⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Huquq


ዳንኤል ፍቃዱ ተስፋዬ በሁሉም የፌደራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃና የህግ አማካሪ
ስልክ - 0913158507 ወይም 0978554559
Daniel Fikadu Tesfaye Certified Attorney of law at all Federal Courts of Ethiopia.
Email- nurotekore@gmail. Com
⚖️⚖️Ethiopian Law by Daniel Fikadu channel ⚖️⚖️⚖️

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Toifa
Huquq
Statistika
Postlar filtri






ጠበቃ ሠብለ በዋስ እንድትፈታ ፍርድ ቤት ወስኗል።


የታክስ_ኦዲት_የሚከናወንበትን_ስርዓት_እና_የታክስ_ስሌት_ማስታወቂያ_የሚወጣበትን_አኳኋን_ስለመወሰን_የወጣ.pdf
5.8Mb
New tips ‼️
የታክስ ኦዲት የሚከናወንበትን ስርዓት እና የታክስ ስሌት ማስታወቂያ የሚወጣበትን አኳኋን ስለመወሰን የወጣ መመሪያ _ 1063/2025


#ግብር #መመሪያ #🔎🔎🔎


የአልኮል ምርቶች ከቴሌቪዥን እና ሬዲዮ ባለፈ በማህበራዊ ሚዲያዎችም ማስተዋወቅ ሊከለከል ነው‼️

የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ መሰናዳቱም ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለሰልጣን የአልኮል ምርቶችን በማህበራዊ ሚዲያዎች ማስተዋወቅን በከፊል የሚከለክል የህግ ረቂቅ ተሰናድቶ በሒደት ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።

ኢትዮጵያ ከዓመታት በፊት የአልኮል ምርቶችን እንደ ቴሌቪዥን እና ራዲዮ ባሉ መገናኛ ብዙኃን ማስተዋወቅ በህግ ማገዷ ይታወቃል።

የአልኮል አምራች ተቋማት በአሁን ሰዓት የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም፤ ምርታቸውን እያስተዋቁ እና ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች እየደረሱ ነው ተብሏል።

ከእነዚህ መካከልም የማህበራዊ ሚዲያ በብዛትና በተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀሙ እንደሆነ ተነግሯል።

ይህንን እየተስፋፋ የመጣውን በማህበራዊ ሚዲያ የአልኮል ማስታወቂያን በተቻለ መጠን ለመገደብ ታስቦ፤ የህግ ማዕቀፍ ተሰናድቶ በሒደት ላይ እንደሚኝ በኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የህግ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ፍሬሰላም ዮሴፍ ተናግረዋል ።
በኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን የተሰናዳው  ረቂቅ ህግ ወደ ጤና ሚኒስቴር መላኩንም ስራ አስፈፃሚዋ ጨምረው ተናግረዋል።
====================




ንብረት_ማስመለስ_አዋጅ_ቁጥር_13642017_1.pdf
39.2Mb
የንብረት ማስመለስ አዋጅ ቁ. 1364/2017

Asset Recovery proclamation 1364/2025






EIC Fee-1.pdf
3.5Mb
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች በዶላርና በብር የሚፈጸም የክፍያ መጠን።


የቴምብር ቀረጥ አከፋፈል ልክ

ሰኔ 12/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

📌 በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ መከፈል የሚገባው የቀረጥ መጠን ከታች በሠንጠረዥ እንደተዘረዘረው ይሆናል፡፡

📌 አንድ ሰነድ በተደጋጋሚ ተፈጻሚ ሲሆን ሊከፈል የሚገባ የቀረጥ መጠን እዚሁ ሠንጠረዥ ውስጥ የተመለከተ ነው፡፡

ምንጭ፥ የኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ግጽ🙏🏾

#ቴምብር_ቀረጥ #Stamp_Duty #ጥቆማ_Tip #ጠቅላላ_General

@Taxation_in_Ethiopia




ኧረ የሚዲያ/ዎች የዘገባ ስህተት...
የዶ/ሩ የንባብ ችግር ...
ወዘተ ብለን የተወዛገብንበት "ህግ" እነኋችሁ!!!



https://vm.tiktok.com/ZMSaRWydJ/


TIKVAH-MAGAZINE dan repost
በአዲስ አበባ ከተማ ለህግ ተመራቃዎች ለምን Judicial Training መስጠት አልተቻለም ?

የአዲስ አበባ ከተማ ተወላጅ የሆኑ የህግ ምሩቃን የ judicial training ስልጠና ባለመኖሩ የሥራ እድል ለማግኘት እንደሚቸገሩ በተደጋጋሚ ሲገልጹ ይስተዋላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያናገራቸው ምሩቃኑ "የ Judicial training ለእኛ አለመሰጠቱ  አንደኛ " ስራ አጥ አድርጎናል፣ ሁለተኛ ስራ የገባነውም በምንፈልገው የስራ መስክ ላይ እንዳንሰማራ አድርጎናል" ሲሉ ገልጸዋል።

"በክልሎች ያሉ ልጆች ግን ተመርቀው ሲወጡ በክልላቸው ስልጠና ይሰጣቸው እና በተማሩበት ዳኛና አቃቢ ህግ ይሆናሉ፣ እኛ ግን ይህን እያገኘን አይደለም።" ነው ያሉት።

አንድ ስሟን መጥቀስ ያልፈለገች የህግ ምሩቅ ከዚህ በተጨማሪ "ፍትህ ሚኒስቴር እና የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ የስራ እድል ለመፍጠር የስራ ማስታወቂያ ሲያወጡ ከሁሉም ክልሎች የሚመጡ የህግ ምሩቃን መወዳደር ይችላሉ። እኛ ግን ክልሎች ላይ ይህን እድል ለማግኘት እንገለላለን" ስትህ ታስረዳለች።

በጉዳዩ ላይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ፣ ፍትህ ሚኒስቴርን እና የኢፌዴሪ የህግና ፍተህ ኢንስቲትዩት እንዲሁም ትምህርት ሚኒስቴርን ለመጠየቅ ጥረት አድርጓል።

ፍትሕ ሚኒስቴር

ጉዳዩ የፌደራል የህግና ፍትህ ኢንስትቲዩትን ነው የሚመለከተው፡፡ እንደ ፍትሕ ሚኒስቴር ግን ስልጠናውን እንደ Requirement በቅጥር ሂደት ላይ አንጠይቅም።

መደበኛ ፈተናውን ያለፈ ባለሙያ ከቅጥር መለስ ተቋሙ የሚያዘጋጀውን የዐቃቢ ህግ የስራ ላይ ስልጠና ይወስዳል የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ

በስልክ እና በአካል ቢሮ ድረስ በመሄድ ሁሉንም የሥራ ክፍል ለግማሽ ቀን ተዘዋውረን በጉዳዩ ላይ ብንጠይቅም ምላሽ የሚሰጥ አካል አላገኘንም።

ምላሽ እንዲሰጡን የጠየቅናቸው የሥራ ክፍል ኃላፊዎችም ፍቃደኛ ያለመሆን እና እኔን አይመለከትም በሚል የተቋሙን ምላሽ ማካተት አልቻልንም። በጉዳዩ ላይ ተቋሙ ምላሽ ለመስጠት ክፍት ከሆነ ኃሳባቸውን ምናስተናግድ ይሆናል።

የኢፌዴሪ ህግና ፍትህ ኢንስትቲዩት

ተቋሙ ጉዳዩ እንደማይመለከተው እና የ Judicial trainig department ወደ  ትምህርት ሚኒስቴር መወሰዱን ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር

የ Judicial trainig department ወደ  ትምህርት ሚኒስቴር ተዛውሯል መባሉን ተከትሎ ከሚኒስቴሩ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

@TikvahethMagazine


For federal Attorneys !!!


Legal Aid Service Providers Interns

Company: Center for Justice (CJ)

👉 Click here to : Apply


⚖Ethiopian law by Daniel Fikadu Law office⚖ dan repost
Anti Money laundering Law -English from COM to HPR.pdf
640.0Kb
Anti Money laundering law Amharic from COM to HPR.pdf
494.2Kb
በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን
ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ DRAFT




Ethiopian Legal insight dan repost
ኢትዮጲያን ሌጋልቴክ የሚሰጣቸው ጥቅሞች

ዘመናዊ የሕግ አስተዳደር ሥርዓት ለጠበቆች አሠራራቸውን በማቀላጠፍ እና ቅልጥፍናን በማሻሻል ጉልህ ጥቅሞችን ይሰጣል።
ቁልፍ ጥቅሞቹ ፡የክስ እና የሰነድ አስተዳደር
፡ ዘመናዊ ስርዓቶች ጠበቆች የክስ መዝገቦችን እና ህጋዊ ሰነዶችን በብቃት እንዲያደራጁ፣ እንዲያከማቹ እና እንዲያነሱ ያስችላቸዋል።
ይህ ፋይሎችን ለመፈለግ የሚጠፋውን ጊዜ ይቀንሳል እና ሁሉም ተዛማጅ መረጃዎች በቀላሉ ተደራሽ መሆናቸውን ያረጋግጣል የደንበኛ እና የመረጃ አስተዳደር፡ እነዚህ ስርዓቶች የደንበኛ ዝርዝሮችን፣ ግንኙነቶችን እና የጉዳይ ታሪኮችን ለመከታተል፣ የደንበኛ አገልግሎትን እና ግንኙነትን ለማሻሻል ይረዳሉ።

ለዚህም በኢትዮጵያ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ ዲጅታል የሕግ ላይብራሪና ኬዝ ማኔጅመንት ሲስተም ለሁሉም የሕግ ባለሙያዎች ፣ ለሕግ ተማሪዎች ፣ ለነጋዴዎችና ለቢዝነስ ተቋማት ከፍተኛ አገልግሎት የሚሰጥ ነው።
ፕሌይ ስቶር በመግባት ሌጋልቴክ/LegalTech ብላችሁ በቀላሉ በመፈለግ ማውረድና መመዝገብ ትችላላችሁ !
አፕሊኬሽኑን ለማውረድ በዚህ ሊንክ ግቡ   👇 👇 👇 👇 👇 👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ethiopianlegaltech.eli


ጠበቆች የሕግ ባለሙያዎች ና ተማሪዎች በዚህ የሕግ ሶፍትዌር
www.ethiopianlegaltech.com በሚለው አድራሻ መግባትና መመዝገብ በነፃ መመዝገብና መጠቀም ትችላላችሁ
#share  #lawyer #legalsupport #legaladvice
#ethiopianlaw #legalcounsel #legalhelp
#ህግ #የህግምክር  #የኢትዮጵያ

https://t.me/Ethiopianlegalinsight


ነገ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ. ም የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 37ኛ መደበኛ ጉባዔ ይካሄዳል

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 37ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል።

ምክር ቤቱ
በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚቀርብ ረቂቅ አዋጅን

አስመልክቶ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የሚያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎም ይጠበቃል።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.
OSZAR »