በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ውጤት በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚመወሰድ ተገለፀ።
በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ውጤት በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚመወሰድ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስቴሩ ይህን ያሉት የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተወያየበት መድረክ ላይ ነው፡፡
በዚሁ ጊዜ ፕሮፌሰር ብርሃኑ "ዩኒቨርሲቲዎች ሰው እውቀትና እውነት ፈልጎ የሚመጣባቸው ተቋማት ሊሆኑ ይገባል" ብለዋል።
አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ተግባራቸው አድርገው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በዚህ ረገድ በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች በመውጫ ፈተና ውጤት ከ25 በመቶ በታች ካስመዘገቡ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል እርምጃ እንደሚወሰድ አመላክተዋል።
Via @mussesolomon