረናል ።

-ስላሳለፍነው ስህተት እንፀፀታለን ...ከሱ ለራቅንበት ጊዜ እንቆጫለን !
- በትንሹ ከመቶ በላይ ተስቢህ ወይም ዚክር እናረጋለን
- እሱ ያለበት ሀያት እና የሌለበት ሀያት ልዩነቱን እናስተነትናለን


ዝግጁ ?

Показано 20 последних публикаций.
OSZAR »