~ ጠር"ጥር ~
የሆነ ግዜ እንዲህ ሆነ
ባል ስራ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ በጣም የሚወዳት ሚስቱ በምሬት እያለቀሰች ያገኛታል።
ይሄኔ ይደነግጥና ለምን እንደ ምታለቅስ ይጠይቃታል።
እሷም እንዲህ ስትል መለሰችለት።
"" እኔ ማንም ከማይደርስበት ወፍ እንኳ ዝር ከማይልበት
ከቤታችን ጓሮ ተተግኜ ልብሴን ሁሉ አወላልቄ
መለመላዬን ሆኜ ገላዬን እየታጠብኩኝ ሳለ
"እዚህ ዛፍ ላይ ያለው አሞራ ሀፍረተ ስጋዬን ሲያየኝ ጊዜ
እኔም አንተ ውዱ ባሌን የከዳሁህ ያክል ወንጅል ሆኖ ስለተሰማኝ ቆጭቶኝ ነው የማለቅሰው..."
ስትል ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች መለሰችለት።
፦፦፦ይሄኔ የዋሁ ባል በዚህ ቁጥብነቷ ተደስቶ
"ተመስገን አምላኬ ምን አይነት መላክ ሚስትን ሰጠኽኝ ብሎ እቅፍ አደረጋትና ግንባሯን ሳማት። ወዲያውም መፍለጫ ይዞ ወጣ'ና አሞራው ሚያርፍበትን ዛፍ እንዳልነበረ አድርጎ ቆረጠው።
👉በሌላ ግዜ እንደ ተለመደው ከዕለታት አንድ ቀን ባል ስራ በግዜ ጨርሶ ባልተለመደ ሰአት ቤት ከች ሲል
.ያችን ቁጥቧን፣ያችን አሞራ አየኝ ብላ ቂያማ ምታስነሳውን ሚስቱን ከውሽማዋ ጋር ተኝታ ያገኛታል።
አንዳች አልተነፈሰም ምንም አላደረገም ማቄን ጨርቄንም ሳይል ትቶ ወጣ እና ወደ ሩቅ ሀገር ሄደ።
👉በመንገዱ ላይ የሆነ ከተማ ሲገባ በጣም ብዙ ሰዎች ቤተ መንግስት በር ላይ ተሰብስበው ያገኛቸው'ና ለምን እንደ ተሰበሰቡ ይጠይቃል። ሰዎቹም"የንጉሱ ወርቅ ማስቀመጫ ተዘርፎ ነው" ሲሉ ይመልሱለታል።
በዚህ ሁኔታ የሆነ ሰውዬ ጤነኛ ሆኖ በእንብርክኩ ሲንፏቀቅ ያየው'ና.."ይህ ሰው ለምን ቆሞ አይራመድም?" ሲል ጠየቀ።እነሱም "አይ ይህማ የከተማችን ትልቁ ነብይ
ለፈጣሪ ልበ ቀናኢ ቅዱስ ፃድቅም ሰው ነው ! ..
በእግሩ ማይራመደው ምክንያት ምናልባት ሳያውቅ በእግሩ ጉንዳን እንዳይገድል ሰግቶ ነው"
ብለው ይመልሱልታል። አአአዎ በቃ እዝች'ጋ ተነቃቁ.....
ሰውየው "በጩኸት መናገር ጀመረ ሌባውን አገኘውት
....እመኑኝ ሌባውን እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው"ብሎ ጮኸ።
ንጉሱም ጋር በፍጥበት ተጠርቶ ገባ'ና ተጠየቀ
"ያኛው ትል እንዳይገድል ፈርቶ በንብርክክ የሚሄደው ፃድቅ የመሰላችሁ ሰው ነው ንብረትህን የሰረቀህ ከፈለግክ አስፈትሸው'ና ውሸቴን ከሆነ አንገቴን ቁረጠው...." አለ። ወታደሮችም በንጉሱ ትዕዛዝ ፃድቅ ተብዬውን ፈትሸው የተሰረቀውን የወርቅ ማስቀመጫ
ተቀምጦበት አገኙት።ሁሉም ተገረሙ ፣ ደነገጡ።ንጉሱም ለሰውዬው "እንዴት እሱ እንደ ሰረቀ ልታውቅ ቻልክ?" አለው ግራ በመጋባት። ሰውዬውም ሚስቱን
እያስታወሰ "ቁጥብነት እና መልካምነትን እንዲህ
{ድንበር ባለፈ ሁኔታ} ስታገኘው ከጀርባው ትልቅ ክህደት እንዳለ ያመላክታል" ብሎ መለሰለት ። ይባላል።