ፍቅር እና ግጥም 🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Криптовалюты


ከሚቀበል:ይልቅ:የሚሰጥ:ብፁዕ:ነው

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Криптовалюты
Статистика
Фильтр публикаций


Репост из: ONLY BETTING
Betty እባላለሁ እድሜ  23 ነው በጣም ቆንጆ  እና ለ kiss የሚገፋፋ ከንፈር አለኝ ስራዬ የ ሆቴል  አስተናጋጅ ነኝ
በምሰራበት ሆቴል በጣም ብዙ ደምበኞች ነበሩኝ  ቀኑን ባላስታውስም ወደ 2:30 አካባቢ ይሆናል ከደንበኞቼ አንዱ መኝታ ቤቱ ድረስ ቢራ እንዳመጣለት ይጠይቀኛል እኔም ቢራዉን ወሰድኩለት ክፍሉ ስገባ ግን ያልጠበኩት
see more....




🙏🙏እናቴን አፍልጉኝ 🙏🙏

ከላይ በምስሉ ላይ የምትመለከቱዋቸው እናታችን በቀን 03/06/2017 ዓ.ም እንደወጡ ወደ ቤታቸው አልተመለሱም ለመጨረሻ ጊዜ የታዩት ሳሪስ አቦ ቤተ/ክርስትያን አካባቢ ነው እና መናገር እና ሃሳባቸው መግለጽ ስለማይችሉ ያሉበትን የምታቁ በዚህ ስልክ ቁጥር ጠቁሙን ።
0953429684
0962171562
0943049266

ይሄንንም ቪድዮ share https://youtu.be/uEnCM15nuS4?si=REElDsn19XZfD4Xm


●በፍቅር ላይ ስትሆን እና ስትጎዳ ልክ እንደ መቆረጥ ነው - ይድናል ግን ሁሌም ጠባሳ ሆኖ ይኖራል።🥀

2.1k 0 11 11 97

💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

      
♥️🌺 የመጨረሻው ክፍል 🌺♥️


◆እነመቅደስም መሞቱን አምነው ሀዘን
ሲቀመጡ መቅደስ እራሷን ለማጥፋት ስትሞክር ሀሉም በንባ
ታጥበው ነበር.............
.........ቢያንስ መቅደስ ከሶስቴ በላይ እራሷን ልታጠፋ ስትል
እየደረሱ አድነዋታል በዚህም የተነሳ ብቻዋን ጥለዋት ወተው
አያውቁም ዛሬ ግን አጋጣሚ ሆነባቸውና ቅብጥብጡን ቅዱስን
አደራ ብለውት ከፊቷ እንዳይጠፋ አስጠንቅቀውት ጉዳይ
ስለነበረባቸው ሁሉም ወጡ እንደእብድ ያረጋት መቅደስ አሁንም
የጌዲዮን መሞት ስታስብ መሞት አማራት ከዛ ብዙ ኪኒን
ለመዋጥ ስታስብ ቅዱስ አለ ከዛም ሱቅ ልትልከው አስባ ቅዱሴ
ስትለው ወዬ አላት ሱቅ ሄደህልኝ ና አለችው አረ ላሽ በይ እነ
ማሚ ጥዬሽ እንዳልሄድ አስጠንቅቀውኛል ሲላት ሴት እኮ ነኝ
ታዲያ ልበላሽ አላሳዝንህም ስትለው ምንድነው የምገዛልሽ አላት
እ .እ. እንትን ልክ እንደፈራች ሆና መርበትበት ጀመረች ደሞ
ከዚህ ውጪ ምንም ቢሆን እንደማሄድላት ታውቃለች ከዛም ካፏ
ቀበል አርጎ እየሳቀ ሲስቱ ብዙ አትጨናነቂ ገባኝ የሴቶች
ፓንፐርስ ነዋ ሲላት ሂ ሞዛዛ ብላ በጥፊ አለችው ከዛም
አደራውን እረስቶ ሊያመጣላት ተስማማና ብር ተቀብሏት ሄደ
እንደሄደም ኪኒኑን ሰብስባ ልትውጠው ስትል የቤታቸው ስልክ
ጮኸ ዝም አለችው አሁንም ልትውጥ ስትል ጮኸ አሁንም
ዝም አለችው ከዛም አሁንም ልትውጥ ስትል ሞባይሏ ጮኸ
በንዴት አንስታ ሄሎ ስትል ሀይ መቅዲዬ ብሩክ ነኝ በቤትስልክ
ስደውል የሚያነሳ የለም ደንዝዛ ቀረች በዛ ላይ የብሩክ ድምፅ
ፍፁም ልክ አልነበረም መልስ ልትሰጠውም አንደበቷ አልፈታም
አለ ከዛም በዛ በተዘበራረቀ ድምፁ አሁን ኤርፖርት ነኝ ነገ ማታ
12 ሰአት ስለምንደርስ ኤርፓርት ጠብቁን አላት ጌዲስ ሞተ
አይደል ብላ ልትጠይቀው አስባ ካፏ ሳታወጣው ስልኩ ተቋረጠ
እንባ ካይኖቿ ዱብ ዱብ እያለ ብቻዋን ስታወራ ቅዱስ ተመልሶ
መጣ ሲያይት ደንግጦ ምን ሆንሽ አላት መልስ አልሰጠችውም
ክፍሏ ገብታ ተኛች ማታ ቤተሰቦቿ መጡ..........
ተሰብስበው ሳሎን ቁጭ ባሉበት ያለወትሮዋ መጥታ መሀላቸው
ሶፋው ላይ ቁጭ አለች ሁሉም አይን አይኗን ማየት ጀመሩ
ምክንያቱም አብራቸው መሆን ካቆመች ቆየች መሬት መሬቱን
እያየች ብሩክ ነገ ይመጣል አለቻቸው ምን አሏት አዎ 12ሰአት
ተቀበሉኝ ብሏል ስትላቸው ጌዲዮንስ አሏት እኔንጃ አላቅም ብላ
ተመልሳ ወደክፍሏ ሄደች......
......መድረስ አይቀርምና የመምጫቸው ሰአት ሲደርስ ሁሉም
ተሰብስበው የኤርፖርቱ በር ላይ በሁለት ስሜት ይጠባበቁ ጀመር
ግማሹ ተሳፋሪ ወጣ ቡሀላም ብሩክ ወደነሱ ቀረበ ግን እሱን
ሳይሆን ሁሉም የሚያዩት ባይናቸው የሚፈልጉት ጌዲዮንን ነበረ
ቢሆንም አጡት አባትየው ቀስ ብሎ መቅደስን ደገፋት ሁሉም
ልባቸው ቀጥ ልትል ምንም አልቀራትም ተስፋቸው ተሟጦ
የጌዲዮን ሞት አምነው ለመጮህ እራሳቸውን ሲያዘጋጁ
በስተመጨረሻ ባልጋ እየተገፋ ቻው ብሏቸው የሄደው ጌዲዮ
ድኖ ጋቢ ለብሶ ከቅዱስ ቡሀላ እየተራመደ መጣ...........
............ሁሉም በህልም አለም ያሉ መሰላቸው መቅደስ
በጩኸት ዘለለች ሌሎቹም እየተንበረከኩ በምስጋና ላምላካቸው
መስገድ ጀመሩ መቅደስ እንደጨቅላ ፍየል እንደንቦሳ ጥጃ ከዛ
ከዚህ መሯሯጥ ጀመረች የታመነችለት ፍቅር ታመነላት ጌዲዮንን
አሳልፎ ለሞት አልሰጠባትም ከሩቅ ገና ሲያያት ጌዲዮን
እየተንደረደረ ወደሷ መጣ እሷም እየሮጠች ወደሱ ስትሄድ
መሀል ላይ ተገናኙ ከዛም ሊያቅፋት ሲል ተመልሳ ወደቤተሰቦቿ
ተንደረደረች ጌዲዮ ደነገጠ እሷን እሷን እያየ እንባውን አዘራ
እሷም እያለቀሰች እየዘለለች አባ አባዬ እሱ ነው ጌዲዮን
አልሞተም እኮ እያለች እውን የሆነውን ህልሟን ትተርክ ጀመር
በሁኔታዋ እንኳን ቤተሰቦቿ ያያቸው የተመለከታቸው አለቀሰ
ከዛም ወደጌዲዮ ተመለሰች አሁንም ሳታቅፈው ተመለሰች
ጌዲዮን ደስታዋ መሆኑን ሲያውቅ ከመሬት ተንበርክኮ በንባ ታጠበ
ፈጣሪውን አመሰገነ ለሶስተኛ ጊዜ ስትመጣ አሁንም
እንዳትመለስ ሁልቱን እጆቿን ጭምቅ አርጎ ይዞ ጉንጮቹ ላይ
አረጋቸው የናፈቀው አይኗ የናፈቃት አይኑ ተፋጠጡ ፍቅር
የተራበው ልባቸው በሀሴት ጮቤ እረገጠ ከንፈራቸው
ተንቀጠቀጠ ናፍቆትና ፍቅር የጋረደው አይናቸው በዙሪያቸው
የሚመለከታቸውን ህዝብ አላስትዋሉም ጌዲዮንም ቤተሰቦቿ
መኖራቸውን እረሳው ብቻ ለመጨረሻ ጊዜ ሳማት የተባለ
ይመስል ያኔ የመጀመሪያ ቀን እንደሳማት ግጥም አርጎ ከንፈሯን
ጎረሰው አቤት ሲያምሩ አቤት ሲያስቀኑ መፋቀርስ እንደነሱ
ፀጉሯን እየዳበሰ እሷም አንዴ ጉንጩን አንዴ ወገቡን አጥብቃ
እየያዘችው እያገላበጠ ያለምንም ፍራት ይሳሳሙ ጀመር
ቡሀላም አለመላቀቃቸውን ቀበጡ ቅዱስ ሲያይ ጠጋ ብሎ
እህህ እህህ አረ እኛንም ሰላም በለን ናፍቀኸናል እኮ ሲለው
ጌዲ ደንገጥ አፈር ብሎ መቅደስን ለቀቃትና ከመጣህ
ትመልስልኛለህ ብላ ያጠለቀችለትን ያንገቷን ማህተብ አውልቆ
አጠለቀላት ከዛም ግንባሯን ስሞ ሁሉንም እያቀፈ በንባ ሰላም
አላቸው..............
.............ወደቤትም እንደሄዱ እራት በሉ ቡናም እየጠጡ
እናቱን ጠየቃቸው ከዛም ገዳም እንደሆኑ እሱ ሲሄድ
እንደሚወጡ ነገሩት መቅደስ ከቅፉ አልወጣችም ነበረ በቃ
ከናንተ ጋር ናፍቆቴን ይህን ያክል ካሳለፍኩ ነገ እሄዳለሁ እሜ
እጅግ በጣም ነው የናፈቀችኝ አላቸው ከዛም የመቅደስ እናት
በቃ መቅደስም አብራህ ትሂድ ባይሆን ጓደኞቿ እሁድ
ስለሚመረቁ በዛውን የደስታችንን ድግስ አብሬ እደግሳለሁ
ቅዳሜ እናትህን ይዛችሁ እንድትመጡ ሲሉት እንዴ መቅዲስ
አትመረቅም አላቸው መቅደስ ቶሎ ብላ አይኗን ከመሬት ተከለች
አባቷም አይ ጌዲ እንኳን ከትምርት ከራሷም አለም ወታ ነበር
እኮ ብለው የተፈጠረውን ተራ በተራ አስረዱት ጌዲዮን የመቅደስ
ፍቅር ካቅሙ በላይ ሆኖበት ከውስጡ ሸሸጋት.......
........ከዛም አገር ቤት ሲሄዱ አገር ምድሩ ተቀበላቸው እናቱም
በልልታ ፀሎቷን የሰማት አምላኳን እያመሰገነች ልጇን ከቅፏ
አስገባችው የናቱም ያባቱም ዘመዶች ጎረቤቱም ሳይቀር ከግሩ
ተንበርክከው ይቅርታ ለመኑት እሱም ይቅር ለእግዚብሄር
አላቸውመረገጣቸው መገፋታቸው ለበጎ ሆነ አሸናፊዎቹ ተሸነፉ
ተሸናፊዎቹ አሸነፉ!!!!!...........

        
💝  ተፈፀመ  💝

                
●የታል Like 👍

○○○○○○○♥️♥️♥️♥️♥️♥️●●●●●●●

2.2k 0 10 17 97

📚#ከመጣጥፍ_ዓለም
~~~~
●ራሳችንን የምናይበት አስገራሚ ታሪክ»

አንዲት ወጣት ሴት ለጉዞ ኤርፖርት ውስጥ ተቀምጣለች።
አውሮፕላኑ እንደሚዘገይ ባወቀች ጊዜ ኤርፓርት ውስጥ
ካሉት ሱቆች ኩኪስና መጽሐፍ ገዛች።

ወደ VIP (የተመረጡ ሰዎች ብቻ ወደ የሚስተናገዱበት)
ክፍል ገብታ ለንባብ ምቹ ወደ ሆነው መደገፊያ ወንበር
አመራች። ተደላድላ ተቀምጣ ማንበብ ጀመረች።

አጠገቧ እንድ ሰው መጽሐፍ ያነባል። በሁለት መደገፊያ
ወንበሮች መሐል ኩኪስ ተቀምጧል። በንባቧ መካከል
መተከዢያ
ሆኗታል።

ታዲያ ከኩኪሷ አንድ ስታነሳ ሰውየውም አንድ አነሳ ገረማት።
ሳያስፈቅዳት መውሰዱ አስደነቃት። ግን ዝም አለች። ቀጥላ
እርሷ አንድ ስትወስድ እርሱም ሌላ ወሰደ አሁን ተበሳጨች።
ድፍረቱ አናደዳት። በዚህ አላበቃም እስከ መጨረሻው
ቀጠለ።
ቅጥል አለች! ግን ንቃ ተወችው።

በአካባቢው ያሉ ሰዎችን አትኩሮት መሳብ አልፈለገችም።
ለዚህ ብቻ
አይደለም በኩኪስ ምክንያት ጸብ ረብሻ መፍጠር
አልፈለገችም።
እንዲህ እንዲህ እያለ የመጨረሻ አንድ ኩኪስ ቀረች።

" ይሄ የተረገመ ሰው ምን ያደርግ ይሆን? " ስትል አሰበችና
በቀስታ ማየት ጀመረች። ከዚያም ሰውየው ኩኪሷን ሁለት
ቦታ ከፈላትና ግማሹን ወሰደ። ለድፍረቱ ጥግ አጣችለት።
ከልክ ያለፈ ስርዓት የለሽ እንደሆነ ደመደመች።

ሰዓቱ ደርሶ አውሮፕላን ላይ እንደተሳፈረች መነጽር
ለማውጣት ቦርሳዋን ስትከፍት አይኗን ማመን
አልቻለችም። ያልተከፈተው የታሸገው ኩኪሷ ቦርሳዋ
ውስጥ አለ። በጣም አፈረች ተሸማቀቀች።

ለካስ የራስዋን ኩኪስ ቦርሳዋ ውስጥ ረስታ የሰውየውን ነበር
ስትበላ የቆየችው። ከሁሉም በላይ በጣም ያጸጸታት ሰውየው
እስከ መጨረሻው አንዲት ኩኪስ እስክትቀር ድረስ ያካፍላት
የነበረው ምንም ሳይቆጣና ሳይመረር በደስታ መሆኑ ነበር።

የራሱን ኩኪስ እየበላች በሰውየው ላይ ስትበሳጭበት
በመቆየቷ እጅግ አፈረች። አሁን ይቅርታ ለመጠየቅ እንኳን
ጊዜው አልፏል። እርሱም በሌላ አውሮፕላን ወደ ሐገሩ
አቅንቷል። እርሱን የማግኘት አንድ ተጨማሪ እድል እንኳን
የላትም።

ብዙ ተመኘች ማመስገን፣ ይቅርታ መጠየቅ፣ ጉዳዩን
ማብራራት፣
ግን ሁሉም እሷው ጋ ቀሩ አልፏል። አራት የማይጠገኑ
ነገሮችን
አሰበች፦
1. ድንጋይ ከተወረወረ በኋላ
2. ቃላት ከተናገርናቸው በኋላ
3. ድርጊቶች ካመለጡን በኋላ
4. ጊዜ ካለፈ በኋላ ዋጋ እንደሌለው

እኛም ምንም ነገር ከመናገራችን ከመፈፀማችን በፊት
መጀመሪያ
ራሳችንን እንይ ።


💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_❷❼

➞የንስሀ አባታቸውም ብዙ አስተማሯቸው ስለይቅርባይነት
ብዙ ነገሯቸው በስተመጨረሻም እግዚያብሄር ሊፈትነኝስ ቢሆን
ብለው አሰቡና ልጄን አትርፍልኝ እንጂ እንኳን ይሄንን ስንቱን
ችያለሁ ብለው ይቅር ለግዚያብሄር አሉ ሰላም ወረደ ገዳምም
ገብተው ፆም ፀሎታቸውን ተያያዙት.................
.........መቅደስ አዘውትራ የምትሄደው ጌዲዮ የሚያጠናበት
ጫካ ነው ነገ ትምርት ጨርሰው ወደየመጡበት ይበተናሉ
ያመጣችው ውጤት ምንም ከሷ የማይጠበቅ ነው ይሄ ወር
ደግሞ ያምስተኛ አመት ተማሪዎች የጌዲዮ ጓደኞች ምርቃት
ነው ህመሟን ጨመረው ስለምርቃቱ ጓጉቶ የነገራት
እያስታወሰች በተለይ ምን ታመጪልኛለሽ ሲላት ያገር አበባ
ያለችው ብቻ ሁሉንም እያስታወሰች በንባ እየታጠበች
ነው........
.....እውነትም አልቀረም የምርቃታቸው ቀን ደረሰ የዛ ቀን
መቅደስ በጠና ታመመች ሀኪም ቤትም እንዳትወሱዱኝ አለች
ከዛም እቤት ድረስ ዶክተር አመጡ ዶክተሩም አክሞ ሲጨርስ
በጣም በናፍቆት ተጎድታለች ምግብም ካለመመገቧ የተነሳ
እራሷን መቆጣጠር ተስኗታል በተቻላችሁ አቅም የናፈቀችውን
ሰው ብታገናኟት ጥሩ ነው ሲላቸው አይ ዶክተር ይሄማ መች
ጠፋን ለማንኛውም እናመሰግናለን አሉት..... በቃ ከዛን ጊዜ
ጀምሮ ጭራሽ ከክፍሏ አልወጣም አለች ያምስተኛ አመት
ትምርቷንም ልክ እንደጌዲዮ አቆመች ቤተሰቦቿ እግሯ ላይ
ቢወድቁም አልማርም አለች ግዜም መሄዱ አይቀርምና ጌዲዮ ሁሉንም ቀዶ ጥገና
በወዳጆቹ ፀሎትና በፈጣሪ ፍቃድ በሰላም አጠናቆ የመጨረሻው
ቀዶ ጥገና ለማድረግ ቀጠሮው ደርሶ ወደ ቀዶ ጥገናው ክፍል
አስገቡት......ብሩክ ከዚህ ቡሀላ ጌዲዮ ያለበትን ሁኔታ ለማወቅ
አልቻለም አንድም መልስ የሚሰጠው ዶክተር አጣ ይሙት ይኑር
ምኑን አውቆት ቤተሰቦቹም አስጨነቁት ግራ ቢገባው ሞቶም
ከሆነ ቁርጤን ንገሩኝ አላቸው የህክምናው ክፍል መግባት
አይቻልም መልስ የሚሰጠው አጣ ለምን የሚል ጥያቄ
ጭንቅላቱ ውስጥ ተፈጥሮበት በከፍተኛ ሀዘን ተዋጠ ለብዙ
ሳምንታትም የተለያየ ምክንያት እየሰጠ ቢሸውዳቸውም በስተ
መጨረሻ ግን አልቻለም ሁሉም አፋጠጡት ስልኩን ሙሉ ለሙሉ
ኦፍ አረገው በቃ ከዚህም ቡሀላ ቤተሰቡ ሀዘን ተቀመጠ
መቅደስ ካንዴም ሁለቴ እራሷን ልታጠፋ ስትል ደርሰው አዳኗት
እንኳን የጌዲዮን የብሩክን ድምፅ ከሰሙ ወራቶች ተቆጠሩ...
.....ጌዲዮና መቅደስ ከትውውቅ ጀምሮ እስካሁን በጣም ብዙ
ፈተናና መከራ አሳልፈዋል ከምንም በላይ ግን ያለፈው ግማሽ
አመትና ይሄ አመት በሳት የተፈተኑበት ወቅት ነው ትምርቷን
አቁማ ከቤት አልወጣም ካለች ይኸው አመት ሊሞላት ነው
ብትወጣ እንኳን አምላኳን ልትለምን ቤተክርስቲያን ብቻ ነው
የጌዲዮ እናትም ገዳም ገብተው ሱባኤ ከጀመሩ ሰንበትበት አሉ
የመቅደስ ቤተሰቦችም የጌዲዮ ጓደኞችም ብቻ የሚያውቁት ሁሉ
በፀሎት አልተለዩትም
ጌዲዮ የመጨረሻውን ቀዶ ጥገና ሊያደርግ ከገባበት ወቅት
አንስቶ አስታማሚው ብሩክ ስለሱ ሁኔታ የሚነግረው አጥቶ
ተስፋ ሲቆርጥ ቤተሰቦቹም እየደወሉ እንዴት ሆነ ሲሉት ስልኩን
ሙሉ ለሙሉ ሲያጠፋ...

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❼ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...


ፍቅር ታጋሽ ነው, ፍቅር ቸር ነው. አይቀናም፣ አይመካም፣ አይታበይም፣ ባለጌ አይደለም፣ የራሱን ጥቅም አይፈልግም፣ አይበሳጭም፣ ቅሬታን አይመዘግብም፣ በፍትሕ መጓደል ደስ አይለውም፣ ግን በእውነት ይደሰታል። ፍቅር ሁሉን ይታገሣል በሁሉ ያምናል ሁሉን ተስፋ ያደርጋል በሁሉ ይጸናል::❤️


❤️‍🩹 ከልብ ያደረጉትን ሰው መሸኘት እንዴት ይከብዳል። ያፈቀሩትን ሰው ሩቅ መስደድ እንዴት ያማል።ከዚህ ሁሉ በኃላ ያሳለፉትን መርሳትስ እንዴት ይቻላል።መቼስ አለማስታወስ፤ትዝ አለማለት፤ከልብ አንቅሎ ማውጣት እየታመሙ ነው እንጂ እየተደሰቱ አይሆን፤እያለቀሱ ነው እንጂ እየተሳሳቁ አይሆን፤ልብ ተሰብሮ ነው እንጂ ተጠግኖ አይሆን።ቢሆን ቢሆንማ፤ቢሳካ ቢሰካማ እንዲሁ እንደዋዛ መርሳቱ ቢኖርማ ሁሉን ረስቶ ነፃ ሆኖ መኖር ይቻል ነበር።

3k 0 11 1 67

💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_❷❻

‍ ​

➜ጌዲዮን ለህክምና ውጪ ከሄደበት ቀን አንስቶ መቅደስ
ሀሳቧን መሰብሰብ ተሳናት ቃሉን ለማክበር ስትል ወደ ግቢ
ብትመለስም ከትምርቷ ይልቅ ሀሳቧ ስለጌዲዮ ሁኔታ ወንድሟ
የሚልክላትን መረጃ ለማወቅ ነበር ጉጉቷ ያው ዶክተሩ እንዳለው
ቀዶ ጥገናው ባንድ ጊዜ የሚከናወን ስላልነበረ ቀዶ ጥገና
አለው ባላት ቁጥር በሀሳብና በጭንቀት ቀድማ የምታልቀው እሷ
ነች........
.....አረ ጌዲዮስ ቢሆን የሞት አፋፍ ላይ ቆሞ ሞትን የሚፈራ
የመጀመሪያው ሰው እኔ ነኝ ብሎ እስኪያስብ ድረስ ሞትን ፈራው
ዳግም የናቱንና የመቅደስን አይኖች አለማየቱን ሲያስብ ሞትን
አብዝቶ እረገመው ከበሽታው በላይ ናፍቆት ጎዳው መለየቱ
ህመም ሆነበት የመቅደስ ፈገግታ ጨዋታዋ ሳቂታነቷ ፍቅሯን
መቋቋም አቃተው በተለይ አብራ የታመመችለት ህመሟ
ከማንም አስበልጣ ተማርኮ የማረከው ፍቅሯ እህህህህ እያረገ
ውስጥ ውስጡን ሌላ በሽታ ሆነበት......... በመመረቂያው
ወቅት ሆስፒታል መተኛቱን እረስቶ መቅደስን አግብቶ ለናቱ
የልጅ ልጅ ማሳየት አማረው ሌላ ተስፋ ምን አልባትም እውን
የማይሆን ህልም...አለቀሰ አብዝቶ አነባ..........
.......ብርሀን ሰአዳ ወይንሸትም ብትሆን መቅደስ እንድትረጋጋ
ዘና እንድትል ብዙ ጥረት እያረጉ ነው ቢሆንም እንዳሰቡት
አልሆነላቸውም ምክንያቱም ከነሱ ጋር ከመሆን ይልቅ በፊት
ጌዲዮ የሚሄድበት የሚያዘወትርበት ስፍራ እየተቀመጠች
ብቸኝነቷን መርጣለች....ከሰው ተራ አውጥቶ ያረገኝ ብቸኛ
አውቃለሁ ፍቅርሽ ነው ይሄ መዘዘኛ ብሎ አይደል የዘፈነው
ጥላሁንስ ቢሆን........
.........የጌዲዮ እናት እነመቅደስ ቤት ትንሽ ከተቀመጡ ቡሀላ
ወዳገርቤት መመለስ እንደሚፈልጉ ለቤተሰቡ ሲናገሩ የመቅደስ
አባት ግራ በመጋባት ምን አጠፋን ሲሉ ጠየቋቸው የጌዲዮ
እናትም አረ ምን ቦጣችሁና የናንተን ውለታ እኮ ነብሴንም
ብሰጥ ከፍዬ አልጨርሰውም ግን ይህን መልካምነታችሁን
እግዚያብሄር ነው በሰማይ የሚከፍላችሁ ሰው የለም ባልኩበት
ወቅት ነው እናንተን አግኝቼ እውነትም የሰው መዳኒቱ ሰው ነው
ያልኩት ስትላቸው ታዲያ ምን አርገን ነው ጌዲዮ ሳይመጣ ልሂድ
የሚሉ ... አዪ እንጃ ብቻ አንድ ያለኝን ያይኔን ማረፊያ ዘሬን
መተኪያዬን ልጄን እንዳላጣው ልቤ ፈራ ታዲያ እዚህ ሆኜ
በሰቀቀን ከማልቅ ከቀያችን አንድ ገዳም አለ እዛው ሄጄ በሱባኤ
ፈጣሪ ጨክኖ እንዳይጨክንብኝ ብለምነው ይሻለኛል ብዬ
ነው..... እንደዛስ ከሆነ መልካም ፈጣሪ ጥሎ አይጥልም
ይለመናል እውነት ብላችኋል የተናቀን ያከብራል የተረሳን
ያስታውሳል አበቃለት የተባለን ታሪክ ይቀይራል አዎድ ይለመናል
........
........እንዳሉትም በንጋታው የጌዲይ እናት ወዳገርቤት ተመለሱ
አመሻሽ ላይ ስለነበር የደረሱት ቤታቸውን አዘገጃጅተው ነገውኑ
ወደገዳም ገብቼ ሱባኤዬን እጀምራለሁ ብለው አሰቡና
ኩርትምትም ብለው ጋደም አሉ የልጃቸው ነገር እያስጨነቃቸው
በሀሳብ ተውጠው በዛው እንቅልፍ ወሰዳቸው ለሊትም በራቸው
በሀይል ተንኳኳ እትዬ አስካል እትዬ አስካል የሚል ድምፅም
ሰሙ በራቸው በመንኳኳቱ ቢደነግጡም የሰሙት ድምፅ የንስሀ
አባታቸው መሆኑን ሲያውቁ ተረጋግተው በሩን ከፈቱ ስኪፍቱት
ግን እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ ብዙ ሽማግሌዎች ጎረቤቶቻቸው
እንዲሁም ለብዙ አመታት የራቋቸው የባለቤታቸውና የራሳቸው
ቤተሰቦቻቸው ደጃቸውን ሞልተውት ነበር የጌዲዮ እናት
በድንጋጤ ደርቀው ቀሩ የልጃቸውን መርዶ ነጋሪዎች መሰሏቸው
አንደበታቸው ተርበተበተ ሰውነታቸው ተንቀጠቀጠ ልባቸው ሄድ
መጣ ይል ጀመር በሚቆራረጥ ድምፃቸውም ልጄ ልጄ ምን ሆነ
አባ ሲሉ የንስሀ አባታቸውን ጠየቁ ነገሩ ግን ካሰቡት ውጪ ነበር
ይሄ ሁሉ ሰው የተሰበሰበው ይቅርታ ለመጠየቅ እንደሆነ ሲረዱ
ነብሳቸው አረፈች ግን ለምን ሲሉም ጠየቁ የልጃቸው
መታመምን ሰምተው እንደሆነም ሲነግሯቸው አለቀሱ በንባቸው
መስታወትም ያሳለፉትን የመከራ ሃያ አመታት ወደኋላ መለስ
ብለው አስታወሱ............
........ጌዲዮን ከልጆቻቸው ጋር አንድም ቀን እንዲጮት
ፈቅደውለት አያውቁም ለግዜር ሰላምታም ቢሆን ይፀየፏቸዋል
በዛላይ አሽሙራቸው መጥፎ ንግግራቸው ከሰው መሀል ሆነው
ሰው የተራቡበትን ጊዜያት ከማህበራዊ ኑሮ ተገለው የኖሩበት
አመታት አረ ስንት መከራ ስንት ስቃይ ግን ይህን ሁሉ ጨክነው
ነበር ጌዲዮን እዚህ ደረጃ ያደረሱት የሳቸው ቅስም እየተሰበረ
የልጃቸውን ሞራል እየጠበቁ ታዲያ ምነው ዛሬ ተስፋቸው ሊሞት
መሆኑን ሲሰሙ ለይቅርታ ሽማግሌ ሰበሰቡ የጌዲዮ እናት
አሻፈረኝ አይሆንም ይቅርታችሁን አልቀበልም አሉ...

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❼ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...


‍ 💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_❷❺

➜ወዲያው ዶክተሮቹ ተሯሩጠው ህክምና አደረጉለት ብዙም
ሳትቆይ መቅደስ መጣች መታመሙን ስታይ ወዲያው ቅዱስ
እንደነገረው ገባትና አንተ ነገርከዋ አለችው ወንድሟ ቅዱስም
መቅዲ ሙች ጠይቆኝ ነው ሲላት አረ ነው እንዴ ድሮም
ጥፋተኛዋ እኔ ነኝ አንተን ሰው ብዬ አምኜህ መሄዴ አሁን ላባ
ሳልናገር ቀጥ ብለህ ውጣ አረ መቅዲ በጥፊ ያላልኩህም
ታላቄ ስለሆንክ ነው ቆይ ቢሞትስ አታስብም እንዴ ስትለው እሺ
ይቅርታ አርጊልኝ ሁለተኛ አይደግመኝም አላት ሁሌ እንዲህ
ትላለህ ግን ሁሌም ታጥቦ ጭቃ ነህ ስትለው እንደምንም
አግባብቷት ይቅርታዋን አገኘ....
......ጌዲዮ ሲነቃ መቅደስ እጆቹን ተንተርሳ ተኝታ ነበር ከዛም
እጁ ሲንቀሳቀስ ነቃች አይኖቿን በንባ ሞልታ ጌዲዬ ደናነህ
ስትለው መቅዲ እሞታለኋ አላት መቅደስ ደንዝዛ ማነው ያለው
ደሞስ ቢሉስ ሰው ፈጣሪ ነው እንዴ አትሞትም ተጋብተን ልጆች
ወልደን አርጅተን ነው የምንሞተው ጌዲዬ ትተኸኝ አትሞትም
ብላ እያለቀስች ፊቱን እየተሽከረከረች ሳመችው ጌዲዮ አለቀሰ
መቅዲ ታቂያለሽ ሁሌ ከንቅልፌ ስነሳ እንደሚጥለኝ
እንደምወድቅ አቃለሁ ግን አንድም ቀን እንኳን እሞታለሁ ብዬ
አስቤ አላውቅም መቅደስ ተስፋዋ ተሟጦ ጮኸችበት ጌዲዮ
አትሞትም አትሞትም ብላ እያለቀስች ትታው ወጣች........
.......ወዲያውም ባስ ይዛ ቀጥታ ጅማ ዩኒቨርስቲ ዋናው
አስተዳዳሪ የዲን ቢሮ ሄደች እንባዋ ያለማቋረጥ ይፈስ ነበር
ሰውነቷ ከስቶ አይኗ ጎርጉዶ ጉንጯ ሟምቶ በተስፋ ማጣት
ተጎሳቁላ ጭራሽ መቅደስ አትመስልም አስተዳዳሪው ደንግጦ
መቅደስ አላት አዎ መቅደስ ነኝ የኔ እንደዚህ መሆን ገረመህ
አዎ ሊገርምህ ይችላል ምክንያቱም አባይን ያላየ ምንጭ
አመሰገነ ጌዲን አላያችሁትማ ካልጋ ተጣብቆ ሞቱን
እየተጠባበቀ ነው አያችሁ የዚህን ዩኒቨርስቲ ስም አራት አመት
ሙሉ አስጠራ ዘንድሮ በመመረቂያው ሲጠፋ ግን ምን ሆኖ ነው
እንኳን አላላችሁትም እሱ ባመጣው ውጤት ለስማችሁ
ለማስጨብጨብ ግን አንደኞች ናችሁ አስተዳዳሪው እንደምንም
አረጋግተዋት ስለተፈጠረው ነገር ለመረዳት ጠየቋት እሷም
ሁኔታውን በሙሉ በዝርዝር ነገረቸው ከዛም የዩኒቨርሲቲው
ኮሚቴዎች ሰብስበው መልስ እንደሚሰጧት ነግረዋት ወጣች
ስትወጣ ወይንሸትና በለጠው አንድላይ እየሄዱ አገኟት
ስለጌዲዮ ሲጠይቋት ሁሉንም ነገረቻቸው ከዛም ተመልሳ አ.አ
መጣች.................
...........ከዛም ጉዋደኞቻቸው እንዳቅማቸው ገንዘብ ማሰባሰብ
ጀመሩ የዩንቨሪስቲው አስተዳዳሪ እንዳሉት ተሰብስበው አንድ
ሀሳብ ላይ በመድረስ ዩኒቨርስቲው ማስታወቂያ ለቀቀ በዚህም
የተነሳ ቤታቸውም ሳይሸጥ ሌላም ከባድ ወጪ ሳያወጡ
የጌዲዮን ሙሉ ህክምና ወጪ የሚችል እስፖንሰር ተገኘ........
......ወዲያውም መቅደስ ጋር ተደውሎ የምስራቹ ተነገራት
ሁሉም ተስፋ በቆረጠበት ሰአት አዲስ ተስፋ በእውነት ደግማ
የተወለደች ያክል ነው የተሰማት ደስታዋንም ለሁሉም አጋርታ
አንድ ላይ ጮቤ እረገጡ ....።
......ዶክተሩም ጋር ሄዳ ገንዘቡ ተገኘ ይድናል አይደል አለችው
መቅደስ ይድናል ብዬ ተስፋ እንጂ እውነታውን ልነግርሽ
አልችልም ምክንያቱም ጌዲዮ የመጨረሻ ከፍተኛውን ቀዶ ጥገና
ነው የሚያደርገው ለዚም ካስር ወር እስከ አንድ አመት
በህክምና ሊቆይ ይችላል አላት የዶክተሩ ንግግር ደስታዋን
ቢያደፈርሰውም ለዚህ ያበቃን ፈጣሪ ነገንም አይጥለንም ብላ
ተስፋዋን ፈጣሪን አደረገች......
አብሮት ለማስታመም ማን መሄድ እንዳለበትም አባቷና እናቷ
ሲጠይቁ መቅደስ እኔ ነኛ አለች ቅዱስ እንዴ አንቺማ አትሄጂም
ልታስታምሚው ነው ወይስ በለቅሶ ልትደፊው መቅደስ ተናዳ አረ
ባክህ ስትለው እህቷም ብሩክም ሁሉም እሷ መሄድ እንደሌለባት
እና የጌዲዮን ቃል ለማክበር መማር እንዳለባት ነገሯት ከዛም
እኔ እኔ በሚል ክርክር ብዙ ከቆዩ ቡሀላ ብሩክ እንዲሄድ ተወስኖ
ፕሮሰሱ ተጀመረላቸው........
........ከዛም የበረራው ቀን እቤት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ሁሉም
ዘመድ ጓደኛ ተሰብስቦ ቤቱ በንባ ታጠበ ጌዲዮ እቤት የመጣው
ባልጋ እየተገፋ ነው ቀና ብሎ እንኳን ቻው ሊላቸው አልቻለም
ነበር መቅደስማ ደግማም የማታየው እየመሰላት ነው በተለይ
ዶክተሩ በቀዶ ጥገና ወቅት ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት
ከባድ ነው ያላት ትዝ ብሏት ለቅሶዋ እርም የምታወጣ ነበር
የሚመስለው...........
............ከዛም ጓደኞቻቸው ያሰባሰቡትን ገንዘብ አስረከቡት
ብቻ ሁሉም የበኩላቸውን እያበረከቱ ሰላም እንዲመለስ
መልካም ምኞት ተመኙለት መቅደስ ግን እንደሌሎቹ ጥቅማ
ጥቅም ሳይሆን በጀሪካን ፀበልና እምነት አርጋ ለወንድሟ አደራ
ሰጠችው.....ኤርፖርትም ስትሸኘው ያንገቷን ማህተብ አውልቃ
ሂወቴ ያላንተ ባዶ ናት እኔ የምኖረው አንተ ስትኖርልኝ ነው
ተመልሰህ ከመጣህ ይህን ማህተብ ታስርልኛለህ ያለበለዚያ
ግን እኔም ተከትዬህ በሰማይ እምነቴን ማህተቤን
ትመልስልኛለህ ብላ ባንገቱ ላይ አሰረችለት ይህን ስትለው
ጌዲዮ ከተወለደ እንደዚህ ቀን አምርሮአልቅሶ አያውቅም አለቀሰ
እጇን እንደምንም ጨብጦ አደራ እግዚያብሄር ያረገውን
ቢያረገኝም እንዳትሸነፊ ነገ አዲስ ቀን ነው ትምርትሽንም አደራ
ተምረሽ የኔን ህልም አንቺ አሳኪልኝ አላት እንኳን እናቱ እንኳን
ቤተሰቦቿ በኤርፖርቱ ዙሪያ ያሉ ሰዎች ሁሉም በንባ ታጠቡ
ወንድሟም እያለቀሰ ሁሌም በዋታሳፕ በቫይበር ሁሌም
እንደሚገናኙ ቃል ገብቶላቸው በለቅሶ ተሰናበቱት........
እውነት ጌዲዮ ድኖ ይመጣ ይሆን????........

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❻ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...


አንዳንድ ሰዎች ከላይ ሲታዩ እኛን ለመርዳት እየሞከሩ ይመስላል። እውነታ ግን ውድቀታችንን ነው የሚጠብቁት።


አነሆ ከለሊቱ 7:00 ሆኗል እስከአሁን ያልተኛችሁ አንድ ጊዜ 🤝 ይቺን ጠቅ እናደርጋለን !!

3.9k 0 16 20 148

💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_❷❹

➜እየውላቹ ይህ ዜና ለናንተ ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ ግን ግዴታ መናገር ስላለብኝ ስሙኝ ጌዲዮ የጭንቅላት እጢ ታማሚ ነው መቅደስ አፏን ይዛ እየተንቀጠቀጠች ምን አለች አዎ ህክምናውን በጊዜ ጀምሮ መዳኒት ስላልወሰደም በሂወት የመኖር ጊዜውን አጥቦታል መቅደስም ሆነች አባቷ እንባቸው ድንገት እንደሚጥል በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ዱብ ዱብ ይል ጀመር መቅደስ በልህ ድምጿን ከፍ አድርጋ እና ይሞታል ልትለኝ ነው አለችው ዶክተሩም አላልኩም የምትችሉት ከሆነ አንድ እድል አላችሁ አላቸው አባቷ እንደምንም አረጋግቷት ምንድነው ንገረን ብቻ ጌዲዮ ይዳን እንጂ የሆነውን ይሁን ለመፈፀም ዝግጁ ነን አሉ ባስቸኳይ ቀዶ ጥገና መደረግ አለበት መቅደስ አይሆንም ብላ ይበልጥ ጮኸች ችግሯ ህመሟ ቢገባውም መረጋጋት ባለመቻሏ ዶክተሩ ተናደደ መቅደስ አዳምጪኝ ቀዶ ጥገናው እዚህ ሀገር አይሰጥም ይህ ማለት በዚህ አራት ወር ውስጥ ካገር ወጥቶ ቀዶ ጥገናውን ካላደረገ በሂወት መኖሩ አስጊ ነው ለህክምናው ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ብሎ ሃሳቡን በቁጣ ገልፆ ቁና ተንፍሶ ላንዴ ዝም አለ መቅደስና አባቷም በህልማቸው እስኪመስላቸው ደርቀው ቀሩ ምንም ሳይናገሩም ቢሮውን ለቀው ወጡ..........

......ከወጡ ቡሀላ መቅደስ ተዝለፍልፋ ወደቀች ነርሶችም ተሯሩጠው አንስተው አስተኟት ስትነቃም ሁሉም ቤተሰቦቿ ተሰብስበው ነበር አባቷ ነግሯቸው ስለነበር ሁሉም አይናቸው በንባ ብዛት በርበሬ መስሎ ነበር እማ ሁለት ሚሊዮን ያስፈልጋል አሉ እኮ አለቻት የቤተሰቦቿን አይን አይን እያየች እህቷም እሷን ለማፅናናት ያንቺ እንዲህ መሆን እኮ ብር አይሆንም ይልቅ ብሩን እንዴት ማግኘት እንዳለብን ብናስብ ነው የሚሻለው ስትል እንዴ ከየት ነው የሚመጣው አለች መቅደስ ቀጥሎም ቅብጥብጡ ወንድሟ ሲስቱ ተነካሽ እንዴ ሁለት መቶ ሺ ማግኘት ከባድ በሆነበት ሀገር እንዴት ብለሽ ነው ሳይጨርሰው የሁላቸውም ታላቅ የሆነው በረከት ከየትም ብለን አግኝተን መታከም አለበት እናትየዋም አዎ ቤታችንንም ቢሆን ሸጠን እናሳክመዋለን ማሟያ ደግሞ ሁላችንም አካውንት ያለውን ብር እናወጣለን ካልሞላም ብድር አናጣም የሚል ተስፋ ለመቅደስ ሰተዋት ከዛን ቀን ጀምሮ በየፊናቸው ብሩን ማፈላለግ ጀመሩ ብዙ ወጪ ስላወጡ የሁሉም አካውንት ውስጥ የተገኘው ብር ስድስት መቶ ሺ ብቻ ነበር ቤቱም ያሰቡትን ብር ሊያወጣ አልቻለም........

.........ሌላ ህመም እንዳይሆንበት ስለፈሩ ነገሩን ለጌዲዮ እስካሁን አልነገሩትም እናቱ ግን ቢሰሙም ደጀ ሰላም እየሄዱ ደጅ ከመፅናት ፈጣሪን ከመለመን ውጭ ምንም ማድረግ አልቻሉም ዘወትር የመቅደስን ቤተሰቦች ሲያዩ እንዲህም አለ ወይ ይላሉ ጌዲዮንን ለማሳደግ ያዩትን መከራ እሳቸውና ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው እንኳን የባለቤታቸው ዘመዶች የገዛ ቤተሰቦቻቸውም ሰላምታ ሰተዋቸው እንኳን አያውቁም የጌዲዮ እናት ያለፉትን አመታት ሲያስታውሱ ደም እንባ ያለቅሳሉ ቢሆንም ፈጣሪ እንደሰው አይደለም ይኸው እነመቅደስን ሰጣቸው እውነት በዚህ ሰአት ብቸኛ ቢሆኑ ኖሮ ጌዲዮ ነብሱ ባልተረፈች ነበር ግን ሳይደግስ አይጣላም ይባል የለ..........

.......ግን ምንም እንዳሰቡት ገንዘቡን ማግኘት አልቻሉም ቤቱንም የሚገዛ አጡ ቢያገኙም የሚጠሩላቸው ዋጋ ለቤቱም ለህክምናውም አይመጥንም በቲቪና በራዲዮንም ማስታወቂያ ሊያሰሩ ቢጠይቁም የጠየቋቸው ገንዘብ ከባድ ነበር በዛላይ ዶክተሩ ያለው ግዜ አጭር ስለሆነ በፍጥነት ፕሮሰስ መጀመር እንዳለበት እየነገራቸው ነው አሁንማ ሁሉም ተስፋ ቆርጠው የሚገቡበት ጠፍቷቸው ወደፈጣሪ እግዚኦ እያሉ ነው........

.........ሁኔታቸው ግራ ያጋባው ጌዲዮ ቅብጥብጡን ቅዱስ ብቻውን ሲያገኘው ቅዱሴ አለው ወዬ ጌዲ አለው የህክምናውን ውጤት ንገሩኝ ስላቸው ደና ነው አሉኝ ደና ከሆንኩ ለምን አልወጣም ስላቸው አይ ትወጣለህ ይሉኛል ሰሞኑን ደግሞ ሁላችሁም ተረብሻችኋል ምን ሆናችሁ ነው በጭንቀት ማለቄ እኮ ነው ሲለው ያው ቅዱስ እስካሁንም ያላወራው አፉን ይዘውት እንጂ ወሬ የሚባል አይደብቅም እናም ምን ባክህ የጭንቅላት እጢ አለበት ውጪ ሄዶ መታከም አለበት ለዛ ደግሞ ሁለት ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ብለውን ተፍ ተፍ እያልን ነው ብሎ ካልታከመ መሞቱ እንደማይቀርም ፍርጥርጥ አርጎ ነገረው ጌዲዮ ተስፋ ቆርጦ እና እሞታለሁ አለው አረ ላሽ ትታከማለህ ደሞ ቤታችን ሊሸጥ እየተስማማ ስለሆነ እግዚያብሄር ከረዳን ብሩ ይገኛል ጌዲዮ ከመቅፅበት ህመሙ ተነሳበት...

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❺ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...

4k 0 10 6 88

°° አንድ መተማመኛ!

ፈጣሪ ባይረዳህ ፅናትና ትዕግስቱን ባይሰጥህ የማታልፋቸው ከባድ ጊዜያት ነበሩ፤ አስተውል ከዚህ በኋላ ለሚገጥሙህ ከባድ ፈተናዎች ሁሉ ልብህ ላይ አንድ ትልቅ መተማመኛ አለህ!

ዝቅ ያልክ ሲመስልህ ከፍ የሚያደርግህ፤ ብታጎነብስም ቀና አርጎ በናቁህ ፊት የሚያከብርህ ታላቁ ፈጣሪ አለህና በታላቅ ድምፅ ተመስገን በል!

4.2k 0 16 12 83

💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_❷❸


➜ጌዲ መታመሙን ተረድተው አጥብቀው
ሲለምኑ ግድ ሆነባቸውና ዛሬ እውነቱን ተናገሩ አይ እናት በሞት መሀል ሆነው ነው አ.አ የደረሱት ያው እነ ብርሀን በለጠው ወይና ሰአዳ እንዱሁም ሌሎቹም መቅደስ ስትቀር ነገ ፈተና ስላለ ተመልሰው ጅማ ሄደዋል መቅደስንም ቢሆን ቤተሰቦቿ እንዲሁም የጌዲ እናት ሄዳ ፈተናዋን እንድትፈተን እየለመኗት ነው እሷ ግን ካልነቃ አልሄድም አለቻቸው የጌዲዮ እናት ለቅሷቸው መራራ ነው የመንገዱ ድካም ሳይሰማቸው ሰውነታቸው መዛሉ ሳይሰማቸው ልጃቸው እግር ላይ ተደፍተው አሁንም መራራ እንባ እያነቡ ነው መቅደስማ እንባዋ አልቆ ፈዛለች
ቡሀላም እንደምንም ለምነው የመቅደስ ቤተሰቦች የጌዲዮንን እናት ይዘው እቤት ሄዱ መቅደስ አሁንም አልጋው ላይ በግንባሯ ተደፍታ እያንቀላፋች ነው የሆነ ሰአት ላይ የጌዲዮን ጣቶች ሲንቀሳቀሱ ተሰማትና ከህልሟ እንደነቃች ሆና ባተተች ስታየው አይኖቹ ግራና ቀኝ እያዩ ነው ደስታዋ አንቋት ላንዴ ጮኸች ተጣድፋ ሄዳ ግንባሩን ደጋግማ ሳመችው ከዛም ጌዲዬ ነገ እኮ ፈተና ነው አብረን እኔዳለን አይደል አለችው መንቃቱን ከነርስ የሰሙት ዶክተሮች እየተሯሯጡ መጡ ወዲያው መቅደስ አያችሁ አይደል
.......መቅደስና ጌዲዮን በብዙ ፈተና ሶስት አመት በፍቅር አሳልፈው አራተኛው አመት ግን አስጊ ሆኗል ጌዲዮን የጓጓለትን ያምስተኛ አመት ትምህርቱን መጨረስ አልቻለም ዋና የሚባለውም ፈተና አምልጦታል ከሆስፒታ ወጥቶ እንዲፈተን መቅደስ ዶክተሩን ብትለምነውም ለሂወቱ አስጊ ስለሆነ እንደማይወጣ ነግሯት እሷም አልፈተንም ብትልም ጌዲዮን በፍቅሩ ለምኗት ፈተናዋን ለመፈተን ጅማ ተመልሳ ዛሬ ወደ አ.አ መጥታለች ሙሉ የህክምናውን ወጪ ችለው እያስታመሙት ያሉት የመቅደስ ቤተሰቦች ናቸው እናቱም ከክፍለ ሀገር መጥተው አብረውት ነው ያሉት ጌዲዮን ከራሱ በላይ የናቱን ህልም አለማሳካቱ ተስፋ አስቆርጦታል መቅደስም በሱ መታመም ሌት ተቀን እያለቀሰች በድን ብትሆንም ዛሬም ትምህርቱን ቀጥሎ እንደሚመረቅ ተስፋ ትሰጠዋለች.......

......ዛሬ ውጤትህ ይመጣል ስለዚህ ለዩኒቨርስቲው አሳውቀን ብትዘገይም ትፈተናለህ እሪሰርችህንም ቢሆን ትጨርሰዋለህ አለችው መቅደስ የፍርሀትና የደስታ ስሜት እየታየባት የጌዲዮ እናትም እንዳፍሽ ያርገው አሏት የሱዋም አባት እንደዛው ጌዲዮን ግን ውስጡ ጤነኝነት እየተሰማው ስላልሆነ የሚመጣው ውጤት ጥሩ ይሆናል ብሎ መገመት ተስኖታል ብቻ ባጠቃላይ አፋቸው መልካም ቢናገርም ውስጣቸው ፈርቷል ሰአቱ ሲደርስም መቅደስና አባቷ ውጤቱን ለመስማት የዶክተሩ ቢሮ ሄዱ እንዲቀመጡም ከጋበዛቸው ቡሀላ ዶክተሩ ከምን መጀመር እንዳለበት ግራ ገብቶት አይን አይናቸውን ያያቸው ጀመር ውስጣቸው ይበልጥ ተረበሸ ዶክተር ችግር አለ እንዴ አሉት...

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❹ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...

4.5k 0 14 11 106

‍ ​​
‍ ​
💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_

‍➜ከዛም ጌዲዬ ጊዜ ፊልም ቢሆን አሳልፌ የምርቃቴ ቀን ላይ አርጌው ነበር ብላ ጎንበስ ብላ በስስት ከንፈሩን ሳመችው ደሞኮ ጌዲ የምርቃትህ ቀን መጀመሪያ እኛ ቤት ነው የምንሄደው አለችው ለምን አላት እንዴ እማዬ እኮ እደግሳለሁ ብላለች ከዛም የማዬ ግብዣ እንዳለቀ ብሩክ(ታላቅ ወንድሟ) ይዞን ቀጥታ እናንተ ቤት አለችው ጌዲዮ ደስታው ተደማምሮ እቅፍ አረጋት
ከዛም ቀጥታ ግቢ ሄዱ እንደገቡም ትንሽ እንደተራመዱ ጌዲዮ አካባቢው ሁሉ ጨለመበት መቅደስን ጥብቅ አርጎ ያዛትና መቅዲ እራሴን አላት እሷም ደንግጣ ምን ሆንክብኝ አለችው እኔንጃ እራሴን መቅዲዬ ያዢኝ ሁሉም ጨለመብኝ አላት መቅደስ ላንዴ አይኗ በንባ ተሞላ እኔን ምንም አትሆንም ፀሀዩ ይሆናል አለችው ከዛም እንደምንም ብላ ወደጥግ አስቀመጠችውና ክብሪት ልትፈልግ ተነስታ ልትሄድ እጇን ከጁ ልታስለቅቅ ስትል መቅዲ የትም አትሂጂ ደግፊኝ እራሴ ሊፈርስ ነው ብሎ በፍርሀት አጥብቆ ያዛት ምንም ጌዲዮ ሁሌ ቢወድቅም እንዲህ ብሏት ግን አያውቅም አቅፋው ስቅስቅ ብላ ማልቀስ ጀመረች ከደቂቃዎች በፊት የነበረው ሳቅና ደስታቸው ላንዴ በሀዘን ተቀየረ ጌዲዮ እንደምንም ፊቷን ፈልጎ እንባዋን እየጠረገላት መቅዲዬ ጠንካራ ሁኚ እኔኮ ሁሉም ጨለመብኝ አላት የሱም እንባ እየወረደ መቅደስ ላንዴ በለቅሶ ሲቃ ሲጥ አለች ወዲያው የግቢው ሰው ሁሉ ግልብጥ ብሎ ተሰበሰበ ጌዲዮም ወዲያው እራሱን ሳተ የሷም ሆነ የሱ ጓደኞች እያለቀሱ ነበር አብዛኞቹ ግን እንዳለፈው አወዳደቁ የወደቀ መስሏቸው ይነቃል እያሉ ነበር ቢሆንም ለተከቴይ ሶስት ሰአት ቢጠብቁትም ሊነቃ አልቻለም መቅደስ ለሁለት ተይዛለች ብቻ እየቀለደብኝ ነው ውሸቱን ነው ንቃ በሉት ትላለች እሱ ግን ቀልዱን አልነበረም በመጨረሻም አንቡላንስ መጥቶ ይዞት ሄደ አንቡላንሱ እያበረረ ጅማ ጠቅላላ ሆስፒታል አደረሳቸው ወዲያው ዶክተሮቹ ተባብረው ድንገተኛ ክፍል አስገቡት አብረውት የመጡት መቅደስ ሰአዳና በለጠው ብቻ ነበሩ ለነገሩ መቅደስ አለች አትባልም እሷም ለህክምና አልጋ መያዝ እንጂ የቀራት ደንዝዛለች ብቻ በር ላይ አንዴ ቁጭ አንዴ ብድግ እያለች ነው ሌሎቹም ጓደኞቻቸው ተከታትለው እየሮጡ ሴክሬተሪዋን ጠይቀው ያሉበት ክፍል እየሮጡ ደረሱ እንደደረሱም እንዴት ነው አሁን አሏቸው በለጠውም ዶክተሮቹ ገና አልወጡም አላቸው ከዛ ሁሉም በጭንቀት ተከበው መጠበቅ ጀመሩ.......

....ከዛም ቢያንስ ካንድ ሰአት ቆይታ ቡሀላ ዶክተሮቹ ወጡ እንደወጡም ሁሉም ተሯሩጠው ከበቡዋቸው ዶክተር እንዴት ነው አሉ አንዱ ዶክተር ሲቀር ሌሎቹ ፊታቸው ሳይፈታ ጥለዋቸው ሄዱ ሁሉም ፈሩ መቅደስማ አንድኛዋን ተዝለፈለፈች ዶክተሩ ቁና ተነፈሰና ሊያወራ ሲል መቅደስ ዶክተር በፈጠረህ ክፉውን እንዳትነግረኝ ሞተ እንዳትለኝ ስትለው ወይንሸት አረ መቅደስ ሶስት ጊዜ አማትቢ አለቻት ዶክተሩም እ.እ መኖሩን አለ እኛም የተቻለንን እርዳታ አርገንለታል ግን አሁንም ሁሉም ግን ምን አሉት አልነቃም የሚያስፈልገውን ህክምና ሰተነዋል ተራ በተራ እየገባችሁ ማየት ትችላላችሁ ከሁለት ሰው በላይ ግን ውስጥ መቀመጥ አይቻልም ሌላው ከታማሚው ጋር ቀረቤታ ያላችሁ ክፍል ቁጥር 24 ቢሮ መታችሁ አናግሩኝ ብሏቸው ሄደ
.መቅደስ ቀድማ ገባች ስታየው ይባስ ሲጥ እስክትል ድረስ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ጌዲዮ ከወገቡ በላይ ብዙ ገመዶች ተጠላልፈውበታል አፍና አፍንጫውም በኦክሲጅን መስጫ ታፍነዋል እጆቹም ተዘርግተው አይንቀሳቀሱም ሳቁ ጠፍቶ ከንፈሮቹ ተከድነዋን የሚያምሩት መቅደስን አይተው የማይጠግቡት አይኖቹም ተከድነዋል እጁን ጭምቅ አርጋ ይዛ እየሳመችው ጌዲዬ ፈተና እኮ አላለቀም ደሞስ ላይብረሪ እንገባለን ተባብለን አልነበር ለምን አትነሳነሳም እንሂዳ ጌዲ የው ውሸት አያምርብህም በኔ አትጨክንማ ተው ተነስ እያለች ለማይሰማት ጌዲ ብዙ አወራችው መቆየቷን የተረዱት ጓደኞቻቸው እዛው እያለች እየገቡ ጌዲዮን እግዚያብሄር ይማርህ እያሉ እሷንም እያፅናኑ ወተው ደጅ ላይ ተቀመጡ ከዛም በለጠውና መቅደስ ዶክተሩ ቢሮ ሄዱ..ሲገቡም እንዲቀመጡ ጋበዛቸው ከዛም በለጠው ዶክተር ችግር አለ እንዴ ብሎ ጠየቀው ዶክተሩም እየውላችሁ አሁን እንዲህ ነው ብሎ መናገር ይከብደኛል ምክንያቱም ሙሉ ምርመራ መደረግ አለበት ላሁን ግን ጥያቄዎችን ልጠይቃችሁ ታማሚው ከዚህ በፊት እራሱን ይስት ነበር??...አዎ ግን እንደዛሬው ሆኖ አያውቅም ህክምናስ ተደርጎለት ያውቃል?? መቅደስ ይህን ጥያቄ ለመመለስ አንደበቷን ፈታች ስንቴ እንደለመንኩት እኮ ይኸው ይሄ ቀን እንዳይመጣ ፈርቼ ነበር ብላ ለቅሶዋን ቀጠለች በለጠው ደግፏት ነበረ ስታለቅስ ግን አቅፎ አባበላት ዶክተሩም ቀጠለ እሺ ያለፈው አልፏል አሁን ማሰብ ያለብን ስለወደፊቱ ነው እናም ለካርድ ላልጋ እንዲሁም ለግዜው ህክምና የሚውል 7ሺ ብር ማስያዝ ይጠበቅባችኋል አላቸው ከዛም እንደወጡ በለጠው....መቅዲ እጄ ላይ ምንም ሳንቲም የለም ምን ይሻላል አላት አታስብ እቤት እደውላለሁ ብላ አባቷ ጋር ደወለች
ሄ..ሎ..ሄ...ሎ አባ ወዬ መቅዲ ደና አደለሽም እንዴ አዎ አባ ጌዲን አሞት ሆስፒታል ነን ይሄን ያክል አዎ አምስት ሰአት ሊሞላው ነው እራሱን ከሳተ ግን አልነቃም አለችው አሁንም እያለቀሰች ነው አባቷም እራሱን ይዞ በቃ አይዞሽ ምንም አይሆንም አሁን ይነቃል ደሞ ሁላችንም ስራ ነን እህትሽ ግን እረፍት ላይ ስለሆነች አሁን እልካታለሁ እሺ እሺ አባ ብትችል
ግን አሁን 7ሺ ላክልኝ አረ እልክልሻለሁ ምንም ችግር የለም ብቻ አንቺ እራስሽን አረጋጊ እሺ አባ አመሰግናለሁ..ጌዲዮ ይነቃል እየተባለ ሲጠበቅ ሳምንት ሞላው የጅማ ጠቅሌ ሆስፒታል ዶክተሮችም የጌዲዮ ነገር ካቅማቸው በላይ ስለሆነባቸው ወደ አ.አ ተክለ ሀይማኖት አጠቃላይ ሆስፒታል ሪፈር ተፃፈለትና ከጅማ ተነስተው አ.አ ገቡ እስካሁን ያልተነገራቸው የጌዲዮ እናትም በጣም እየደወሉ ልጄስ እያሉ ሲጠይቁ በብዙ ምክንያት መታመሙን ቢደብቋቸውም የወለደ አንጀት ነውና...

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❸ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...

4.9k 0 17 24 123

‍ ​ 
💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_❷❶
‍ ​

➜የመቅደስ ድንጋጤ አንደበቷን አሰረው ሰውነቷን አደነዘዘው የምትሆነው ግራ ገባት ብቻ ደጋግማ ጌዲ ጌዲ ትላለች ጌዲዮ ግን አውቆ ስለነበር መጨረሻ ላይ በሳቅ ተንፈራፈረ ወይኔ መቅዲ ብሞትም አትጮሂም ማለት ነው እያለ የማያቋርጠውን ሳቁን ይስቅ ጀመር....በድንጋጤ ብቻ ቢሞት መቅደስ ሞታ ነበር ሞቶ መመለስም እንዲህ ከሆነ መቅደስ ግማሽ መንገድ ሄዳ ነው የመጣችው...እንደምንም እራሷን አረጋግታ እውን ቀልድ መሆኑ ሲገባት ንዴት ፊቷን በርበሬ አለበሰው...እሱ ግን አሁንም ይስቅ ነበር ቀልደህ ልብህ ወልቋል አለችው ጌዲም እየሳቀ እንዲህ ልበቢስ መሆንሽን ባቅ ኖሮኮ እንዲህ አይነት ቀልድ አልቀልድም ነበር ሲላት መቅደስ ቦርሳዋን አንስታ ያዘዘችውም ቁርስ ሳይመጣ ጥላው ወጣች እሱም አረ ቁርሱ ቢቀር ልልበስና አብረን እኔዳለን አላት እሷ ግን እንዳልሰማች ሆና ከንዴቷ ብዛት መሬቱን አጥብቃ እየረገጠች ጥላው ሄደች።..ከዛም ቡሀላ ደጋግሞ ብዙ ጊዜ ቢደውልላትም ልታናግረው ፍቃደኛ አልሆነችም በመጨረሻም እንደተቀየመችውና እንደማታነሳው ሲገባው ወይንሸት ጋር ደወለ ወይናም ገና ከማንሳቷ አንተ ልጅቱን ምን አርገሀት ነው እንዲህ አደንዝዘህ የላካት ነው ወይስ ድንግልናዋን ዛሬ ነው የወሰድከው ብላ እየሳቀች ጠየቀችው ጌድዮም ባማረው ሳቁ አጅቦ እሱንማ እኮ ቆየሁ ከተረከብኩት ባይሆን ትዝታው ይሆናል አላት ወይናም ሳቁን ተቀብላ እየሳቀች ትዝታ እንዲህ ቢያረግማ እኔ በሽተኛ እሆን ነበር አለችው እሱም ወይናዬ ባክሽ በሆነ ነገር አስቀይሚያት እኮ ነው ስልኳንም አላነሳም አለችኝ በማሪያም አገናኚኝ አላት እሷም ውይ ጌዲዬ ገና ስወጣ ነው የደወልክልኝ አሁን ደግሞ ላይብረሪ ልገባ ነው ባይሆን ብርሀንና ሰአዳ ዶርም ስላሉ አንድኛቸው ጋር ደውል አለችው

እሱም መልሶ ሰአዳ ጋር ደወለና እንድታገናኘው ጠየቃት መቅደስ ግን አላናግረውም ስትል ብርሀን ለመነቻትና እሺ አለች ስልኩንም ተቀብላ ምን ፈለክ አለችው ጌዲም መቅዲ እግዚያብሄርን እንዲህ ያስከፋሻል አላልኩም ይቅርታ አርጊልኝ አላት ብዙም ካባበላት ቡሀላ ይቅርታ አረገችለትና ሁሌ የሚገናኙበት መናፈሻ እንደሚጠብቃት ነገራት.....
የሚገርም ነው ጌዲዮና መቅደስ ፍቅረኛሞች ከሆኑ በኋላ ብዙ ሴቶች ጌዲዮን ለፍቅር ጠይቀውታል በተለይ አደራ የተባለችው የክፍሉ ተማሪ ተፈታትናዋለች ይኸው ዛሬም ሆን ብላ መቅደስን እየጠበቀ የተቀመጠበት መናፈሻ ድረስ ሄዳ አጠገቡ ተቀመጠች ብዙ ብሏት እንቢ ስላለችው ዞርበይም አላላትም ዝም ብሏት ተቀመጠ እሷም ጌዲ ሰላም ነው አለችው እሱም እግዚያብሄር ይመስገን አላት ይቅርታ መቅደስን እየጠበክ እንደሆነ አውቃለሁ ግን በጣም ስለናፈከኝ ነው የመጣሁት አለች ጌዲዮም በግርምት ፈገግ ብሎ እኔ ናፍቄሽ አላት እሷም አዎ ብላ ተጠግታ እጁን ያዘችው መቅደስ ፊትለፊት አየቻቸው እንዳየቻቸውም ቆመች
ጌዲዮም ቀስ ብሎ እራሱን ያዘ ከዛም ሰውነቱን አንቀጠቀጠው በተቀመጠበት ወድቆ ሲንፈራፈር አደራ ሰቀጠጣት እንኳን ልታነሳው የጨበጡት እጆቿን ተፀይፋ እየጠራረገች ጥላው እየበረረች ሄደች መቅደስ ግን ከመቅፅበት እየሮጠች አጠገቡ ደርሳ ስታቅፈው እየሳቀ ነቃና ወይ የዘንድሮ ፍቅር አለ መቅደስ በድጋሚ ተናደደች ምን ለማለት ነው አለችው እሱ እንዴ እሰቢው ጤነኛ እያለሁ አፈቀርኩክ ናፈከኝ አበድኩልህ ስትል የነበረችው ልጅ ታምሜ ስወድቅ ግን ተፀይፋ ጥላኝ ሄደች ታዲያ ይሄ ፍቅር ነው መቅዲዬ ካፈቀሩ አይቀር እኮ ልክ እንዳንቺ ነው ከነ ሙሉ ማንነት የኔ እናት አንቺኮ ትለያለሽ እኔ ማለት እኮ..... በጆቹ ጉንጮቿን ጨብጦ አይን አይኗን እያየ ቀጠለ....ከድለኞች መሀል አንዱ ነኝ አንቺን የሰጠኝን ፈጣሪ በምን ቃል እንደማመሰግነው አላውቅም ብሎ ጥብቅ አርጎ ግንባሯን ስሞ አቀፋት.....መቅደስም
ጌዲዬ እኔም እኮ ያንተ በመሆኔ እድለኛ ነኝ ደግሞ ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ አትቀልድ እኔኮ ህመምክ ያስፈራኛል አለችው እሱም ድጋሚ እንዲህ አይነት ቀልድ እንደማይቀልድ በፈጣሪ ስም ምሎ ቃል ገባላት ....እንዲህ እንዲህ እያሉ ደሞ ሌላ ወራቶች አሳለፉ

ፈተና እየተፈተኑ ስለነበር አሁን በብዛት ጥናት ላይ ናቸው ሰሞኑን ግን ጌዲዮ በጣም እያመመው ነው ቢሆንም ጌዲዮ ህልሙን ለማሳካት ጠንክሮ እየተማረ ነው ዛሬ ደግሞ ከመቅደስ ጋር አብረው ሁሌ የሚያጠኑበት ጫካ ሄደው እያጠኑ ነው ጥናታቸውንም እንደጨረሱ ጌዲዮ የመቅደስ እግር ላይ ተኝቶ እንደለመደው አይናይኗን እያየ ምን እንደናፈቀኝ ታውቂያለሽ አላት እሷም ምንድነው አለችው የምመረቅበት ቀን አላት ውይ አሁንማኮ ጨረስክ ግማሽ አመት እኮ ነው የቀረህ ግን ለምን ጓጓህ ጌድዬ አለችው እንዴ መቅዲ የማዬን ደስታ ለማየት ነዋ የኔን አለም የምታሳየኝ ተምረህ ተመርቀህ ነው ትለኝ ነበር ታዲያ አለሟን ለማሳየት ለምን አልጓጓም አላት መቅደስም ፈገግ ብላ እሱማ መመረቅክ የኔም አለም እኮ ነው ስትለው ግን ምንድነው ስጦታዬ አላት እሷም ያገር ቀይ አበባ ተሸክሜ እሰጥሀለሁ አለችው በቃ አላት እህ ብችልማ ቀይ ምንጣፍም ባስነጥፍልህ ደስ ይለኛል አለችው ጌዲዮም ስቆ ሀሳብሽም በቂዬ ነው የኔ እናት ደግሞ የዛሬ አመት አንቺ ስትመረቂ እኔም በተራዬ በዛ ሁሉ ህዝብ ፊት ተንበርክኬ የኔ እመቤት አግቢኝና የፍቅርሽ ታዛዥ ባሪያሽ ሆኜ እድሜ ዘመኔን ልገዛልሽ እልሻለሁ

አላት...መቅደስ ዛሬ ላይ ሆና የቀጣዩን አመት ምርቃቷን ቀን በምትወድደውና በምታፈቅረው የጌዲዮ የጋብቻ ጥያቄ አጣምራ ደስታዋን በህሊናዋ ሳለችው...

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❷ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...


~ ጠር"ጥር ~
የሆነ ግዜ እንዲህ ሆነ
ባል ስራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ በጣም የሚወዳት ሚስቱ በምሬት እያለቀሰች ያገኛታል።
ይሄኔ ይደነግጥና ለምን እንደ ምታለቅስ ይጠይቃታል።
እሷም እንዲህ ስትል መለሰችለት።
"" እኔ ማንም ከማይደርስበት ወፍ እንኳ ዝር ከማይልበት
ከቤታችን ጓሮ ተተግኜ ልብሴን ሁሉ አወላልቄ
መለመላዬን ሆኜ ገላዬን እየታጠብኩኝ ሳለ
"እዚህ ዛፍ ላይ ያለው አሞራ ሀፍረተ ስጋዬን ሲያየኝ ጊዜ
እኔም አንተ ውዱ ባሌን የከዳሁህ ያክል ወንጅል ሆኖ ስለተሰማኝ ቆጭቶኝ ነው የማለቅሰው..."
ስትል ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች መለሰችለት።
፦፦፦ይሄኔ የዋሁ ባል በዚህ ቁጥብነቷ ተደስቶ
"ተመስገን አምላኬ ምን አይነት መላክ ሚስትን ሰጠኽኝ ብሎ እቅፍ አደረጋትና ግንባሯን ሳማት። ወዲያውም መፍለጫ ይዞ ወጣ'ና አሞራው ሚያርፍበትን ዛፍ እንዳልነበረ አድርጎ ቆረጠው።
👉በሌላ ግዜ እንደ ተለመደው ከዕለታት አንድ ቀን ባል ስራ በግዜ ጨርሶ ባልተለመደ ሰአት ቤት ከች ሲል
.ያችን ቁጥቧን፣ያችን አሞራ አየኝ ብላ ቂያማ ምታስነሳውን ሚስቱን ከውሽማዋ ጋር ተኝታ ያገኛታል።
አንዳች አልተነፈሰም ምንም አላደረገም ማቄን ጨርቄንም ሳይል ትቶ ወጣ እና ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ።
👉በመንገዱ ላይ የሆነ ከተማ ሲገባ በጣም ብዙ ሰዎች ቤተ መንግስት በር ላይ ተሰብስበው ያገኛቸው'ና ለምን እንደ ተሰበሰቡ ይጠይቃል። ሰዎቹም"የንጉሱ ወርቅ ማስቀመጫ ተዘርፎ ነው" ሲሉ ይመልሱለታል።
በዚህ ሁኔታ የሆነ ሰውዬ ጤነኛ ሆኖ በእንብርክኩ ሲንፏቀቅ ያየው'ና.."ይህ ሰው ለምን ቆሞ አይራመድም?" ሲል ጠየቀ።እነሱም "አይ ይህማ የከተማችን ትልቁ ነብይ
ለፈጣሪ ልበ ቀናኢ ቅዱስ ፃድቅም ሰው ነው ! ..
በእግሩ ማይራመደው ምክንያት ምናልባት ሳያውቅ በእግሩ ጉንዳን እንዳይገድል ሰግቶ ነው"
ብለው ይመልሱልታል። አአአዎ በቃ እዝች'ጋ ተነቃቁ.....
ሰውየው "በጩኸት መናገር ጀመረ ሌባውን አገኘውት
....እመኑኝ ሌባውን እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው"ብሎ ጮኸ።
ንጉሱም ጋር በፍጥበት ተጠርቶ ገባ'ና ተጠየቀ
"ያኛው ትል እንዳይገድል ፈርቶ በንብርክክ የሚሄደው ፃድቅ የመሰላችሁ ሰው ነው ንብረትህን የሰረቀህ ከፈለግክ አስፈትሸው'ና ውሸቴን ከሆነ አንገቴን ቁረጠው...." አለ። ወታደሮችም በንጉሱ ትዕዛዝ ፃድቅ ተብዬውን ፈትሸው የተሰረቀውን የወርቅ ማስቀመጫ
ተቀምጦበት አገኙት።ሁሉም ተገረሙ ፣ ደነገጡ።ንጉሱም ለሰውዬው "እንዴት እሱ እንደ ሰረቀ ልታውቅ ቻልክ?" አለው ግራ በመጋባት። ሰውዬውም ሚስቱን
እያስታወሰ "ቁጥብነት እና መልካምነትን እንዲህ
{ድንበር ባለፈ ሁኔታ} ስታገኘው ከጀርባው ትልቅ ክህደት እንዳለ ያመላክታል" ብሎ መለሰለት ። ይባላል።


 💝💝 የልቤ ትርታ 💝💝

‍ ​​         
            ◅አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ▻

                 
#ክፍል_❷⓪
‍ ​

#ከሁለት_አመት_በኋላ

➜መቅደስን ወሎ ድረስ ወስዶ ከናቱ ጋር አስተዋወቃት እናቱም ልክ እንደኔ ሆነሽ ልጄን ተንከባከቢልኝ ብለው አደራ ሰጧት መቅደስም ብትሆን ያለምንም ፍርሀት ቤተሰቦቿ ጋር ወስዳ አስተዋወቀችው ከዛም ሁሉም ቤተሰቦቿ በተሰበሰቡበት በሽታው ተነስቶበት ወደቀ የሚገርመው ግን አንድም ሰው አልተቃወማትም እንደውም ኮሩባት ልጃችን ገንዘብ ቤት መኪና መልክ ቁመና ዝና ሳትል ፍቅርን መረጠች ብለው ልክ እንደጌዲዮ እናት የመቅደስም ቤተሰቦች መረቋቸው እህት ወንድሞቿም ታናሻችን ብትሆኚም ሁሌ አርአያችን ነሽ ብለው ተራ በተራ እያቀፉ ሳሟት።.. ያው በሽታው ሲብስበት ፀበል ይዛው እየሄደች ታስታምመዋለች እናም በዚህ መልኩ ጌዲዮና መቅደስ ድፍን ሌላ ሁለት አመት በፍቅር ዘለቁ ከሁለት አመት ቡሀላ ምን ሊፈጠር ይችል ይሆን አብረን የምናየው ይሆናል የመቅደስና የጌዲዮ ትውውቅ ድፍን ሶስት አመት ሊሞላው አንድ ሳምንት ብቻ ነው የቀረው አሁን አመቱ አዲስ ነው የረፍት ጊዜያቸውን ጨርሰው መቅደስ ያራተኛ አመት ጌዲዮ ደግሞ ያምስተኛ አመት ትምህርታቸውን ለመቀጠል ነገ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ ይጓዛሉ በተለይ ለጌዲዮ ይህ አመት ልዩ ነው ዛሬ ላይ እንዲቆም በትምርቱ ገፍቶ ሰው የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ከፈጣሪ በታች መሰላል የሆነችውን የናቱን አደራ የሚወጣበት ተመርቆም ለቁም ነገር የሚበቃበት ልዩ አመት ነው እንኳን ለናቱ እንኳን እራሱ መቅደስም የዚህን አመት መጨረሻ ናፍቃለች ደወለችለት

....ሄሎ ጌዲ ወዬ ፍቅር እንዴት ነህልኝ እግዚያብሄር ይመስገን ደናነኝ አንቺ እንዴት ነሽ እማ ደናነኝ አንተ ግን እያመመህ ነዋ አለችው አረ ደናነኝ ደሞ ደናነኝ ትላለሀ ቅድም እኮ ስደውል ማዘር አንስተው እንዳመመህ ነግረኛል ውይ መቅዲ እማን አታውቂያትም እና ነው እራሴንም ስል እኮ ነው አቋረጠችው በቃ እራስ ምታት ላንተ በሽታ አይደለማ ለማንኛውም ነገ መናህሪያ እንደደረስክ ደውልልኝ አባዬ አደርሳችኋለሁ ብሎኛል ለሊት ስለምትነሳ አሁን ተኛ አለችው እሺ ደናደሪልኝ እንደደረስኩ እደውልልሻለሁ እሺ ቻው።

.......በንጋታውም ልክ እንዳለችው ተያይዘው ባባቷ መኪና ተያይዘው ጅማ ገቡ አባቷም ምሳ ጋብዞ ግቢ አድርሷቸው ወደአ.አ ተመለሰ.......መቅደስና ጌዲዮ ግቢ እንደገቡ ከሁሉም ጓደኞቻቸው ጋር ተገናኙ ወይና ብርሀን ሰአዳ በለጠው ሌሎቹም ተሰባሰቡና ቡና ለመጠጣት ሻንጣዎቻቸውን አሳርፈው ወጡ.......

በለጠው በጓጓው ልቡ እናንተ የተገናኛችሁበትን ሶስተኛ አመት እንዴት ነው የምታከብሩት አላቸው መቅደስም እንዳምናው ነዋ አለችው በቃ ይቀወጣል አላት ብርሀንም ሙድ ስትዪዝበት የሰውንማ ለማሞቅ አንደኛ ነህ ግን ያንተ መቼ ነው ስትለው ሁሉም ሳቁበት እንዴ ትቀልጂያለሽ እንዴ ባንድ ሳምንት አንድ ሴት እቀይራለሁ ታዲያ እኔ ለየትኛዋ ፓርቲ ላዘጋጅ ስታዪኝ ከበርቴ ቱጃር መሰልኩሽ እንዴ ጌዲዮም ቀጠለና አንድ መያዝ ነዋ አለው ወይ አንድ ትቀልዳለህ መሰል እንደዛ ሲል ሰአዳ ወሬ ቀይር አለችው ከዛም ትንሽ እንደተዝናኑም ጌዲዮ አመመው ብዙም ሳይዝናኑ ወዲያው ወደግቢ ተመለሱ።......

........ሶስተኛ አመት የትውውቅ ልደታቸውንም በደመቀ መልኩ እያከበሩት ሳለ ዛሬም ጌዲዮ አመመው ቢሆንም እስኪነቃ ጠብቀው ሻማቸውን አብርተው ሲደሰቱ ነው ያደሩት

ቢሆንም ግን መቅደስ የፍቅረኛዋ ነገር እያሳሰባት ነው ጭራሽ እንቅልፍ አልወሰዳትም ጌዲዮ ሲነቃ እንቅልፍ አልያዛትም መቅዲ ምን ሆንሽብኝ ለምን አተኚም ሲላት እንቅልፌ ስላልመጣ ነው አንተ ተኛ አለችው ፊቷ ተቀያይሮ ስለነበር ጌዲዮ ወዲያው አወቀባት ምን እያሰብሽ ነው ስለኔ ነዋ አላት አዎ ስላንተ ቆይ እስከመቼ ነው እንዲህ በሽታህን ተሸክመህ የምትኖረው መቅዲዬ እሺ ምን ላርግ ምን ላርግ አትበለኝ ይኸው ሀኪም ቤት ለመሄድ አይደል እንዴ ዛሬ ነገ እያልክ ስንት ጊዜ የሆነክ መቅዲ ብሄድም ምንም ለውጥ አይኖረውም እኮ እንዴት አወክ መቅዲዬ የኔ በሽታኮ አትጨርሰው ከልጅነቴ ጀምሮ ነው ልትለኝ ነዋ አዎ ደሞኮ ሰዎች ሲያወሩ እንደሰማሁት ከሆነ እጀ ሰብ ነው ይባላል አረ ጌዲ እንደተማረ አስብ ለስሙ ነው እንዴ አራት አመት ሙሉ አገር አቀፍ ውጤት አሸንፈህ የተሸለምከው ለነገሩ ጌዲ ሀሳቧን እንድትቀይር እንጂ በንደዚህ አይነት ነገር አያምንም

.....መቅዲዬ ምንም አልሆንም ደሞ ፀበል እየሄድኩ አይደል ይሻለኛል ጌዲ ልታባብለኝ አትሞክር እኔ እንቅልፍህም ያስፈራኛል እንባ ባይኗ ሞልቶ ፈሰሰ ደግሞ የትኛው ፀበል ነው ሀኪም የሚከለክለው ሁሌ ይሻለኛል ትላለህ ግን እያባሰብህ ነው ጌዲ አንተን ካጣን እኔም ሆንኩ እናትህ አንድ ቀን አናድርም መቅደስ ስቅስቅ ብላ አለቀሰች ጌዲም ሊያስቀይሳት ፈልጎ ማታ ወድቄ አሳፈርኩሻ አላት መቅደስ ባንዴ አራስ ነብር ሆነች ባለ በሌለ አቅሟም በጥፊ ሞላችለት ለመናገር ተስኗት ትንፋሿ ተቆራረጠ ጌዲዮም ጉንጩን ይዞ እየሳቀ አረ እየቀለድኩ ነው አመረርሽ እኮ ሲላት በንዴት ደረቱን እየወቀረች እኔ ጨንቆኛል አንተ ትቀልዳለክ ጌዲዩ በፍቅር የሚመቱትን ሁለት እጆቿን ግጥም አርጎ ይዞ አቀፋት መቅደስ ይበልጥ አለቀሰች የምታጣው የምታጣው እየመሰላት ነው ጌዲዮም ሁኔታዋ ግራ ገብቶት አረ በቃ አንቺ ደስ ካለሽ የሳምንቱ መጨረሻ ላይ እኔዳለን አላት እስኪ ማሪያምን በል አለችው በንባና በሳቅ መሀል ሆና ማሪያምን እኔዳለን ብሎ አባበላትና አቅፏት ተኙ።..........

.......መቅደስ ከጌዲዮ ቀድማ ነቃች ሻውር ወስዳ ለባብሳ ስትጨርስ ልትቀሰቅሰው ጌዲ አለችው መልስ አልሰጣትም አሁንም ተጣራች ዝም አላት አንተ ጌዲ ተነስ ሰአት እረፍዷል ግቢ ክላስ መግባት አለብን አለችው አሁንም መልስ አልሰጣትም ክው አለች ከወንበሯም ተነስታ ወዳልጋው አመራች በጆቿም እየደበደበች ብጠራውም ሊሰማት አልቻለም እንደበረዶ ቀለጠች ሰውነቷ ደነዘዘ የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋ ጌዲ ጌዲ ደጋግማ እየተጣራች አቤት በለኝ አለች ጌዲዮ ግን...

🥀አንብበው ሲጨርሱ #LIKE ማድረግ አይርሱ


➜ ክፍል ❷❶ ከ ❶⓪⓪ 👍 በኃላ ይቀጥላል...

Показано 20 последних публикаций.
OSZAR »