የህይወት ቅኔ🥀


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Telegram


🙏WELCOME TO OUR CHANNEL 🙏
✍️1መልካምና አስተማሪ የሆኑ ሀሳቦችን ማጋራት
✍️2 አንድነትን ማጠንከር
ፍቅራችንን ያብዛው 🙏ሌሎችን ወደቻናሉ ውስጥ ማስገባት ቁም ነገር ያላቸውን ነገሮች ለሌሎች ሼር ማድረግ አንርሳ ያለንን እውቀት ማካፈል የሁል ግዜ ተግባራችን እናድርግ
📩For any comment, promotion
@Lil_ezrael

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




ማሳሰብያ !!!

ለሴቶች እና እግር ኳስ ለማያቁ ወንዶች አይመከርም!

ትክክለኛ የእግር ኳስ አፍቃሪ ለሆነ ብቻ👇👇👇

@Premier_League_Sport
@Premier_League_Sport


ከኅሊና ዳኝነት ማምለጥ የሚችል የለም🙌🏽

ኅሊናው የሚያሳድደው ሰው የትም ቢገባ ሊደበቅና ሊያመልጥ አይችልም።ኅሊናው ያልዳኘው ሰው የትኛውም ውጫዊ ዳኛ ሊዳኘውና ፍትህ ሊያሰጠው አይችልም

ንፁህ ኅሊና ምቹ ትራስ ነው🙂


ከኅሊና ጋር ተስማምቶ እንደመኖር ምቹ ዕረፍትና ንፁህ ፍትህ የለም.....😌አንድ ጣትህን ወደ ሌሎች ስትጠቁም አራቱ ጣቶችህ ወደ አንተ እንደሚዞሩ አስብ ሌሎችን ከማሳደድህ በፊት ኅሊናህን አፅዳው... ንፁህ ኅሊና ይኑረን🤌❤️‍🔥

አመሻቹ🫶🏽🌸✨


እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ❤➊➋🙏


ከእንቅልፍ ያነቃኛል የደጅህ ደወል
በሌሊት መጥቼ ቤትህ እንድውል
በሄድኩበት ሁሉ ካፌ አትነጠልም
የማር ወለላ ነው ሚካኤል ያንተ ስም🥹❤️‍🔥

ማር ሚካኤል ስልህ ማር ማር አለው አፌ🫠
መውደዴ የእውነት ነው በምልጃህ ተርፌ❤️‍🩹



ደጉ አባቴ ዛሬም ከእቅፍህ አትለየኝ ወዳጄ ብዙ የማዋይህ አለኝና 🥺....ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሚካኤል 🫀✨

ሰኔ 12 🕯🕯🕯


ላላወራህ ምዬ እራሴን ገስጬ አላወራውም አልደርስም አጠገቡ ይበቃኛል መጎዳት ማውራት እሱን ብዬ ልክ ድምፅህን ስሰማ ያሁሉ ጉራ ዛቻ ይጠፋል ተመልሼ አንተው ጋር እገኛለው ልቤም አፌም አልገጥም አሉኝ ተሸነፍኩኝ ። መች ይሁን ይሁሉ ነገር አብቅቶ ልቤ ሚቆርጥልኝ ወይ እንዳወራውት አልሆን ወይ ቆርጦ አይቆርጥልኝ እንዲው በጉራ በዛቻ እስከመች እንደምቆይ ። እንዳንዴ ብን ብዬ ልጥፋ ይሆን ከቆረጠልኝ እላለው ግን አያስችለኝም ዛሬም ነገም ትላንትም አንተው ጋር ነኝ ። መርሳትም መተውም አልቻልኩም ባለመቻል ታስሬ እየኖርኩኝ አለው.......😔

✍🏼 Miss moon 🪐🥀.......


ከሰው የሚሻል ሰው እንጂ ከሰው የሚበልጥ ሰው የለም 😒🙌🏽......ከንቱ አለም 😔



ዋላቹ😒🤞🏾


72.547አችሁም reacte አድርጉልኝ ፈልጌው ነው💔 እመርቃችኋለሁ


ለማቀፍ የራቀ ለመፍረድ ማይተኛ
አለም ሁሉ አስመሳይ ሆኖ ወረተኛ
ስጋሽ አፈር ሳይቀምስ በቁም ስትሞቺ
ማነው እንባ አውጥቶ የሚያዝንልሽ ላንቺ
መከራ እና ስቃይ ህይወት ምን ቢያስከፋ
ሁሌም ልብሽ ያድርግ በፈጣሪ ተስፋ🤍🥀✨



ከመይ አምሲሁም ሰብዐይ🫀🥹🌸✨


ታሪካችን ባያሌው የጦርነት ነው ፤ በጦርነት ያሸነፈው የተሸናፊውን ንብረት እና ሚስት ይማርካል፤ ዳግማይ ቴዎድሮስ በሀያልነታቸው አነጋግ ላይ የሸዋን ግዛት በጦር አስገበሩ፤ ያጤ ምኒክን አባት የሸዋው ንጉስ ሀይለመለኮት የድል አድራጊውን ፊት ከማየታቸው በፊት ታመው አረፉ: :

ቴዎድሮስ በተሸናፊው ቤት ሰተት ብለው ገቡ፤ ሀይለመለኮት ሁለት ሚስቶች ጥለው ሄደዋል ፤ የመጀመርያዋ የምኒልክ እናት ወይዘሮ እጅጋየሁ ሲሆኑ ሁለተኛይቱ ወይዘሮ ትደነቂያለሽ የተባሉት ወይዘሮ ናቸው ፤ ትደነቂያለሽ እጅግ ውብ ነበሩ ይባላል፤ ቴዎድሮስ ባልየውን ሊማርኩ መጥተው በሚስቲቱ ተማረኩ፤ ግን ፍቅር አለዝቧቸው፥ አሽከራቸውን “ ያዝና ጫናት “ ለማለት ሳይደፍሩ ቀሩ፤

“ እቴጌ! በጌምድር አብረን እንሂድ”
ብለው ጋበዟቸው፤

ሴት ያልፈለገችውን ሀይለኛ ወንድ የምታመልጥበት መሳርያ አላት፤ ያ መሳርያ መላ ወይም በሾፐንሀወር አገላለጽ “ ማታለል “ሊሆን ይችላል፤ ወይዘሮ ትደነቂያለሽ የአሸናፊውን ንጉስ ልብ በሚያቀልጥ ፈገግታ የታጀበ መልስ ሰጡ፤“ደስ ይለኛል ፤ ግን ከዛ በፊት ኢየሩሳሌምን ተሳልሜ ለመመለስ አስቢያለሁ፤ ይፍቀዱልኝ “

ንጉሱ ስንቅ ሰጥተው፥ አጃቢ ጨምረው ወደ እየሩሳሌም ሸኗቸው፤

ውቢተን ሸኝተው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የሀይለመለኮት እናት ወይዘሮ በዛብሽ ፤ “ሸዋ እንዲገብር እርዳታ አድርጊያለሁና ሹመት ይስጡኝ “ ብለው ጠየቁ፤

በዚህ ጊዜ ነበር አሸናፊው ንጉስ ከወደ ኢየሩሳሌም መርዶ የሚያክል ዜና የመጣላቸው፤ "ወይዘሮ ትደነቂያለሽ “ከሀይለመለኮት ወድያ አለም አልሻም ብለው መንነዋል “

ይህንን ሲሰሙ ቴዎድሮስ ይቺን ግጥም ወደ ታሪክ ወረወሩ፤

“አወይ ጉድ
ሚስቱ መናኝ
እናቱ ሹመት ለማኝ “

ታሪክ መዝጋቢው ዘንግቶት ይሆናል እንጂ ግጥሙ “ እኔን ብሎ ሰው አማኝ “ ብሎ የሚደመደም ይመስለኛል።




ማዘንበል መውደቅ አይደለም
መውደቅ መሰበር አይደለም

የህይወት ንፋስ ትንሽ ዘንበል ካደረገህ ወደኩ ብለህ በፈጣሪ ተስፋ አትቁረጥ ምክንያቱም.....🙂


"❤️‍🩹🥀ፈጣሪ ቀና ሊያደርግህ ቀን አለውና✨"


አመለወርቅ❤️‍🔥

ዋላቹ✨🌸


ካለፈ ታሪክ ይልቅ የወደፊት ህልም ደስ ይላል....ላወቀበት ላስተዋለው ከትላንት የበለጠ መምህር ከዛሬ የተሻለ ደስታ ከነገ የሚበልጥ ተስፋ አይገኝም ህይወት ይቀጥላል...በአላፊ አለም ቋሚ ነገር የለም !!! 🤍✨




ሠውን ለመቀበል ራስን መሸኘት💔😞


ወንድሜ🥹🤌🏽

ትንሽ ነገር ልበልህ....እየውልህ እግዚአብሔር ላንተ የሚበጅህን ያውቃልና...ከሁሉም ከሁሉም ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባትን ልባም ሴት ያድልህ አሜን በል...ነገርግን ማመስገንህን ፈፅሞ እንዳትረሳ.....🤎🥀🙂✨


ዋላቹ🌸✨


ብር ፍቅርን አይገዛም.. ፍቅር ምንጊዜውም አሸናፊ ነው..


ከጊዜ ወደጊዜ ይህ አባባል እውነት ሳይሆን አባባል ብቻ እየሆነ ነው.. በተለይ በፍቅር ግንኙነት እና በጋብቻ ሕይወት.. ገንዘብ በሰው ልጅ ክፋት እና እርስ በእርሱ መጨካከን ምክንያት አስፈላጊነቱ ብቻ ሳይሆን ገዢ እና አስተዳዳሪ መሆኑን ቀን መሽቶ ቀን በነጋ ቁጥር እያሳያየ እያሳመነ ነው.. ይሁን ብቻ የባሰ አያምጣ..🙂

ለማንኛውም እህታችን አንቺ የልቡ ገዢ ከሆንሽ.. ፍቅር አስገድዶት ራሱን ከሰጠሽ.. ከወንድ ልጅ የተሻለ የማመዛዘን የማሰብ መፍትሄ የመፈለግ እና የተንኮል ጭንቅላት እንዳለሽ ግልፅ ነው.. ስለዚህ ዘውድ ሁኚ ልንግስናው.. ሚስት እናት እህት ሁኚ ለባለቤትነቱ.. ገንዘብ እና ጥቅም እንደ ሸቀጥ እንደ ዕቃ አይግዛሽ.. አይለውጥሽ.. እንደ ባለሱቅ እንደነጋዴ በገንዘብ መጠን ፀባይሽ አይቀያየር..

በተቻለሽ መጠን ራስሽን ሁኚ.. የራስሽም ሁኚ..


GREETINGS Fams 🫡 RASTAFARI 🔥


ያለህበት ቦታ የአንተን value ካላየህበት ያንን ቦታ ተወዉ!


እኛ አምላክ አይደለንም

እንደክማለን እንወድቃለን…

እኛ ግን የሰው ልጅ ነን

ደክሞ መበርታትን

ወድቆ መነሣትን እናውቃለን …


አንዳንዴ የምንኖርበት ምክንያቱ ሁሉ ይጠፋናል። ጨለማው  ሲጫነን ፈተናው ሲበዛብን "ለምን ይሆን የምኖረው" እንላለን አደል ? አምላካችን ጋር እንጣላለን ። ለበጎ መሆኑን ፈፅሞ እንረሳዋለን።
ሳይደግስ አይጣላም ማለት ይሳነናል ።  ማማረሩ መጮሁን ማልቀሡን እንመርጣለን ። ግን  በእነዚህ ነገሮች ፈተና እና ችግርን ያለፈ ማንም የለም።ማንም‼
ዛሬ ያለነው በምክንያት   ነው።  በፈጣሪ ደግ ፈቃድ ፈተናው ችግሩም የመጣው ፈጣሪ ስለወደደ እና  ደና ደረጃ የምንደርስበት ደረጃ ወይም መሠላል ስለሆነ  እና ድጋሚ እንዳንወድቅ  ነው እንጂ ፈተና እና ችግሩ የበዛው ። እሱ ልጆቹ ሲቸገሩ እና ሲፈተኑ ማየት አስደስቶት አደለም እንዲያውም ከእኛ በላይ እሡ ነው የሚያዝነው ።

ስለዚህ ማማረር መፍትሄ ሆኖ አያቅም ።
ለማማረር የሚከፈቱትን ልሳኖች ለምስጋና እንጠቀማቸው ። ስንነሳ ምስጋናን እንልመድ ። ከተኙበት ያልተነሡ  ብዙ አሉ እና።

መልካም    ቀን ተመኘሁ 🙏🏽🙏🏽

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »