✝️ የጥያቄዎች መልስ ክፍል 255 ✝️
▶️፩. "ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና። ነገር ግን ሕግ በሌለበት ጊዜ ኃጢአት አይቈጠርም" ሲል ምን ማለት ነው? ሮሜ 4፥15 የኦሪት ሕግ ባይኖርስ ሰው የኅሊናውን ሕግ ይተላለፍ የለም ወይ?
✔️መልስ፦ ኃጢአት ሕግ ሳይወጣ በፊትም ነበረ። ለዚያ ነው ሕግ እስከ መጣ ድረስ ኃጢአት በዓለም ነበረና ያለው። ቀጥሎ ሕግ በሌለበት ኃጢአት አይቆጠርም ይላል። ይህም ማለት ፍዳው ይቀንሳል ማለት ነው። ሕግ ካለ ግን ፍዳው ይበዛል ምክንያቱም ከሕገ ልቡናው በተጨማሪ አድርግ አታድርግ የሚል ውጫዊ ሕግ አለና ከአንድ ምስክር ሁለት ምስክር ይጸናልና ነው።
▶️፪. ሮሜ 5፥16 የኃጢአት ፍርድ ከአዳም ወደ ልጆቹ ተላልፋ ነውን?
✔️መልስ፦ አዎ። የኃጢአት ፍርድ የተባለችው ፍዳ ወይም መርገም ወደ ሰው ሁሉ ተላልፋ ሰውን ስትጎዳ ኖራለች። ኃጢአቲቱ ሳትሆን ፍዳዋ ናት የተላለፈችው።
▶️፫. "ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ" ይላል (ሮሜ 5፥14)። በአዳም መተላለፍ በሰው ሁሉ ኃጢአት ይተላለፍ የነበረው እንዴት ነው? የኃጢአት ውጤቱ ወይስ ኃጢአቱ የሚተላለፍ?
✔️መልስ፦ ኃጢአት አልተተላለፈም። ከዚህ ላይም አዳም ተላለፈ (ማለት የእግዚአብሔርን ሕግ አልፎ በደለ) ተባለ እንጂ የእርሱ ኃጢአት ወደ ሌሎች ሰዎች ተላለፈ አልተባለም። ወደሰዎች የተላለፈ የኃጢአት ውጤቱ፣ ፍዳው፣ መርገሙ፣ ሞቱ ነው። ከዚህም ሞት ነገሠ ያለው ይህንኑ ፍዳውን ነው።
▶️፬. ሮሜ 5፥20-21 ላይ "በደልም እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ። ዳሩ ግን ኃጢአት በበዛበት ኃጢአት በሞት እንደ ነገሠ እንዲሁ ደግሞ ጸጋ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ የተነሣ በጽድቅ ምክንያት ለዘላለም ሕይወት ይነግሥ ዘንድ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በለጠ" ሲል ምን ማለት ነው? ኃጢአት በበዛበት የእግዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች ማለትስ ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ በደል እንዲበዛ ሕግ ጭምር ገባ ማለት ሕግ የበደልን ምንነቷን በመግለጽ አጉልታ አሳየች ማለት ነው። ሕግ አትሥሩ ብላ መሥራት ዝም ተብሎ ከመሥራት የበለጠ በደል ነውና መግለጿን በደልን ማብዛት ብሎታል። በጸጋ የዘለዓለም ሕይወት ሆነልን ማለት ክርስቶስ በቸርነቱ ባደረገልን የቤዛነት የካሣ ሥራ ዘለዓለማዊ ሕይወትን ማግኘት የምንችል ሆንን ማለት ነው። ክርስቶስ ሰው የሆነው በጥንተ አብሶ የመጣውን መርገም ለማራቅ ብቻ ሳይሆን በምልአተ ኃጢአት የመጣውን መከራም ለማራቅ ነው። እርሱ የመጣው ኃጢአት በመብዛቱ ምክንያት ኃጢአትን አጥፍቶ የእውነት መንገድን ለማሳየት ነው። ክርስቶስ መጥቶ ጸጋን የሰጠን ኃጢአት በመብዛቱ ምክንያት ስለሆነ ኃጢአት በበዛበት የእግዚአብሔር ጸጋ ትበዛለች ተብሏል። በዛች ማለት ነው። እንጂ አሁንም ኃጢአትን በማብዛት ጸጋ ይመጣል ማለት አይደለም።
▶️፭. "ነገር ግን ለማይሠራ ኃጢአተኛውንም በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ኾኖ ይቈጠርለታል" ይላል (ሮሜ 4፥5)። በብሉይ ኪዳን ለእግዚአብሔር ልጅነት ግዝረት ያስፈልግ ነበር። በሐዲስ ኪዳን ልጅነትን ለማግኘት ጥምቀት ያስፈልጋል። አብርሃም ግዝረትን ሳይፈጽም ልጅነትን አግኝቷል። በሐዲስ ኪዳንም በእምነት ብቻ ልጅነትን ማግኘት አንችልም?
✔️መልስ፦ በብሉይ ኪዳን ልጅነት የለም። ግዝረትም ለልጅነት ሳይሆን በረድኤት ለመጠበቅ ነበር። በሐዲስ ኪዳን ጥምቀት ግን ለልጅነት ነው። አብርሃም ግዝረትን ሳይፈጽምም ፈጽሞም ልጅነትን አላገኘም ነበር። አብርሃም ልጅነትን ያገኘው ጌታ በተሰቀለ ጊዜ በዕለተ ዓርብ ነው። ጌታ በዕለተ ዓርብ ወደ ሲኦል ወርዶ ቀኝ እጁን ቢያሳያቸው ያ ጥምቀት ሆኗቸው ከሲኦል ወጥተው ወደ ገነት ወጥተዋል። "የማነ እዴየ መጠውክዎሙ ወኮነቶሙ ጥምቀተ" እንዲል። በሐዲስ ኪዳንም በእምነት ብቻ ልጅነት አይገኝም። ልጅነትን ለማግኘት መጠመቅም ይገባል። ያልተጠመቀ መንግሥተ ሰማያት አይገባም ተብሏልና (ዮሐ.3፥5)። እምነት ጽድቅ ሆኖ የሚቆጠረው እምነቱን በሥራ ለሚገልጥ ሰው ነው። እምነት ያለ ሥራ የሞተ ነውና። አብርሃም ሕገ ኦሪት ከመሠራቷ በፊት የነበረ ደግ ሰው ነው። ጸደቀ መባሉ ሕገ ኦሪትን ሳይፈጽም ነው። ሕገ ኦሪትን ሳይፈጽሙ መጽደቅ ከተቻለ አሁንም ሕገ ኦሪትን ሳይፈጽሙ ሕገ ወንጌልን በመፈጸም መጽደቅ ይቻላል ማለት ነው።
▶️፮. ያለ ሥራ ኃጢአት ይቅር ይባላል ማለት ነው? ሮሜ 4፥6።
✔️መልስ፦ ኃጢአት በብዙ መንገድ ይቅር ይባላል። በማመን ይቅር የሚባል ኃጢአት አለ፣ መልካም ሥራን በመሥራት ይቅር የሚባል ኃጢአት አለ፣ ንስሓ በመግባት ይቅር የሚባል ኃጢአት አለ። ከዚህ ያለሥራ ኃጢአት ይቅር ይባላል እያለ የሚገልጻት ያለ ኦሪት ለማለት ነው። አይሁድ በኦሪታቸው ብቻ ተመክተው በኦሪት ብቻ የሚዳን ይመስላቸው ስለነበር ቅዱስ ጳውሎስ በሚወዱት በአብርሃም ምሳሌነት ይነግራቸዋል። አብርሃም ቅዱስ የተባለ ያለ ሥራ (ያለ ኦሪት) መሆኑን ነግሯቸዋል። አብርሃም በእግዚአብሔር አምኖ፣ ማመኑንም በምግባር ገልጾ እንደጸደቀ ለሁሉ የታወቀ ነው።
▶️፯. ሮሜ 4፥2 ላይ "አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢኾን የሚመካበት አለውና ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም" ይላል። በእግዚአብሔር አይመካም ማለቱ ነውን? ቢብራራ።
✔️መልስ፦ ሰው ያለ እግዚአብሔር ቸርነት ምንም ቢሠራ መጽደቅ አይችልም። አብርሃምም በሥራዬ ጸደቅሁ አላለም። በሥራዬ ጸደቅሁ ማለት ከእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም ማለቱ ያለ እግዚአብሔር ቸርነት በሥራ ብቻ መጽደቅ አይቻልም ማለት ነው።
▶️፰. ሮሜ. 6፥4 ላይ "በሞቱም እንመስለው ዘንድ ከእርሱ ጋር በጥምቀት ተቀበርን" ይላል። በጥምቀት ተቀበርን የሚለው እንዴት ይተረጎማል?
✔️መልስ፦ ስንጠመቅ ወደ ውሃው መግባታችን የክርስቶስ የመቀበሩ ምሳሌ ነው። ከውሃ መውጣታችን የክርስቶስ የመነሣቱ ምሳሌ ነው። ስለዚህ ክርስቶስን በሞቱም በትንሣኤውም እንመስለው ዘንድ እንጠመቃለን። ይህንን ነው በጥምቀት መቀበር ያለው።
▶️፱. ሮሜ. 5፥10 ላይ "ከታረቀን በኋላም በልጁ ሕይወት እንዴት የበለጠ ያድነን" ሲል እንዴት ይተረጎማል?
✔️መልስ፦ አብ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ታርቆናል። ከታረቀን በኋላ ደግሞ ስንጠመቅ በልጁ ሕይወት ማለት በልጅነት የበለጠ ያድነናል ማለት ነው። ለመዳን የክርስቶስ መሰቀል ብቻ ሳይሆን በስሙ ተጠምቀን ልጅነትን ገንዘብ ማድረግ ይገባልና።
▶️፲. ሮሜ. 5፥2 ላይ "ወደ ቆምንበት ወደ ጸጋው በእምነት ተመራን" ሲል ጸጋው የተባለ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ከዚህ ጸጋው የተባለች በመጠመቅ የምናገኛት ልጅነት ናት።
▶️፲፩. ሮሜ 4፥4 ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ለሚሠራ ሰው ደመዎዙ የሥራው ውጤት ነው እንጂ እንደ ጸጋ (በነጻ የተሰጠ) ተደርጎ አይቆጠርለትም ማለት ነው። እንደ ዕዳ ማለት እንደ ግዴታ ማለት ነው። የእንግሊዘኛው መጽሐፍ ቅዱስና የግእዙ የተሻለ ገልጸውታል። Now when a man works, his wages are not credited to him as a gift, but as an obligation.
▶️፲፪. ሮሜ 4፥5 ላይ "ነገር ግን ለማይሠራ ኃጢአተኛውንም በሚያደድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል" ሲል ምን ማለት ነው?