✔️መልስ፦ ለማይሠራ ማለት የኦሪትን ሕግ ለማይሠራ ኃጢአተኛውንም በሚያጸድቅ በእግዚአብሔር ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቆጠርለታል ማለት ማመኑ ራሱ ጽድቅ ነው ማለት ነው። ሳያምኑ ከሚሠሩ ሰዎች ይልቅ ያመኑ ሰዎች እንደሚጸድቁ ያመለክታል።
▶️፲፫. ሮሜ 6፥13 ላይ "ብልቶቻችሁንም የዐመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ። ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ" ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ብልቶቻችሁ ማለቱ ሕዋሳቶቻችሁ ለማለት ነው። ሕዋሳቶቻችን የዐመፃ የጦር ዕቃ መሆን የለባቸውም ማለት በሕዋሳቶቻችሁ ክፉ ልትሠሩባቸው አይገባም ማለት ነው። ከዚያ ይልቅ የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጓቸው ማለት ጽድቅ ሥሩባቸው ማለት ነው።
▶️፲፬. ሮሜ 4፥24-25 ላይ "ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቈጠርልን ዘንድ አለው" ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ ስለበደላችን አልፎ የተሰጠ የተባለ ክርስቶስ ነው። እኛን ስለማጽደቅ የተነሣው ማለት በትንሣኤው ትንሣኤን ሰጥቶ የሚያጸድቀን እርሱ ነው ማለት ነው። ክርስቶስን ከሙታን ባስነሣው በእግዚአብሔር እናምናለን ማለት ነው። ይኸውም በአብም በወልድም በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን ማለት ነው።
▶️፲፭. "ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋራ ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋራ እንተባበራለን" ይላል (ሮሜ 6፥5)። ትርጓሜው ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ የክርስቶስን ሞት የሚመስል ሞት የሚባለው ልጅነትን አግኝተን፣ ምግባር ትሩፋት ሠርተን የምንሞተው ሞት ነው። በእንዲህ ዓይነት ሞት ከሞትን በትንሣኤው እንመስለዋለን ማለት በክብር እንደተነሣ በክብር እንነሣለን ማለት ነው።
▶️፲፮. "ነገር ግን በአዳም መተላለፍ ምሳሌ ኃጢአትን ባልሠሩት ላይ እንኳ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ሞት ነገሠ። አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው ለእርሱ አምሳሉ ነውና" ይላል (ሮሜ 5፥14)። ከሙሴ በኋላ በሰዎች ላይ ሞት አልነገሠም?
✔️መልስ፦ ከዚህ ሙሴ ያለው ክርስቶስን ነው። በወንጌል ዮሐንስ መጥምቅን ኤልያስ እንዳለው ሁሉ ከዚህ ደግሞ ክርስቶስን ሙሴ ብሎታል። ሙሴ እስራኤል ዘሥጋን ከግብፅ ወደ ከነዓን እንዳስገባ ክርስቶስም እስራኤል ዘነፍስን ከሲዖል ወደ ገነት አስገብቷልና በግብር መመሳሰላቸውን ለመግለጽ ሙሴ ብሎታል።
▶️፲፯. ሮሜ 5፥7 ላይ "ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል" ሲል ምን ማለት ነው?
✔️መልስ፦ በሰዎች ዘንድ ስለሌላው ሰው መሞት ጭንቅ ነበረ። ስለሌላው ሰው ስለጻድቅም ስለቸር ሰውም የሚሞት ሰው ቢኖር እንኳ ክብር አገኝበታለሁ ብሎ ነው። ክርስቶስ ግን ስለሁሉ የሞተ እከብራለሁ ብሎ ሳይሆን በቸርነቱ ሊያድነን እንደሆነ ያመለክታል።
▶️፲፰. ሮሜ 6፥14 ላይ "አሁን የምትኖሩት ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆነ ኃጢአት ሊገዛችሁ አይችልም" ሲል ምሥጢሩ ምንድን ነው?
✔️መልስ፦ ምሥጢሩ ጸጋ በተባለች ወንጌል አምናችሁ በሕገ ወንጌል ስለምትኖሩ በሕገ ኦሪት ስለማትኖሩ ኃጢአት አይገዛቸሁም ማለት ነው። በወንጌል ስንኖር ፍዳ ስለሌለ ኃጢአት አይገዛንም። ይኸውም በፈቃዳችን ለኃጢአት ካልተገዛን በስተቀር ነው።
© በትረ ማርያም አበባው
✝️የዩቲዩብ ቻናሌ:- We belong to Christ ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
🌻የፌስቡክ ገጼ Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው።