Addis Admass


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
=====
አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx
ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv
የእርስዎና የቤተሰብዎ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
አምስት ተሽከርካሪዎች የተጎዱበት ክስተት

በአዲስ አበባ ኮተቤ 02 አካባቢ፣ ኮንቴነር የጫነ ከባድ የጭነትተሽከርካሪ፣ ወደ ኋላ በመንሸራተቱ ከኋላ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል፡፡ ተሽከርካሪዎቹ በጣም እንደተጎዱ ከሚታየው ቪዲዮ መረዳት ይቻላል፡፡


የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በ3 ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ



የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ በዛሬው ዕለት ባካሄደው 4ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ስብሰባ፣ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል።


በዚህም መሰረት፡-

1. የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ አጽድቋል።

2. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግል ትምህርት አገልግሎት ክፍያ አሰራር ስርዓት ረቂቅ ደንብ አጽድቋል።


3. በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው ፕሮጀክቶች የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶ በሰፊው ከተወያየ በኋላ የውሳኔ ሀሳቡን አጽድቋል።


ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የጥራት ዕውቅና ያገኘ መሆኑ የተነገረለትን የላብራቶሪ ማሽን ሥራ ያስጀመረ ሲሆን፤ ማሽኑ የላብራቶሪ ምርመራ ወደ ውጪ መላክን በመቀነስ የውጪ ምንዛሪን እንደሚያድን ተጠቁሟል፡፡


በሆስፒታሉ በዛሬው ዕለት በይፋ ሥራ የጀመረው "Mindray BS-680M' (intergrated)"
የተሰኘው የላብራቶሪ ማሽን በምሥራቅ አፍሪካ 2ኛ፣ በኢትዮጵያ የግል ሕክምና ተቋማት ደግሞ የመጀመሪያ ያደርገዋል ተብሏል፡፡


የኢትዮ ኢስታንቡል ሆስፒታል መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ብርሃን ተድላ በሥራ ማስጀመሪያ ሥነስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ይህንን ዘመናዊ ማሽን ያስገቡበት ዓላማ ለህብረተሰቡ የተሻለና ጥራቱ የተረጋገጠ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት መሆኑን ገልጸዋል።

የማሽኑ ሥራ መጀመር ለላብራቶሪ ምርመራ ወደ ውጪ ሀገር የሚደረግ ጉዞን በማስቀረት ለሀገር የውጪ ምንዛሪ የማዳን ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ሥራ አስፈጻሚው አክለውም፤ "'Mindray BS-680M' የላብራቶሪ ማሽን በሰዓት ከ840 በላይ የተለያዩ የህክምና ምርመራዎችን የማድረግ አቅም ያለው ሲሆን፣ ከሰው ንክኪ የጸዳ በመሆኑ የውጤቶችን ትክክለኛነት በእጅጉ ይጨምራል። ይህ ባህሪ የምርመራ ሂደቶችን ፍጥነት ከማሳደጉም በላይ የውጤቶችን አስተማማኝነት በማረጋገጥ፣ ለታካሚዎች ትክክለኛ የህክምና ክትትል እንዲያገኙ ያስችላል።" ሲሉ አብራርተዋል፡፡
የማይንድሬይ የምስራቅ አፍሪካ የሴልስ ማናጀር ዊልያም ፌኔል በበኩላቸው፤ ማይንድሬይ በመላው ዓለም ለህክምና ተቋማት በርካታ የህክምና መሳሪያዎችን በጥናት ላይ ተመስርቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ኩባንያው ለጥናትና ምርምር ብቻ 500 ሚሊዮን ዶላር መድቦ እየሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

የኩባንያው የምርት ሽያጭ ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ዳይላን በሰጡት ማብራሪያ፤ ይህ ማሽን የላብራቶሪ ምርመራ ውጤቶችን ስህተቶች በመቀነስና በአነስተኛ የሰው ኃይል ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዳለው አስረድተዋል።

የሆስፒታሉ የላብራቶሪ ክፍል ኃላፊ አቶ ደሳለኝ መርጊያው፣ ሆስፒታሉ ገና ሁለት አመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ገልጸው፣ ለሆስፒታሉ ባለቤት ለአቶ ብርሃን ተድላ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህ አዲስ ማሽን የሆስፒታሉን የላብራቶሪ አገልግሎት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

የኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ላብራቶሪ፣ በቅርቡ ከኢትዮጵያ አክሬዲቴሽን አገልግሎት የጥራት ሰርተፊኬት ማግኘቱ ይታወቃል፡፡


ዓለማቀፍ የጥራት ዕውቅና የተሰጠው የላብራቶሪ ማሽን ሥራ ጀመረ


• ማሽኑ በሰዓት ከ840 በላይ የተለያዩ የህክምና
ምርመራዎችን የማድረግ አቅም አለው

⬇️⬇️


" No More"
አዲስ ትያትር
አርብ ሰኔ 6 በዓለም ሲኒማ
በድምቀት ይመረቃል


በግብረ ሰዶም ሙከራ ወንጀል በሌለበት የ15
ዓመት እስራት የተፈረደበት ተከሳሽ ተያዘ

ተከሳሹ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሙከራውን የፈጸመው ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ከሚገኝ ጫካ ውስጥ ነው።

የግል ተበዳይ የሆነው ህጻን ብቻውን ወደ ጸጉር ቤት ሲሄድ ተስፋ በቀለ የተባለው ተከሳሽ በኃይል ጎትቶ ወደ ጫካ በመውሰድ ጥቃት ሊፈጽምበት ሲል፣ ህጻኑ ባሰማው ጩኸት፣ የአካባቢው ህብረተሰብ ደርሶ ከጥቃት በማዳን ወዲያው ለፖሊስ ጥቆማ ሊሰጥ ችሏል።

ፖሊስ ጥቆማ ከደረሰው በኋላ አስፈላጊ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በተከሳሽ ተስፋ በቀለ ላይ በአቃቤ ህግ ክስ እንዲመሰረትበት መደረጉን የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

ተከሳሽ ዋስትና ተፈቅዶለት በቀጠሮው ቀን ያልተገኘ ሲሆን፤ ጉዳዩን የተከታተለው በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የካ ምድብ 7ኛ ወንጀል ችሎት፣ በበቂ ማስረጃ ካረጋገጠ በኋላ፣ ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሌለበት 15 ዓመት ከ1 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎ በታል።

ተከሳሹ ተይዞ ቅጣቱ ተግባራዊ እንዲሆን ፍ/ቤቱ ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ፣ ፖሊስ ብርቱ ጥረት በማድረግ በቁጥጥር ስር በማዋል ለማረሚያ ቤት እንዳስረከበው ፖሊስ መምሪያው ጠቅሷል።


የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊልያም ሩቶ ሴት ልጅን የህይወት ታሪክ የጻፈው ደራሲ ተከሰሰ። ግለሰቡ የፕሬዚዳንቱን ሴት ልጅ ፍቃድ ሳያገኝ የህይወት ታሪኳን ጽፏል በሚል መከሰሱን ተከትሎ፣ የኬንያ የህግ ባለሙያዎችና የመብት ተሟጋቾች ድርጊቱን አውግዘዋል።

የፕሬዚዳንቱ ልጅ ቻርሊን ሩቶ ደራሲውን ዌብስተር ኦቾራ ኤላይጃህ ከሷ ፍቃድ ሳያገኝ በመጻፉ "ስሜን ያላግባብ ተጠቅሟል" ስትል ነው የከሰሰችው።

ደራሲው "Beyond the Name: Charlene Ruto and the Youth Uprising በሚል ርዕስ ባወጣው መጽሐፉ ምክንያት ትላንት ማክሰኞ ክስ ተመስርቶበታል። ግለሰቡ ጥፋተኛ እንዳልሆነ ለፍርድ ቤት ቃሉን ከሰጠ በኋላ የዋስ መብቱ ተከብሮ ወጥቷል።

ክሱን የመሰረተችው ቻርሊን ጉዳዩን አስመልክቶ ለፖሊስ እንዳመለከተችና ህጋዊ አሰራር መከተሏን ለጋዜጠኞች ተናግራለች።

ተከሳሹ መጽሐፉን ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ወይም ከዚያ በፊት ከሌሎች አጋሮቹ ጋር በመሆን ማሳተሙ የማጭበርበር አላማ ያለው ነው የሚል ክሱ ላይ ተካቶበታል። ከተከሳሹ ጋር መጽሐፉን ያሳተሙት ግለሰቦች ክስ እንዳልተመሰረተባቸው ተገልጿል።

የፕሬዚዳንቱ ልጅ መጽሐፉ ያለ ፈቃዷ ስለመጻፉ እንጂ በይዘቱ ላይ ቅሬታ አላቀረበችም። ተቺዎች ግን ይህ አሰራር ህገወጥ አይደለም ይላሉ።

ፖለቲከኛውና የህግ ባለሙያ የሆኑት ዊልስ ኦቶኖ "ደራሲነትን ለመወንጀል" የመንግሥትን ስልጣን ያለ አግባብ እየተጠቀሙበት ነው ይላሉ፡፡ የስነ ጽሑፍ ሃያሲው ምቡጉዋ ንጉንጂሪ በበኩላቸው፤ ደራሲው ምንም ያጠፋው ጥፋት የለም፤ ብለዋል፡፡

ሃያሲው ለዚህም ዋቢ የሚያደርጉት በአውሮፓውያኑ 2014 የታተመው፣ በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የህይወት ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነውንና ፍቃድ ያልተጠየቀበትን መጽሐፍ ነው።

ደራሲውን የወከሉት የህግ ባለሙያዎች፣ግለሰቡ የፕሬዚዳንቱን ልጅ የህይወት ታሪክ መጻፉ ወንጀል እንዳልሆነ ተከራክረዋል።

(ቢቢሲ)


የዊሊያም ሩቶ ሴት ልጅን የህይወት ታሪክ የጻፈው ደራሲ ተከሰሰ


• የኬንያ የህግ ባለሙያዎች ክሱን አውግዘዋል

⬇️⬇️


የስሎቫኒያ ፕሬዚዳንት ለ2 ቀናት ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባሉ

የስሎቫኒያ ፕሬዝዳንት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው እንዳስታወቁት፤ የስሎቫኒያ ፕሬዚዳንት ናታሻ ፒርች ሙሳር፣ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባሉ።

በቆይታቸውም ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው፣ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ያደርጋሉ ተብሏል፡፡


ቢል ጌትስ በናይጄሪያም የክብር ሜዳሊያ ተሸለሙ



ከዓለማችን ቢሊየነሮች አንዱ የሆኑትና በበጎ አድራጎት ሥራቸው የሚታወቁት ቢል ጌትስ፣ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከሁለት የአፍሪካ አገራት ታላላቅ ሽልማቶችን አግኝተዋል - ከአዲስ አበባ ኢትዮጵያና ከሌጎስ ናይጄሪያ፡፡


የማይክሮሶፍት መሥራቹ ቢል ጌትስ፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የክብር ኒሻን በተሸለሙ ማግስት ነው ከናይጄሪያም አቻ የክብር ሽልማት የተበረከተላቸው፡፡


የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ቦላ አህመድ ቲኒቡ፣ ቢል ጌትስ በጤና፣ በትምህርትና በድህነት ቅነሳ በተለይም በናይጄሪያና በመላው አፍሪካ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ‹‹ኮማንደር ኦፍ ዘ ኦርደር ኦፍ ዘ ፌዴራል ሪፐብሊክ›› የተሰኘውን የክብር ሜዳሊያ ሸልመዋቸዋል፡፡


ሽልማቱ የተበረከተው ትላንት ማክሰኞ ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ቢል ጌትስ ናይጄሪያን በጎበኙበት ወቅት ሲሆን፤ ከፕሬዚዳንት ቲኒቡና ከሌሎች የመንግስት ባለሥልጣናት ጋር በመገናኘት በሀገሪቱ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አጠባበቅ ስርዓት ማሻሻያዎች ላይ መወያየታቸውን የናይጄሪያ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡


የቢል ጌትስ ጉብኝት በናይጄሪያ Goalkeepers Nigeria በተባለው ኹነት ላይ መሳተፍን ጨምሮ ከሳይንቲስቶችና ባለድርሻ አካላት ጋር በአርቴፊሻል አስተውሎት የሚመሩ የጤና መፍትሄዎችን በማስፋት ዙሪያ ያተኮሩ ስብሰባዎችን ያካትታል ተብሏል።


የአትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ እና የቺቤት ትንቅንቅ በሮም


በ2025 ዳይመንድ ሊግ አርብ በሚደረገው የሴቶች 5ሺ ሜትር ውድድር የርቀቱ የአለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው ጉዳፍ ጸጋዬ እና የኦሎምፒክ ሻምፒዮኗ ቢያትሪስ ቺቤት የሚያደርጉት ፉክክር ተጠባቂ ሆኗል።


በ5ኛዋ ከተማ ሮም በሚካሄደው ውድድር በሴቶች 5ሺ ሜትር ስድስት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉ ሲሆን፤ አትሌት ጉዳይ ጸጋዬ ለአሸናፊነት ከኬንያዊቷ ቺቤት ጠንካራ ፈተና ይጠብቃታል።


ሁለቱ አትሌቶች በተመሳሳይ ርቀት በዢያመን ባደረጉት ዳመንድ ሊግ፣ ኬንያዊቷ ቺቤት ስታሸንፍ ጉዳፍ ጸጋዬ 2ኛ ወጥታለች።


ጉዳፍ ጸጋዬ ለመጨረሻ ጊዜ ቢያትሪስ ቺቤትን ያሸነፈቻት በ2023 ኢዩጂን ዳይመንድ ሊግ ላይ ሲሆን፤ በወቅቱ ጉዳፍ 14 ደቂቃ 00.21 ሰከንድ በመግባት የ5ሺ ሜትርን የዓለም ክብረ ወሰን የሰበረችበት እንደነበር ይታወሳል።


የሁለት ጊዜ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮኗ ፍሬወይኒ ኃይሉ፣ ማርታ አለማየሁ፣ አሳየች አይቸው፣ አለሽኝ ባወቀ እና ጫልቱ ዲዳ በውድድሩ የሚሳተፉ ሌሎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ናቸው።


(ኢቢሲ)


በዓለም ባንክ ድጋፍ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ሊገነባ ነው

በሱማሌ ክልል የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ የተጣለ ሲሆን፤ ግንባታው ከ20 ሺህ ካ.ሜ በላይ መሬት ላይ እንደሚያርፍ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ባጋራው መረጃ ጠቁሟል፡፡

2ኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከሉ አርብቶ አደሩና ነጋዴው ያለደላላ ጣልቃ ገብነት በቀጥታ የሚገበያዩበት እንዲሆን የታሰበ ሲሆን፤ ለቁም እንሰሳትና ስጋ ላኪዎች እንዲሁም ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የአቅርቦት ምንጭ ይሆናልም ተብሏል።

ማዕከሉ በዓለም ባንክ ድጋፍ እንደሚገነባና በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች 6 የሁለተኛ ደረጃ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከላትን ለመገንባት የተያዘው ዕቅድ አካል መሆኑን ስፑትኒክ ጠቁሟል፡፡


ብሔራዊ ባንክ በ50 ሚ. ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ያካሂዳል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ ገበያን ለማረጋጋትና ለመቆጣጠር ያለመ የ50 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ጨረታ፣ ነገ ሐሙስ ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡ ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ ከሚያካሂዳቸው የውጭ ምንዛሪ ጨረታዎች ሰባተኛው ነው።


የአንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ "ፕሮፌሰሮቹ እና ሌሎች" መፅሐፍ ለንባብ በቃ

በአንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ ተሾመ ብርሀኑ ከማል የተዘጋጀው "ፕሮፌሰሮቹ እና ሌሎች" የተሰኘ መጽሐፍ በገበያ ላይ መዋሉ ተገለጸ፡፡

መፅሐፉ በኢትዮጵያ የታሪክ ገፆች የተዘነጉ በኢትዮጵያና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ሙስሊም ምሁራንን (ፕሮፌሰሮችንና ሌሎች የዕውቀት ሰዎችን) ሕይወትና ታሪክ የያዘ መፅሐፍ ነው ተብሏል፡፡

"ፕሮፌሰሮቹ እና ሌሎች"፤ በሁለት ቋንቋዎች የተዘጋጀ ሲሆን፤ የመጀመሪያው 202 ገጾች በአማርኛ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ 182 ገጾች ደግሞ በእንግሊዝኛ ተዘጋጅተዋል። ይህም አቀራረብ መጽሐፉ ሰፊ አንባቢዎችን እንደሚያስገኝለት ተገምቷል፡፡

በመጽሐፉ ውስጥ ከተካተቱ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ምሁራን መካከል፤ ፕሮፌሰር አደም ዓሊ አሕመድ፣፣ረዳት ፕሮፌሰር አደም ካሚል፣ ፕሮፌሰር አሕመድ አብዱልሙኢን፣ ፕሮፌሰር አሕመድ ዓሊ አሕመድ፤ ፕሮፌሰር አሕመድ ዘከሪያ አቡበክር፣ ፕሮፌሰር ሑሴን አሕመድ፣ ፕሮፌሰር ጀማል አብዱልቃድርና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡


መፅሐፉ እነዚህ ምሁራን ለኢትዮጵያ አካዳሚክስ፣ ጥናትና ምርምር እድገት ያበረከቱት አስተዋፅኦ፣ እንዲሁም የገጠሟቸውን ተግዳሮቶችና የፈጠሩትን ተፅዕኖ በጥልቀት እንደሚያሳይ ተነግሯል፡፡

መጽሐፉን በቀጥታ ከደራሲው ተሾመ ብርሃኑ ከማል ወይም ከጃፋር መፅሐፍ መደብር እንዲሁም አንዋር መስጂድ፣ ነጃሺ እና አልተውባ ማግኘት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም በአብዱ ቡክ ደሊቨሪ በኩል ማግኘት እንደሚቻል ታውቋል፡፡


2 ሚ. የሚጠጉ ሙስሊሞች ሐጂ ለማድረግ ሳኡዲ ገብተዋል


የዘንድሮው የሐጅ ሥርዓት ዛሬ መጀመሩን ተከትሎ በመላው ዓለም የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ በሁሉም የትራንስፖት አማራጭ ሐጅ ለመፈፀም መካ ከተማ እየገቡ እንደሆነ የሳዑዲ ዓረቢያ ሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር ገልጿል።

ከ1.2 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በየብስ፤ ከ63 ሺህ በላይ በአየር እንዲሁም ከ5 ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በባሕር በድምሩ 2 ሚሊዮን የሚጠጉ ሙስሊሞች ሐጂ ለማድረግ ሳዑዲ መድረሳቸውን የቱርኩ የዜና ወኪል አናዶሉ ዘግቧል፡፡

የሐጅ ጸሎት ሥርዓት ሙስሊሞች በፈጣሪያቸው ዘንድ ምንዳ የሚያገኙበት፣ አብሮነትን የሚያጠናክሩበት፣ ከሌሎች ሀገራት ወንድም እህቶቻቸውን የሚተዋወቁበት፣ ፈጣሪያቸውን የሚያወድሱበት፣ ከእስልም መሠረቶች አንዱ እንደሆነ የእምነቱ አስተማሪዎች ይናገራሉ።

ባለፈው ዓመት ከ200 አገራት ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ሙስሊሞች ዓመታዊውን የሐጂ ሥርዓት እንደፈጸሙ ዘገባው አስታውሷል፡፡




ከኢትዮጵያ ወደ አውሮፓ ሀገራት የሚላክ የአበባ ምርት ውስጥ በተለምዶ "የእሳት እራት" ተብሎ በሚጠራው የቢራቢሮ ዝርያ መገኘት ምክንያት፤ ምርቱ የጥራት ጉድለት እንዳለበት ተደርጎ መቆጠሩን "ትሬድ ማርክ አፍሪካ" ለአሐዱ አስታውቋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የአውሮፓ ሕብረት በራሪው ነፍሳት ከአበባ ምርቶች ጋር ተቀላቅሎ እንዳይገባ ክልከላ ማድረጉ ተገልጿል።

የትሬድ ማርክ አፍሪካ ዳይሬክተር አቶ እውነቱ ታየ፣ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ከምታገኝባቸው ምርቶች መካከል አበባ አንዱ መሆኑን አስታውሰው፤ አበባ አምራቾች አበባው ላይ የሚታዩ ነፍሳትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ስርዓት በፍጥነት ካልዘረጉ፣ የአበባ ምርት ወደ አውሮፓ ገበያ እንዳይገባ ሊታገድ የሚችልበት ዕድል እንዳለ ለጣቢያው ተናግረዋል።

በእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል ኤፍ ሲ ኤም (FMC) የተባለው ተባይ፤ የቢራቢሮ ዝርያ ያለውና በእኛ ሀገር "የእሳት እራት" የሚል ስያሜ ያለው ሲሆን፤ የአውሮፓ ሕብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ኬንያና አንዳንድ አበባ ላኪ የአፍሪካ ሀገራት ላይ እያጋጠመ ያለውን ይህን በአበቦች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ተባይ አስመልክቶ ባለፈው ዓመት አዲስ ሕግ ማውጣቱን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ይህም ሕግ ከዚህ ቀደም ወደ ሕብረቱ አባል ሀገራት የሚገቡ የአበባ ምርቶች ላይ ይደረግ የነበረው አምስት በመቶ የላብራቶሪ ቁጥጥር፤ ወደ 25 በመቶ ከፍ እንዲል የሚያዝ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት ሕብረቱ መስፈርቱን የማያሟሉ ሀገራት የአበባ ምርቶቻቸውን ወደ አውሮፓ እንዳያስገቡ እገዳ የጣለ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም፣ ኢትዮጵያ በአንዳንድ አበባ እርሻዎች ላይ እያጋጠመ ያለውን "የእሳት እራት" ተባይ ለማጥፋት ከእርሻ ጀምሮ ወደ ውጭ እስኪላክ ድረስ ከፍተኛ ቁጥጥርና ክትትል እያደረገች መሆኑ ተገልጿል።

አሐዱ ያነጋገራቸው የኢትዮጵያ ሆልቲካልቸር አምራችና ላኪዎች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ዘውዴ በበኩላቸው፤ የአበባ ምርቱ የአውሮፓ ገበያ ላይ ያጋጠመው ችግር አበቦቹ ላይ በሚታዩት የእሳት እራት የተሰኙ በራሪ ነፍሳት ብቻ እንጂ የጥራት ችግር እንዳልሆነ ገልጸዋል። ችግሩን ለማስወገድም ማኅበሩ በዘርፉ ለተሰማሩ አምራቾች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ አንስተዋል።

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 1 ሺህ 550 ሄክታር መሬት የአበባ እርሻ መኖሩ የተገለጸ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ከአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ በዓመት ከ500 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ እንደሚገኝ የአሃዱ ዘገባ ያመለክታል፡፡ ዘርፉ ከ200 ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠሩም ተጠቁሟል፡፡


"የእሳት እራት" የኢትዮጵያ የአበባ ኤክስፖርት ላይ እክል ፈጠረ


• ምርቱ ወደ አውሮፓ ገበያ እንዳይገባ ሊታገድ ይችላል ተብሏል


⬇️⬇️


የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የአፍሪካ ቀንድን ለማተራመስ እየጣሩ ነው፣ በሴምና ኩሽ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝቦች መካከል ጥላቻን በመፍጠር ውጥረትና ግጭት እንዲፈጠር እየሰሩ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተቹ።

ፕሬዚዳንቱ፤ “ኢትዮጵያንና ሰፊውን የአፍሪካ ቀንድ ለማተራመስ የሚያደርጉትን ጥረት እንዲቀጥሉ ሊፈቀድላቸው አይገባም" ሲሉም አሳስበዋል።

የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ የነበሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ሆርን ሪቪው ድረገጽ ላይ ባሰፈሩት አስተያየት፤ “የኢሳያስ አፈወርቂ የወቅቱ ፕሮጀክት ዋነኛ ትኩረት፣ የአማራና የትግራይ ሚሊሻዎችን በማስተባበርና በማቀናጀት የኢትዮጵያን የፌደራል መንግስት ለመጣል ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

አምባሳደር ዲና በጽሁፋቸው የኤርትራው ፕሬዝዳንት፤ “የኦሮሞ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲጠላ ለማድረግ እየሞከሩ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፤ አምባሳደሩ ለዚህም ፕሬዝዳንቱ “ፍጹም ያልተረዱትን ፅንሰ ሀሳብ፣ ኦሮሙማን” በንግግራቸው ጠቅሰዋል" ሲሉ ተችተዋል።

የፕሬዝዳንቱ ጣልቃ ገንብነት “በቃላት ብቻ የተገደበ አይደለም” ሲሉ የኮነኑት አምባሳደር ዲና፤ “የኢትዮጵያ መንግስትን በትጥቅ ለመታገል የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን የቁሳቁስ ድጋፍ እያደረጉ ነው” ሲሉ ኮንነዋል፤ “ይህም አስከፊ ውጤት ይኖረዋል” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት “ወታደሮቹን ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት እንዲያስወጣና በኢትዮጵያ ትጥቅ አንስተው መንግስትን ለመውጋት የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን ከመደገፍ እንዲቆጠብ ግፊት ልናደርግበት ይገባል ብለዋል።

(አስ)



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »