EBSTV NEWS


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.
https://t.me/ebstvworldwide
Inbox - @EbswhatsnewBot

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የሰኔ 17/2017 ዓ.ም የምሽት 1፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፦

🎯የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለሰብዓዊ እርዳታ የሚሆን ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን በተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ መጋዘኖቹ ከላከ በኋላ በትክክል ስለመድረሱና ለተረጂዎች ስለመከፋፈሉ የሚያረጋግጥበት ሥርዓት አልዘረጋም ተብሎ በዛሬው እለት በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ተወቅሷል።

🎯ቢግ 5 በሚል ሥያሜ የሚካሄደው የምሥራቅ አፍሪካ የመሰረተ ልማትና የውሃ ኤክስፖ ከነገ በስቲያ ሰኔ 19 ጀምሮ እስከ ሰኔ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለ3ኛ ጊዜ እንደሚካሄድ ተነግሯል።

🎯 በኢትዮጵያ ተፈናቃዮች፣ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ዜጎችና ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭ የሚባሉ የማህበረሰብ ክፍሎችን በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

🎯ዘንድሮ በአዲስ አበባ መስተዳድር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከተፈተኑ 70 ሺህ 525 ተማሪዎች ዉስጥ 62 ሺህ 639 ተማሪዎች ወይም 88 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደቀጣዩ ክፍል መዘዋወራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

🎯በ28 አገራት ከ7,500 በላይ የቡና መሸጫዎች አሉት የተባለው ኮቲ ኩባንያ የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት እሴት ጨምሮ በቻይና እንዲሁም በሌሎች ሀገራት ሊሸጥ መሆኑ ተሰምቷል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


እስራኤል እና ኢራን ትላንት ምሽት በዶናልድ ትራምፕ አማካኝነት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረሳቸው ቢነገርም ፣ ዛሬ ረፋድ ላይ ኢራን በእስራኤል ላይ ሚሳኤል ማስወንጨፏን ተከትሎ ስምምነቱ መፍረሱን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

አስራ ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የእስራኤል ኢራን ጦርነት በመካከለኛው ምስራቅ አንጃቦ የነበረውን የቀውስ አዙሪት በዚሁ የሰላም ስምምነት መፍትሄ ይበጅለታል ተብሎ ቢገመትም ዛሬ መጣሱ ግን ቀጠናውን ለሌላ ውድመትና እልቂት እንዳይዳርግ እየተሰጋ ነው፡፡

ከትላንት ወዲያ አሜሪካ በኢራን ሶስት ቁልፍ የኒውክለር መሰረተ ልማቶች ላይ የቦምብ ድብደባ ማድረጓን ተከትሎ ኢራንም አጸፋዊ እርምጃዬ ነው ባለው ጥቃት ኳታርና ኢራቅ የሚገኘውን የአሜሪካ የጦር ሰፈር ደብድቢያለሁ ብላለች፡፡

ከአሜሪካ የቦምብ ድብደባ በኋላም ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን እንድትዘጋ የሀገሪቱ ፓርላማ መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን ይህ ውሳኔ እንዲተገበር ደግሞ የኢራን ጠቅላይ ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤትን ይሁንታ እስከዛሬ ድረስ እየጠበቀ ይገኛል፡፡

የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ የተለያዩ የነዳጅ ምርቶችን የጫኑ መርከቦች በዋነኝነት የሚተላለፉበት ሲሆን የዓለም አንድ አምስተኛው ወይም ከ20 በመቶ በላይ የነዳጅ ፍጆታ በዚሁ ሰርጥ በኩል ነው የሚሳለጠው፡፡

በየቀኑ ብቻ 20.3 ሚሊዮን በርሜል የነዳጅ ምርት ይተላለፍበታል የሚባለው የሆርሙዝ ባህር ሰርጥ ቢዘጋ ኢትዮጵያን ጨምሮ ህንድ፣ ቻይና፣ ጃፓን፣ ደቡብ ኮሪያና የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የገፈቱ ቀማሽ ይሆናሉ፡፡

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ የነዳጅ ምርቶችን በከፍተኛ ወጭ የሚያስገቡ ሀገራት በዚሁ የመካከለኛው ምስራቅ ግጭት የተነሳ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ የዋጋ ንረቱ በቀጥታ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል፡፡

እንዴት የሚለውን ደግሞ እንመልከት!

ዘ ኦቭዘርቫቶሪ ኦፍ ኢኮኖሚክ ኮምፕሌክስ የተባለና ዓለም አቀፋዊ የንግድና ኢኮኖሚያዊ መረጃዎችን በማቅረብ የሚታወቀው የበይነ መረብ የመረጃ ማዕከል ይዞት የወጣው መረጃ እንደሚያመላክተው ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2023 ብቻ 2.5 ቢሊዮን ዶላር አውጥታ ድፍድፍ ነዳጅ በመግዛት ከዓለም 72ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡

እንደመረጃው ከሆነ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2022 እና 2023 ድፍድፍ ነዳጅ ከገዛቻቸው ሀገራት መካከል የገልፍ ሀገራት ቀዳሚ ሲሆኑ፣ ኩዌት ደግሞ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ነዳጅ አቅራቢ በመሆን ቅድሚያውን ትይዛለች ፤ ከኩዌት በማስከተልም ሳዑዲ አረቢያና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ይከተላሉ፡፡

ታዲያ እነዚህ ነዳጅ ሻጭ ሀገራት ምርታቸውን ለማጓጓዝ አብዛኛውን የሆርሙዝ ባህረ ሰርጥን የሚጠቀሙ እንደመሆናቸው ይሄው መተላለፊያ ከተዘጋ የነዳጅ ዋጋ ከ13 በመቶ በላይ ሊጨምር እንደሚችል ነው ትንበያዎች የሚያመለክቱት፡፡

ከትላንት ወዲያ ንጋት አሜሪካ የኢራን ኒውክሌር ማብላያዎችን በቦምብ ከደበደበች በኋላ እንኳን የነዳጅ ዋጋ ላይ ወደ 1.4 በመቶ ገደማ ጭማሪ መስተዋሉን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

ኢትዮጵያም በነዳጅ ግብይት በኩል የሆርሙዝ ሰርጥን ከሚጠቀሙ ሀገራት ጋር ቀጥተኛ የንግድ ትስስር ያላት እንደመሆኑ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ቀውስ ጫናው አይቀሬ ያደርገዋል፡፡

የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ዴስክ ይሄንኑ ጉዳይ በተመለከተ ለነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት እንዲሁም ለንግድና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስትር የሆርሙዝ ሰርጥ ቢዘጋ በኢትዮጵያ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ይኖረው ይሆን?! የሚለውን ለመጠየቅ ያደረግነው ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራ አልተሳካም፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews




ዘንድሮ በአዲስ አበባ መስተዳድር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከተፈተኑ 70 ሺህ 525 ተማሪዎች ዉስጥ 62 ሺህ 639 ተማሪዎች ወይም 88 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደቀጣዩ ክፍል መዘዋወራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ለአካል ጉዳተኞችና ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የማለፊያ ነጥቡ 45 በመቶ እና ከዛ በላይ እንዲሆን መወሰኑን የገለፀው ቢሮው በዚህ ዓመት ከተፈተኑት 168 ተማሪዎች ውስጥ 151 የሚሆኑት ወደቀጣይ ክፍል ማለፋቸውንና የ2017 ዓ.ም አጠቃላይ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ትልቁ ውጤት 97 ነጥብ 3 ሆኖ መመዝገቡን ገልጿል::

ውጤቱን ለማየት ከዚህ በማስከተል ያስቀመጥንላችሁን ማስፈንጠሪያ መጠቀም ትችላላችሁ 👉 https://aa.ministry.et/#/result
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የኢትዮጽያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአትሌቶች ይልቅ ለፌዴሬሽኑ የበላይ አመራሮች ከፍተኛ የሽልማት ክፍያ ከህግ ውጭ እየፈፀመ መሆኑ ተነገረ።

ይህ የተነገረው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ዛሬ ለህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት ባቀረበው የሂሳብ ህጋዊነትና ክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ላይ ነው።

ፌዴሬሽኑ በዉጭ ሃገር ውድድር ለሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ከሚከፈለው ሽልማት በላይ ለፌዴሬሽኑ ሰራተኞችና አመራሮች ከፍተኛ ክፍያ እንደሚፈጽም ነው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት በሪፖርቱ የገለፀው።

ፌዴሬሽኑ ከመንግስት ለተሸላሚዎች የሚሰጥ ሽልማትንም ሙሉ በሙሉ አለማስተላለፉ ተነግሯል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🇺🇸🇮🇱🇮🇷የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እስራኤልና ኢራን ደርሰውበት የነበረውን የተኩስ አቁም ስምምነት መጣሳቸውን ገልፀው እስራኤል በቴህራን ላይ ተጨማሪ ጥቃት እንዳትፈፅም አሳስበዋል።
🇺🇸🇮🇱🇮🇷የኢራን የጤና ሚኒስቴር እስራኤል ባለፉት 12 ቀናት ባካሄደችው ጥቃት 606 ሰዎች ተገድለው ከ5,300 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን አስታወቀ።
🇺🇸🇮🇱🇮🇷የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ አሜሪካ ከሰሞኑ በቴህራን ላይ በፈፀመችው ጥቃት ኢራን ከዚህ በኋላ የኒውክለር የጦር መሳሪያ ማምረት እንዳትችል ሆናለች ሲሉ ተናገሩ።
🇺🇸🇮🇱🇮🇷የኢራን የአቶሚክ ኢነርጂ መ/ቤት ዋና ኃላፊ ሞሀማድ ኢስላሚ በበኩላቸው ሀገራቸው የኒውክለር መርሃግብሯን መልሳ ለመጀመር ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል።
🇺🇸🇮🇱🇮🇷እስራኤል በቴህራን ላይ ወሰደችው እርምጃ አንድ የኢራን የኒውክለር ሳይንቲስት ከነቤተሰቦቹ መገደሉ ተገለጸ።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


ሊ ኗሪነቱ በቻይና ዥጃንግ ግዛት ውስጥ ነው፤ ሺኣሚ ኤስ-7 ማክስ የተሰኘች ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና በቅርቡ ገዝቶ ደስታውን በደንብ ሳያጣጥም ከገዛት መኪና ጋር አለመግባባት ፈጥሯል፡፡

ይህ ሊሆን የቻለው ደግሞ ሊ በተፈጥሮው አይኖቹ እጅግ በጣም ጠባብ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ ከገዛት መኪና ፊት ለፊት ያለውና የአሽከርካሪውን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠረው ሴንሰር ትንሽ ማሽከርከር እንደጀመረ “እባክህ ለደህንነትህ በጥንቃቄ አሽከርክር፤ ደክሞሃል እረፍት አድርግ!” የሚል ማስጠንቀቂያ በተደጋጋሚ ያሰማዋል፡፡

ታዲያ ሊ ማሽከርከር ከጀመረ ከ2 ደቂቃ በኋላ ይሄው ማስጠንቀቂያ ያለማቋረጥ ይስተጋባል፤ ሁኔታው እያበሳጨውና እየረበሸው እንደመጣም ይናገራል፡፡ ዓይኑን በጣም ከፍቶ በሚያሽከረክርበት ጊዜ ደግሞ ምንም አይነት የማስጠንቀቂያ ድምጽ እንደማይሰማ ይናገራል፡፡

ሊ እኔ በገዛኋት ዘመናዊ መኪና እየተሰቃየሁ ያለሁት ዓይኔ ትንሽ በመሆኗ ምክንያት ነው በማለት ሁሉንም ድርጊቶች በግል የማህበራዊ ሚዲያው ካጋራ በኋላ በብዙዎች ዘንድ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

በቻይና አብዛኛውን ጊዜ ዓይናቸው ጠባብ የሆኑ ዜጎች እንደ ሊ አይነት ችግር እንደሚገጥማቸው ግለሰቡ ካጋራው ቪዲዮ ስር ሃሳባቸውን የሰጡ ሰዎች የተናገሩ ሲሆን እንደ ሊንክ እና ኮ፣ ዴፓል፣ ሺኣሚና ሌሎችም የመኪና ብራንዶች ተመሳሳይ አይነት የማንቂያ ድምጾችን እንደሚያሰሙ ኦዲቲ ሴንትራል ድንቃድንቅ ብሎ ይዞት በወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

ሌላው አግራሞትን የሚያጭረው ነገር ሊ ከገዛ መኪናው ጋር አላግባባ ያለው ነገር ከመኪናው ምስለ መመልከቻ ወይም ዳሽ ቦርድ ላይ ያለውና ያለማቋረጥ ይረብሸኛል ያለው ድምጽ በቀላሉ ሴቲንግ ውስጥ ገብቶ ማስተካከል የሚቻል መሆኑን አምራች ኩባንያው መግለጹ ነው፡፡


የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የሰኔ 17/2017 ዓ.ም የእኩለ ቀን 7፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፦

🎯በኳታር ዶሃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አሁን ላይ በቀጠናው ያለውን ሁኔታ ተከትሎ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

🎯ርዕሰብሔር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የአሜሪካ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ በተለያዩ የግብርና ዘርፎች መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል።

🎯\የኢትዮጵያ ቡና ላኪዎች በአሜሪካ የቡና ገበያ ላይ የበለጠ ለመሳተፍ ያግዛቸዋል የተባለ ምክክር በአሜሪካ ኤምባሲ የውጭ ገበያ አገልግሎት ዘርፍ አዘጋጅነት ተካሂዷል።

🎯በ28 አገራት ከ7 ሺህ 500 በላይ የቡና መሸጫዎች አሉት የተባለው ኮቲ ኩባንያ የኢትዮጵያን ቡና በመግዛት እሴት ጨምሮ በቻይናና ሌሎች አገራት ሊያቀርብ እንደሆነ ተሰምቷል።

🎯የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት በኋላ እንደሚለቀቅ የከተማዋ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


በኳታር ዶሃ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዛው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን አሁን ላይ በቀጠናው ያለውን ሁኔታ ተከትሎ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ሲል ጥሪ አቅርቧል።

ኢራን በኳታር ዶሃ አካባቢ ያለውን የአሜሪካ የጦር ሰፈር በሚሳኤል መደብደቧን ያስታወሰው ኤምባሲው በዶሃ ከፍተኛ ፍንዳታ ተሰምቷል ነው ያለው።

በመሆኑም በሀገሪቱ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በመጠለያቸው እንዲቆዩ የመከረው ኤምባሲው በሀገሪቱ መንግሥት የሚወጡ ይፋዊ መመሪያዎችን እንዲተገብሩም ሲል ነው መልዕክት ያስተላለፈው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ለድሬዳዋ ፖሊስ እጁን የሰጠው ጅብ!

በድሬዳዋ ከተማ ሰባተኛ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ትናንት አንድ የነጋበት ጅብ የአካባቢውን ማኅበረስብ በማስደነገጡ ተሰባስበው በዱላ፣ ድንጋይ እና ሌሎች ነገሮች ድብደባ እንዳደረሱበት ፣ ከዛም ወደ ፖሊስ ጣቢያ ማቅናቱን የከተማዋ ፖሊስ ግርምትን አጭሮብኛል ብሎ በማሕበራዊ ገፁ ባጋራው መረጃ ተመልክተናል፡፡

ነገሩ እንዲህ ነው ፣ ድብደባውን መቋቋም የከበደው ጅብ ህይወቱን ለማትረፍ እግሬ አውጭኝ በማለት በአካባቢው የነበሩ የግል መኖሪያ ቤት የንግድ ድርጅት የመንግስት ተቋማትን አልፎ ሳቢያን በተሰኘው አካባቢ በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ ቢሮ ሰተት ብሎ በመግባት እንደተደበቀ ተገልጿል፡፡

የድሬዳዋ ፖሊስ ማህበረሰብን ካረጋጋ በሗላ ከዱር እንሰሳ ጥበቃ ጋር በመወያየት ጅቡን ማህበረሰቡን በማይጎዳ መልኩ ወደ ጫካ እንዲለቀቅ ማድረጉን አስታውቋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


እስራኤል እና ኢራን የደረሱት እና ተግባራዊ መሆን የጀመረዉ የተኩስ አቁም ስምምነት 24 ሰአታት ሳይሞላዉ መጣሱ ሲነገር በሌላ በኩል የእስራኤሉ የመከላከያ ሚኒስትር ኢስራኤል ካትዝ ስምምነቱን በጣሰችዉ ቴህራን ላይ እርምጃ ለመዉሰድ ዝተዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የማለፊያ ውጤት 50% እንዲሆን በዛሬው እለት መወሰኑን አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የዘንድሮው የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከአምናው የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የ2017 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰአት በኋላ ይፋ ይሆናል ነው የተብለው።

በቀጣይ ጥቂት ቀናትም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ውጤት ይፋ ይደረጋል ነው የተባለው።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 ዓ.ም 70 ሺህ 525 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መውሰዳቸው ይታወሳል።

መረጃውን ከአዲስ አበባ ትምህር ቢሮ ነው ያገኘነው፡፡
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🇺🇸🇮🇱🇮🇷በአሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይፋ የተደረገው የእስራኤል እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መሆን ጀመረ።
🇺🇸🇮🇱🇮🇷በተያያዘ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት እስራኤል እና ኢራን ተግባራዊ መሆን የጀመረዉን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዳይጥሱ አሳሰቡ።
🇺🇸የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታናያሁ በአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ይፋ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ቴላቪቭ መቀበሏን ተናገሩ ።
🇺🇸🇮🇱🇮🇷ኢራን ከእስራኤል ጋር የደረሰችዉን የተኩስ ስምምነት ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ
አንድም ሚሳኤል አለማስወንጨፏ ተዘግቧል።
🇺🇸🇮🇱🇮🇷የጀርመኑ መራሄ መንግስት ሜርዝ ፍሬድሪክ እስራኤል ና ኢራን ተፈፃሚ መሆን የጀመረዉን የተኩስ ስምምነት እንዲያፀኑ ጠይቀዋል።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የሰኔ 16/2017 ዓ.ም የምሽት 1፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፦

🎯ለተቋማት የሚመደበው በጀት በትክክል ለታለመለት ዓላማ መዋሉን የገንዘብ ሚኒስቴር ሊከታተል እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

🎯ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር የሚያደርጉትን ውይይት ዛሬ ከህዝብና ከግል መገናኛ ብዙሃን ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር ባካሄዱት ውይይት መቋጨታቸውን አስታውቀዋል።

🎯ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ከጤና ባለሙያዎች ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥት ለህክምናው ዘርፍ 130 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት መበጀቱን ገልጸዋል።

🎯ነዳጅ እያለ በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት በማይሰጡና ህገወጥ ተግባር ላይ በተሰማሩ የነዳጅ ኩባንያዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።

🎯በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ረፋድ 3 ሰዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በተለምዶ አባሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ረፋድ 3 ሰዓት ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ9 ሰዎች ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

ከሟቾቹ መካከል የ3 ዓመት ዕድሜ ያለው ህፃን የሚገኝበት ሲሆን በ8 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

አደጋው ሊከሰት የቻለው ከሃይሌ ጋርመንት ወደ ዩኒሳ አደባባይ ይጓዝ የነበረ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አውቶቡስ ከሌላ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱና መንገድ ስቶ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ በመግባቱ መሆኑ ታውቋል።

መረጃው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኪሚሽን ነው፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🇺🇸🇮🇱🇮🇷እስራኤል በኢራኑ የፎርዶ የኒውክሌር ጣቢያ ላይ ዛሬ አዲስ ጥቃት መፈፀሟ ተነግሯል።

🇺🇸🇮🇱🇮🇷የአውሮፓ ህብረት ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን እንዳትዘጋ ጥሪውን አቀረበ።

🇺🇸🇮🇱🇮🇷የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አርጋቺ ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ዋሽንግተን በቴህራን በፈፀመችው ጥቃት ዙሪያ በሞስኮ መምከራቸው ተነግሯል።

🇺🇸🇮🇱🇮🇷ኢራን ዛሬ ማለዳ በእስራኤል ላይ በሰነዘረችው የሚሳኤል ጥቃት 8ሺ ሰዎች የመብራት አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል ተባለ።

🇺🇸🇮🇱🇮🇷የአለም አቀፉ የአቶሚክ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ራፋኤል ግሮሲ በኢራን የኒውክለር ተቋማት ላይ ክትትል ለማካሄድ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቁ።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews






የኢቢኤስ አዲስ ነገር ዲጂታል ሚዲያ የሰኔ 16/2017 ዓ.ም የእኩለ ቀን 7፡00 ሰዓት የሀገር ውስጥ ዋና ዋና ዜናዎች፦

🎯ነዳጅ እያለ በሙሉ አቅማቸው አገልግሎት በማይሰጡና ህገወጥ ተግባር ላይ በተሰማሩ የነዳጅ ኩባንያዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጠል የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ አስታወቁ።

🎯የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሰሞኑን በአዲስ አበባ የተከሰተው የነዳጅ እጥረት አንድ አንድ የነዳጅ አመላላሽ ሹፌሮች ከጅቡቲ የጫኑትን ነዳጅ ዋጋ ይጨምራል በሚል ሆን ብለው መንገድ ላይ በማዘግየታቸው የተፈጠረ መሆኑን ጠቁሟል።

🎯ሀገር በቀል የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዓለም አቀፋዊ ሥራዎችን እንዲሰሩ የሚፈቅድ ህግ ሊዘጋጅ ነው ተብሏል።

🎯ጤና ሚኒስቴር በሀገሪቱ በሚገኙ ሁሉም ክልሎች በአጠቃላይ 125 የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከላት ተደራጅተው ለአገልግሎት ዝግጁ ሆነዋል ብሏል።

🎯በኢትዮጵያ ከሚገኙ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖቹ መካከል ቦሌ ለሚና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሙሉ በሙሉ በባለሃብቶች ተይዘዋል ተብሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


ትላንት እሁድ ከለሊቱ 9 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ሳሪስ አካባቢ በአንድ ፔንሲዎን ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ 2 ሰዎች በጪስ ታፍነዉ ህይወታቸዉ ማለፉን የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

በጪስ ታፍነዉ በአንድ ክፍል ዉስጥ ህይወታቸን ያጡት የ30 ዓመት ወንድና የ25 ዓመት ሴት መሆናቸውን የጠቆመው ኮሚሽኑ የፔኔሲዮኑ የዉስጥ ክፍሎች እሳትን መቋቋም ከማይችሉና አደጋን አባባሽ ከሆኑ ቺፑድና ጣዉላ የተከፋፈሉ መሆናቸዉ እሳቱ እንዲባባስና ጪስ እንዲፈጠር ምክንያት መሆኑን ነው የተነገረው።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ባደረጉት ርብርብ በፔንሲዮኑ ተኝተዉ የነበሩ ሌሎች 6 ሰዎችን ማትረፍ መቻሉ ሲገለጽ የእሳት አደጋዉ ሳይስፋፋ በፍጥነት መቆጣጠር ተችሏል ብሏል ኮሚሽኑ።

የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስራ አመራር ኮሚሽን ፔንሲዮኖችና የሆቴል አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች እንግዶች የሚያርፉባቸዉን ክፍሎች የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ያሟሉ በማድረግ የደንበኞቻቸዉን ደህንነት ለመጠበቅ አስፈላጊዉን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው ነው የገለፀው።

ኮሚሽኑ አክሎም የአደጋ ደህንንነት መስፈርትን በማያሟሉ አገልግሎት መስጫዎች ላይ አስፈላጊዉን ዕርምጃ እንደሚወስድ ማሳሰቢያ መስጠቱን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »