ኮሌጁ የጤና ባለሙያዎች ቅጥር እንዲካሄድ ወስኗል
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ፣ በሥራ ማቆም አድማ የተሳተፉ ባለሙያዎች ተሰናብተው በምትካቸው ቅጥር እንዲካሄድ ወስኗል፡፡ ቅሬታ ያለው እስከ ነገ ግንቦት 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ በአካል ቀርቦ ይቅርታ መጠየቅ ይችላል ብሏል - ኮሌጁ፡፡
በተመሳሳይ፣ ከግንቦት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በትምህርትና በሥራ ላይ ባልተገኙ የመጨረሻ ዓመት የህክምና ተማሪዎች (ኢንተርን) ከትምህርታቸው እንዲሰናበቱ የኮሌጁ ሴኔት ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚህም መሰረት በእጃቸው ላይ የሚገኝ ንብረት አስረክበው ከግቢው እንዲወጡ አሳስቧል፡፡ ቅሬታ ያለው ኢንተርን ይግባኝ መጠየቅ እንደሚችል ኮሌጁ አስታውቋል፡፡