የሰ/መ/ቁ.247605
በቤተሰብ ህጉ ድንጋጌ ከባልና ሚስት ያለ አንደኛዉ ተጋቢ ፊቃድ ወይም ስምምነት የተደረገ ዉል እንዲፈርስ የሚቀርብ ዳኝነት ጥያቄ ዉሉ መደረጉ ከታወቀበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወር ጊዜ ዉስጥ ሆኖ በማንኛዉም ሁኔታ ዉሉ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በሁለት ዓመት ጊዜ ዉስጥ መቅረብ እንዳለበት ይደነግጋል፡፡ ይሁንና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁጥር 105652 ላይ በሰጠዉ ዉሳኔ ከባልና ሚስት አንደኛዉ ተጋቢ ያለ ሌላኛዉ ተጋቢ ፊቃድ ወይም ስምምነት የተደረገ የስጦታ ዉል እንዲፈርስ የሚቀርብ የዳኝነት ጥያቄን አስመልክቶ ተፈፃሚነት ያለዉ የይርጋ ድንጋጌ የስጦታ ዉልን ልዩ ባህሪ መሠረት ያደረገ ሊሆን ይገባል የሚል ምክንያት በመስጠት፣ ተፈፃሚነት ያለዉ በቤተሰብ ህጉ ላይ የተመለከተዉ ሳይሆን በፍትሐብሔር ህጉ አንቀጽ 1845 ላይ የተመለከተዉ የአስር ዓመት የይርጋ ጊዜ ሊሆን እንደሚገባ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል በማለት ሰበር በስር ፍ/ቤት የቤተሠብ ህጉን መሠረት በማድረግ የተሠጠውን ብይን ሽሮታል።