በትራንስፖርት ተርሚናል ውስጥ መጠጥና ጫት መጠቀም ተከለከለ።
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ያዘጋጀው ደንብ፣ በሕዝብ ትራንስፖርት ተርሚናል የአልኮል መጠጥ የጠጡ፣ ጫት የቃሙና ሲጋራ የሚያጨሱ ሰራተኞች ባሏቸው ኢንተርፕራይዞች ላይ ቅጣት የሚጥል መሆኑ ገልፃዋል።
በተርሚናል አገልግሎት ላይ እያለ አልኮል የጠጣ፣ ሲጋራ ያጨሰ ወይም ጫትየቃመና ለመልካም ሥነ ምግባር ተቃራኒ የሆነ ድርጊት የፈፀመ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥፋት 10 ሺህ ብር እንደሚቀጣ እና ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋት ከፈፀመ ኢንተርፕራይዙ ውሉ እንደሚቋረጥ የተደነገገ ሲሆን፥ በተመሳሳይ ማንኛውም የተርሚናል ኢንተርፕራይዝ አባል ያለ ደንብ ልብስና መታወቂያ ሥራ ላይ ከተገኘ ተመሳሳይ ቅጣት እንደሚጠብቀውም ደንቡ ያሳያል።
Via @mussesolomon