🫴በዚህ ጉዳይ የመጨረሻ ይሁንና እኔሰወች አሞሪም ግትርነውሲሉ አይገባኝም ግትርነቱ ባመነበት መፅናቱ ከሆነ በሚጫወትበት ፎርሜሽን መቀጠሉ ከሆነ... ይሄን እንዴውም እፈልገዋለሁ ተመችቶኛል እንደሱ እንዴውም ሁሉንም ነገር ሞክሮ ዩናይትድን ያጋለጠው አሰልጣኝ የለም ቡድኑ ያለበትን ሁኔታ አጋልጦት ስላየን ሊመሰገን ይገባል .... በመጨረሻ ደቂቃዎች ለምን ፎርሜሽን አይቀይርም ምናምን ትላላችሁ ፎርሜሽኑን ለመቀየርምኮ ጥሩ ጥሩ አማራጮች ሊኖት ይገባል ቸግሮት ማግዌርን አጥቂ እያደረገ ሚሰቃይን አሰልጣኝ ደረቅነው ማለት አልችልም... ሁሉንም ነገር ሞክሮታል ሁሉንም... እየተቸገረ ያለው ቡድኑ ብዙ ድክመት ስላለበትነው...
እስካሁን የመጡት አሰልጣኞች በሙሉ ይወቀሳሉ ግትር ይባላሉ ከራሱ የአጨዋወት ስልት ወጦ ማታለያ ሰጦን የሰነባበተው ቴንሃግ እንኳን ግትርተብሏል ቴንሃግ ያልሞከረው ነገር ነበረ እንዴ..?
ምንድነው ምትፈልጉ ቡድኑ ሲሸነፍ ለምን እገሌ ተቀመጠ ተነሳ ፎርሜሽኑ ምናምን ወሬይበዛል እግርኳስነው ሁሌም ቢሆን አነጋጋሪ ነገሮችን አያጣም የዩናይትድ ጉዳይግን የአሰልጣኞች ድክመት አደለም
ለኔ አሞሪም በሲስተሙ መቀጠሉና መፅናቱ የወደፊቱ ትልቅ አሰልጣኝ እንደሚሆን ያመንኩበትነው ጫናን በዚህልክ መቋቋም ጥንካሬን ያሳያል ከራሴ ሃሳብ አልወጣም ሲስተሙ ካልሰራ ለቅቄ እሄዳለሁ እንጂ ይላል ለጊዜው ተብሎ በሚቀየር ሃሳብ ትንሽ ጊዜያዊ ደስታ ትመጣ ይሆናል እንጂ ቡድኑ አይድንም ዩናይትድ እንዲድን ከተፈለገ መሞት አለበት
ሁሉም ነገር ከዜሮ መጀመር አለበት ራኜሊክ የሆነጊዜ ቀዶጥገና አደለም ትልቅ የልብ ቀዶጥገናነው ለዚህ ቡድን ሚያስፈልገው ያለውንነገር ሁሌም እወደዋለሁ አሁን ዩናይትድ ሙቷል ይሄ የመጨረሻው ደረጃነው በምንም ይምጣ ምንም ያድርጉ ጥሩ ድጋፍ ከተደረገለት አዲስ ቡድን መገንባት ይችላል ...
ለዩናይትድ እንደዚህ መሆን ተጠያቂ መሆን ያለባቸው ግሌዘሮች እንጂ አሰልጣኞች ወይም ተጨዋቾች አደሉም
የተጨዋቾች ኳሊቲ ማነስ የአሰልጣኞች ብቃትችግር በለውጥ መስተካከል የሚችልነው አሞሪምን ማሰናበትኮ በጣም ቀላሉነገርነው ካሳ እንኳን አልፈልግም እያለነው እሱን አሰናብቶ ሌላ ማምጣት ይቻላል ነገርግን ሚመጣውም ኢንቨስትመንት ይፈልጋል
ግሌዘሮች ከባድ ናቸው ነገ የሆነ ውሳኔ ወስነው ትኩረቱን ወደሌሎች ማዞር ያውቁበታል ለምሳሌ አሰልጣኝ ቢቀይሩ ሁሉም ነገር ይረሳና ደጋፊው አዲሱን አሰልጣኝ እያሰበ ማለም ይጀምራል ይሄነው ዩናይትድን የገደለው አሰልጣኙን እንፈልገዋለን እናንተናችሁ በሽቶቻችን ማለት ሲጀምሩና ደጋፊው በፅናት ሲቃወም ስታዲየሙን ደጋግመው ባዶ ሲያረጉት ወደዱም ጠሉም እነዚህ ሰወች ይሄዳሉ እነሱ ካልወጡ ማንም ይምጣ ይውጣ ለውጥ አይኖርም
አንድን ትልቅ የነበረ ቡድን እንደዚህሁኖ ለማየት የተገደድነው በቂ ኢንቨስትመንት ስላላደረጉ ብቻም አደለም የምልመላ ኔትወርካቸውም ችግሮች ስላሉበትነው
ቢያንስ ሚወጣው ገንዘብ ጥሩፈራሚ ሊያስገኝ ይገባል ነገርግን ምርጫቸው ላይም ችግሮች በዝተዋል እነዚህ ሰወች ቢወጡና ሌሎች ባለሃብቶች ቢመጡ ከ INEOS ሰወችጋር ጥሩ ነገር መስራት ይቻላል ዩናይትድ አሁንላይ እውቀት ያላቸውን ባለሙያዎች ይዟል ያጣው ኢንቨስትመንትነው
በዩናይትድ ቤት የመጡት አሰልጣኞች ሁሉም አቅም ያላቸው ምርጦች ናቸው ከጆሴ በላይ ልምድ የነበረው ሊጉን ሚያውቀው ለሻምፒዮንነት የተሰራ አሰልጣኝ የለም እሱም ሌሎችም የወጡትግን በቂኢንቨስት ሳይደረግላቸውና የማይረቡ ውሳኔዎች እየተወሰኑ ለዩናይትድ ማይመጥኑ ተጨዋቾች እየመጡነው አሁንም ወደፊትም ግሌዘሮች እያሉ ዩናይትድ አይድንም.... ነገርግን እስከ ሂወታችን ፍፃሜ ከዚህ ክለብጋር አብረን እንቆያለን..!
#
@the_red_forever_mv