Фильтр публикаций


በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን በአገር ውስጥ ማምረትም ሆነ መገጣጠም ተከለከለ

በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ቁጥር ወደ 500 ሺሕ የማድረስ ዕቅድ መያዙ ተገልፆ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች በአገር ውስጥ እንዳይመረቱና እንዳይገጣጠሙ መታገዱን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) የቻይናው ሁዋጂያን ኩባንያ ከጂኤሲ አዮን ኩባንያ ጋር በመተባበር ግንቦት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ባስተዋወቀበት መድረክ ባደረጉት ንግግር፣ ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ታበረታታለች ብለዋል፡፡

አያይዘውም ‹‹በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ብቻ እናበረታታለን፡፡ በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይመረቱ፣ እንዳይገጣጠሙና ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ለማድረግ ቁርጠኞች ነን፡፡ የምናበረታታው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ እንዲመረቱ፣ እንዲገጣጠሙና ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ነው፤›› ብለዋል፡፡

Via @mussesolomon


ለግል ተጓዦች የሚፈቀደው የውጭ ምንዛሪ ከፍ ተደረገ።

ለውጭ ሀገር ተጓዦች የሚፈቀደው የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ መጠን ወደ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር፣ ለንግድ ሥራ መንገደኞች ደግሞ 15 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ከፍ መደረጉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አሳውቋል።

ለውጭ ሀገር ተጓዦች ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል ወደ ውጭ ሀገር ለሚጓዙ ኢትዮጵያውያን በጥሬ ገንዘብ የሚፈቀደው የውጭ ምንዛሪ መጠን እንዲጨምር ተደርጓል ሲል አሳውቋል።

ይህንንም የውጭ ምንዛሪ በጥሬ ገንዘብ ወይም በካርድ መውሰድ እንደሚቻል ተገልጿል።

Via @mussesolomon


የእንጀራ እናቶች ቀን

ስለ "የእናቶች ቀን" ስናስብ አእምሯችን ብዙውን ጊዜ ወደ ስጋ እናቶች ይሄዳል. ነገር ግን ወደ እናትነት ሚና የሚገቡት በውልደት ሳይሆን በምርጫ፣ በልብ እና በፍቅር ዋጋ ስለሚከፍሉ የእንጀራ እናቶች ይህ ቀን የሚከባረው።

የእንጀራ እናት ቀን በየአመቱ ከእናቶች ቀን በኋላ እሁድ ይከበራል። እ.ኤ.አ. ሚይ 18 ይከበራል ።

Via @mussesolomon


🛑 25% ብቻ በመክፈል ለውጥ ፈጣሪ ኮርሶችን እንደ Graphics design, video Editing, Digital Marketing, Upwork የምትወስዱበት የዘውድ ቴክ 6ተኛ ዙር ምዝገባ ከወራቶች ቆይታ በኋላ ተጀመረ።

✅100% የስራ እድል
✅ጥራት ያለው ስልጠና በ professional አስተማሪዎች
✅አንዴ ከፍለው 4 ስልጠናዎችን የሚወስዱበት
✅ certificate ያለው

️ያሉት ቦታዎች ውስን ስለሆኑ አሁኑኑ ከታች ባለው የዘውድ ቴክ ቻናል ሊንክ ተቀላቅለው orientation ይመልከቱ በመቀጠልም እዛ ላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች መልዕክት መላክ ወይንም መደወል ይችላሉ።

📩ቻናል ሊንክ👇

https://t.me/zewdtech/43


ትራምፕ በታሪክ ትልቁን የመከላከያ ሽያጭ ስምምነት ከሳውዲ አረቢያ ጋር ተፈራረሙ።

አሜሪካና ሳውዲ አረቢያ በ142 ቢሊዮን ዶላር የመሣሪያ ሽያጭ ስምምነት ፈርመዋል፤ ይህንንም ስምምነት "በታሪክ ውስጥ የሆነው ትልቁ የመከላከያ ሽያጭ ስምምነት” ተብሎ ተገልጿል።

በጉዞው ወቅት ዋይት ሀውስ ትራምፕ ከአዲሱ የሶሪያ መሪ አህመድ አል-ሻራ ጋር እንደሚገናኙ አረጋግጧል።

Via @mussesolomon


Репост из: Nexline Business Group
🚘 አዳዲስ መኪናዎችን በቀላሉ ከ Nexline!

እርስዎን ምርጫ ለመሟሟት
📌 የፈለጉት የመኪና አይነት
📌በምትመርጡት ሞዴል እና ቀለም
📌 በተመጣጣኝ ዋጋ
📌 በፈጣን እና ቀላል ሂደት

በተመቾት የክፍያ አማራጮች፦
✅ በካሽ
✅ በባንክ 20/80
✅ ወይም 50/50 በሆነ ክፍያ አሁኑኑ መኪናዎን ፈጥነው ከኛ ይውሰዱ።

📞መኪናዎን በቀላሉ ይውሰዱ ዛሬውኑን ይደውሉ !
+251911593030
+251912775652

👇ለበለጠ መረጃ እና ምርጫ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ።👇

👉 https://t.me/NexlineBusinesGroup


ፑቲን እና ዘለንስኪ ከጦርነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊገናኙ ነው

ቭላድሚር ፑቲን ከዩክሬን አቻቸው ቮለድሚር ዘለንስኪ ጋር "ቀጥተኛ ውይይት" ለማድረግ መስማማታቸው ተገልጿል።

የቀጥታ ውይይቱ በመጪው ሐሙስ ከፑቲን ጋር በቱርክ መቅሮጣቸዋል ዘለንስኪ አሳውቀዋል:: ቅድሚያ ግን የተኩስ አቁም ስምምነት አንዲኖር ጠይቀዋል።

Via @mussesolomon


በትራንስፖርት ተርሚናል ውስጥ መጠጥና ጫት መጠቀም ተከለከለ።

የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ያዘጋጀው ደንብ፣ በሕዝብ ትራንስፖርት ተርሚናል የአልኮል መጠጥ የጠጡ፣ ጫት የቃሙና ሲጋራ የሚያጨሱ ሰራተኞች ባሏቸው ኢንተርፕራይዞች ላይ ቅጣት የሚጥል መሆኑ ገልፃዋል።


በተርሚናል አገልግሎት ላይ እያለ አልኮል የጠጣ፣ ሲጋራ ያጨሰ ወይም ጫትየቃመና ለመልካም ሥነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ ድርጊት የፈፀመ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥፋት 10 ሺህ ብር እንደሚቀጣ እና ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋት ከፈፀመ ኢንተርፕራይዙ ውሉ እንደሚቋረጥ የተደነገገ ሲሆን፥ በተመሳሳይ ማንኛውም የተርሚናል ኢንተርፕራይዝ አባል ያለ ደንብ ልብስና መታወቂያ ሥራ ላይ ከተገኘ ተመሳሳይ ቅጣት እንደሚጠብቀውም ደንቡ ያሳያል።

Via @mussesolomon


🛑 25% ብቻ በመክፈል ለውጥ ፈጣሪ ኮርሶችን እንደ Graphics design, video Editing, Digital Marketing, Upwork የምትወስዱበት የተራዘመው የዘውድ ቴክ 4ተኛ ዙር ምዝገባ ሊጠናቀቅ ነው።

✅100% የስራ እድል
✅ጥራት ያለው ስልጠና በ professional አስተማሪዎች
✅አንዴ ከፍለው 4 ስልጠናዎችን የሚወስዱበት
✅ certificate ያለው

️ያሉት ቦታዎች ውስን ስለሆኑ አሁኑኑ ከታች ባለው የዘውድ ቴክ ቻናል ሊንክ ተቀላቅለው orientation ይመልከቱ በመቀጠልም እዛ ላይ ባሉት ስልክ ቁጥሮች መልዕክት መላክ ወይንም መደወል ይችላሉ።

📩ቻናል ሊንክ👇

https://t.me/zewdtech/43


የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል።

የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ / የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል። የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ይሆናል።

የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 23 ፣ ሰኔ 24 እና ሰኔ 25/2017 ዓ/ም የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሰኔ 26 ፣ ሰኔ 27 እና ሰኔ 30/2017 ዓ/ም ይሰጣል።

የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ወረቀት ፈተናቸውን የሚወስዱ ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም በበየነ መረብ (ኦንላይን) /ፈተናቸውን የሚወስዱ የ1ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 1 ፣ ሐምሌ 2 እና ሐምሌ 3/2017 ዓ/ም የ2ኛ ዙር ተፈታኞች ፦ ሐምሌ 4 ፣ ሐምሌ 7 እና ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም ይሰጣል።

Via @mussesolomon


የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አዲስ ሊቀ ጳጳስ መረጠች

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን አዲሱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሮበርት ፕሬቮስት መሆናቸው ታውቋል።

ቤተ-ክርስቲያኒቱን ሲመሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሊዎ 14ኛ ተብለው ይጠራሉ።

የ69 ዓመት እድሜ ባለፀጋ የሆኑት ሮበርት ፕሬቮስት የመጀመሪያው አሜሪካዊ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሆነዋል።

Via @mussesolomon


ጥቁር ጭስ በቫቲካን ጉባኤ 1ኛ ዙር ላይ መታየቱ ጳጳስ እንደማይመረጥ ያሳያል ተባለ

ረቡዕ እለት በሲስቲን ቻፕል አናት ላይ ካለው የጭስ ማውጫው ውስጥ ጥቁር ጭስ ሲወጣ ታይቷል ፣ ይህም በጳጳሱ ጉባኤ የመጀመሪያ ዙር ምርጫ አዲስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን መምረጥ አለመቻሉን ያሳያል ።

ለዘመናት የቆየውን ባህል በመቀጠል 133 ካርዲናል መራጮች ባለፈው ወር የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ሞት ተከትሎ 267ኛውን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ ለመምረጥ በቫቲካን ተሰብስበው ይገኛል። በ2013 ፍራንቸስኮን የመረጠውን ጉባኤ በመምራት በብፁዕ ካርዲናል ጆቫኒ ባቲስታ ሬ በተከበረው በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በቅዳሴ ቀኑ መጀመሩ ይታወሳል።

ከዚያም ካርዲናል መራጮች በፖልላይን ቻፕል ውስጥ ተሰብስበው ወደ ሲስቲን ቻፕል ገብተዋል። ስብሰባው ቀጥሏል። በማይክል አንጄሎ ምስሎች ያጌጠው የሲስቲን ቻፔል አዲስ ጳጳስ እስኪመረጥ ድረስ ከውጪው ዓለም ተዘግቶ ይቆያል። በኮንክላቭ ህግ መሰረት ቀጣዩን ጳጳስ ለመምረጥ ሁለት ሶስተኛው ድምጽ ያስፈልጋል።

Via @mussesolomon


ያለ ረዳት የሚያሽከረክሩ የከተማ ታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ አሳወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ በብዛት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት "ሚኒባስ" ታክሲዎች ያለ ረዳት መንቀሰቀሳቸው ሕገ-ወጥ እንደሆነ እና ደንቡን ተላልፈው በተገኙ አሽከርካሪዎች ላይ የቅጣት እርምጃ እንደሚወሰድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በኮሚሽኑ የትራፊክ አደጋ ምርመራ የግድያና አደጋዎች መርማሪ ኢንስፔክተር ተመስገን ደሳለኝ በሰጡት ምላሽ፤ "የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ያለ ረዳት ማሽከርከራቸው በሕግ የተከለከለ ነው" ብለዋል።

"መሰል ድርጊቶች ለመንገድ ላይ አደጋዎች መፈጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው" ያሉት ኢንስፔተክተር ተመስገን፤ አሽከርካሪዎች ሙሉ ትኩረታቸውን በማሽከርከር ሥራቸው ላይ አለማድረጋቸው የመንገድ ላይ ክስተቶችን ለመቆጣጠር እንዳይችሉ እና አደጋ እንዲፈጠር የሚያደርግ በመሆኑ የተከለከለ መሆኑን ተናግረዋል።

"ይህንን ደንብ ተላልፈው በተገኙ አሽከርካሪዎች ላይም ቅጣት ይጣላል" ሲሉ አሳስበዋል።

Via @mussesolomon


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ዓመታዊ የ'ጥቁር ፊት' ፌስቲቫል በቻይና

ከ 1,000 ለሚበልጡ ዓመታት በቻይና የሚከበረው የጥቁር ፊት ቀን ተሳታፊዎች እራሳቸውን እና በአቅራቢያ ያለ ማንኛውንም ሰው ጥቁር ቀለም በመቀባት ያሳልፋሉ - ሃብት እና መንፈሳዊ ጥበቃን ያመጣል በሚል እስከ አሁን መከበሩን ቀጥሏል ።

Via @mussesolomon


ምንም ብር የሌላው ሰው

ብዙ ብር ያለዉ ሰዉ ሚሊየነር እና ቢሊየነር እንደ ሚባለው ሁሉ ምንም ገንዘብ የሌላው ሰው ኒሊየነር ይባላል።

ለዛ ኒሊየነር ለሆነ ጓደኛዎች ላኩላቸው።

Via @mussesolomon


ራሱን ለጠቆመ 1ሺ ዶላር ይከፈለዋል

የትራምፕ አስተዳደር ወደ ትውልድ አገራቸው ለሚመለሱ ለእያንዳንዱ ሰነድ አልባ ስደተኞች ለጉዞ የሚሆን 1,000 ዶላር እንደሚሰጥ ተናግሯል።

የሀገር ውስጥ ደህንነት ፀሐፊ ክሪስቲ ኖም እዚህ በህገ ወጥ መንገድ ከሆናችሁ እራስን ማፈናቀል ምርጡ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ብዙ ወጪ ቆጣቢ መንገድ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

በፈቃዳቸው ለሚባረሩ  ሰዎች የሚሰጠው 1000$ አበል እና የአየር ትራንስፖርት ዋጋ በግዴታ  ከምናባርረው ዋጋ ያነሰ ነው ብሏል ኤጀንሲው። ህጋዊ ሰነድ የሌለውን ሰው በቁጥጥር ስር የማዋል  እና የማስወጣት አማካይ ወጪው በአሁኑ ጊዜ 17,000 ዶላር ነው ብለዋል።

Via @mussesolomon


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በኬንያ ፕሬዝዳንት ላይ የጫማ ጥቃት

ፖሊስ ዊሊያም ሩቶ እሁድ እለት በሚጎሪ ካውንቲ የሕዝብ ንግግር እያደረጉ በነበረበት ወቅት የተፈጠረው ክስተት ድንገት የሆነ ወይስ ታቅዶ የተፈፀመ እንደሆነ እየመረመረ መሆኑን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

የቅድሚያ መረጃዎች ጥቃቱ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ እና የታሰበ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

የናይሮቢ ካውንቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ኤስቴር ፓሳሪስ "በፕሬዳንቱ ላይ ጫማ መወርወር ተቃውሞ አይደለም፤ ትንኮሳ ነው። በሚጎሪ የተከሰተውን አሳዛኝ ክስተት አጥብቄ አወግዛለሁ። ይህ በቀስቃሽ ግለሰብ የተፈፀመው አሳፋሪ ድርጊት የኬንያውያንን እሴት እና ምኞት አያንጸባርቅም" ሲሉ ተናግረዋል።

Via @mussesolomon


ትራምፕ ለ60 ዓመታት በላይ ተዘግቶ የቆየው የከባድ ወንጀለኞች እስር ቤት እንዲከፈት መመሪያ ሰጡ

የአሜሪከው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሀገሪቱ ከባድ ወንጀል የሚፈፀሙ እስረኞች የሚቆዩበት አልካትራዝ እስር ቤት ታድሶ ዳግም እንዲከፈት መመሪያ መስጠታቸውን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ በትሩዝ ማህበራዊ ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥
እጅግ አደገኛ ወንጀለኞች በማንም ላይ አደጋ እንዳያደርሱ ለማድረግ እስር ቤቱ እንደገና ታድሶ እንዲከፈት ለሀገሪቱ የማረሚያ ቤቶች ቢሮ፣ የፍትህ ሚኒስቴር፣ የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ እና የሀገር ውስጥ ደህንነት መመሪያ ሰጥቻለሁ ብለዋል።

በካሊፎርኒያ የሚገኘው አልካትራዝ እስር ቤት በደሴት ላይ ያለ በመሆኑ ከዚህ በፊት ሰብረው ለማምለጥ የሞከሩ እስረኞች ከመስጠም በቀር ምንም ዓይነት ዕድል አልነበራቸውም ተብሏል።

ከስልሳ ዓመታት በፊት ተዘግቶ የነበረው እስር ቤቱ አሁን በግዛቷ ዝነኛ ፓርክና የቱሪቶች መዝናኛ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ተዘግቧል።

Via @mussesolomon


የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራንፕ የ ካቶሊክ እምነት ተከታዮችን አስቆጡ

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) የተሰራ የካቶሊክ ጳጳስ አድርጎ የሚያሳያቸውን ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸው  ከካቶሊክ እምነት ተከታዮች ዘንድ ቁጣና  ነቀፌታ አስከትሏል።

አርብ ማታ በትራምፕ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራው ይህ ምስል ጳጳሳት የሚለብሱትን ነጭ ልብሰ ተክህኖ እና ቆብን አድርገው የሚያሳየው በኤአይ (AI) የተሰራው ምስል የተጋራው ዶናልድ ትራምፕ ለጋዜጠኞች "ጳጳስ መሆን እፈልጋለሁ" ብለው ከቀለዱ በኋላ ነው።

ምስሉ መጋራቱን ተከትሎም የኒው ዮርክን ጳጳስ የሚወክለው የኒው ዮርክ ግዛት የካቶሊክ ጉባዔ "ክቡር ፕሬዝዳንት በዚህ ምስል ላይ ምንም ዓይነት ጥበብ ወይንም የሚያስቅ ነገር የለም" ሲል ቅሬታውን አስታውቋል።

Via @mussesolomon


116ኛውን የኢትዮጵያ ፖሊስ ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።
በዚህም መሠረት፦

👉 ከ22 አደባባይ ወደ ወደ ቅዱስ ዑራኤል -መስቀል አደባባይ (22 አደባባይ በተመሣሣይ ዘሪሁን ህንፃ መስቀለኛ ላይ )
👉 ከአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ (አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ)
👉 ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ)
👉 ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት
👉 ከመስቀል ፍላዎር አደባባይ ወደ ጋዜቦ አደባባይ (መስቀል ፍላዎር አደባባይ ላይ )
👉 ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኤግዚብሽን ውስጥ ለውስጥ ወደ ፊላሚንጎ (ጋዜቦ አደባባይ ላይ )
👉 ከቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክርሰቲያን ወደ ለገሃር መብራት ( ቅዱስ ቂርቆስ ወደ ጋዜቦ ላይ )
👉 ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ
👉ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሀር መብራት (ሜክሲኮ አደባባይ ላይ)
👉ከፓርላማ መብራት ወደ ውጭ ጉዳይ (ፓርላማ መብራት ላይ )
👉ከጥይት ቤት ወደ ቅዱስ ገብርኤል (ጥይት ቤት መታጠፊያ ላይ )
ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ (ሴቶች አደባባይ ላይ )
👉ከሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ቶታል (ሴቶች አደባባይ ላይ) ከንጋቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።
በተጨማሪም፦
👉 ከቅዱስ ዑራኤል ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
👉 ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም
👉 ከብሔራዊ ቤተጰመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ ከዛሬ ማለትም ከ25/08/2017 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግ ሲሆን እንዲሁም ለዚሁ ፕሮግራም ሲባል ከቀኑ 10:00 ሰዓት ጀምሮ በመስመሮቹ ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።


Via @mussesolomon

Показано 20 последних публикаций.
OSZAR »