Postlar filtri


የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

እሁድ ሰኔ 08 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በመካኒሳ ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ሥራ ስለሚያከናውን በሐና ማርያም፣ በጋርመንት፣ በላፍቶ፣ በጀሞ፣ በጀርመን አደባባይ፣ በሀጫሉ ጎዳና፣ በካፒታል ሲሚንቶ ፋብሪካ፣ በቆሼ እና አካባቢው የአቅርቦት ኃይል ተቋርጦ ይቆያል፡፡

በተመሳሳይ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀኑ 8:30 ድረስ የሲዳማ ሪጅን የጥገና ሥራ ስለሚያከናውን በሃዋሳ ከተማ ታቦር ሴራሚክ እና በአካባቢው ኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡

በመሆኑም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተከናውኖ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ከቁልፍ ደንበኞችና እና ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጭሮ ሪጅን በዛሬው ዕለት ከቁልፍ ደንበኞች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

በፎረሙ አስተማማኝና ጥራት ያለው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመስጠት፣ አዳዲስ ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲሁም ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ገንቢ ሃሳቦች ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

በተጨማሪም ሪጅኑ የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ ለማሳደግ፣ የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ እና ከተቋረጠም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት በትኩረት መስራት እንዳለበት ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የጅማ ሪጅን የአገልግሎት አሰጣጡ በሚሻሻልበት ሁኔታ፣ የደንበኞች እርካታ በሚሻሻልበት እና የሃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ለመቀነስ እየተከናወኑ በሚገኙ ተግባራት ዙሪያ ከቁልፍ ደንበኞችና እና ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።

ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial
[Telegram] https://t.me/eeuethiopia
[Website] http://www.eeu.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/@EthiopianElectricUtility
[Tiwtter] https://x.com/EEUEthiopia
[TikTok] https://www.tiktok.com/@ethiopian.electri
[Whatsapp] https://www.whatsapp.com/channel/0029VbAAvBDE50UZXJlIl507


ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎት ተመልሷል

በድሬዳዋ ከተማ ቢካፒታል ሆቴል፣ ኒው ሌቭል ሆቴል፣ ኮካ ኮላ ፋብሪካ፣ ግሪክ ካምፕ፣ ድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከንቲባ ቢሮ፣ ከዚራ ሙሉ በሙሉ፣ ጎሮ በከፊል፣ ገንደቆሬ፣ መምሪያ፣ ብሪጅ፣ ሰኢዶ እና አካባቢዎቻቸው ተቋርጦ የነበረው የኃይል አቅርቦት ወደ አገልግሎትተመልሷል።

የጥገና ስራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት ለጠበቃችሁን ክቡራን ደንበኞቻችን ከልብ እናመሰግናለን።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በድሬዳዋ ከተማ በኤሌክትሪክ መስመር ላይ በደረሰ ጉዳት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

የቤት ግንባታ ሲከናወን በኤሌትሪክ መስመር ላይ ጉዳት በመድረሱ ከትናንት ሌሊት ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ ቢካፒታል ሆቴል፣ ኒው ሌቭል ሆቴል፣ ኮካ ኮላ ፋብሪካ፣ ግሪክ ካምፕ፣ ድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ከንቲባ ቢሮ፣ ከዚራ ሙሉ በሙሉ፣ ጎሮ በከፊል፣ ገንደቆሬ፣ መምሪያ፣ ብሪጅ፣ ሰኢዶ ሙሉ በሙሉና አካባቢዎቻቸው የኤሌትሪክ ኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡

በአካባቢዎቹ የምትገኙ ውድ ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ፤ ጥገናው ተከናውኖ መስመሩ ወደ አገልግሎት እስኪመለስ ድረስ በትግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እያሳወቅን፤ በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሱ መሰል ጉዳቶች ለኃይል መቋረጥ መንስኤ በመሆናቸው ለመከላከል በሚደረገው ጥረት የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ የተለመደ ትብብራችሁን እንጠይቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ ስርቆቶችና ውድመቶች ለመከላከል የፀጥታ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡


ዛሬ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀን 9:30 የመልሶ ግንባታ ሥራ ለማከናወን በእቅድ የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች:-


👉እህል በረንዳ ፣ አውቶቢስ ተራ፣ አዲስከተማ ት/ቤት፣ገነሜ ት/ቤት፣መርካቶ፣አብነት፣ተክለኃይማኖት ፣አማኑኤል ቤ/ክ፣ብርጭቆ፣አስኮ፣ ፊሊጶስ ቤ/ክ፣እስላም መቃብር፣ ሎሚ ሜዳ፣ ጠሮ

👉ንፋስስልክመምሪያ፣ፔፕሲ፣ቄራ፣አርባምርጭ አሳ፣ጨርቆስ፣እውቀት ፋና፣ካራ ቆሬ፣ረጲ፣ወሌ ኮንዶሚኒየም ፣ወለቴ

👉አርኪውሃ፣ሱሉልታ፣ለገዲማ፣
ጫንጮ፣ለገጣፎ፣ለገዳዲ፣44 ማዞሪያ፣ ቡራዩ፣ሲዲሲ፣ኮሰሮ፣10 ኪሎ፣ቀንብሬ፣ አፍሪካ ልህቀት ማእከል

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ውድ ደንበኞቻችን ነገ ቅዳሜ ሰኔ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ድረስ በሁሉም የተቋማችን ሪጅኖች እና አገልገሎት መስጫ ማዕከላት አገልግሎት ማግኝት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

7.2k 0 70 19 27

የዲስትሪቢዩሽን መሰረተ-ልማት ማስፋፋያና ማሻሻያ ማስተር ፕላን ጥናት እየተካሄደ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገር አቀፍ የዲስትሪቢዩሽን መሰረተ-ልማት ማስፋፋያና ማሻሻያ ማስተር ፕላን ጥናት እያካሄደ ደረ መሆኑን የስትራቴጂክ ፕላኒንና ኢንቨሰትመንት ሥራ አስፈፃሚ አቶ ገመቹ ይመር ገልፀዋል፡፡

የዲስትሪቢዩሽን መሰረተ-ልማት ማስፋፋያና ማሻሻያ ማስተር ፕላን ጥናቱ የመጪውን የ25 አመት የኃይል ፍላጎት ለማወቅ የሚያግዝ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስፈፃሚው የመሰረተ-ልማት ማስፋፊያና የመልሶ ግንባታ አቅም ማሳደግ እቅድ፣ የኤሌክትሪክ መስመር እና ትራንስፎርመር የኃይል ጭነት ትንበያ፣ የአካባቢና የማህበራዊ ተፅዕኖ ምዘና፣ የመሰረተ-ልማቶችን በቴክኖሎጂ የማስተሳሰርና ሌሎችን ጉዳዮችን የሚያካትት መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የማስተር ፕላን ጥናት ከበፊቱ የሚለየው የሕዝብ እድገት፣ የከተማ እድገት፣ የነፍስ-ወከፍ ኢነርጂ ፍላጎት ባሻገር ቴክኖሎጂ እድገት የሚጠይቀውን የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው ተብሏል፡፡

ጥናቱን የሚደረገው ከዓለም ባንክ በተገኘ 4 ነጥብ 9 የአማሬካ ዶላርና 12 ነጥብ 9 ብር ሲሆን አማካሪው የኢራን ሞኔንኮ እንደሆነ አቶ ገመቹ ገልፀዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ጥናቱ 25 በመቶ የተጠናቀቀ ሲሆን እስከ መጪው ዓመት ጥር ድረስ ሙሉ ለሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል፡፡

ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial
[Telegram] https://t.me/eeuethiopia
[Website] http://www.eeu.gov.et


ዛሬ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ.ም.ከጠዋቱ 2:30 እስከ ቀን 9:30 ድረስ በአዲስ አበባ እና ሸገር ከተሞች በእቅድ የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት :-


👉ጀሞ  -2 ኮንዶሚኒየም ፣ የስ ውሃ ፣ዓለምገና ማርስ ብስኩት ፣ ፉሪ አካባቢ

👉ጨፌ ኮንዶሚኒየም፣ ማሩ ብረታ ብረት አካባቢ፣ ቁስቋም አካባቢ፣ ሸገር ዳቦ፣ ሃና ማርያም ፣ ሰፈራ

👉አየር ጤና ፣ናትራን ፣ ለማ ነገዎ ሰፈር፣ አየር ጤና ሞቢል ጋዝ

👉ስልጤ ሰፈር መውጫ፣ ፋኑኤል ቤ/ክ፣ አጃንባ ኮንዶሚኒየም


#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


የፕሮግራም_ጥቆማ !

ውድ ደንበኞቻችን ዛሬ ምሽት 3፡20-3፡40 በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ /ኦ.ቢ.ኤን/ ቴሌቪዥን በአፋን ኦሮሞ ቋንቋ የሚተላለፈውን ተከታታይ የቴሌቪዥን ፕሮግራማችንን እንድትከታተሉ በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡

Odeeffannoo Kabajamtoota maamiltoota keenyaaf!
Hardha galgala 3፡20 hanga 3፡40-tti sagantaan Afaan Oromootiin torban lama gidduutti altokko Oromiyaa Biroodkaastiing Neetwoork (OBN) irratti tamsa’u akka hordoftan kabajaan isin affeerra.

TAJAAJILA ELEKTIRIKII ITIYOOPHIYAA

6k 0 3 17 23

Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ለቴሌቪዥን አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች በሙሉ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1278/2015 ዓ.ም መሰረት ወርኃዊ የኤሌክትሪክ የፍጆታ መጠናቸው ከ50 ኪሎ ዋት ስዓት በላይ የሆኑ ደንበኞች ለአንድ የቴሌቪዥን አገልግሎት በየወሩ 10 ብር ከወርሃዊ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ላይ በመጨመር እየሰበሰበ ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) ገቢ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ነገር ግን ከአንድ ቴሌቪዥን በላይ ለሚጠቀሙና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል ዓመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ለማይከፍሉ ዜጎች የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) በዘረጋቸው ሌሎች አማራጮች የሚሰበሰብ መሆኑን እየገለፅ፤ ከወርሃዊ ኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ጋር ለተከፈለ የአገልግሎት ክፍያ ተጨማሪ የክፍያ ጥያቄ የማይጠየቅበት መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

ሆኖም መሰል ጥያቄዎች ከመጡ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቲቪ) በማመልከት ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ተመላሽ የሚደረግ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

6.3k 0 15 20 31

በኤሌክትሪክ በአንድ ቀን የሥራ ዘመቻ ከ200 በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በወላይታ ሪጅን ስር የሚገኙ 2 የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በኤሌክትሪክ በአንድ ቀን የሥራ ዘመቻ 219 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አድርገዋል፡፡

የሃላባ እና ቦዲቲ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የሥራ ዘመቻውን ከጀመሩበት ግንቦት 18 ቀን ጀምሮ 2 መቶ19 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ችለዋል፡፡

ማዕከላቱ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያደረጉት የተለያዩ የመልሶ ግንባታ ስራዎችን በማከናዎን አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ችለዋል፡፡

በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሆሳዕና ቁጥር አንድ አገልግሎት መስጫ ማዕከል 377 አዳዲስ ደንበኞችን በኤሌክትሪክ በአንድ ቀን ዘመቻ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

አገልግሎት መስጫ ማዕከሉ ነሬባ ሮማ እና ቢሮ ዋቸሞ አካባቢዎች ላይ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን በነሬባ ሮማ የሚገኙ ነዋሪዎች እንደ ትራንስፎርመር ምሰሶ እና መሰል የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በራሳቸው ወጪ በመሸፈን የኤሌክትሪከ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በሌላ በኩል በቢር ዋቸሞ 2500 ሜትር መካከለኛ እና 2300 ሜትር ዝቅተኛ መስመር የተዘረጋ ሲሆን የአንድ ትራንስፎርመር ተከላም ሥራ ተከናውኗል፡፡

በአጠቃላይ የቢር ዋቸሞ አካባቢ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከ 3.8 ሚሊየን በላይ ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial


አዲስ አባበ እና ሻገር ከተሞች የቅድመ ጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል በእቅድ የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው ቦታዎችን ለማየት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ: http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/power-interruption?lang=am


ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለተቋማችን እውቅና ሰጠ

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ማኔጅመንት አባላት ተቋማችን ባለፉት ዓመታት ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት በመስራት ላበረከተው አስተዋፅኦ ዛሬ በተቋማችን ዋና መ/ቤት በመገኘት እውቅና ሰጥቷል።

በእውቅ ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የኔትወርክ ኢንፍራስትራክቸር ማኔጅመንት ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ገበየሁ ሊካሳ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፉት ረጅም አመታት ባደረገው እንቅስቃሴ የሀገራችንን ገፅታ በመገንባት ረገድ ታላቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን ጠቅሰው ተቋማችንም እንደ ከዚህቀደሙ ሁሉ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በእውቅና ምስጋና ፕሮግራሙ ላይ የተቋማችን ኔትወርክ ኢንፍራስትራክቸር ማኔጅመንት ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ገበየሁ ሊካሳን ጨምሮ ሌሎች የተቋሙ የሥራ ሃላፊዎች ተገኘተዋል።

የእውቅና ፕሮግራሙ የተካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 25ኛ አመት ክብረ በዓል በማስመልከት ነው።

ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial
[Telegram] https://t.me/eeuethiopia
[Website] http://www.eeu.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/@EthiopianElectricUtility
[Tiwtter] https://x.com/EEUEthiopia
[TikTok] https://www.tiktok.com/@ethiopian.electri
[Whatsapp] https://www.whatsapp.com/channel/0029VbAAvBDE50UZXJlIl507


የሥራ ማስታወቂያ

8k 0 97 45 26

ውድ የድህረ ክፍያ ተጠቀሚ ደንበኞቻችን ባሉበት ሆነው ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎን በቀላሉ በቴሌ ብር፣ በሲቢኢ ብር፣ በሲቢኢ ሞባይል ባንኪንግ ወይም በአዋሽ ብር ፕሮ አማካኝነት ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይፈፅሙ፡፡ በወቅቱ ባለመክፈል ከሚመጣብዎ ተጨማሪ የአገልግሎት ቅጣትና ወጪም ይዳኑ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

7.2k 0 13 24 18

ተቋማቱ በመቀናጀት ጊዜን የቀደሙ ሥራዎች መስራት አለባቸው - የሁለቱ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች

አስተማማኝና ተደራሽ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናበው ጊዜን የቀደሙ ሥራዎችን ማከናወን እንዳለባቸው የሁለቱ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ማናጅመንት ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ገበየሁ ሊካሳ እንደገለፁት ሁለቱ ተቋማት እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ በአንድ ተቋም ሥር የኃይል አቅርቦቱን ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ሥራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል፡፡

የኃይል ፍላጎት እያደገ በመምጣቱ እና ዘርፉ ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ መሆኑን በመረዳት ዓለምአቀፋዊ ተሞክሮዎችን በመገምገም አቅርቦቱንና ተደራሽነቱን ለማሳደግ ሲባል በጥናት ላይ በመመስረት ሁለቱ ተቋማት ራሳቸውን ችለው እንዲደራጁ መደረጋቸውን ተናግረዋል።

የተቋማቱ ወደ ሁለት መከፈል ትኩረት እንዳይበታተን በማድረግ እንዲሁም የፋይናንስ ጫናዎችን በማቃለል አቅርቦቱን ከማዘመን እና ተደራሽነቱን ከማስፋት አንጻር አበረታች ውጤት እንዲመዘገብ ማስቻሉን ጠቁመዋል።

ዶ/ር ገበየሁ አክለውም የውስጥ አሰራርን በማዘመን የነባር ኔትወርኮችን መልሶ ግንባታ እና የአቅም ማሳደግ ሥራዎችን በማከናወን የኃይል መቆራረጡን በመቀነስ ተደራሽነቱን ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።

በዚህም ባለፉት 11 ዓመታት ተቋማቱ ባከናወኗቸው ሥራዎች የደንበኞችን ቁጥር ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ወደ 5 ነጥብ 2 ሚሊዮን እንዲሁም የተደራሽነት ሽፋኑን ከ30 በመቶ ወደ 54 በመቶ ከፍ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡

ተቋማቱ በአደረጃጀት ለሁለት ቢከፈሉም ሥራቸው ተመጋጋቢ እና ኔትወርኩም የተያያዘ በመሆኑ እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለመመለስና ተደራሽነቱን ለማሳደግ የጋራ የግንኙነት ጊዜ አስቀምጠው እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በበኩላቸው 78 ከመቶ ከግሪድ እንዲሁም 22 ከመቶ ከግሪድ ውጭ የኃይል አቅርቦቱን ተደራሽ ለማድረግ የተያዘውን ሀገራዊ ዕቅድ ለማሳካት ሁለቱ ተቋማት ተናበው መስራት እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡

የኃይል ተደራሽነቱን ከማሳደግ በተጨማሪ ቀደም ሲል የኃይል ተጠቃሚ የነበሩ አካባቢዎች የኃይል ፍላጎት በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መሆኑንና ይሄን ጥያቄ ለመመለስ ሁለቱ ተቋማት ተናበው ጊዜን የቀደሙ ሥራዎች መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ መናበቡን መዋቅራዊ አድርጎ ለመቀጠል በሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የሚመራና ሥራዎችን የሚገመግም ቡድን ተዋቅሮ እየተሰራ ነው።

ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃችን ለማግኘት ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
[Facebook] http://www.facebook.com/EEUOfficial
[Telegram] https://t.me/eeuethiopia
[Website] http://www.eeu.gov.et
[YouTube] https://www.youtube.com/@EthiopianElectricUtility
[Tiwtter] https://x.com/EEUEthiopia
[TikTok] https://www.tiktok.com/@ethiopian.electri
[Whatsapp] https://www.whatsapp.com/channel/0029VbAAvBDE50UZXJlIl507



18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »